Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • May 2023
    M T W T F S S
    1234567
    891011121314
    15161718192021
    22232425262728
    293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘ኖትረዳም’

የፓሪሱ ካቴድራል ሲቃጠል የኦባማ ሚስት እዚያ ነበረች | የትራምፕ ልጅ ደግሞ በእስክስታ ሱስ ተጠመደች

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 18, 2019

አንዳንድ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት፤ ይህ የእሳት ቃጠሎ ሆን ተብሎ እንደተቀሰቀሰ እና፤ ድርጊቱ በፕሬዚደንት ማክሮን፣ ካንዝለር አንጌላ ሜርከል እና ጠቅላይ ሚንስትር ተሪዛ ሜይ አቀነባባሪነት እንዲሁም በ ጳጳስ ፍራንሲስኮ ተባባሪነት ነው የተፈጸመው።

ባለፈው ሣምንት ላይ ተሪዛ ሜይ ወደ በርሊን ከተማ በመጓዝ ከ አንጌላ ሜርከል ጋር ከተገናኘች በኋላ – በፐርጋሞን ሙዚየም (የሰይጣን ዙፋን የሚገኝበት ቦታ ነው) አቅራቢያ ነበር የተሰባሰቡት – ወደ ፓሪስ አምርታ ከሦስተኛው “M” ማክሮን ጋር ተገናኘች። በርሊን የክርስቶስ ተቃዋሚው መቀመጫ ከሆኑት ከተሞች መካከል አንዷ ናት፤ ፖለቲካዊ ዋና ከተማ።

ማክሮን – ሜርከል – ሜይ – ኦባማ – ኢቫንካ

________________________

Posted in Conspiracies, Curiosity, Ethiopia | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ተዓምር በፓሪስ | በተቃጠለው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ኢየሱስ ታየ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 17, 2019

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ ብዙ ሰዎች እየመሰከሩ ነው። ድንቅ ነው። የዛሬዎቹ ከሃዲ ፈረንሳይ አባቶች ይህን ድንቅ ቤተ ክርስቲያን ለጌታችን ክብር ሲሉ ከስምንት መቶ ዓመታት በፊት በስንት ድካምና መስዋዕት ሠሩት። የአሁኑ ተልካሻ ትውልድ ግን ከአውሬነት ነፃ አውጥቶ እየባረከ ፀጋውን የሰጣቸውን ጌታችንን በመተው እንደ ይሁዳ የክህደት ኑሮውን መረጡ። በዚህም ይህን ድንቅ ቤተክርስቲያን ለፀሎት፣ ለመንፈሳዊ ሕይወታቸው እና ለነፍስ ማደሻ በመገልገል ፈንታ ጎብኝዎችን በመጋበዝ የገንዘብ ማምረቻ መሣሪያ አደረጉት።

አዎ! ጌታችን በዚህ እጅግ በጣም አዝኗል፤ ስለዚህ፡ ቤቱ ለእርሱ ሲባል የተሠራ ነውና፤ እርሱ የማይመለክበት ከሆነ “እንግዲያውስ” በማለት እንዲቃጠልና እንዲፈርስ ፈቀደ። ፈረንሳዮች ሙሉ በሙሉ እንዳይፈራርሱ ከፈለጉ በጣም ማልቀስና ወደ ጌታችን መመለስ ይገባቸዋል።

አባቶቻቸው ቤተ ክርስቲያኑን ሠርተው ለመጨረስ ሁለት መቶ አመት ፈጅቶባቸው ነበር፤ ለስምንት መቶ ዓመታት ያህል ብዚ ጦርነቶችን እና የተፈጥሮ አደጋዎችን ምንም ሳይነካ አሳልፏል፤ ዛሬ ግን፡ እውቀት ጨምሯል፣ ቴክኖሎጂው ሁሉ በጣም ተራቅቋል በሚባልበት ዘመን፤ ሕንፃው በሰዓታት ውስጥ ወደመ። በሰሜን ተራሮች ቃጠሎ አገራችን “ውሃ፣ ውሃ!” እንደሚል ሕፃን “ሄሊኮፕተር፣ ሄሊኮፕተር!” በማለት ለመነች፤ “የመጠቅችው” ፈረንሳይ ግን በታላቅ ንብረቷ ላይ የደረስውን እሳት ከበሰተላይ ለማጥፋት አንድም ሄሊኮፕተር መጠቀም አልቻለችም። ዋው! አይገርምምን?!

