💭 የአማራ ልሂቃን ሞተዋል፤ ወይንስ አክሱም ጽዮን ጭምብላቸውን በጥቅምት ፳፬/፪ሺ፲፫ ዓ.ም ገለጠችባቸው?
🌑 ክፍል ፩
👉 መጋቢት መግቢያ ላይ ከሻለቃ ዳዊት ወልደ ጊዮርጊስ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ
ትርጓሜው የኔ ነው፦
“ትግራይን አስመልክቶ እየወጣ ያለው መረጃ ከሦስተኛ አካል ነው፤ ከ፬ ወራት በኋላ“ማስረጃ ካላየን” ምንም መናገር አንችልም።” ስለዚህ የትግራይ ሕዝብ ይበደል፣ ግፍ ይድረስበት፤ ለጊዜው የምናውቀው ነገር የለምና!”
💭 ይገርማል፤ ዛሬም ወያኔ! ወያኔ ወያኔ! ሁሌ ወያኔ፤ ምንም የተሻለ አማራጭ ሳይመጣና በጎ የተሠራ ነገር ሳይኖር። አገሪቷ ከምንግዚውም በከፋ ሁኔታ ላይ በምትገኝበት በዚህ ወቅት ለአገሪቷ ውድቀት ተጠያቂ የሆነው ህገ-ወጡ የግራኝ ፋሺስታዊ አገዛዝ በትግራይ ህዝብና በወያኔ ላይ ማን ፈራጅ አረገው?
ሞራላዊ ልዕልናስ አለውን? መቼስ ከኦሮሞ ብልጽግና ጋር ሲነጻጽር ትግሬ ወያኔ ሞኝ እና መልአክ እንደሆነ እያየነው እኮ ነው!
ሻለቃ “ወያኔ የኢትዮጵያን ኤኮኖሚ ደቁሷታልና ካሳ መክፈል ይኖርበታል (ይህች በአማራ ልሂቃኑ ዘንድ ተወዳጅ የሆነች ከንቱ ፕሮጀክሽን ናት።) አቤት! አቤት!ሻለቃ፤ የፋሺስት ደርግን ዘመን ረሷት እንዴ?
ሚሊዮኖች የረገፉበት ረሃብ ስንቴ ተከሰተ? ያውም በትግራይ ሕዝብ ላይ? ሦስት ጊዜ!!ለምን ሐሰት ይናገራሉ? ሌላው ቢቀር ኢትዮጵያ በታሪኳ ከፍተኛ የኤኮኖሚ ዕድገት ያሳያቸው በወያኔ ዘመን መሆኑን ምናለ ያለ ቅናትና ምቀኝነት ሃቁን ብትቀበሉት? ምነው ጃል?! ዓይናችን እያየው? ባዕዳውያኑ ሳይቀሩ እየመሰከሩ? ለምድን ነው ጥሩውን ጥሩ? መጥፎውን መጥፎ የማትሉት? ዕድገቱን ያመጡት ትግሬዎች ስለሆኑ?
አይ ሻለቃ! የኢትዮጵያውያን ሳይሆን የአማራ መሬት? ወልቃይት እርስቴ? በትግራይ ሕዝብ ላይ እየተካሄደ ያለውን ጭፍጨፋ “የኢትዮጵያ ሕዝብ ዛሬም ይደግፈዋል”። የትኛው “ኢትዮጵያዊ?”
የሚገርምና የሚያሳዝን ነውዛሬ “ወያኔ” ማለት ናዚዎች “አይሁድ” ይሉት እንደነበረው
“የትግራይን ሕዝብ” መሆኑ ነው። ዛሬም አረቦችና ፀረ-ሴማውያን አይሁዶችን ለማጥቃት ሲያስቡ “እስራኤል” እንደሚሉት ፀረ- ሴማዊ-ትግራዋያንም “ወያኔ” “ጁንታ” የሚሉትን የኮድ ቃላት ሲጠቀሙ ይታያሉ።
💭 ልብ በሉ፦ ስለ ህዋሃት ፕሮፓጋንዳ ያዘኑ በመምሰል ይህን ሊደብቁት ያልቻሉትን መልዕክት ለማስተላለፍ ይሻሉ፤ “የትግራይ ሕዝብ የዚህ ጥፋት አካል ነው፤ ልክ እንደ ናዚ ዘመን ጀርመን ህሊናቸው በሂትለር ፕሮፓጋንዳ ታጥቧል”፤ ሃሳቡ ሲገለበጥ፤ “ስለዚህ እንደ ፮ ሚሊየን አይሁዶች መጨፍጨፍ አለባቸው”። ዋው!
ግን ሻለቃ፤ እርስዎ ማን ነዎትና ነው ከሌላው “ኢትዮጵያዊ ነኝ” ባይ በላቀ ፈሪሃ እግዚአብሔር ባለው የትግራይ ሕዝብ ላይ ይህን ያህል የሚፈርዱት?
