ከሦስት ዓመታት በፊት የአማራ፣ ትግሬ እና ኦሮሞ ልሂቃን ስለ ፀረ–ትግሬ ዘመቻ
[፩ኛ የዮሐንስ መልእክት ምዕራፍ ፬፥፳]
“ማንም። እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል?”
ይህ ከሦስት ዓመታት በፊት፤ በ የካቲት ፪ሺ፲ /2010 ዓ.ም የተቀዳው የቪኦኤ ውይይት የፀረ–ትግሬ ዘመቻው እውነት ከህወሀት ጋር የተያያዘ ነውን? የሚል ጥያቄ እንድንጠይቅ ይረዳናል። ውይይቱ ዛሬ የደረስንበትን ሁኔታ በተለይም በዘረኝነትና በሃይማኖት ላይ የተመሠርተ የጦርነት ነጋሪት እየጎሰሙ ያሉትን የልሂቃኑን ውድቀት በደንብ ያሳየናል፤ ባጠቃላይ ችግሩ የት እንዳለ፣ ማን ምን ይፈልግ እንደንበረ ቁልጭ አድርጎ ያሳየናል፤ ለታሪክ ይቀመጣል።
እንደሚታወቀው ሁሉ፣ አገራችን በዓለም ተፈርታና ተከብራ ከመኖር ተዋርዳና ተሸማቃ የኖረችው በተካሄደባት የረዥም ዘመናት የእርስ በርስ ጦርነት ነው፡፡ የአክሱም ዘመነ መንግሥት ጥንታዊውን የኩሽ መንግሥት፣ የአክሱምን መንግሥት የዛጉዌ ኩሻዊ ሥርወ መንግሥት፣ የዛጉዌን ሥርወ መንግሥትን የሸዋ ሰለሞናዊ ሥርወ መንግሥት፣ የሸዋ ሥርወ መንግሥትን ለመጣል የአዳል ሡልጣኔት፣ የአዳል ሡልጣኔትን ለመጣል የኦሮሞ ገዳዊ ሥርዓት፣ የኦሮሞ ገዳዊ ሥርዓትን ለመጣል ዘመነ መሳፍት፣ ዘመነ መሳፍንትን ለማስወገድ አፄ ቴዎድሮስ፣ አፄ ቴዎድሮስን ለመጣል አፄ ዮሐንስ፣ አፄ ዮሐንስን ለመጣል አፄ ምኒልክ፣ ከአፄ ምኒልክ በኋላ ልጅ እያሱ፣ ልጅ እያሱን ለመጣል አፄ ኃይለ ሥላሴ፣ አፄ ኃይለ ሥላሴን ለመጣል ደርግ፣ ደርግን ለመጣል ኢሕአዴግ፣ አሁን ደግሞ “ህዋሀትን” እና ትግሬዎችን ለማስወገድ ጦርነት በተለይም በዘረኝነትና በሃይማኖት ላይ የተመሠርተ የጦርነት ነጋሪት በተለይ “ልሂቃን” በተባሉት ግብዞች ዘንድ እየተጎሰመ ነው፡፡ እንግዲህ በዚህ ሁሉ ዘመን እጅግ አሰቃቂ የሰዎች፣ የእንስሳት፣ የደን፣ ወዘተ ዕልቂት ተፈጽሟል። የአገር ሀብት ወድሟል።
ጦርነት ለማያውቁና በቀጥታ ለማይሳተፉበት ቀላል ነው፡፡ በርካሽ ዋጋ የገዙትን በውድ ዋጋ በመሸጥ አትራፊ ለመሆን ለሚፈልጉ ደግሞ መልካም አገጣሚ ነው፡፡ ተደብቀው የፖለቲካ ዓላማቸውን ለሚያራምዱም ጥሩ የሚሆን ሊመስላቸው ይችላል፡፡ በትርፍ ጊዜያቸው ለሚያራግቡ ደግሞ የሚጎዳቸውም ሆነ የሚጠቅማቸው ላይሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን ጦርነት ከተነሳ የአክሱም ሥልጣኔንና የዛጉዌ ሥልጣኔን ያጠፋው ጦርነት