_________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

በኒው ዮርክ ከተማ ቅዱስ ዮሐንስ ካቴድራልም የእሳት አደጋ ደርሶ ነበር

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 16, 2019

በዚህችው በ ኒው ዮርክ ከተማ ከሦስት ዓመታት በፊት፡ በ ኦሮቶዶክስ ዕለተ ትንሳኤ፡ ታሪካዊው የቅዱስ ሳቫ የሰርቢያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሕንፃ የእሳት አደጋ ሰለባ ሆኖ ነበር፤ በዚሁ ዕለት በ ፬ የኦርቶዶክስ ዓብያተክርስቲያናት ላይ በመላው ዓለም ጥቃት ደርሶ እንደነበር በጦማሬ ላይ አውስቼው ነበር።

__________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ተዓምር በፓሪስ | መስቀሉ ብቻ ከቃጠሎ ተረፈ፤ ሰማዩ ላይ የላሊበላ መስቀል ታየ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 16, 2019

በኖትረዳም ካቴድራል የተቀስቀሰው እሳት በቁጥጥር ሥር ከዋለ በኋል ሕንፃ ውስጥ እሳት አጥፊዎች ሲገቡ መስቀሉ ምንም ሳይሆን እና ሳይቃጠል ኃይለኛ ብርሃን አንጸባርቆ የታያቸው መስቀሉ ነበር። ይህ ትልቅ ምልክት ነው፣ ለመስቀሉ ጠላቶችም ማስጠንቀቂያ ነው። ዲያብሎስ ጠላት ይፈር፣ ቅጥል ይበል!

በጣም ድንቅ ነው! ይህ ሁሉ ነገር በሥላሴ ዕለት ነው የተፈጸመው፤ የፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ሴት ልጅ ቅድስት ሥላሴን በጎበኝበት ዕለት።

በሌላ በኩል ደግሞ፤ ቢቢሲ በቀጥታ ሲያስተላለፍ ነበረው የቪዲዮ ምስል፡ ሰማዩ ላይ ነጭ ቀለም ያለውን መስቀሉን እሳቱ በፈጠረው ጥቁር ጭስ መካከል ጎልቶ ያሳየናል።

እንዴት ደስ ይላል! ተመስገን አምላካችን!

__________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , | Leave a Comment »

በኢየሩሳሌሙ ታዋቂ መስጊድም እሳት ተቀሰቀሰ | በተመሳሳይ ሰዓት ከፈረንሳዩ ካቴድራል ቃጠሎ ጋር

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 16, 2019

ኒው ስዊክ እንደዘገበው ከሆነ በአላክሳ መስጊድ ውስጥ ነው እሳቱ የተቀሰቀሰው፤ ጉዳት ግን አልደረሰበትም። እንግዲህ አላህ እና አጋንንቱ የፓሪሱን ካቴድራል መውደም በሺሻ እያከበሩ ሳይሆን አይቀርም። በማህበራዊ ሜዲያ ብዙ ሙስሊሞች ሲደሰቱ፣ ሲስቁና ሲያፌዙ ማንበብና መስማት ይቻላል።

የፓሪሱ ካቴድራል ቃጠሎ ሆን ተብሎ እንደተቀሰቀሰ አንዳንድ የትዊተር ምንጮች ይናገራሉ። ከሦስት ዓመታት በፊት የኖትረዳም ካቴድራልን በቦምብ ልታፈነዳ የነበረችው ሙስሊም ባለፈው ዓርብ ዕለት የስምንት ዓመት እስራት ፍርድ ተሰጥቷት ነበር።

የሚያሳዝን ዘመን ላይ ደርሰናል። አምላክአልባ የሆነ ኑሮ የሚያካሂዱት ፈረንሳዮች ከዚህ የባሰ እሳት እንደሚመጣባቸው ነው የካቴድራሉ ቃጠሎ የሚጠቁመን።

ጦርነቱ በምዕራቡ ኢአማንያን እና በሙስሊሞች መካከል ነው የሚሆነው – የሉሲፈር ልጆች እርስበርስ ይባላሉ ማለት ነው – አላርፍ ያሉት ሙስሊሞች እራሳቸው በሚቀሰቅሱት እሳት የሚለበለቡበት ዘመን እየመጣ ነው።

በነገራችን ላይ በዚህ የኢየሩሳሌም መስጊድ እና በመካ ጥቁር ድንጋይ መካከል ያለው ርቅት በትክክል 666 የባሕር ጉዞ ማይሎች ነው።

__________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , | Leave a Comment »

እኅተ ማርያም ይህን ባወሳች ማግስት ድንቁ የፈረንሳይ ካቴድራል የእሳት አደጋ ሰለባ ሆነ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 15, 2019

በጣም የምያሳዝን ነገር ነው፤ ይህ ፈረንሳይ ውስጥ በጎብኝዎች ብዛት የመጀመሪያውን ቦታ የያዘ ታሪካዊ ቦታ ነው። በስምንት መቶ ዓመት ታሪኩ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው የእሳት አደጋ ሰለባ ሲሆን፤ እጅግ ያሳዝናል፤ የአንድ ሺህ ዓመት ታሪክ ያለው የፈረንሳውያን ብሔራዊ ማንነትና ኩራት በአንድ ሰዓት ዕልም ብሎ ጠፋ፡ ዋው!

