በምድር ላይ የመጨረሻዋ መንግሥት ዋነኛዎቹ አስር አገሮች
አውሮፓ በአራት መንግሥታት ነበር የተነሣችው
“አዉሬይቱ አስር ቀንዶችም ነበሯት።“
አውሬይቱ አውሮፓ፣ አስሩ ቀንዶች፦ አስር ኃያላን ተዋጊ መንግሥታቷ ናቸው።
በአሁኑ መልክና ስም የምናውቃቸው የአውሮፓውያን መንግሥታት አገሮች በአንድ ጊዜ ይህንን ቅርጽና ስም በትክክል አልያዙም። አሁን ያሉበት የሀገር ቅርጽና የሚጠሩበትን ስሞች ለመያዝ ከመካከለኛው ዘመን ጀምሮ እስከ 19ኛውና እስከ 20ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ድረስ ፈጅቷል።
በረጅም የታሪክ ዘመን ውስጥ እንኳንስ የአገሮችን የአንድን አገር ትክክለኛ ክልልና ስም ወስኖ ለመናገር በጣም ከባድ ነው።
ለምሳሌ ሲጀመር ኢትዮጵያ ተብላ የተጠራችው አገር ኩሽ በመባል የታወቀች ሳለች መካከላዊ መነሻዋ የግዮን መፍለቂያ ቆላ ደጋ ዳሞት፥ ሰከላ፤ ቅርጽዋም ግዮን (አባይ) ወንዝ የሚከበው መሪት አሁን ጎጃም የምትባለው ክፍለ ሀገር እንደ ነበረች በግልጥ ተቀምጧል። (ዘፍ.2፥13) በኋላም ሕዝቡ መንቀሳቀስ ሲጀምርና በየአቅጣጫው ሲሄድ አሁን ሱዳን የምትባለው ኑቢያ እስከ ደቡብ ግብጽ ድረስ ሁሉም የኢትዮጵያ ክልል እንደነበሩ ይታወቃል። ግብጽ በኢትዮጵያ ድንበርተኝነት በኢሳያስ 20፥3 በሕዝ. 29-10 ተመዝግቦ እናያለን። እስከ ኢርትራ፣ ጂቡት፣ ሶማሊያ ሁሉ የኢትዮጵያ ግዛቶች ነበሩ።
ታዲያ በምድር ላይ ያሉ አገሮች ሁሉ እንዲሁ በብዙና በተለያዩ ምክንያቶች የተወሰነና ቋሚ ቅርጽና ስም ይዘው አልኖሩም።
በትክክል አዉሮፓን አዉሮፓ ያሰኙዋትና ተግባራቸውንም ማከናወናቸውን ግልጽ ያደረገው በ1941 ዓ.ም የአቋቋሙት “የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን አገሮች፦ የ
1ኛ. እንግሊዝ |
6ኛ. ዴንማርክ |
2ኛ. ፈረንሳይ |
7ኛ. አይስላንድ |
3ኛ. ቤልጂየም |
8ኛ. ኢጣሊያ |
4ኛ. ኔዘርላንዶች |
9ኛ. ኖርዌና |
5ኛ. ሉክሰንበርግ |
10ኛ. ፖርቱጋል |
ሕብረት ነው።
ካናዳና የተባበሩት የአሜሪካ ክፍለ ግዛቶች (USA) አባል ቢሆኑም የአውሮፓ ማሕበረሰብ ስለአይደሉ አይካተቱም። የአባላቱ ቅደም ተከተልነት አስፈላጊ ነው፤ ምክኒያቱም በዓለማችን ላይ ለሚደረጉት አውሮፓዊ ተጽዕኖዎች ሁሉ የመሪነቱን ሚና የምትጫወተው በእንግሊዝ የምትተዳደረዋ ታላቋ ብሪታኒያ ነች።
አሜሪካ = እንግሊዝ |
ካናዳ = ስኮትላንድ |
አውስትራሊያ / ኒውዚላንድ = አየርላንድና ዌልስ |
