በጣም የሚገርም ነው፤ ልክ በእህቶቻችን ላይ የደረሰው ግፍ ነው በአረቦቹ ልጆቻቸው ላይ እየደረሰ ያለው፤ “እርስበርስ አባላቸው!” እያልን ስናደርስ የነበረው ጸሎታችን እየሠራ ነው ማለት ነው።
የምታስለቅስ ሴት ናት፤ እግዚአብሔር ይድረስላት!
ይህን ቪዲዮ ህንድ አካባቢ ከሚገኝ መርከብ ላይ ሆና ነው የለቀቀችው። ይህን “የመጨረሻዬ ነው” ያለችውን ቪዲዮ ከለቀቀች በኋላ የት እንዳለች አይታወቅም፤ ጠፍታለች።
የ 33 ዓመቷ ምስኪን፡ ልዕልት ወይም ሼካ ላቲፋ መሀመድ አል ማክቱም ትባላላች። የዝነኛው የዱባይ እና የተባበሩት አረብ ኤሚራቶች መሪ የሸክ መሀመድ ቢን ራሺድ አል ማክቱም ነው (መሀመድ ሁልጊዜ መቅሰፍት ነው)። በጥቂቱ የሚከተለውን ለማመን የሚከብድ (100% አምናታለሁ፡ እግዚአብሔር ይርዳት) ትናገራለች ትላለች፦
በዱባይ የመኖር ምንም ምክኒያት የለኝም
በርግጥ እዚያ የምወዳቸው ሰዎች ቢኖሩም ለመሄድ አልሻም፣ እነርሱ እዚህ መጥተው ሊያዩኝ ይችላሉ።
ከዚህ በኋላ የት፣ እንዴት እንደምኖር አላውቅም፣ በሌላ በኩል አማራጭ ስላለኝ ጥሩ ነገር ነው
አባቴ ለብዙ ሰዎች ሞት ተጠያቂ ነው! ትልቅ ወንጀለኛ ነው!
በዱባይ ፍትህ የለም፤ በተለይ ለሴቶች! እዚያ የሴቶች ህይወት ዋጋ የለውም!
ይህ ቪዲዮ የህይወት ዋስትናዬ ነው፤ ከለቀክኩት በኋላ ምናልባት በህይወት እኖር ወይም አልኖር ይሆናል።
እናቴ ከአልጀርያ ስትሆን፣ አባቴ ደግሞ የኤሚራቶች ጠ/ ሚኒስትር እና የዱባይ መሪ ሸክ መሀመድ ቢን ራሺድ አል ማክቱም ነው
አባቴ ከእናቴ ሦስት ሴት ልጆች አሉት እኔ የመካከለኛዋ ነኝ።
አባቴ ከ6 ሚስቶቹ ባጠቃላይ 30የእኔ ወንደሞችንና እህቶችን በተጨማሪ ወልዷል።
ይህን ቪዲዮ ለመሥራት የፈልግኩት ምናልባት የመጨረሻው ቪዲዮየ ሰለሚሆን ነው።
ምናልባት ይህ ቪዲዮ የአባቴን ቅሌት ለማጋለጥ ይበቃ ይሆናል። አባቴ ክብሩን ለመጠበቀ ሲል
ንጹሃን ሰዎችን የሚገድል ጨካኝ ሰው ነው።
አባቴ የራሱ ጉዳይ ብቻ ነው የሚያሳስበው እንግዲህ ይህ ቪዲዮ እኔንም ያስገድለኝ ይሆናል።
ቪዲዮን በምትመለከቱበት ወቅት ምናልባት ተገድዬ ልሆን እችላለሁ።
በ2000 ዓ.ም የ18 ዓመቷ እህቴ፡ ሻምዛ ወደ እንግሊዝ አገር አመለጠች። ዱባይ ነፃነት ሰላልነበራት ነበር ያመለጠችው። ነፃ በሆኑ አገሮች የሚፈቀዱትን ነገሮች እዚያ ማድረግ ስላልቻለች፤ ለምሳሌ፦ መኪና መንዳት፣ መጓዝ ወዘተ
በኑሯችን የመምረጥ መብት የለንም። እህቴ ስታመልጥ እኔ የ14 ዓመት ልጃገረድ ነበርኩ