የጎንደርን፣ የሸዋንና የሌሎችን ሥልጣኔ አይምርም፡፡ መፈክሩ “የማን ቤት ጠፍቶ የማን ሊበጅ፣ የአውሬ መፈንጫ ይሆናል እንጂ፤ የተባለው ይደርሳል፡፡ ትውልድ ይጠፋል፡፡ በሚሊየን የሚቆጠሩ የጦርነት ማገዶ ይሆናሉ፡፡ ይህን በምሳሌ ለማረጋገጥ ሶሪያን፣ ኢራቅን፣ ወዘተ መጥራት አያስፈልገንም፣ የጦርነት ታሪካችን ራሱ ምስክር ነው፡፡ በጦርነትና በግጭት ወቅት ሰው፣ እንስሳትና ዕፅዋት ይጠፋሉ፡፡ ማኅበራዊ ሕይወት ይመሳቀላል፡፡ ኢኮኖሚ ይወድማል፡፡
በትግሬ ኢትዮጵያውያን ላይ እየታየ ያለው የጥላቻ ዘመቻ በአውሮፓ አይሁዳውያን ላይ ሲታይ የነበረውንና ዛሬም የሚታየውን የፀረ–አሁድ ዘመቻ ያስታውሰኛል። በአውሮፓ ከጥንት ጀምሮ ለሁሉም ነገር የሚኮነኑት አይሁዶች እንደሆኑ ሁሉ በኢትዮጵያም ላለፉት ፻፶/150፤ አዎ! መቶ ሃምሳ ዓመታት የሚኮነኑት ትግርኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን ናቸው። እንግዲህ በዛሬዋ ዓለማችን አይሁዶች አስራ አምስት ሚሊየን አይሞሉም፤ ትግርኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያንም ኤርትራን ሳይጨምር ስድስት ሚሊየን ብቻ ናቸው። በሁለቱ ሕዝቦች ላይ የሚታየው የአድሎና ጥላቻ ዘመቻ መንስ ዔው አንድ እና አንድ ነው፤ “ቅናት”፤ “መንፈሳዊ ቅናት”።
👉 እስራኤል ዘስጋ = አይሁድ
👉 እስራኤል ዘመንፈስ = ተዋሕዶ ክርስቲያን ኢትዮጵያ
እስኪ እውነቱን ፍርጥ እናድርገው እና ይህ የካቲት ፪ሺ፲ /2010 ዓ.ም የተቀዳው የቪኦኤ ውይይት ላይ ተንታኞቹ የተወያዩበት የፀረ–ትግሬ ዘመቻ ዛሬ እንዴት ሊቀጥል ቻለ። በትክክል የተጠላው የሀዋሀት አገዛዝ ሰዎቹንም፣ ወንበሩንም ጠረጴዛውንም፣ በዕሩንም ከአዲስ አበባ ነቅሎ በማውጣት ወደ ትግራይ አምርቷል፣ ከ”መከላከያ ተብየው እስከ ደህነነትና ሌሎች ተቋማት ድረስ ሁሉንም ቁልፍ የተባሉ ነገሮችንም አስረክቦ ሄዷል። ይህን ሁሉ “ስጦታ” በብር ሳህን ላይ የተረከቡት አብዮት አህመድን እና ለማ መገርሳ ታይቶ በማይታወቅ ደስታና እልልታ በሁሉም ኢትዮጵያውያን ዘንድ(ትግሬዎችን ጨምሮ)ተቀባይነት ለማግኘት ከቻሉ ከሦስት ዓመታት በኋላ እነዚህ መስራትና አገር ማገልገል የተሳናቸው ሰነፎች ልቡን ሰጥቷቸው የነበረውን አማራውን እና ትግሬውን ማጥቃት፣ ማፈናቀል፣ መግደል እና መጨፍጨፍ ጀመሩ። ይህ አልበቃቸውም ስልጣኑን እና ተቋማቱን ሁሉ አስረክበዋቸው የሄዱትን ትግሬ ኢትዮጵያውያንን ላለፉት ሦስት ዓመታት በሰላም