መሆናቸው ነው።
በምድር ላይ ባሁኑ ጊዜ ተንሠራፍቶ የሚታየው የፓለቲካ፣ የኅይማኖት፣ የባህል እንዲሁም የምጣኔ ኅብት ችግር ሁሉ የተፈጠረው በእንግሊዝ (ታላቋ ብሪታኒያ) ቆሽቋሽነት ነው። ታላቋ ብሪታኒያ ግዛቶቿን በአንድነት ለመያዝና የተቀረውንም ዓለም ለመቆጣጠር ያመቻት ዘንድ በጣም ጠንካራና በሕዝቦቿ ዘንድ ተቀባይነት ያላትን የንጉሣዊ ሥርዓት ትንከባከባልች፤ እንደ ኢትዮጵያ ባሉት አገሮች ግን የንጉሣዊ ሥርዓታት እልም ብለው እንዲጠፉ ከፍተኛ ሚና ትጫወታለች/ተጫውታለች። ልብ ብለን ከታዘብን፤ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ኢጣሊያ ኢትዮጵያን እንድትወር ከወረረችም በኋላ የዓለም ማሕበረስብ ወረራውን እንዳያወግዝ ያደረገችው እንግሊዝ ነበረች። በዚህ ወቅት ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ በእንግሊዟ ሳውዝሃምፕተን ጥገኝነት አግኝተው በኢትዮጵያ የብዙ ሺህ ዓመታቱን የነገሥታት ሥርዓትን ለመገርሰስ ሁኔታዎችን በማመቻቸት ፀረ–ንጉሣዊ ተል ዕኳዋን ቀስበቀስ በሥራ ላይ ለማዋል በቃች።
በኋላም፡ አፄ ኃይለሥላሴን በማድከም እና በማታላል እሳቸው ከአረቦች ጋር፤ ከኢራኑ ሻህ ጋር ያላቸውን ግኑኝነት እንዲያጠናክሩ በዚህም ሰበብ ከእስራኤል ጋር እንዲኳረፉና እንዲረቁ ተደረገ። የንጉሡ መውደቂያቸው የሆነውን የወሎንና የትግራይን ሰው ሰራሽ ድርቅ ካመጡባቸው በኋላ፡ በንግሥቲቷ የዜና ማሠራጫ፡ በቢቢሲ እንዲጋለጡና እንዲዋረዱ ተደረጉ። ከዚያም፡ እላይ የተጠቀሱት የ ናቶ አባላት እንዲሁም ጀርመን በ“እርዳታ” ሰጭዎች ስም ወታደሮቻቸውን ወደ ወሎና ትግራይ አሠፈሩ። በእንግሊዞች የሚመራው የአውሮፓውያኑ ሠራዊት በዓየር ሲያበራቸው የነበረው አውሮፕላንና ሄሊኮፕተር በጣም ብዙ ነበሩ ፡ በምድርም ወታደሮቹ በሠፈሩባቸው ቦታዎች ሁሉ የተለያዩ ሰፋፊ ካምፖችን በመገንባት ሲንቀሳቀሱ፡ ኢትዮጵያውያን ልጃገረዶችን እያታለሉ ሲደፍሩ ነዋሪው ትንፍሽ እንኳን ለማለት አለምብቃቱን በጊዜው በቦታው የነበሩ አንድ ባለሥልጣን በሃዘን አጫውተውኛል። ሁሉም ለርዳታ የመጡ መስሏቸው ነበር። ብዙም አልቆየም አፄ ኃይለሥላሴ ከውጭ በተቀነባበረው የንጉሣን ሥርዓት ግልበጣ ዘውዳቸውን እንዲያስቀምጡ ተገደዱ።