ነገር ግን፤ በአገራችን ተንኮል ሲሠሩ በእነርሱ ላይ የፍርድ እሳት ይዘንብባቸዋል። የሰሜን ተራሮች ቃጠሎ ከሰማይ ይታያል። ባለፈው ወር ላይ ሰዶማዊው የፈረንሳይ ፕሬዚደንት ማክሮን ከ ዶ/ር አህመድ ጋር ሆኖ ላሊበላን አላግባብ ረግጦ ነበር። “ላሊበላን እናድሰው” ብለው ነበር፤ ግን ጉዳዩ ተንኮል እንዳለበት የላሊበላን ድንቅ ዓብያተክርስቲያናት እንዲሠሩ አባቶችን እና መላዕክቱን ያዘዘው ኃያሉ እግዚአብሔር ያውቃል። እስኪ ይታይን፤ ወገኖቼ፤ በጣም ብርቅ የሆነውን እና በጎብኝዎች ዘንድ የመጀመሪያውን ቦታ የያዘውን ላሊበላ ንብረታችንን በእድሳት መልክ ሲተናኮሉ የራሳቸው አንደኛ ቱሪስት ሳቢ ካቴድራል ተቃጠለ። ሆኖም፡ በተለይ በእነርሱ ፋሲካ ቅዱስ ሣምንት ይህ አደጋ መከሰቱ እጅግ በጣም አሳዛኝና አጠራጣሪም ነው። የመሀመድ አርበኞች ይህን ካቴድራል እናፈርሰዋለን በማለት ደጋግመው ይዝቱ ነበር።

ያም ሆነ ይህ፡ በላሊበላ ቅዱስ አማኑኤል ቤተክርስቲያን ያላግባብ ካባውን ለብሰው የነበሩት ፕሬዚደንት አማኑኤል ማክሮን እና ዶ/ር አብይ አህመድ ለራሳቸውም ለአገሮቻቸውም መጥፎ ዕድልን ይዘው መጥተዋል።

ማክሮን በላሊበላ ካባ ለብሶ በተመለስ ማግስት ፓሪስ በተቃዋሚዎቹ ጋየች | የድል ሐውልት ላይ አውሬው ታየ”

ሰዶማዊው ማክሮን ላሊበላን አርክሶ ከተመለስ በኋላ ፲፪ የፈረንሳይ ዓብያተክርስቲያናት ላይ ክፉኛ ጥቃት ደርሶባቸዋል

በሚለው ቪዲዮ ላይ ይህን ጽፌን ነበር፦

ፕሬዚደንት ማክሮን ከአጋሩ ጠ/ሚንስትር ግራኝ አህመድ ጋር በመሆን ወደ ላሊበላ ሄደው ቅዱስ ዓብያተክርስቲያናቶቻንን አርክሰዋል። የሚገርመው ደግሞ፤ የራሱን አገር ዓብያተክርስቲያናት በአግባቡ መንከባከብና መጠበቅ ያልቻለው አማኑኤል ማክሮን የላሊበላ ዓብያተክርስቲያናትን “ለማደስ ቃል ገብቷል” መባሉ ነው።

በክርስቶስ ተቃዋሚዎቹ አማኑኤል ማክሮን እና አብይ አህመድ ላይ መዓት በመምጣት ላይ ነው። የለበሱት ካባ መዘዝ? እነዚህን ሁለት የኢትዮጵያ ጠላቶች ካባዎቹ አቦዝነዋቸው (deactivate) ይሆን?“

የሚገርም ነው፤ ከጥቂት ዓመታት በፊት እዚህ በእድሳት ላይ ከነበረው ካቴድራል ፊት ለፊት ቁጭ ብዬ አጠገቤ የነበርችው ሕፃን አሜሪካዊት እናቷን እንዲህ ብላ ስትጠይቃት መስማቴን አስታውሰዋለሁ፦

ማሚ እነዚያ ሰዎች እዚያ ሕንፃ ላይ ምን እያደረጉ ነው?እናትየዋም፦ “ቀለም እየቀቡት ነው፤ ዛሬ ቀብተው ከጨረሱ በኋላ ነገር ተመልሶ ጥቀርሻ ይሆናል” አለቻት፤ የአየር ብክለቱን ለመጠቆም።

__________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: