Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 20, 2022
✞✞✞ብዙ ፈውሶች የተካሄዱባት የቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን (ፀበል) አዲስ አበባ ✞✞✞
“የተጠመቅኩት፣ በመሰቀል የተሰቀልኩትና የተሰዋኹት ለአመኑኝና ቃሌን ለተቀበሉኝ ሁሉ ለስጋቸው በረከት ለነፍሳቸው ድኽነት ለመስጠት ነው!”
ለእያንዳንዱ ለተጠመቀው ክርስቲያን፣ ስጋው ለተቆረሠለት፣ ደሙ ለፈሰሰለትና እግዚአብሔር ሰው ለሆነለት ክርስቲያን ጠባቂ መላእክት አሉት።
ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ከፍተኛ የትምህርት ተሰጥዎ ያለው በመሆኑ ትምህርቱን በጣም አስደናቂ በሆነ መንገድ ፈጽሞ ዲያቆን ሆነ ፡፡ ከመምህሩ ከአባ ጌዴዎን በተማረው መሠረት የእብራይስጥና የግሪክ ቋንቋዎችን ደህና አድርጉ ያውቅ ነበር ይባላል ፡፡ ስለዚህ በመጽሐፍ ቅዱስና እንዲሁም በውጭ አገር ቋንቋዎች የአጉቱን የመምህር ጌዴዎንን ሙያ አጠናቆ ቻለ ፡፡ ያሬድ አጉቱ ሲሞት የዐሥራ አራት አመት ልጅ ቢሆንም የአጉቱን ሙያና የትምህርት ወንበር ተረክቦ ማስተማር ጀመረ። በግንቦት ፲፩ (11) ቀን ስንክሳር በተባለው የቅዱሳን የሕይወት ታሪክ መጽሐፍ ውስጥ “ያሬድ በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶና ተነሣሥቶ የዜማ ድርሰቶቹን አዘጋጀ” ይላል።
በዚሁ ስንክሳር እንደ ተጻፈው እግዚአብሔር በዚች ምድር እንዲመስገን በፈለገ ጊዜ ያሬድን በራሱ ቋንቋ ሰማያዊ ዜማ እንዲያስተምሩት በአእዋፍ አምሳል ሦስት መላእክትን ከገነት ላከለት ይላል ፥፡ እነሱም ያሬድ ካለበት ሥፍራ አንጻር ባለው አየር ላይ ረበው(አንዣብበው) ጣዕም ያለውና ልብን የሚመስጥ አዲስ ዜማ አሰሙት ፡፡ ያን ጊዜ ያሬድ በጣዕመ ዜማቸው ተመስጦ ቁሞ ሲያዳምጥ ወዲያውኑ ወፎቹ በግዕዝ ቋንቋ “ብጹዕ ወክቡር አንተ ያሬድ ብጽፅት ከርሥ አንተ ጾረተከ ውብጹዓት አጥባት አላ ሐአናከ” ብለው በአንድነት አመስግኑት። ትርጉሙ “የተመሰገንክና የተክበርክ ያሬድ ሆይ ፡ አንተን የተሸከመች ማኅፀን የተመስገነች ናት ፡፡ አንተን ያሳደጉ ጡቶችም የተመሰገኑ ናቸው” ብለው አመሰገኑት፡፡
ከዚያም ሐያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ዜማ ወደ ሚዘምሩበት ወጋ ሰማያዊት ኢየሩሳሌም አሳረጉት ፡፡ ቅዱስ ያሬድም በመንበረ ጸባዖት ፊጓ ቁሞ ከሐያ አራቱ ካህናተ ሰማይ በፍጥነት የሰማው ማኀሌት ሁቦ በመንፈስ እግዚአብሔር ተገለጸለትና በልቦናው የተሣለበትን ጰዋትዜ ዜማ በቃሉ ያዜም ጀመር ፡፡ ከዚያም ወደ ቀድሞ ቦታው ወደ አክሱም በተመለሰ ጊዜ ክጥዋቱ በ፫ ሰዓት ወደ አክሱም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገብቶ በታቦተ ጽዮን አንጻር ቆሞ እጆቹን ወደ ሰማይ ዘርግቶ ፡ በከፍተኛ ድምፅ በአራራይ ዜማ ሃሌ ሉያ ለአብ ፡ ሃሌ ሉያ ለወልድ ፡ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ ቅዳሜሃ ለጽዮን ሰማየ ሳረረ ወዳግም አርአዮ ለሙሴ ዘክመ ይገብር ግብራ ለደብተራ” ብሉ ሥነፍጥረቱንና ሰማያዊት ጽዮንን አሰመልክቶ ዘመረ ይህችንም ማኅሌት አርያም ብሎ ጠራት ዞ አርያምም ማለት ልዕልና ሰባተኛ ሰማይ መንበረ እግዚአብሔር ማለት ነው ፡፡ ያሬድ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተመርቶ መላእክት እንደ ከበሮ እንቢልታ፣ ጸናጽል ፣ ማሲንቆና በገና በመሳሰሉት የማኅሌት መሣሪያዎች እየዘመሩ አምላካቸውን እግዚአብሔርን ሊያመሰግኑ ስለስማ እነዚህን መሣሪያዎች በሥራ ላይ እንዲውሉ አደረጋቸው ፡፡
✞✞✞[ፈጥኖ የሚረዳን የቅዱስ ሚካኤል ክብር በሊቁ በቅዱስ ያሬድ ድጓ]✞✞✞
- 😇 የ፺፱/99ኙ ነገደ መላእክት አለቃ ስለኾነው ስለ ቅዱስ ሚካኤል ክብር፣ ውበት፣ ምልጃ ማሕቶተ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ያሬድ በመጽሐፈ ድጓው እንዲኽ ይላል፦
- “ክብረ ሚካኤል ናሁ ተዐውቀ
- በትሕትናሁ ዐብየ ወልሕቀ
- ዲበ አእላፍ ዘተሰምየ ሊቀ
- ዘይትዐፀፍ መብረቀ ይተነብል ጽድቀ”
(የሚካኤል ክብረ እነሆ አኹን ታወቀ፤ በትሕናውም ፈጽሞ ላቀ ከፍ ከፍ አለ፤ በአእላፍ ነገደ መላእክት ላይ አለቃን የተባለ መብረቅን የሚጐናፀፍ ርሱ ጽድቅን ይለምናል) ይላል፡–
❖ የ፺፱/99ኙ ነገደ መላእክት አለቃ ከመኾኑ ጋር ይልቁኑ ዮሐንስ በራእዩ በምዕራፍ ፰፥፪ ላይ “በእግዚአብሔርም ፊት የሚቆሙትን ሰባቱን መላእክት አየሁ” ካላቸው፤ ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት በመዠመሪያ የሚጠቀሰው ቅዱስ ሚካኤል ነውና ሊቁ ያሬድ፡–
❖ “እስመ እምአፉሁ ይወጽዕ ነጐድጓድ
- ሕብረ ክነፊሁ ያንበለብል ነድ
- እምሊቃነ መላእክት የዐቢ በዐውድ
- ሚካኤል ውእቱ መልአኩ ለወልድ”
(የወልድ አገልጋዩ ሚካኤል ነው፤ በዙሪያው ኹሉ ካሉት ከሊቃነ መላእክት ይበልጣል፤ የክንፉ መልክ ነባልባላዊ እሳትን ያቃጥላል፤ ከአንደበቱ ነጐድጓድ ይወጣልና) ይላል፨
❖ “አዕበዮ ንጉሠ ስብሐት
- ለሚካኤል ሊቀ መላእክት
- ዘይስእል በእንተ ምሕረት
- መልአከ ሥረዊሆሙ ለመላእክት”
(የምስጋና ባለቤት ክርስቶስ ለመላእክት ጭፍሮች አለቃቸው የኾነ ስለ ምሕረት የሚማልድ የመላእክት አለቃ ሚካኤልን ከፍ ከፍ አደረገው) በማለት ይጠቅሰዋል፡፡
❖ የስሙ ትርጓሜንም ስንመለከት ሚካኤል ማለት ቃሉ የዕብራይስጥ ሲኾን ሚ– ማለት “ማን”፤ ካ– “እንደ”፤ ኤል– “አምላክ” ማለት ነውና ሚካኤል ማለት “መኑ ከመ አምላክ” (ማን እንደ አምላክ) ማለት ነው፡፡
❖ የመልክአ ሚካኤል ደራሲም ይኽነን ይዞ
❖ “ሰላም ለዝክረ ስምከ ምስለ ስመ ልዑል ዘተሳተፈ