የሚኖርበት “ክልል” ድረስ ሄደው በውጊያ አውሮፕላኖች አጠቁት፤ ይህም አልበቃቸውም፤ በአዲስ አበባ እና ኦሮሚያ በተሰኘው ህገ–ወጥ ክልል የሚገኙትን ትግርኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን ልክ አርሜኒያውያን በቱርኮች፣ አይሁዶች በአውሮፓውያን ሲደረግባቸው እንደነበረው የጥላቻ ስም በመስጠት እያደኗቸው ይገኛሉ።
„Give a dog a bad name and hang him” / ለውሻ መጥፎ ስም ስጠው እና ስቀለው” እንዲሉ። በመላው ዓለም ያሉት ፀረ ሴማዊያን/ፀረ-አይሁዶች ዘረኝነታቸውን ወይንም የዘር ጥላቻቸውን ለመደበቅ “እኔ እኮ የእስራኤልን መንግስት ነው እንጂ የምቃወመው/ኔተንያሁን የምጠላው፤ አይሁዶችን አይደለም፣ ጎረቤት፣ ጓደኛ አለኝ!” እንደሚሉት የእኛዎቹም በአማራ ላይ ያላቸውን ጥላቻ በ”ነፍጠኛ”፣ በትግሬ ላይ ያላቸውን ጥላቻ ደግሞ “ወያኔ” በማለት ዘረኝነታቸውን ለመሸፈን/ለመሸፋፈን ሲሞክሩ ይሰማሉ።
ውጊያው መንፈሳዊ ነው፤ የስጋ ማንነትና ምንነት ባላቸው የክርስቶስ ተቃዋሚዎች እና የመንፈስ ማንነትና ምንነት ባላቸው የክርስቶስ ልጆች መካከል ነው።
በደርግ ጊዜ የስጋዊ ማንነት ያላቸው ጋሎች እና ጋላማራዎች ስልጣኑን በሚቆጣጠሩበት ጊዜ በትግርኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን ላይ ከፍተኛ አድሎና በደል ይፈጸም ነበር። በዚህ ጉዳይ ላይ ከአምስት ዓመት በፊት ለአንድ ዩኒቨርሲቲ ጥናታዊ ጽሑፍ አቅርቤ ነበር። በወቅቱ የነበሩትንና እውነተኛና ግልጽ የሆኑትን ከሁሉም ብሔረሰቦች የመጡ ወገኖቻችንን ለማነጋገር በቅቼ ነበር፤ ሙሉውን ለመስማት ስለሚከብድ ዛሬ በአዲስ አበባ በትግርኛ ተናጋሪ ወገኖቻችን ላይ ከሚደርሰው በደል ጋር ተመሳሳይ ነውና አንድ ምሳሌ ላቅርብ፦
እየተደረገ ያለው ልክ በደርግ ጊዜ እንደነበረው ነው፤ ልጅ ሆኜ በብዙ ትግርኛ ተናጋሪ ጎረቤቶቻችን ላይ ከቀበሌ እስከ ስኮላርሺፕ ቢሮዎች ይደርስባቸውን የነበረው ነገር ተመልሶ መምጣቱን ነው በግልጽ የምናየው። ያኔም ጋሎቹ/ጋላማራዎች ነበሩ ቁልፍ የሆኑትን ቦታዎች ተቆጣጥረው ትግርኛ ተናጋሪዎችን በየመስሪያ ቤቱ እድገት እንዳይኖራቸው ሲለዩአቸው፣ ወደ ውጭ እንዳይሄዱና እንዳይማሩ ሲከለክሏቸው የነበሩት። በዚህ ሪሰርቼ ለምሳሌ በደርግ ጊዜ የኢትዮጵያ ፓስፖርት የነበራቸው ትግርኛ ተናጋሪዎች በተለይ ከኤርትራ የነበሩ ወገኖቻችን ከየዩኒቨርስቲው