እስኪ በዚህ ጉዳይ ላይ ደግማችሁ ደጋግማችሁ አስቡበት፤ አንድ የኢትዮጵያ መሪ ነው የተባለ ሰው በሃገረ ኢትዮጵያ ቁጥር አንድ ሽብር ፈጣሪ ከሆነውን ኢትዮጵያን በመዋጋት ላይ ካለው አንድ ውርንጭላ ጋር ህብረት ሲፈጥር። አስቡበት! ይህ በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶና ተሰምቶ አይታወቅም። ጂኒዎቹ ጃዋር፣ አብዮትና ለማ በአንድ ላይ ሆነው ኢትዮጵያውያንን እያረዱ ነው፤ ይህ ሁሉ ጉድ ግልጥልጥ ብሎ እየታየን እነዚህን የሃገር ጠላቶች ፈጥኖ እንደመዋጋት ዛሬም ወራዳውን አብዮት አህመድን “አንቱ፣ እሳቸው፣ ክቡርነታቸው ወዘተ” እያሉ ህዝቡን የሚያዘናጉትና የሚያደበዝዙት ግብዝ ወገኖች አሉ ፥ የሚገርም ነው፤ “ለክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ግልጽ ደብዳቤ” እያሉ አላስፈላጊ መልዕክት ለማስተላለፍ እንቅልፍ የሚነሳቸው አሉ። ሂትለርን፣ ሙሶሊኒንና ስታሊንን “አንቱ” ትላላችሁ? ስንት ወገን ማለቅ አለበት እነዚህን ወራዶች ሙሉ በሙሉ ለመትፋት?!