(የያሬድ ልጅ ሄኖክ እንደጻፈው ከልዑል ስም ጋር ለተባበረ ስም አጠራርኽ ሰላምታ ይገባል) ይለዋል፡፡
😇 ቅዱስ ያሬድም፡–
❖ “መልአከ ፍሥሐ ሚካኤል ስሙ
- ለመላእክት ውእቱ ሊቆሙ
- መልአኮሙ ሥዩሞሙ
- የሐውር ቅድሜሆሙ እንዘ ይመርሆሙ”
(ስሙ ሚካኤል የተባለ የደስታ መልአክ ለነገደ መላእክት አለቃቸው ነው፤ የተሾመላቸው አለቃቸው ርሱ እየመራቸው በፊት በፊታቸው ይኼዳል) ይላል
❖ በብሉይ ኪዳን ለአበው ነቢያት እየተገለጠ፤ ለሐዋርያትም በስብከት አገልግሎታቸው እየተራዳ፤ ለሰማዕታት፣ ለቅዱሳን አበው በተጋድሏቸው እየተገለጠላቸው አስደሳች መልኩን ያዩት ነበር።
❖ ይኽነን የቅዱስ ሚካኤልን ውበት ቅዱስ ያሬድ እንዲኽ ይገልጠዋል፡–
❖ “መልአከ ፍሥሐ ዘዐጽፉ መብረቅ
(መጐናጸፊያው መብረቅ የኾነ የደስታ መልአክ፤ አለቃ ሚካኤል የወርቅ ዐመልማሎ ነው)
❖ የመልክአ ሚካኤል ደራሲም ይኽነን ውበቱን ሲገልጠው፡–
❖ “ሰላም ለአክናፊከ እለ በሰማያት ያንበለብሉ
(የጸዳሉ ውበት እንደ ፀሓይ አወጣጥ የኾነ በሰማያት ለሚያንበለብሉ ክንፎችኽ ሰላምታ ይገባል) ይለዋል፡፡
❖ ቅዱስ ያሬድ ደግሞ፡–
❖ “ውእቱ ሊቆሙ ወመልአኮሙ ሚካኤል ስሙ
- ዐይኑ ዘርግብ ልብሱ ዘመብረቅ
- ሐመልማለ ወርቅ”
(ዐይኑ የርግብ (እንደ ርግብ የዋህ፣ ጽሩይ) የኾነ ልብሱ የመብረቅ መጐናጸፊያ የኾነለት የወርቅ ዐመልማሎ ስሙ ሚካኤል የተባለ ርሱ የመላእክት አለቃቸው መሪያቸው ነው) ይላል፡፡
❖ የቅዱስ ሚካኤል ተራዳኢነትና አማላጅነት ቅዱስ ያሬድ እንዲኽ ይገልጠዋል፡–
❖ በ፲ወ፬ቱ ትንብልናከ ዐቢይ ልዕልናከ
- በመንክር ትሕትናከ
- አስተምህር ለነ ሰአልናከ”
(በዐሥራ አራቱ ልመናኽ ምልጃኽ፤ በታላቅ ልዕልናኽ በሚያስደንቅም ትሕትናኽ ሚካኤል ትለምንልን ዘንድ ማለድንኽ)
❖ “ዘወሀበ ትንቢተ ለኤልዳድ ወሙዳድ
- አመ ምጽአቱ ይምሐረነ ወልድ
- ሰአል ለነ ሚካኤል መንፈሳዊ ነገድ
- ከመ ንክሃል አምስጦ እምሲኦል ሞገድ”
(ለኤልዳድና ለሙዳድ የትንቢትን ጸጋ የሰጠ የሚኾን ወልድ በሚመጣ ጊዜ ይምረን ዘንድ ከረቂቅ ነገድ ወገን የኾንኸው ሚካኤል ከሲኦል እሳታዊ ሞገድ ማምለጥ እንችል ዘንድ ለእኛ ለምንልን) ይላል፡፡
❖ “ከናፍሪሁ ነድ ዘእሳት አልባሲሁ ዘመብረቅ ሚካኤል ሊቀ መላእክት ውእቱ ይዕቀብክሙ ነግሀ ወሠርከ ሌሊተ ወመዐልተ” (ከናፍሮቹ የእሳት ልብሶቹ የመብረቅ የኾነ የመላእክት አለቃ ሚካኤል በተራኢነቱ በጠዋትም፤ በሠርክም፤ በቀንም በሌሊትም ይጠብቃችኊ) አለ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ፨
😇 ፈጣኑ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ሆይ አስቀድሞ የተጣላህን በቀል ባለመርሳት ጋሻህን አንሣ። ፈጣኑ መልአክ ሆይ ነበልባላዊ ሰይፍህን በጠላታችን በዲያብሎስ ላይ መዘህ ተነሣሣበት።