እንግሊዝ እያለች አልፎ አልፎ እንጻጻፍ ነበር፣ ሁልጊዜ እነደ እናቴ አድርጌ ነበር የማያት። በማምለጧ ደስ ቢለኝም ግን አጠገቤ ባለመኖሯ ሁሌ ይከፋኝ ነበር።
እህቴ ዱባይ ከነበረችው ጓደኛዋም ጋር ትደዋወል ነበር፤ አባቴ ይህን ስላወቀ በሮሌክስ ሰዓት ደልሎ አድራሻውን እንድታጣራለት ጠይቋት ነበር።
እህቴንም ከሴትየዋ ጋር እንዳትደዋወል አስጠነቀቅኳት ግን በብቸኝነት መደዋወሏን ስለቀጠለችበት
ያለችበትን ቦታ አጣርተው አገኙባት።
የአባቴ ሰዎች በእንግሊዝ መንገድ ላይ እየሄደች እያለች ጠልፈው በመኪና ወደ አንድ ሂሊኮፕተር ወሰዷት።
ከዚያም በፈረንሳይ አድርገው ወደ ዱባይ አመጧት። በግል አውሮፕላን ውስጥ ማደንዘዣ መርፌ ተወግታ ነበር። ዱባይ መጥታ ቤተመንግሥት ውስጥ በሚገኝ አንድ ድንኳን ውስጥ ታሠረች።
እኔና ሌላው እህቴ ልብሶች እና ስልክ በድብቅ እንልክላት ነበር
ስልኩንም እንዳገኘች እንግሊዝ ከሚገኙ ጋዘጤኞች ጋር ግኑኝነት ማድረግ ቻለች
ግንቦት 2001 ዓ.ም አካባቢ ታሪኳ በጋርዲያን ጋዜጣ ወጣ። ይህን ስሟን ጉግል በማድረግ ማጣራት ይቻላል።
ፖሊሶች ይህን ባወቁ ጊዜ እህቴን አምጥተው እንድትናዘዝ ገረፏት፤ ስለግርፋቱም ወደ እኔ መጥታ አጫወተችኝ።
ሌላዋ እህቴም አንድ ክፍል ውስጥ ተዘግቶባት ነበር የምትኖረው። አንድ ቀን ስላመለጠችው እህቴን ታሪክ
በወረቀት ላይ ጽፌ በበሯ ሥር እኒድወረወርላት አደርግኩ።
እንዳነበበቸውም በጣም አበደች፣ ክፍሏን ስታተራምሰው፣ መስኮቱን ስተሰብረው ይሰማ ነበር
ከክፍሏም ወጥታ በመሮጥ የአባቴን አገልጋዮች በቢለዋ ታስፈራራ ነበር።
በኋላ ተያዘች፣ ወደ እስር ቤትም አስገብተው እርሷንም ገረፏት፤ ግን ምንም እንደማታውቅ ተገነዘቡ።
በዚያ ዕለት ሁሉንም እህቶቼን አጣኋቸው ግኑኝነት ሁሉ ተቋረጠ፣ ከዓመት በኋላ የ16 ዓመት ልጃገረድ ሆኘ ከቤት ማምለጥ ፈለግኩ።
በ2002 ዓ.ም ኢንተርኔት እንድጠቀም አይፍቀደልኝም፤ ስልክም ቢሆን ጓደኛየ ደብቃ የሰጠችኝ ነበር።
ሰለዚህ ኤሚራቶችን ለቅቄ መውጣትና ወደ ሌላ አገር ሄጄ ጠበቃ እፈልጋለሁ ብዬ አሰበኩ፤
ወደ ኦማን ማምለጥ ፈለግኩ።
ብያዝ፡ ቢከፋ ቢከፋ እስርቤት ከእህቴ ከሻምዛ ጋር ነው የሚጨምሩኝ፤ ከርሷ ጋር መሆኔ ደስታዬ ነው
ስለዚህ በ2002 ዓ.ም አመለጥኩ፤ ግን ጠረፍ ላይ ተያዝኩ፤ የዋህ ስለነበርኩ፡ በረሃው ክፍት መስሎኝ ነበር፤ ጠረፍ የሚጠበቅ አይመስለኝም ነበር፤ ማን መሆኔን እንዳወቁ ወደ ዱባይ መለሱኝ
የአባቴ ታመኝ ሰው በአባቴ ትዕዛዝ እስር ቤት አስገባኝ።
እስር ቤት ውስጥ ይገርፉኝ ነበር አንዱ ሰው ሲይዘኝ ሌላው ደጋግሞ ይገርፈኛል። መጀመሪያ ላይ ለግማሽ ሰዓት ያህል ሲገርፉኝ፡ ድንዝዤ ስለነበር ብዙም አለተሰማኝም ነበር፤ ቀጥሎ ግን የቤተመንግሥቱ እስር ቤት ውስጥ ለአምስት ሰዓታት ያህል ይገርፉኝ ነበር።
„አባትሽ እስክትሞች ድረስ እንድንገርፍሽ አዘውናል!”፡ አሉኝ።

የዱባይ ገዥው አባቴ ለሰብዓዊ መብት ቆሚያለሁ ማለቱ ቅጥፈት ነው። በህይወቴ እንደ አባቴ እርኩስ ሰው አይቼ አላውቅም። ምንም በጎ ነገር የለውም፤ አባቴ ለብዙ ሰዎች ሞትና የተመሰቃቀለ ኑሮ ተጠያቂ ሰው ነው። ግድ የለውም፤ ሰው ለመግደል ትዕዛዝ በቀላሉ ይሰጣል። አጎቴ እንደሞተ ከሚስቶቹ አንዷን ሞሮኳዊት ገድሏታል፤ ምን ዓይነት ሰው እንደሆነ ሁሉም የሚያውቁት ነው።
እስር ቤት የቆየሁት ባጠቃላይ ለ3 ዓመታት ከ4 ወራት ያህል ነበር።
አንድ ግዜ፡ በመሃል ለአንድ ሣምንት ያህል ከእስር ቤት ወደ ቤት፡ ቤት አልለውም፡ መልሰውኝ ነበር፤ ወደ እናቴ ቤት።
እናቴን ማየት ጓጉቼ ነበር፤ የምታዝንልኝም መስሎኝ ነበር። ምክንያቱም የእስር ቤቱ ኑሮ በጣም ከባድና አስቃቂ ስለነበር ነው።
እንደወጣሁ ብዙ ኪሎ ቀንሼ ነበር፤ ግን ምንም ነገር እንዳልተፈጠረ፡ በእኔ ላይ ምንም እንዳልደረስ ሆኖ ነበር ሰው ሁሉ የሚያነጋግረኝ።
ከእስር ቤት ለብዙ ወራት ስላልተቀንሳቀስኩ፡ መኪናው ሁሉ በጣም ፈጥኖ የሚሄድ ይመስለኝ ነበር።
ዘመዶች ምንም ነገር እንዳልተፈጠረ ታዲያስ? እያሉ ሲቀርቡኝ በጣም ተገርሜ እናደድ ነበር።
ለእኔ ሁሉም ሰቀቀን ሆነበኝ፤ አሁንም ኮሽ የሚል ድምጽ ሰሰማ እባንናለሁ፡ በጣም መጥፎ ጊዜ ነበር።
እናቴ ግን የእኔ ስቃይ ብዙም አልረበሻትም፤ ቀዝቃዛ ነበረች፤ እናቴ፡ እንደ አንድ እናት፡ ለእኔ ባለማዘኗ በጣም አዝኜ ነበር፤ ሌላዋ እህቴም እንደዚሁ አላዘነችልኝም፣ አላጽናናችኝም።
መርዳት ቢፈልጉ ሊረዱኝ ይችሉ ነበር፤ ግን አላደረጉትም፤ ቢፈልጉ ኖሮ እስርቤት ይጎበኙኝ ነበር፤ ግን አላድረጉትም።
እኔ ምንም ያጠፋሁት ነገር ኖሮ አይደለም፤ ለእህቴ ለሻምዛ ጠበቃ በመቆሜ ብቻ ነው ይህ ሁሉ በደል የተፈጸመብኝ።
ለአንድ ሳምንት እንደተመለስኩ፤ በአንድ ወቅት፡ ቤት ውስጥ “የታሰረችውን እህቴን ሻምዛን ማየት
እፈልጋለሁ!” እያልኩ እጮህ እንደነበር አስታውሳለሁ። ፖሊሶች ይዘውኝ እንደነበርና፤ ዶክተር ነገር መርፌ እንደወጋኝ ትዝ ይለኛል።
ከዚያም በመኪና ወደ ሆስፒታል ወሰዱኝ፡ ብዙ ከመጮሄ የተነሳ ድምጼ ተዘግቶ ነበር።
ለአንድ ሣምንት ያህል በሆስፒታል ተኛሁ ከዚያም መልሰው ወደ እሥር ቤት አስገቡኝ
እስር ቤት የቆየሁት ባጠቃላይ ለ3 ዓመታት ከ4 ወራት ያህል ነበር።
በአባቴ ትዕዛዝ ሊገድሉኝ ሞከሩ፤ ግን አልሆነላቸውም
ለሁለተኛ ጊዜ ከእስር ቤት እንደወጣሁ ሁሉንም ሰዎች እጠላቸው ነበር፤ ማንንም ማመን አልቻልኩምና።
አብዛኛውን ጊዜዬን ከእንስሶች ጋር ነበር የማሳልፈው፤ ከፈረሶች፣ ውሾች፣ ድመቶችና ወፎች ጋር። በተረፈ በክፍሌ ውስጥ ፊልሞችን አይ ነበር። ከሰዎች ጋር የመገናኘት ፍላጎት አልነበረኝም።
ከእስር ቤቱ አስከፊ ልምድ ለመመለስ የብዙ ዓመታት ጊዜ ወስዶብኛል።
በጋ 2017 ዓ.ም ላይ የእህቴ ጉዳይ ስለረብሸኝና ምንም ላደርግላት እንደማልችል በመረዳቴ እንደገና ለመጥፋት አሰብኩ።
በዚህ መልክ ብቻ ነው ሻምዛንና ሌሎችንም ልረዳ የምችለው እዚህ ሆኜ እህቴን ልረዳት አልችልም።
2017 ላይ አንድ ጥሩ ጓደኛየን አጣሁ ህይወት አጭር ናት፣ ዋስትና የለም፤ ሌሎች ለውጥ እስኪያመጡ መጠበቅ ከትንቱ ነው፤ ትልቅ እርምጃ ወስዶ ማምለጥ ብቻ ነው ያለው አማራጭ።
ይህን ቪዲዮ ለመስራት የመረጥኩት ለዚህ ነው። ይህን ሠርቼ ብሞት እንኳን አይጸጽተኝም።
የመጨረሻ ቪዲዮዬ ሊሆን ስለሚችል ሁሉንም ማስታወስ ፡ አለብኝ፤ ሌላስ ስለምን መናገር ይኖርብኝ ይሆን?
ይህን ቪዲዮ እንደሚያጣጥሉት ጥርጥር የለውም፤ ውሸት ነው፡ ቅብርጥሴ ይሉ ይሆናል።
ስለ እኔ ህይወት በጥቂቱ የምለው፦
በዱባይ የእንግሊዝኛና የዓለም አቀፍ የሴቶች ትምህርት ቤቶች ውስጥ ተምሬያለሁ። ፈረስ መጋለብና የጥልቅ ባህር ዋና እንዲሁም የሰማይ ዝላይ ትምህርት ሁሉ ለመማር በቅቻለሁ።
አሁን ፊቴን የሚያይ ሁሉ በደንብ ያውቀኛል፤ ሊያጣጥሉ ቢሞክሩ ማን እንደሆንኩ ያውቃሉ።
ታዋቂ ከሆኑት እህቴና ወንድሜ ጋር እመሳሰላለሁ፡ ስለዚህ ውሻትም ሊሉኝ አይችሉም።
የፓስፖርቴናን የሌሎችን መረጃዎች ኮፒ አድርገው ሰጥተውኛል፤ አሁን በነገራችን ላይ፣ ፓስፖርት የለኝም
ተነጥቂአለሁ።
በዱባይ መኪና መንዳት እንኳን አይፈቀደልኝም ነበር ከ2000 ዓ.ም ጀምሮ አንዴም አገሩን ለቅቄ እንደወጣ ተፈቅዶልኝ አያውቅም።
ወደ ቤት የምገባበትና የምወጣበት ሰዓት ውሱን ነበር። እናቴና ሾፌሮቿ የት እንዳለሁ፣ ምን እንዳደርግኩ
በመከታተል ሁሉን ነገር እየተቆጣጠሩ ለአባቴ ቃል ያቀብሉት ነበር።
ነፃነት አልነበረኝም፤ ያለፈቃድ ወደ ሌላው የኤሚረቶች ግዛት እንኳን መጓዝ አይፈቀደለኝም ነበር፤ ከዱባይ እንድወጣ እከለከል ነበር።
አሁን የምናገረውን ሁሉ ሊያጣጥሉት ይሞክሩ ይሆናል፤ ነገር ግን አይችሉም፤ እራሳቸው ይጋልጣሉ እንጅ፤ ምክኒያቱም ብዙ መረጃ አለኝና።
አያድርገውና፣ ምናልባት ይህ የመጨረሻ ቪዲዮየ ሊሆን ይችላል።
የእኔ ትልቅ ምኞት ፓስፖርቴን ማግኘት፣ የመምረጥ ነፃነት ማግኘትና እህቴን መርዳት ነው። ለእህቴ ፓስፖርት ቢሰጧትና መውጣት ብትችል መልካም ነበር
የ6 ዓመት ህፃን እያለሁ የአባቴ እህት፡ አክስቴ ከእናቴ ነጥላ ወሰደችኝ። ስለዚህ ቤተመንግስት ውስጥ ለአስር አመት ያህል ከእርሷ ጋር ኖርኩ፤ አክስቴ ሁሌ የወለደችኝ እናቴ ትመስለኝ ነበር።
ሌላ ስለምን ላውራ? በህይወቴ ብዙ ስላየኋቸው ነገሮች ማለት እችላለሁ። የወለደችኝ እናቴን በዓመት አንዴ ነበር እንድጎበኛት የሚፈቀድልኝ። ከርሷ ጋር ማደር እንኳን አልችልም፤ ማታ ላይ ወደ ቤት መመለስ ግድ ነው።
ትንሹ ወንደሜም በአክስቴ እንጀራ ነበር ያደገው፡ እናታችን ማን እንደሆነች ሳናውቅ ለአስር አመት ያህል
ከኖርን በኋላ ነበር ሃቁን አውቀን እርሷን የተዋወቅናት
እህቴ ሻምዛ ነበርች ወደ እናታችን ያስጠጋችን፡ ያዳነችኝ ሻምዛ ነበርች፤ ለዚህ ነው ላድናት የምሻው
ግን እስካሁን አልተሳካልኝም።
አሁን ሻምዛን ቪዲዮ ሠርተሽ እኔን አንቋሺያት ብለው ሊያዙት ይችላሉ፤ በደንብ አውቃቸዋለሁና!
ሻምዛ ባሁኑ ሰዓት በህክምና ላይ ናት24 ሰዓት የምታደርገውን ሁሉ ይቆጣጠራሉ፤ ህሊናዋን ይቆጣጠሩ ዘንድ ኪኒኖችን በስነሥርዓት እንድትወስድ ያስገድዷታል።
በጋ 2017 ላይ ሻምዛ ብዙ ሞባይሎችን ደብቃ ስለተገኘች ነበር ወደ ህክምና የገባችው።
እናቴና ሰዎቿ ከእንግሊዝ ጋዜጠኞች ጋር ትገናኝ ይሆናል በማለት ስለተርበተበቱ ነበር ተቆጣጣሪ ዶክተሮች ያዘዙላት። በእውነት መፈናፈኛ የሌለው የዋሻ ኑሮ ነው የምትኖረው፤ ስለዚህ እኔን ለማጥላላት ሻምዛ እህቴን ይጠቀሙባት ይሆናል።
እኔን ቆሜ ከእነ ህይወቴ ሊይዙኝ አይችሉም፤ የሲዖል ኑሮየ 20 ዓመታት ሊሞሉት ነው
የብዙ ሰዎች ኑሮ ተመሰቃቅሏል፤ ብዙዎች ተገርፈዋል፣ ተገድለዋል። አባቴ ግድ የለውም፤ የገደላቸውን ሰዎች ማንነት ይደብቃል አባቴ በጣም የከፋ ወንጀለኛ ሰው ነው።
አባቴ እርሱን ዘመናዊና ተራማጅ እንደሆነ ለማስመሰል ይሞክራል፤ አታላይ!
የ31 ልጆቹን ፎቶ በየክፍሉ በመስቀል የቤተሰብ ሰው እንደሆነ ለማሳየት ይሞክራል፡ ማታለያ ነው!
ሌባኖስ አንድ ወንደ ልጅ አለው፤ በዓመት አንዴ ሲያገኘው፡ የእጅ ሰላምታ ብቻ ነው የሚሰጠው። የአባትነት ፍቅር የለውም! በጣም አሳፋሪ ሰው ነው! አባቴ ሜዲያው እንደሚያሳየው ሳይሆን፤ በእውነተኛው ኑሮ ጥሩ ሰው አይደለም።
በዱባይ ልክ እንደ ሌላው የመካከለኛው ምስራቅ አገር ሜዲያው ነጻ አይደለም
ሌላ ምን እንደምል አላውቅም… ምናልባት ከሞትኩ ያው ይህን ቪዲዮ አቅርቤዋለሁ።
ይህን ቪዲዮ እንዳወጣ መገደዴ አሳዛኝ ነው፤ ግን ሌላ አማራጭ አልነበረኝም። ሌላ ምን እንደምል አላውቅም…
በወደፊቱ ተስፋ አደርጋለሁ፤ ሁሉም ቀላል እንዳልሆነ ይገባኛል፤ የመምረጥ ነፃነቴ ግን መጠበቅ አለበት።
ለህይወቴ አዲስ ምዕራፍ የሚከፈትበት ወቅት ነው ጸጥ በይ! የምባልበት ዘመን አልፏል። ስለ ኑሮዬ ስለ ሻምዛ እህቴ ኑሮ ደፍሬ እናገራለሁ።
በዚህ ተስፋ አደርጋለሁ፤ ጠዋት ላይ ስነቃ እንደ ሌላው የመረጥኩትን የማድረግ መብት እንዳለኝ ሆኖ ይሰማኛል።
ነፃነት በሌለበት አገር ለሰው ልጅ መብት መከበር ሲባል ብዙ ሥራ መሥራት ይቻላል፤
ለሻምዛ እህቴ የተሻለ ኑሮ እመኝላታለሁ።
አሁን ለህይወቴ አዲስ ምዕራፍ የሚጀምርበት ወቅት ነው። በዱባይ የመኖር ምንም ምክኒያት የለኝም። በእርግጥ እዚያ የምወዳቸው ሰዎች ቢኖሩም ለመሄድ አልሻም፤ እነርሱ ከፈቀዱ እዚህ መጥተው ሊያዩኝ ይችላሉ።
ከዚህ በኋላ የት፣ እንዴት እንደምኖር አላውቅም፤ በሌላ በኩል አሁን አማራጭ ስላለኝ ጥሩ ነገር ነው።
ያልተናገርኩት ነገር ይኖር ይሆን?
ስለግድያዎቹ ልናገር? ረጅም ስለሚሆን ልተወው!
አባቴ ለብዙ ሰዎች ሞት ተጠያቂ ነው! ትልቅ ወንጀለኛ ነው!
በዱባይ ፍትህ የለም፤ በተለይ ለሴቶች! የሴቶች ህይወት ዋጋ የለውም!
አባቴ ማስረጃዎችን ለመደበቅ ቤቶችን ያቃጠለ እብድ ነው! ለሠራቸው ወንጀሎች ሁሉ ተጠያቂ የሚሆንበት ጊዜ ነው፤ ፈጠነም ዘገየም ለፍርድ ይቀርባታል! የፈለገውን ቢያደርግ እኔ አልፈራውም! ወሽካታ ሰው ነው!
ለሠራቸው ወንጀሎች ሁሉ ተጠያቂ የሚሆንበት ጊዜ ይመጣል፤ ፈጠነም ዘገየም ለፍርድ ይቀርባታል!
ለአሁኑ ሌላ የምለው ነገር የለም፤ ይህን ቪዲዮም መሥራት ባላስፈለገኝ ነበር
የመጨረሻ ቃላት… የእኔ ጉዳይ ለሚያሳስባቸው ጓደኞቼና አንዳንድ ቤተሰቦቼ ሁሉ ምስጋናየን ላቀርብ እወዳለሁ።
______
Like this:
Like Loading...