ሻለቃ፤ ምን ያህል ቢንቁት ነው፤ ከሌሎች በጠነከረ ተዋሕዶ ክርስቲያን የሆነውን የትግራይን ሕዝብ ለኢ-አማንያኑ ህወሃቶች ፕሮፓጋንዳ እንዲህ በቀላሉ ሰለባ ሆኗል ለማለት የደፈሩት? ፺/ 90% የሚሆነውን ሜዲያውን የተቆጣጠሩት የእናንተ የአማራ ልሂቃኑ ፕሮፓጋንዳ አይብስምን? እንግዲህ የአንድ ፕሮፓጋንዳ ውጤታማናት የሚለካው በተግባር በሚታዩ ሥራዎች ነው። ናዚዎች ባካሄዱት ፕሮፓጋንዳ አብዛኛው የጀርመን ሕዝብ ሂትለርን ተቀብሎት ነበር። የሂትለሯ ጀርመን ደግሞ ከብሪታኒያ እስከ ሶቪየት ሕብረት በጣም ብዙ ሃገራትን ለመውረርና ብዙ ሕዝቦችን ለመጨረስ፣ ስድስት ሚሊየን አይሁዶችንና ብዙ ጂፕሲ/ሮማዎችንና ሌሎች አናሳ ብሔሮችን የጨፈጨፈች ሃገር ነበረች። ታዲያ መቼ ነው ትግራይ፣ የትግራይ ሕዝብ ወይንም ወያኔ ሌሎች ሃገራትንና ሕዝቦችን በመውረር ጭፍጨፋ ያካሄዱት። ከሦስት ዓመታት በፊት እንደ ኢትዮጵያውያን የራሳቸው ከተማ የሆነችውንና ከደርግ ጨለማ ነፃ ያወጧትን አዲስ አበባን አንድ ጥይት ሳይተኩሱና ዜጎችን ሳይገድሉ ለቅቀው በመውጣት ወደ መቀሌ አልገቡምን። እውነት እንነጋገር ካልን የናዚን ዓይነት ፕሮፓጋንዳ ተጠቅመው በሥራ ላይ ያዋሉት የትግራይን ሕዝብ እግዚአብሔር የሰጣቸው የትግራይ ምድር ድረስ ተከታትለው በመግባት ወረራውን ያካሄዱት የአማራ እና ኦሮሞ ሕዝቦች አይደሉምን? በ፮ ሚሊየን ትግራዋያን ላይ እንደ ሂትለር የጅምላ ጭፍጨፋ እየፈጸሙ ያሉት ኦሮሞዎችና አማራዎች አይደሉምን? ታዲያ ለናዚ ዓይነት ፕሮፓጋንዳ ሰለባ የሆኑት ኦሮሞዎችና አማራዎች አይደሉምን? በዳዩ ተበዳይ ሆኖ የሚቀርብበት ዓለም የፈሪሃ እግዚአብሔር የሌለበት የዋቄዮ-አላህ ዓለም ብቻ ነው።
💭 እንደምናየው ዛሬ አማራዎች በተቀላቀሏት የአህዛብ (መሀመዳውያን፣ ሂንዱዎች፣ ኦሮሞዎች፣ ግብረ-ሰዶማውያን፣ ዘረኞች) ዓለም ይህ ዓይነት ባሕርይ ወይም የውጊያ ስልት፤ በእንግሊዝኛው “Projection” አንጸባራቂነት (ማስመሰል/ማሳየት) ይባላል፤ ማለትም እራሳቸው ቆሻሾች መሆናቸውን ስለሚያውቁ ከመቀደማቸው በፊት እራሳቸውን ንጹህ አድርገው ሌላውን ቆሻሻ ያደርጋሉ። እነርሱ መናፍቅ ሆነው ሌላውን ኩፋር/ መናፍቅ ይላሉ፣ እነርሱ በአመንዛሪነት፥ በዝሙት፥ በሌብነት፥ በውሸት፣ በስድብ፣ በግድያ ዓለማቸው ውስጥ ተዘፍቀው ሌሎች እነዚህ ሃጢአቶች ፈጽመዋል ብለው ይኮኑኗቸዋል ፣ እነርሱ በዳዮች እና ገዳዮች ሆነው እኛ ተበድለናል እያሉ ሌላውን ይወቅሳሉ። ወራሪዎቹ አቴቴ ኦሮሞዎች “ምኒሊክ ጡት ቆራጭ ነበር” ሲሉ “እኛ ጡር ቆራጮች ነበርን ወደፊትም እንሆናለን” ማለታቸው ነው።
🌑 ክፍል ፪
👉 ሻለቃ ዳዊት ከቴዎድሮስ ፀጋዬ ጋር፤ በጦርነቱ ማግስት ፥ ከ፬ ወራት በፊት፤
“አላውቅም !አላየሁም! አልሰማሁም!” ፥ ግን በትግራይ በአማራዎች ላይ ጀነሳይድ ተፈጽሟል
እግዚኦ!ጀነሳይድ በአማራዎች ላይ ብቻ ነው! ሌሎቹሽ ሻለቃ? በትግራይ ሕዝብ ላይ እየተፈጸመ ስላለው፡ ታይቶም ተሰምቶም ስለማያውቀው ጀነሳይድ ግን ያው እስከ ዛሬ ድረስ ጸጥ ብለዋል! እንዲያውም “የትግራይ ሕዝብ የናዚ ዓይነት ፕሮፓጋንዳ ሰለባ ሆኗል” ብለው ያለአግባብ ፍርድ ይሰጣሉ። እንደው ምን ነካዎት፤ ሻለቃ?
