Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 12, 2020
ዘነበ – ለዘንባራ – ተቤራ
ይህ አካባቢ የተጠለፉት እህቶቻችን አሳዛኝ ጉዳይ የተፈጸመበት አካባቢ ነው፤ ለጅማ ቅርብ ነው፤ አጋቻቸው አብዮት አህመድ “ሰበርናቸው/ የተሰረቁት ሃያ አበቦች (ልጃገርድ ተማሪዎችን በማለት እንደለመደው መሳለቁ ይሆናል)” ትናንታና ወደ ጂሃድ ጅማ በማምራት የድል አቀባበል እንዲደረግለት አዘጋጅቶ ነበር። ነገ ደግሞ አረብ ሞግዚቶቹ ፊት ለመምበርከክ ወደ ጂሃድ አረቢያ ያመራል። በደቡብ የወረደው እሳት በሄደበት ይከተለው!
“የእግዚአብሔርም እሳት በመካከላቸው ስለነደደች የዚያን ስፍራ ስም “ተቤራ” ብሎ ጠራው”
[ኦሪት ዘኍልቍ ምዕራፍ ፲፩,፥፩፡፫]
“ሕዝቡም ክፉ ሆነው በእግዚአብሔር ላይ አጕረመረሙ፤ እግዚአብሔርም ሰምቶ ተቈጣ፤ የእግዚአብሔርም እሳት በመካከላቸው ነደደች፥ የሰፈሩንም ዳር በላች። ሕዝቡም ወደ ሙሴ ጮኹ፤ ሙሴም ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፥ እሳቲቱም ጠፋች። የእግዚአብሔርም እሳት በመካከላቸው ስለነደደች የዚያን ስፍራ ስም ተቤራ ብሎ ጠራው።”
በደቡብ ኢትዮጵያ በከምባታ ጠምባሮ ዞን ዱሬ፣ ሲገዞ፣ “ለዘንባራ” እና ሆዶ ቀበሌዎች ዓርብ ለቅዳሜ አጥቢያ ከሰማይ ወረደ በተባለ እሳት ሰላሳ በላይ የሳር ቤቶች የተቃጠሉ ሲሆን ስድስት ከብቶች እና የጢርፍ ክምርም የጉዳቱ ሰለባ ሆኗል።
የእሳቱ መንስዔ በግልጽ ባይታወቅም የአካባቢው ኅብረተሰብ በተመሳሳይ ሰዓት ከሰማይ ወርዶ ጉዳት እንዳደረስ እና ተፍጥሯዊ ነው ብለዋል።
______________________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: ለዘንበራ, ሰማይ, ተቤራ, ነብዩ ሙሴ, ነብዩ ዮናስ, አብዮት አህመድ, እሳት, ከምባታ, የታገቱ እህቶች, ደቡብ ኢትዮጵያ, ጾመ ነነዌ | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 12, 2020
ጾመ ነነዌ (የኢትዮጵያ ጾም) ዘመነ ዮሐንስ፤ ዛሬ ረቡዕ ፬ – ፪ሺ፲፪ ዓ.ም ነው፤ ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ነው።
ነቢዩ ዮናስ ነነዌ መሬት ላይ እንደደረሰ ባወቀ ጊዜ ከእግዚአብሔር መሸሽ አለመቻሉን ተረዳ። የነነዌ ሰዎችንም ንስሐ ግቡ እያለ መስበክ ማስተማር ጀመረ፡፡ የነነዌ ሰዎችን የዮናስን ትምህርት ሰምተው ንስሐ በገቡ ጊዜ እግዚአብሔር አምላክ ይቅር ብሎ ከጥፋት አድኗቸዋል፡፡ነቢዩ ዮናስም ሐሰተኛ እንዳይባል እሳቱ እንደ ደመና ሆኖ ከላይ ታይቷል።
ዮናስ ማለት የስሙ ትርጉም ርግብ ማለት ነው።
በጾማችን እግዚእብሔር አምላክ መዓቱን በምሕረቱ ቁጣውን በትዕግስቱ መልሶ በኃጢአት ለጠፋው ዓለም ይቅርታውን ይላክልን፡፡
___________________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: ነብዩ ዮናስ, አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ, ኢትዮጵያና ቀለማቷ, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት, የኢትዮጵያ ካርታ, የካቲት ፫, ደመና, ጨረቃ, ጾመ ነነዌ | Leave a Comment »