ቀደም ሲልም እንግሊዝ፡ ታሪካዊ ጠላቶች አድርጋ በምታያቸው፤ በፈረንሳይ፡ በሩሲያና በጀርመን የሚገኙትን የንጉሣን ሥርዓታት ተራበተራ እንዲገረሰሱ አድርጋ ነበር። አሁን ዓይኗን በስፓኙ እና በሳውዲው የንጉሣውያን ሥርዓቶች ላይ ነው ያሳረፈችው። ካቫቲካኑ ጳጳስ ጋር የሚደረገው ሽኩቻም እንደቀጠለ ነው። በዓለም ላይ አንድ ንጉሥ/ንግሥት መኖር አለበት/አለባት እነሱም ከለንደን ሆነው የበላይነቱን ማሳየት አለባቸው የሚል ተልዕኮ ነው የዳን ዘሮች የሆኑት እንግሊዛውያን ተልዕኮ። በቅርቡ የተካሄደው የንግሥት ኤልሳቤጥ ሁለተኛ የኢዮቤልዮ በዓል አከባበር፡ እንዲሁም በመካሄድ ላይ ያሉት የኦሎሚፒክ ጨዋታዎች ይህን ነው የሚያመለክቱት። በለንደን ስቴዲየም የተካሄደውን የመክፈቻ ስነሥርዓት ታዝበን ከሆነ፡ ስቴዲየም የነበረው 80ሺህ ሕዝብ ከፍተኛ ጭብጨባ ሲደረግላቸው የነበሩት ተሰላፊ አገሮች፤ አሜሪካ፣ ካናዳ፣ አውስትራሊያ፣ ኒውዚላንድ ብሎም በክሪኬት ስፖርት የደም ትስስር ውስጥ ለገቡት የሕንድና ፓኪስታን ተሰላፊዎች ነበር። ኢትዮጵያና የተቀሩት የአፍሪቃ አገሮች ተሰላፊዎች ስማቸው ሲጠራ የግዴለሽነት ፀጥታ ሰፍኖ ነበር።
በመላው ዓለም የሚፍተለተለው ገንዘባዊ እንቅስቃሴም ቢሆን የሚውጠነጠነው ከለንደን ከተማ ሆኖ ነው። ሰሞኑን ባንዳንድ ባንኮች (ባርክሌይስ፥ HSNBC) የታየው ቅሌት እነዚህ በለንደን ተቀማጭነት ያላቸው የገንዘብ ተቋሞች ምን ያህል ብልሹና ኢ–ሰብዓዊ (አውሬአዊ) የሆነ ድርጊት እንደሚፈጽሙ ነው የሚያሳየው። እነዚህ ባንኮች ለ ዋሃቢ ሽብር ፈጣሪዎች ቢሊየን ዶላር ይለግሳሉ፣ እንደ ሶሪያና ሊቢያ ባሉት አገሮች የአልቃይዳን ተዋጊዎች እንዲያሰለጥኑ የሚላኩትን እንግሊዛውያን ባለሙያዎች ይደጉማሉ። እዚህች ይመልከቱ፡“Club of the Isles”
እነዚህ ደም መጣጮች በየቦታው ህውከትና ሽብር በመፍጠር አንዱ በሌላው ላይ እየተነሳ ሕዝቦች ሁሉ እንዲበጣበጡና እንዲተላለቁ የማድረግ ኃይል/ፍላጎት አላቸው። የዓለም ሕዝብ ቁጥር ከአሁኑ ከ7ቢሊየን ወደ 1ቢሊየን ለማውረድ የተቻላቸውን ተንኮል ሁሉ በመጠንሰስ ላይ ይገኛሉ። በተለይ ዋናው ትኩረታቸው በአፍሪካ ላይ ነው፤ አፍሪካውያንን በድህነት እንዲማቅቁ፤ እንደ ኮሙኒዝምና እስልምና በመሳሰሉ ጠንቀኛ ርዕዮተ ዓለሞች እንዲታሠሩ ብሎም በበሽታዎች እየተለከፉ እንዲያልቁ በማድረግ ለዘመናት ብዙ ሞክረዋል፤ ነገር ግን ይህ አልተቻላቸውም፤ እንዲያውም የአፍሪቃውያኑ የሕዝብ ቁጥር በጣም እየጨመረ ፡ የክርስትና እምነትም በይበልጥ እየተስፋፋ ነው የመጣው፤ ስለዚህ አሁን አፍሪቃውያኑን በክህደት ማዕበል በማጥለቅለቅ፤ ገንዘብ አፍቃሪ፣ በእንግሊዝኛ የከረባት ባህልና ቋንቋ ኮሪ፣ ሰዶማዊነትን እንደዘመናዊነት ቆጣሪ እንዲሁም የአክራሪ እስልምና ተቀባይ እንዲሆን በማድረግ እየበጠበጡት ነው። እነርሱ ላቆሙት ምስል ያልሰገዱት አፍሪቃውያን፤ ከነርሱ ጋር ያልተባበሩትና፡ ሉሲፈራዊ ተልዕኳቸውን ለመዋጋት የሚቃጡትን አፍሪቃውያን መሪዎችን በድብቅ እየመነጠሩ ያስወግዳሉ፤ ይገድላሉ።
ላይ ከተጠቀሰው የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ጋር ጎን ለጎን በመተባበር የሚጓዘው በ1949 ዓ.ም የተቋቋመው የአውሮፓ የምጣኔ ሀብት ኮሚሽን (European Economic Commission) ወይም የአውሮፓ ማሕበረሰብ (European Community) የሚባለው ነው። በመጨረሻም የአውሮፓ ሕብረት (European Union) ተብሏል። እነርሱም፦
1ኛ. እንግሊዝ |
7ኛ. ኢጣልያ |
2ኛ. ፈረንሳይ |
8ኛ. ፖርቱጋል |
3ኛ. ቤልጂየም |
9ኛ. ጀርመን |
4ኛ. ኔዘርላንዶች |
10ኛ. ስፔን |
5ኛ. ሉክስምበርግ |
11ኛ. ግሪክ |
6ኛ. ዴንማርክ |
12ኛ. አየርላንድ |
ናቸው።
የአውሮፓው የጦር ቃል ኪዳንም ሆነ የአውሮፓውያን የምጣኔ ሀብት (የኢኮኖሚ) ኅብረተሰብ አባል አገሮች መጽሐፍ በዳን. 7፥8-24 በራእ. 13፥1 ፤ 17፥12 በሚለው ቁጥር (ከአሥር ቀንዶች)በልጠው ቢታዩም አንዳንዶች አባላት በማሕበሩ አገልግሎት ምንም ያህል አስተዋጽኦ የሌላቸው ናቸው። ለምሳሌ ፖርቱጋልና ግሪክ የመሰሉም አርጅተውና አብቅተው የተቀመጡት አገሮች ናቸው።
ላላፉት ወራት በአውሮፓ የሚታየው የኢኮኖሚ ቀውስ የሚያሳየንም የአንዳንድ ማኅበርተኞች አገሮችን የማኅበሩ አስተዋጽኦ ዝቅ ያለ (ግሪክ፣ ምስራቅ አውሮፓ) ያንዳንዶቹን አገልግሎት ደግሞ የበረታ (ጀርመን)፤ ያንዳንዶችን ደግሞ ገለልተኛ እንደሆነ(ታላቋ ብሪታኒያ)ነው የሚያሳየን። ስለዚህ በማኅበሩ ከልብ የሚሳተፉ አገሮች ቁጥር ከፍና ዝቅ ሲል ይታያል። እስያዊቷ ቱርክ ደግሞ ለጦር ከቃልኪዳኑ ኅብረት ያላት አስተዋጽኦ ቀላል አይደለም። የአውሮፓው የኢኮኖሚ ኅብረተሰብ አባል ለመሆንም ትሻለች።
በአውሮፓውያን ኅብረተሰብ አንድነት መካከል አንዳንድ የሀሳብ ልዩነት ቢኖርም በጽኑ ኅብረት (አንድነት) እንዲያውም ከቱርክና አረብ አገሮች ጋር ሳይቀር በመተባበር ለጥፋት መቆማቸው አይቀሬ ነው።
ከአውሮፓ ግዙፍ ምድር ጋር በእግሯ አውራ ጣት ብቻ የምትገኘው ቱርክ ከሁሉም ይበልጥ ከፍተኛውና ውስብስቡን ሚና ተጫውታለች። በቀዝቃዛው ጦርነት ጊዜ የአሜሪካ የጦር ተዋጊ ጠያራዎች ከቱርክ እየተነሱ በመብረር የሶቪየት ግዛት በነበሩት በጆርጂያ፣ አርሜኒያና አዘርበጃን እንዲሁም በእስያው ክፍል ብዙ የስለላ በረራዎችን ሲያካሂዱ ነበር። በኢራቅ ጦርነትም ጊዜ ብዙ በረራዎች ከቱርክ ተነስተው ነበር ወደ ኢራቅ የሚላኩት። ለዚህም አገልግሎት ቱርክ ከ15 ቢሊየን ዶላር በላይ የገንዘብ ስጦታ እንዳገኘች ማስረጃዎች ይናገራሉ።
የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳንና የአውሮፓ ኅብረት (የካውካስ ዘሮች) እየተጠናከሩ መምጣታቸው በግልጽ እየታየ ነው፤ ይህም ትንቢት ጊዜውን ጠብቆ መፈጸም ለመጀመሩ ግልጽ የሆነ ማረጋገጫ (ምስክር) ነው።
ስለዚህ ወደ አሜሪካ ሄደው የሠፈሩት ሕዝቦች የተነሱባቸው አገሮች በአሁኑ ቅርጾቻቸውና ስሞቻቸው እንዲህ ሆኖ ተበጥሮና ተንጠርጥሮ በምናያቸውና በምናውቃቸው በሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን አገሮች እነርሱም የአውሮፓ ኅብረት በሚባሉት አሥር አገሮች ልብና ፍሬ ሆነው ተጠቅለው ያሉ ስለሆኑ፤ ትንሹን ቀንድ፡ አሜሪካን ያበቀለችው ባለ አሥር ቀንድ አውሬ (አራተኛ መንግሥት) አውሮፓ ሆና ተገኝታለች።
ይህች አውሬ (አውሮፓ)የምድርን ሕዝብ ሕይወት እያደቀቀች ንብረቱን ሁሉ ለዘመናት በመብላት ላይ ትገኛለች። እ.አ.አ በ1872 ዓ.ም ታላላቅ አውሮፓውያን (የአውሬይቱ አሥር ቀንዶች)በበርሊን ከተማ በመሰባሰብ በእስያ እንዳደረጉት የአፍሪካንም አሕጕር ከነሕዝቦችዋ ለመከፋፈል ወሰኑ። ከ1877 እስከ 1892 ዓ.ም ድረስ የተካሄደው የአፍሪካ መሬትና ሕዝብ ክፍፍል ውጤት በሆነው የቅኝ ግዛት (የባርነት ሥርዓት) የአውሮፓውያን ግዥዎች በተቻለ ፍጥነት ብዙ ሀብት የማግኘት ፍላጎት የአገሬውን ሕዝቦች በሀብታም መሬቶቻቸው ላይ የተመሠረቱ መንደሮቻቸውን እንዲለቁ ሲያደርጋቸው ለገዥዎችም መሬት ጎርጉሮዖዖኦ ናዳ እስኪቀብረው ድረስ መቋቋም በማይችል ቃጠሎ ውስጥ ሥራ ቀን ከሌት ትጋትን የሚጠይቅበት የሲዖል ኑሮ ሆኖበት ነበር። እንዳያልፍ የልም ይህ ሁሉ መዓት አልፏል በቅን የማይታዘዝ ቢኖር በግርፋት የማይቀናም አሟሟቱ የከፋ ነበር። እግዚአብሔር በሰጠውና ባሰፈረው መሬት(አገር)ላይ መኖር ካልተቻለ የት መሄድ እንደሚቻል እስካሁን ድረስ መልስ የሌለው ጥያቄ ሆኖ ቀርቷል።
ይህንን አውሮፓውያን ከአሜሪካ አሕጉሮች እስከ እስያ ዳርቻ እስከ አውስትራሊያና አፍሪካን በሙሉ በአጠቃላይ በምድር ሕዝብ ላይ ማለት ነው የፈጸሙትን የግድያ፣ የዘረፋ ግፍና በደል ተንኮል ለሚያስበው ያቅለሸልሻል፣ ያሳምማል፡ አዙሮ ይጥላል።