አይ ሻለቃ፤ ከዚህ ወንጀለኛ “መሪ” ጋር ተደምረው ሳሉ “አብይ በትግራይ ሕዝብ (በ“ወያኔ”)ላይ መዝመቱ ተገቢ ነው” ይሉናል! ታዲያ እርስዎም ግራኝ በትግራይ ሕዝብ ላይ በሚያካሂደው ጀነሳይድ ተባባሪ ሆኑ እኮ! አማራው “እርስቱን” ያስመልስ ዘንድ ብቻ ነው ድጋፉን የሰጡት? በዚያ ላይ የኢሳያስ ጣልቃ መግባት ወያኔን/ትግራዋይን እስካጠፋልን ድረስ ተገቢ ነው! ይሉናል። እንዴ ምን ዓይነት ግብዝነት ነው?!
አዩ አይደል፤ ሻለቃ! ትክክለኛው ኢትዮጵያዊ ልክ እንደ ቴዎድሮስ ፀጋዬ ዓይነቱ ነው። ከቻሉ ይመስክሩለት።
የትግራይ ሲሆን፤ “እ እ እ…ማስረጃ፣ ማረጋገጫ” ፥ ከዚያም ወዲያው ርዕሱን ወደ “ወያኔ! ወያኔ! ወያኔ!” መቀየር። ሁሉም ነገር በግልጽ ይታያል እኮ!“አማራው ብቻ ነው ለኢትዮጵያው የቆመ! አማራ ሃጢዓት የለውምና “ኢትዮጵያ! ኢትዮጵያ!የሚለውን “ወልቃይት እርስቴ” አማራን ተከተሉ፤”
ሻለቃ፤ ታዲያ ከ፬ ወራት በኋላ ምነው ዛሬ እንደ ቴዲ ለትግራይ ሕዝብ አልቆሙም? ይህ አቋም እኮ እንኳን ለንስሐ ለአብሮ መኖር እንኳ አያበቃም።
💭 የተከበሩ ሻለቃ ዳዊት ወልደ ጊዮርጊስ፤ በግልጽነትዎ አከብርዎት ነበር፤ በእነዚህ ፬ ወራት ግን ደስ የማይለውን ማንነትዎን ለማየት በመቻሌ እያዘንኩ፤ ያወገዙትን የደርግ አገዛዝ የገረሰሰዎለትን የትግራይ ሕዝብን በሰማዕቱ በቅዱስ ጊዮርጊስ ስም ይቅርታ ጠይቀው “ንሰሐ ይግቡ!” ለማለት እንድደፍር ይፍቀዱልኝ። ያኔ በብዙ ሚሊየን የሚቆጠሩትን ትግራዋይን ለረሃብ የቀጣውን የመንግስቱ ኃይለ ማርያምን የኦሮሞ አገዛዝ ያገለግሉ ነበር። አላውቅም፣ ለመፍረድም አልደፍርም ፥ ሆኖም መንግስቱን ትተውት ወደ አሜሪካ የሸሹት ምናልባት ከተጠያቂነት ለማምለጥ ሊሆን ይችላል ፥ ወይንም ደግሞ ተጸጽተው ይሆናል። ተጸጽተው ከሆነ በጣም ጥሩ፤ ዛሬም ሥልጣን ላይ ያሉት የኦሮሞው የግራኝ አብዮት አህመድ አገዛዝ ባለሥልጣናት የእርስዎን የጸጸት ፈለግ ተከትለው የሥልጣን ወንበሮቻቸውን ባፋጣኝ ቢያስረክቡ ይሻላቸዋል፤ በእርስዎም በኩል በድጋሚ ተጸጽተውና ሰሞኑን የያዙትን አቋም ቀይረው በምዕራብ ትግራይ በጀነሳይድ እና ዘር ማጽዳት ወንጀል የሚያስጠይቅ ከፍተኛ ግፍ በመስራት ላይ ያሉት የፋሺስት አማራ ሚሊሺያዎች የትግራይን ግዛት ለቀው እንዲወጡ ጥሪዎትን እንዲያስተላልፉ እላለሁ።
______________________