እንዲባረሩ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች እንዲፈርሙ ተደርገው/ተገድደው ነበር። ብዙዎች ትምህርታቸውን እያቋረጡ እንዲባረሩ ተደርገዋል። ዛሬም ይህ ነው የተመለሰው። ደርግ 2.00። መቼ ነው አንድ ጋላ ማንነቱ መታወቂያ ላይ እየታየ አድሎ ሲፈጸምበት፣ ስፈናቀልና ሲገደል የንበረበት ዘመን? በጭራሽ አንድም ጊዜ አልነበረም። በዛሬዋ ኢትዮጵያ አምራኛ እና ትግርኛ ተናጋሪዎች ብቻ ናቸው “ነፍጠኛ”፣ “ወያኔ” እየተባሉ የሚበደሉት። ይህን በተለይ አማራ እና ትግሬዎች “ለምን እኛ ብቻ?” ብለው ሊያስቡበት ይገባል።
ባጠቃላይ ከእነዚህ ዛረኞችና እርጉሞች ጋር የሚያብሩና ለእነርሱ እርዳታ የሚያበረክቱ ትግሬዎችና አማራዎች ኢትዮጵያን በይበልጥ እየጎዷት ነው ያሉት። ያው እኮ ህወሀት ሚጢጤየ ክልል ለትግራይ ኢትዮጵያውያን አስቀርተው በታሪክ ያልነበሩትን በጣም ግዙፎቹን ክፍለ ሃገራት ለኢትዮጵያ ጠላቶች አስረክበዋል። ዛሬ የትግራይ ሰዎች ጡት አጥብተው ባሳደጉት ግራኝ አብዮት ከአዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን ከራሳቸውም ክልል እየወጡ ወደ ሱዳን እንዲሰደዱ እየተደረጉ ነው። ይህን አውሬ ሊደፋ የሚችል ትግሬ ወይም አማራ መጥፋቱ አሳዛኝና አሳፋሪ ነው!
ብዙ ፈረንጆች ከጥቁር ክርስቲያን ይልቅ ነጭ እስላም እንደሚመርጡት ሁሉ፣ ብዙ “ተዋሕዶ ነን” የሚሉ ወገኖችም ከተዋሕዶ ትግሬ ይልቅ ጋላ መናፍቅ ወይም እስላም የሚመርጡበት ዘመን ላይ ደርሰናል። ኡ! ኡ! ያሰኛል። አብዮት አህመድን እና ለማ መገርሳን ገና ምንም በጎ ነገር ሳያሰሩ “ትግሬ ስላልሆኑ እና ኢትዮጵያ ሱሴ!” በማለታቸው ብቻ እየጨፈሩ የተቀበሏቸው ወገኖች፤ ላለፉት ሦስት ዓመታት ከወያኔ ዘመን እጅግ በከፋና በሃገራችንም ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ዘግናኝ ጭፍጨፋ እገታ፣ መፈናቀል፣ መሬትና ንብረት ዘረፋ መከላከያ በተሰኘው የጋላ ሠራዊት ከተካሄደ በኋላ ዛሬም እንደገና ከገዳያቸው ግራኝ አህመድ ጎን በመቆም “ከመከላከያችን ጋን ነን! ትግሬውን በለው፣ ጨፍጭፈው!” ይላሉ። የማከብረው ወንድም አቻምይለህ ታምሩ የምጠይቀው፤ በተለይ ይህ የቄሮ ፋሺስታዊ አገዛዝ አማራዎችን ከመላዋ ኢትዮጵያ ለማጽዳት ባለው ዕቅድ ምንም ዕውቀቱ የሌላቸውን ምስኪን ገበሬዎችን ወደ ጦር ግንባር ወስዶ የሚያስቆላቸውን“መከላከያውን” እንዴት ያየው ይሆን?
_________________________