_______
_______
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia, Faith, Saints/ቅዱሳን, War & Crisis | Tagged: Abiy Ahmed, Addis Ababa, Addis Abeba, Aksum, Anti-Ethiopia, Axum, ረሃብ, ቅዱስ ሚካኤል, ቅዱስ ያሬድ, ትግራይ, ንፋስ ስልክ, አረመኔነት, አብይ አህመድ, አዲስ አበባ, ኢሳያስ አፈወርቂ, ኢትዮጵያ, ኤዶማውያን, እስማኤላውያን, ኦሮሚያ, ኦሮሞ, ክርስትና, ወንጀል, ዜማ, የጦር ወንጀል, ግራኝ አህመድ, ግድያ, ጠላት, ጥላቻ, ጥምቀት, ጦርነት, ጭካኔ, ጭፍጨፋ, ጸናጽል, ጽዮናውያን, ፀረ-ኢትዮጵያ ሤራ, ፀበል, ፈውስ, Ethiopian Orthodox, Famine, Genocide, Massacre, Rape, St. Michael, St.Yared, Tewahedo, Tigray, War Crimes | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 15, 2022
❖❖❖[ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ ፳፫፥፩]❖❖❖
የማሰማርያዬን በጎች ለሚያጠፉና ለሚበትኑ እረኞች ወዮላቸው! ይላል እግዚአብሔር።
💭 “የዛሬዎቹ አባቶቻችን ምን ይመስላሉ? | ለተዋሕዶ አባቶች የተጻፈ ኃይለኛ ደብዳቤ”
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 2, 2020
“ቤተ ክርስቲያናችን ተዋህዶ እምነታችን በጠራራ ፀሐይ በመንግሥት ተቀናብሮ የከሱ በጎች ሁሉ በአውሬው መንግሥት ተብዬ ሲታረዱ፣ ሲዘረፉ የአፍ ውግዘት ብቻ፤ ይብስ ድርድር አልፎም መሸለም ገንዘብ መለገስ። ታዲያ ከዚህ በላይ ምን ወንጀል አለ። ለመሆኑ በመትረየስ የተረሸኑት አቡነ ጴጥሮስ ስለበጎቻቸው አደራ አይደልም እንዴ የተዋጉ? ከጣሊያን ተስማምተው መነገድ፣ ሕንፃ መገንባት፣ መወፈር፣ ብር ማከማቸት አይችሉም ነበር እንዴ? እውነተኛ እረኛ ስለበጎቹ ነፍሱን ይሰጣል። እናንተ እንኳን ነፍሳችሁን በወደቀበት በደቀቀበት ስፍራ እንኳን ብቅ ብላችሁ አላያችሁትም። ተመዘናችሁ ቀለላችሁ። ተፈረደባችሁ። ግብራችሁ ተክተላችሁ። አብራችሁ የምትሞዳሞዱበት መንግሥት ይታደጋችሁ። እናንተ ለምትፈሩት፣ ለምትታመኑበት ለምትለማመጡት ዓለምን ሁሉ እያጠፋ ያለው በነአሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ቻይና፣ ሳኡዲ አረቢያ፣ በነግብጽ፣ በነአውሮፓ የሚደገፈውን የአብይ የእስላምና የመናፍቅ መንግሥት ፍፃሜውን እናንተም እየተፈፀማችሁ የምታዩት ይሆናል። ትላንት ለወያኔ ዛሬም ለከፋው ዘረኛ ጭምብል ለባሽ የምትታዘዙ ለሥጋ ትርፋችሁ ስትሉ በአገሪቱ የተበተኑትን የተዋህዶ ልጆች ሲበሉና ለአውሬ ንጥቂያ ሲሆኑ እያያችሁ፣ ለአውሬው የምትሰግዱ ከሆነ፣ ጠባችሁ ግጭታችሁ ከማን ነው? አዎን ከልኡል ነው። ካከባራችሁ፤ የከበረውን ሃላፊነት የእረኝነት ሥራ ከሰጣችሁ ከሃያሉ እግዚአብሔር ጋር መሆኑን በተግባራችሁ አረጋግጣችኋል። እግዚአብሔር ፈራጅ አምላክ ነው። በጎቹን ለአውሬ የሰጣችሁ። እግዚአብሔር ፈርዶባችኋል። ከእረኝነቱም ተሰናብታችኋል። ፍርዳችሁም ይከተላችኋል።”
