Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • March 2023
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    2728293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘ንግሥት ሕንድቄ’

ተዓምር በ ሱዳን | ንግሥት ሕንድቄ ከሻሪያ እስረኝነት ነፃ ወጣች | ፕሬዚደንት ኦማር አልበሽር ታሠረ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 11, 2019

ባለፈው ባቀረብኩት ቪዲዮ ላይ የሃይድ ፓርኩ ጀግናው ክርስቲያን “ቦብ”፡ የኑቢያኖችን ስቃይ በሚመለከት ሃይለኛ መልዕክት አስተላልፎ ነበር፣ እኔም ቀጥዬ ስለ ሰሜን ሸዋ ባቀረብኩት ቪዲዮ ላይም ለኢትዮጵያ እውነተኛ ፍቅር ያለው ሰው ከጦር ሠራዊታችን ቶሎ መነሳት አለበት ብዬ ነበር፤ ግን የሱዳን “ኢትዮጵያውያን” ቀደሙን!

ኑቢያዊቷላ ሳላህ ትባላለች፤ ባላፉት ወራት በሱዳን የፀረሻሪያ መንግሥት እንቅስቃሴውን ከሚመሩት ሴቶች አንዷ ናት። አሁን ግን የእንቅስቃሴው ዋና ምልክት ለመሆን በቅታለች። እናም ሐንዳቃ” በሚል ስያሜኑቢያ ንግሥትተብላ ትጠራለች ተሳክቶላታል፤ ጎበዝ፣ ጀግና!!!

በግራኝ አህመድ መንግስት ውስጥ በአረብ መጋረጃ ተሸፋፍነው ወገኖቻችንን ለረሃብና ለመፈናቀል እያበቁ ያሉት ከሃዲዎች እንዴት ያፍሩ፤ አሁን ጆንያ ውስጥ መደብቅ ይኖርባቸዋል።

ያው እንግዲህ፡ የእስልምና ባርነት በጣም የታከታት፣ ጥቁሩን መጋረጃ መልበስ የመረራት ወጣቷ ሱዳናዊት ነጭ ልብስ ለበሳ በአደባባይ ላይ በመውጣት የመሬት መንቀጥቀጥ በሱዳን አስከትላለች።

በዛሬው ዕለት ለሠላሳ ዓመታት ያህል የእስልምና እና የሻሪያ ሕግን አጥብቆ በመከተል ለብዙ ሚሊየን ሱዳናውያን ክርስቲያኖች በደቡብ ሱዳን፤ እንዲሁም ሌሎች ሚሊየን “ጥቁር” ሙስሊሞች በዳርፉር እንዲጨፈጨፉ የሠራው ፕሬዚደንት ኦማር አልባሽር ከሥልጣኑ እንዲወርድ ተደርጎ ታሥሯል። የመንግስት ፍንቀላውን ያደረገው በመከላከያ ሚንስትሩ የሚመራው የሱዳን ጦር ሠራዊት ነው።

በኢትዮጵያም በፍጥነት ተመሳሳይ እርምጃ መወሰድ ይኖርበታል፤ ንግሥት ሕንድቄ መነሳት ይኖርባታል፤ የተዋሕዶ ኢትዮጵያ ልጅ የሆነ እውነተኛ አገር ወዳድ ከጦር ሠራዊቱ በመውጣት እጁን መዘርጋትና ግራኝ አህመድን እና ኢሳያስ አፈወርቅን በማስወገድ ኢትዮጵያዊ የሽግግር መንግሥት እንዲቋቋም ማድረግ ይኖርበታል።

________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Infos | Tagged: , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: