__________________________
Posts Tagged ‘ነጎድጓድ’
ከባድ ጎርፍ አስገራሚ የመብረቅ ጋጋታ በግብጽ | ወላሂ! ወላሂ! የግብጽን ጥቅም አልነካም!
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 8, 2020
Posted in Curiosity, Ethiopia, Infos | Tagged: Alexandria, ህዳሴ ግድብ, መብረቅ, ነጎድጓድ, አሸዋ, አባይ, አንበጣ, እሳት, እስክንድርያ, ካባ, ዝናብ, ግብጽ, ጎርፍ, ፀረ-ኢትዮጵያ, Egypt, Flood, Lightning, Nile | Leave a Comment »
ግብጽ ላይ ፍርድን አደርጋለሁ | የጎርፍ ዶፍ እያወረደ ባለው ደመና የኢትዮጵያ ካርታ
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 17, 2020
በአባይ ጉዳይ ፀረ–ኢትዮጵያ የሆነ ሤራ በመጠንሰስ ላይ ያሉት ግብጽ እና እስራኤል፡ እስከ አሁን የ21 ሰዎችን ህይወት በወሰደውና “Dragon Storm / ዘንዶ” በተሰኘውበከባድ አውሎ ንፋስ ባስከተለ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የዝናብ ማዕበል እየታመሱ ነው።
ልክ በራያ ኦሮሞዎች የሚመራው ህዋሃት የኢትዮጵያውያን ጠላት ከሆኑት ኦሮሞ ሙስሊሞች ጋር ዛሬም ዲያብሎሳዊ “የስትራቴጂ ጥምረት ፈጥርያለሁ” እንደሚለው እስራኤልም “አይሁዶችን ወደ ባሕር እንወረውራችዋለን!” ከሚሉት ከታሪካዊ አረብ ሙስሊም ጠላቶቿ ጋር ተመሳሳይ ጥምረት ለመፍጠር ወስናለች። በዚህም ከእነርሱና ውሀችንን ለጠላት አሳልፈው በመስጠት ላይ ካሉት ከሃዲ የሃገራችን መሪዎች ጋር አብራ በድጋሚ ትቀጣለች።
_________________________________
Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: መቅሰፍት, መብረቅ, በሽታዎች, ነጎድጓድ, አባይ, አውሎ ነፋስ, ኢትዮጵያ, እስራኤል, ካይሮ, ዘንዶ አውሎ ነፋስ, የእግዚአብሔር ቁጣ, ግብጽ, ግዮን, ጎርፍ, Dragon Storm, Ethiopia | Leave a Comment »
እንዲሁ በግብጽ ላይ ፍርድን አደርጋለሁ | ነጎድጓድ፣ አውሎ ነፋስ፣ ጎርፍ፣ ቸነፈር
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 13, 2020
ግብጽ፤ የግዮን ወንዝ የኔ ነው አልሽ፤ ከሃዲውም የኢትዮጵያ ፈርዖን “ወላሂን!” ማለልሽ ፥ እንግዲያውስ ያውልሽ!
[ትንቢተ ሕዝቅኤል ምዕራፍ ፳፱]
፰ ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። እነሆ፥ ሰይፍ አመጣብሃለሁ፥ ሰውንና እንስሳንም ከአንተ ዘንድ አጠፋለሁ።
፱ የግብጽም ምድር ባድማና ውድማ ትሆናለች፥ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፤ አንተ። ወንዙ የእኔ ነው የሠራሁትም እኔ ነኝ ብለሃልና።
፲ ስለዚህ፥ እነሆ፥ በአንተና በወንዞችህ ላይ ነኝ፥ የግብጽንም ምድር ከሚግዶል ጀምሮ እስከ ሴዌኔና እስከ ኢትዮጵያ ዳርቻ ድረስ ውድማና ባድማ አደርጋታለሁ።
____________________________
Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: መቅሰፍት, መብረቅ, ተላላፊ በሽታዎች, ቸነፈር, ነጎድጓድ, አባይ, አውሎ ነፋስ, ኢትዮጵያ, ካይሮ, ኮሮና ቫይረስ, ወረርሽኝ, ግብጽ, ግዮን, ጎርፍ, Ethiopia | Leave a Comment »
የኖኅ ዘመን እንደ ነበረ | እንግሊዝ እስካሁን ታይቶ የማይታወቅ መብረቅ ወረደባት፤ የኢትዮጵያ ቀለማት ታዩ
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 28, 2018
[የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፳፬፥፴፯]
“የኖኅ ዘመን እንደ ነበረ የሰው ልጅ መምጣት እንዲሁ ይሆናልና።”
እጅግ በጣም የሚገርም ነው፤ አመጸኞቹ አውሮፓውያን የዔሳውና የእስማኤል ዘሮች የእግዚአብሔርን አሠርቱ ት ዕዛዛት ሙሉ በሙሉ በማፍረስ የራሳቸው የሆነ ዓለም በመፍጠር ከራሳቸው አልፈው እኛንም በጽኑ በመጉዳት ላይ ናቸው። ግን ፈጣሪያችን ትዕግሥቱ እያለቀበት ነው፤ ምልክቶቹን ለመጨረሻ ጊዜ እያሳየን ነው።
በአገራችን ላይ እያውጠነጠኑት ያለውን ዲያብሎሳዊ ሤራ ብዙዎቻችን አሁንም አልተረዳነውም፤ ሁሉን የሚያይ እግዚአብሔር ግን ዝም አይለም። ኢትዮጵያ በእግዚአብሔር የተመሰረተችና በቅዱሳን ቃል ኪዳን የተጠበቀች፤ ከሁሉ በላይ ደግሞ የእመቤታችን አስራት አገር ስለሆነች እንኳን በአገር ዉስጥ ለጥፋቷ የተሰለፉ አይደለም፤ እርሷን ለማጥፋት የተሰለፉ የዉጭ መንግሥታት በሙሉ በእግዚአብሔር ቁጣ ይጠፋሉ፤ ከምድር ይጠረጋሉ። እርሷ ግን በእግዚአብሔር መንግሥትነቷ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ትቆያለች።
ቅዳሜ ሌሊት ላይ፡ በእንግሊዝ አገር ታይቶ የማይታወቅ ነጎድጓድና የመብረቅ ብልጭልጭታ ብዙዎችን ከእንቅልፋቸው ቀስቅሷል። በአንድ ምሽት ብቻ 22 ሺህ ጊዜ የለንደን ሰማይ በመብረቅ ተብለጭልጯል።
ቪዲዮው መጨረሻ ላይ እንደሚታየውም በሆነ ወቅት ላይ ደመናው በአረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ቀለማት ተቀብቶ ነበር። የሚገርም ነው።
ይህ ሁሉ የተከሰተው፤ እንግሊዝ ፀረ–እስላም የሆኑ ጋዜጠኞችን ማሠር በጀመረችበት፣ ወኪሏን አቶ አንዳርጋቸውን የኢትዮጵያ መንግስት እንዲፈታ ትዕዛዝ ካሰተላለፈች፣ እንዲሁም እህቷ አየርላንድ ደግሞ የጸነሱ ሴቶቿ ጨቅላዎቻቸውን እንዲያስወርዱና እንዲገድሉ በሬፈረንደም አጽድቃ ፈቃዱን በሰጠቻቸው ማግስት መሆኑ ነው።
ጻድቁ አባታችን፡ አቡነ ተክለሃይማኖት በሀገሬ ላይ የታዘዙ አምስት መቅሰፍቶች አሉ ብለው ነበር።
እነሱም፡–
1. መብረቅ፣
2. ቸነፈር፣
3. ረሃብ፣
4. ወረርሽኝ፣
5. የእሳት ቃጠሎ ናቸው፡፡
______
Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: ለንደን, መብረቅ, ማስጠንቀቂያ, ምልክቶች, ሰማይ, ሰዶም እና ገሞራ, ነጎድጓድ, እንግሊዝ, የኢትዮጵያ ቀለማት | Leave a Comment »
በዝሙት፣ በክፋት፣ በተንኮልና በስጋት የኖራችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃል ፤ ያለዚያ የእሳት ዝናብ ይዘንባል
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 12, 2017
ድንቅ ነው! ከስብከቱ ጋር፡ ሰማዩ ላይ ደመናው የተከማቸው በአንድ ትንሽ ቦታ ላይ ብቻ ነበር ፤ ሌላ ቦታ ደመና አልነበረም። ጥቂት የደመና ክምችት መብረቁን ሲያብለጨለጭውም ብዙ ጊዜ አይታይም። የደመናው ቅርጽም ያስገርማል፤ አቶም ቦምብ የሠራው የጅብ ጥላ ይመስላል።
ትንቢተ ኢዮኤል ምዕራፍ ፪ ፥ ፩ ፡ ፫
፩ የእግዚአብሔር ቀን መጥቶአልና፥ እርሱም ቀርቦአልና በጽዮን መለከትን ንፉ፥ በቅዱሱም ተራራዬ ላይ እሪ በሉ፤ በምድርም የሚኖሩ ሁሉ ይንቀጥቀጡ፤ የእግዚአብሔር ቀን መጥቶአልና፤
፪ የጨለማና የጭጋግ ቀን፥ የደመናና የድቅድቅ ጨለማ ቀን ነው፤ ታላቅና ብርቱ ሕዝብ በተራሮች ላይ እንደ ወገግታ ተዘርግቶአል፤ ከዘላለምም ጀምሮ እንደ እነርሱ ያለ አልነበረም፥ ከእነርሱም በኋላ እስከ ብዙ ትውልድ ድረስ እንደ እነርሱ ያለ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም።
፫ እሳት በፊታቸው ትባላለች፥ በኋላቸውም ነበልባል ታቃጥላለች፤ ምድሪቱ በፊታቸው እንደ ዔድን ገነት፥ በኋላቸውም የምድረ በዳ በረሃ ናት፤ ከእነርሱም የሚያመልጥ የለም።
የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ ፲፯ ፥ ፳፮ ፡ ፳፯
በኖኅ ዘመንም እንደ ሆነ፥ በሰው ልጅ ዘመን ደግሞ እንዲሁ ይሆናል።
ኖኅ ወደ መርከብ እስከ ገባበት ቀን ድረስ፥ ይበሉና ይጠጡ ያገቡና ይጋቡም ነበር፥
የጥፋት ውኃም መጣ ሁሉንም አጠፋ።
______
Posted in Ethiopia | Tagged: መስከረም ፪ሺ፲, መብረቅ, መድኃኔ ዓለም, ትንቢተ ኢዮኤል, ነጎድጓድ, ኖኅ ዘመን, አዲስ አበባ, አዲስ ዘመን, ኢትዮጵያ, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት, Ethiopian Orthodox Tewahedo Faith | Leave a Comment »