ከደብዳቤው ጋር ሙሉ በሙሉ እስማማለሁ። ወቅቱን ጠብቆ በጥንቃቄ የተጻፈ ደብዳቤ ነው። እስኪ ተመልከቱት፦ የቅኔ ተማሪ ህፃናት እየተራቡ(አቡነ ሀብተማርያም ገዳም) ቤተክህነት ግን “ከንቲባ” ለተባለው ወሮበላ አሥር ምሊየን ብር ትሰጣለች። ከንቲባው ደግሞ ይህን ገንዘብ የሰይጣን አምልኮ መስጊድ ማሰሪያ ይውል ዘንድ ለአህዛብ ይለግሳል። በዚህ አጋጣሚ የማሳስበው የተዋሕዶ ልጆች መሀመዳውያኑ እራሳቸው ላቃጠሉት መስጊድ ማሰሪያ ብለው አንድም ሳንቲም ማዋጣት እንደማይኖርባቸው ነው። ይህን ካደረጉ ትልቅ ቅሌት ነው።
_______
_______
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia | Tagged: Abiy Ahmed, Anti-Ethiopia, Axum, መንፈሳዊ ውጊያ, መንፈሳዊ-ውጊያ, ረሃብ, ሰይጣን-አምልኮ, ሰይፍ, በጎች, ቤተ ክሕነት, ተዋሕዶ, ትግራይ, ንፋስ ስልክ, አረመኔነት, አባቶች, አክሱም, አውሬው-መንግስት, ኢትዮጵያ, ኢትዮጵያዊነት, ኢየሱስ ክርስቶስ, እረኞች, ኦርቶዶክስ, ክርስትና, ወረርሽኝ, ዋቄዮ-አላህ, ዘር ማጥፋት, ዲያብሎስ, ጀነሳይድ, ግራኝ አህመድ, ጠላት, ጥላቻ, ጦርነት, ጭፍጨፋ, ጽዮን, ፀረ-ተዋሕዶ, ፀረ-ኢትዮጵያ ሤራ, Ethiopia, Famine, Genocide, Human Rights, Massacre, Sheep, Shepherd, Tewahedo, Tigray, Trinity, Zion | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 9, 2021
ይህ የእባቡ ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ ሴራ እንደሆነ እርግጠኛ መሆን ይቻላል። “አል ነጃሽ” የተባለ መስጊድ የአፍሪቃው ሕብረት ሕንፃ ፊት ለፊት፤ የሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ንብረት በሆነው ቦታ ላይ ከታከለ ኡማ ጋር ፈቃዱን ሰጥቷቸው የለ። አሁን ደግሞ ግራኝ አማራዎችን ወደ አደባባይ እየወጡ፤ “ዳውን ዳውን አብይ!” እንዲሉ አድርጎ በትግራይ ሕዝብ ላይ ከሚሰራው ወንጀልና ዲያብሎዊ ተግባር እራሱን ነፃ ለማድረግ እንደሞከረው ዛሬ ለሙስሊሞቹ፤ “ወደ መስቀል አደባባይ ሂዱና፤ ‘ዳውን ዳውን አብይ!’ በሉ”ብሏቸዋል። ግራኝ ኦሮሞዎች ቀስበቀስ ተደላድለው ወደ አዲስ አበባ እየገቡ ከተማዋን ይቆጣጠሩ ዘንድ መሀመዳውያኑን እንደ መጥርጊያ አድርጎ እየተጠቀመባቸው ነው። የኦሮሞውም የሙስሊሙም ዓላማ አንድ ዓይነት ነው፤ እርሱም፤ ኢትዮጵያን ማፈራረስ፣ ተዋሕዶ ክርስትናን ማዳከምና ክርስቲያኖችን ለዋቄዮ-አላህ መስዋዕት አድርጎ መጨረስ።
እናታችን ቅድስት ማርያም ግን አትፈቅድላቸውም!
እንደሚታወቀው ኦሮሞዎች ልክ በግንቦት የልደታ ማርያም ዕለት የአምልኮ ዛፎቻቸውን በቅቤ መቀባት ይጀምራሉ። አዎ! “ዋቄዮ-አላህ”
👉 ከሦስት ዓመታት በፊት ይህን አቅርበን ነበር፦
✞✞✞“በልደታ ማርያም ዕለት የጣዖቱ ዋቄዮ–አላህ ድል ተነሳ ፥ ተዓምረኛ የቅድስት አርሴማ ጸበል ፈለቀ”✞✞✞
በጎጃም ይኖሩ የነበሩ ሁለት ክርስቲያኖች በራዕይ ተመርተው ወደ አዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ በመምጣት ቪዲዮ ላይ የሚታየውን የቅድስት አርሴማን ተዓምረኛ ጸበል ለማግኘት በቅተው ነበር።
ጸበሏ በፈለቀችበት ቦታ ላይ፡ ከ20 ዓመታት በፊት፡ ጣዖታዊውን አምላክ ዋቄዮን የሚያመልኩት ወገኖች ከአርሲ እና ባሌ ድረስ ወደዚህ ቦታ በመምጣት ከግንቦት ልደታ ማርያም አንስቶ ለአንድ ወር ያህል የዋንዛ ዛፉን ቅቤ እየቀቡ ይቀቡበት ነበር። በራዕይ የተመሩት ወገኖች ልክ እዚህ ቦታ ላይ እንደደረሱ በመቶ የሚቆጠሩ ታዛቢ ም ዕመናን በተገኙበት የፀበሉ ውሃ ፊን ብላ ወጣች። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ በቦታው የቅድስት አርሴማ እና ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያናት ህንጻዎች ጎን ለጎን ተሠሩ፡፡
በአዲስ አበባ ነፋስ ስልክ ለቡ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በምትገኘው በዚህች ጸበል ብዙ ወገኖች፤ አህዛብ ሳይቀሩ እንደተፈወሱ የተለያዩ ምስክርነቶች ለመስማትና በቦታውም ሱባኤ ገብተው እየተፈወሱ ያሉ ብዙ እህቶችና ወንድሞችን በዓይኔ ለማየት በቅቼ ነበር።
እንግዲህ ይታየን፤ ላለፉት 150 ዓመታት ለኢትዮጵያ ውድቀት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱት ዛፍ–አምላኪዎቹ “ኦሮሞዎች”እዚህ ድንቅ ቦታ ላይ ከግንቦት ልድታ አንስቶ ለአንድ ወር ያህል የጣዖቱን ኦዳ ዛፍ ቅቤ እየቀቡና ደም እያፈሰሱ ሲያመልኩበት ነበር። መንፈሳውያን ኢትዮጵያውያን መምጣት እንደጀመሩና ጸበሉም እንደፈለቀ የስጋ ፍጥረታቱ እንደ ጉም ብትን ብለው ሄዱ። እስኪ ዛሬ የዋቄዮ–አላህ አህዛብ መንግስት ቦታውን ያስመልስ እንደሆነ እናያለን፤ የ፮ ወር ጊዜ ነው ያለው።
በጎጃም ይኖሩ የነበሩ ሁለት ወጣቶች በራዕይ ተመርተው ወደ አዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ በመምጣት ይህችን ተዓምረኛ ጸበል ለማግኘት በቅተዋል። ጸበሏ በፈለቀችበት ቦታ ላይ፡ ከ20 ዓመታት በፊት፡ ጣዖታዊውን አምላክ ዋቄዮን የሚያመልኩት ወገኖች የዋንዛ ዛፉን ቅቤ ይቀቡበት ነበር።
አንድ ሌላ የገረመኝ ነገር፡ ቪዲዮው ላይ እንደሚሰማው፡ አንድ አባት እኔን በቅድስት አርሴማ ጸበል በሚያጠምቁበት ወቅት አንዲት እርግብ በርራ በመምጣት እራሳቸው ላይ ልታርፍባቸው መብቃቷ ነው። በዕለቱ እንዴት ከሩቅ ሠፈር ወደዚህ ቦታ ተመርቼ ለመሄድ እንደበቃሁ አላውቅም፤ ታክሲው ዝምብሎ አወረደኝ፤ ያውም እዚያ የደረስኩት የመጠመቂያው ሰዓት ካለፈ በኋላ ነበር። ተዓምር ነው!
በአዲስ አበባ ለቡ አካባቢ በምትገኘው በዚህች ጸበል ብዙ ሱባኤ የሚገቡ እህቶችና ወንድሞችን ለማየት በቅቼ ነበር።
እንኳን አደረሰን!”
_____________________________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith | Tagged: ለቡ, ልደታ ማርያም, መስቀል አደባባይ, መጠመቅ, ሙስሊሞች, ቅድስት አርሴማ, ንፋስ ስልክ, አርሴማ, አብይ አህመድ, አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ, ኦሮሞዎች, ኦዳ, ዋቄዮ-አላህ, ዛፍ, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት, ጂሃድ, ግንቦት, ፈውስ | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 21, 2020
እንኳን ለሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤል አመታዊ የንግስ በዓል አደረሳችሁ። በዓሉን የበረከት በዓል ያድርግልን።
_______________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: Addis Abeba, መልክአ ቅዱስ ሚካኤል, ቅዱስ ሚካኤል, ንፋስ ስልክ, አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ, ክርስትና, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት, ፀበል, Ethiopian Orthodox Tewahedo Faith, St. Michael | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 23, 2019
“የተጠመቅኩት፣ በመሰቀል የተሰቀልኩትና የተሰዋኹት ለአመኑኝና ቃሌን ለተቀበሉኝ ሁሉ ለስጋቸው በረከት ለነፍሳቸው ድኽነት ለመስጠት ነው!”
ለእያንዳንዱ ለተጠመቀው ክርስቲያን፣ ስጋው ለተቆረሠለት፣ ደሙ ለፈሰሰለትና እግዚአብሔር ሰው ለሆነለት ክርስቲያን ጠባቂ መላእክት አሉት።
_____________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: Addis Abeba, ቅዱስ ሚካኤል, ንፋስ ስልክ, አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ, ክርስትና, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት, ጥምቀት, ፀበል, Ethiopian Orthodox Tewahedo Faith, St. Michael | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 10, 2018
በጎጃም ይኖሩ የነበሩ ሁለት ወጣቶች በራዕይ ተመርተው ወደ አዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ በመምጣት ይህችን ተዓምረኛ ጸበል ለማግኘት በቅተዋል። ጸበሏ በፈለቀችበት ቦታ ላይ፡ ከ20 ዓመታት በፊት፡ ጣዖታዊውን አምላክ ዋቄዮን የሚያመልኩት ወገኖች የዋንዛ ዛፉን ቅቤ ይቀቡበት ነበር።
አንድ ሌላ የገረመኝ ነገር፡ ቪዲዮው ላይ እንደሚሰማው፡ አንድ አባት እኔን በቅድስት አርሴማ ጸበል በሚያጠምቁበት ወቅት አንዲት እርግብ በርራ በመምጣት እራሳቸው ላይ ልታርፍባቸው መብቃቷ ነው። በዕለቱ እንዴት ከሩቅ ሠፈር ወደዚህ ቦታ ተመርቼ ለመሄድ እንደበቃሁ አላውቅም፤ ታክሲው ዝምብሎ አወረደኝ፤ ያውም እዚያ የደረስኩት የመጠመቂያው ሰዓት ካለፈ በኋላ ነበር። ተዓምር ነው!
በአዲስ አበባ ለቡ አካባቢ በምትገኘው በዚህች ጸበል ብዙ ሱባኤ የሚገቡ እህቶችና ወንድሞችን ለማየት በቅቼ ነበር።
እንኳን አደረሰን!
______
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: ለቡ, መጠመቅ, ቅድስት አርሴማ, ንፋስ ስልክ, አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ, እርግብ, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት, ፈውስ | Leave a Comment »