“የግራኝ አህመድ መንግሥት ከአሸባሪዎች ጋር አብሮ የሚያደርስብንን በደል አለም ይወቀው!”
አዎ! አሁን የተቃውሞውን ማዕበል ወደ አራት ኪሎ ወስዳችሁ የቤተ መንግስቱን አጥር በመነቅነቅ ባለሥልጣን የተባሉትን ወሮበሎች እንደ አቧራ አራግፏቸው። አዲስ አበባን ለዋቄዮ–አልህ ልጆች አትተውላቸው፤ ባለፈው ጊዜ ቤተክርስቲያን እንዲሁም ባልደራስ በአዲስ አበባ ሊያካሂዷቸው ያቀዷቸውን የተቃውሞ ሰልፎች አለማድረጋቸው አዲስ አበባ የኢትዮጵያ አይደለችም እንደማለት ነበር ያስቆጠረው፤ ስለዚህ የማንንም ሰነፍ የማስፈራሪያና ተስፋ ማስቆረጫ ቃል ሳትሰሙ በአዲስ አበባ ግልብጥ ብላችሁ ውጡ፤ ተቃውሞው ያኔ ምናልባት የዓለም አቀፉን ትኩረት ሊያገኝ ይችላል።
አሁን ግን በሉሲፈራውያኑ የምትመራዋ ዓለማችን የቅጥረኛ ልጇ አብዮት አህመድ ጉድ እንዳይሰማባት ፀጥ ማለቱን መርጣለች። ለፀረ–ኢትዮጵያና ፀረ–ተዋሕዶ አጀንዳዎች የተመደቡት እንደ አሶሺየትድ ፕሬስ፣ የአሜሪካ ድምጽ፣ ቢቢሲ፣ የጀርመን ድምጽ የመሳሰሉት ዓለም–አቀፍ ሜዲያዎችና የዜና ወኪሎች በሃገራችን እየተካሄደ ስላለው ጂሃዳዊ ጭፍጨፋ ትንፍሽ አይሉም። በተለይ በኢትዮጵያ ቋንቋዎች ታይቶና ተሰምቶ በማይታወቅ መልክ ዲያብሎሳዊ ቅስቀሳዎችን የሚያካሂዱት ቢቢስ፣ ቪኦኤ እና ዶቼ ቬሌ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ሜዲያዎች ከማይደርሱባቸው ቦታዎች ሁሉ መረጃ የሚሏቸውን ነገሮች ለአድማጩና አንባቢው በማቅረብ ላይ ናቸው። እነ ጽዮን ግርማና ባልደረቦቿ ስለተጠለፉት እህቶቻችን ሆነ በሕዝበ ክርስቲያኑ ላይ እየተካሄደ ስላለው ጂሃድ የዓለም ዓቀፉ ማሕበረሰብ በሚገባ መልክ እንዲያውቅ ቢፈልጉ ኖሮ በአንድ ሕንፃ ውስጥ አብረው ለሚሰሩትና በእንግሊዝኛ እና በሌሎች ብዙ ቋንቋዎች 24 ሰዓት ዜና ለሚያስተላልፉት የጋዜጠኞች እና የአርትኦት ባለሙያዎች አስፈላጊውን መረጃ በሰጡ ነበር። ነገር ግን በቢቢሲ፣ ቪኦኤ እና ዶቼ ቬሌ የሚሠሩት ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሁሉም ነፍሳቸውን የሸጡ ቅጥረኞች መሆናቸው ያሳዝናል።
በሌላ በኩል፤ አሸባሪው አብዮት አህመድ ልክ ወደ አስመራ ሲያመራ እና ወገኖቻችን የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ በሚዘጋጁበት ወቅት፡ በ27 ጃንዩወሪ 2020 ዓ.ም፡“የሰብዓዊ መብት ተማጓቾች ” ከሚባሉት ወሸከቲያም የሉሲፈራውያኑ ድርጅቶ መካከል አንዱ የሆነው “አምነስቲ ኢንተርናሽናል” ስለታገቱት እህቶቻችን ሳይሆን ስለሚከተለው ጉዳይ ይህን መግለጫ አውጥቶ ነበር፦
አምነስቲ በኢትዮጵያ የጅምላ እስር እየበረታ መሆኑ ያሳስበኛል አለ። “ይህ ድንገቴ የጀምላ እስር የዲሞክራሲ መብቶችን ሚሸረሽር ነው፤ በተለይም ነጻና ገለልተኛ እንዲሆን በሚጠበቀው የመጪው ምርጫ ላይ ጥላውን ያጠላል“በተለይ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ደጋፊ የሆኑ 75 ሰዎች በሳምንቱ መጨረሻ በጅምላ ተስረዋል፤ በአስቸኳይ ይፈቱ ሲል አሳስቧል።
Amnesty International has confirmed that at least 75 supporters of the Oromo Liberation Front (OLF) were arrested over the weekend from various places in different parts of Oromia Regional State, as Ethiopian authorities intensify the crackdown on dissenting political views ahead of the general elections.
አሁን አሁንማ ምንም የሚደብቁት ነገር የለም፤ ያው ለሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ ናቸው የሚባሉት ድርጅቶች ለሚታገቱት ወጣት ተማሪዎችና ለሚታረዱት ንጹሐን ሕፃናት፣ አባቶችና እናቶች ሳይሆን የሚቆረቆሩት እንደ ኦነግ ለመሳሰሉት አሸባሪዎች መሆኑ እያየን ነው።
እነዚህ እርካሾች፣ አጭበርባሪዎችና ግብዞች፤ እንዴት እንደሰለቹኝ! ሂውማን ራይትስ ዋች” የተባለውስ የት አለ?