የአውሮፓውያን አበላል በዚህ አላበቃም። ሌላውን እንተወውና ከቅኝ ግዛት በኋላ በተለይ እንግሊዝ በቀየሰችው መሠረት የአገሮች ድንበር (ወሰን)አከፋፋይ ሆነች። በዚያም ጥል የተነሳ እስከ አሁን ለምናየው የጦርነት እልቂት የጦር መሣሪያ ሽያጭ ከፍተኛ የደም ገንዘብ እየጋበሱ ነው። አንዱ ይህን ሌላው ደግሞ ያንን የወገነ በመምሰል የየዋሀንን ደም እያፈሰሱ የድህነት ሀብቱን ይበላሉ፤ አገሮቻቸውንም ያደቅቃሉ። የእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ (ባርነት) አልቀረም።
“አራተኛይቱ አዉሬ በምድር ላይ አራተኛ መንግሥት ትሆናለች፤ እርሱም ከመንግሥታት ሁሉ የተለየ ይሆናል፥ ምድሪቱንም ሁሉ ይበላል፥ ይረግጣታል፥ ያደቃትማል። አሥሩም ቀንዶች ከዚያ መንግሥት የሚነሡ አሥር ነገሥታት ናቸው።” (ዳን.7 ፥ 23-24)
ለመሆኑ የፈረንጆች እምነቶች፣ ሕይወት፣ ታሪክና ፍሬ በትንቢት መጽሐፍ ምን ይመስላል? የትኛውስ እምነት ነው ትክክል ሊባል የሚችለው?
በእርግጥ የእምነቶችን መለያ ወይም መጠሪያ ስም በቀጥታ ጠቅሶ እከሌ የተባለው ሃይማኖት ትክክል ነው፤ እከሌ፥ እከሌ የሚባሉት እምነቶች ግን ትክክለኞች አይደሉም፤ የሚሉ ቃሎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አይገኙም። ምክኒያቱም የእምነቶች ስሞች ከጊዜ በኋላ በሰዎች እየተሰጡ የመጡ ሰለሆኑ።
ነገር ግን በነቢያቱ “እኔ ሳልፈጠር አይኖችህ አዩኝ፥ የተፈጠሩ ቀኖች ሁሉ፤ አንድ ስንኳ ሳይኖር በመጽሐፍ ተጻፉ።” (መዝ. 138፥15-16፤ ራእይ 13፥8 ፤ 17 ፤ 8 ፤ 20 ፤ 5)ብሎ እንዳስነገረው የሚሆነውን ሁሉ አስቀድሞ ስላየው የአገሮችና አካባቢዎችን ምግብረ ሥራቸውን ሁሉ በሕጉ መሠረት እያንጠረጠረ፥ በስፋት እንደቀረበው፥ ከባቢሎን መንግሥት አንስቶ በተዋረድ እስካለንበት ዘመን አምጥቶ የመረጡትን እምነቶቻቸውን ፍሬዎቻቸውን፥ እጣ ፈንታቸውን አስቀምጦታል። “ከፍሬአቸው ታውቋቸዋላችሁ።” በተባለው መሠረት በማቴዎስ 7፥17-20። የእምነት ዓይነቶች ደግሞ በዋነኝነት በአገር በአካባቢና በዘር ተዋረድ እየተስፋፋ እንደመጡ በማስተዋል በግልጥ ማየት የሚቻል ነው። መካከለኛው ምስራቅ፦ አይሁድ ፡ ኢትዮጵያ፦ ተዋሕዶ ክርስቲያን፤ ዐረቦች፦ እስላም፤ ምሥራቅ አውሮፓ፡ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን፤ ምዕራብ አውሮፓ፦ ካቶሊክና ፕሮቴስታንት ከነዘርፉ፤ ምሥራቅ እስያ፦ ሂንድ፥ ቡዳ ወዘተ ናቸው። በእነዚህም ሁኔታ ስለ እስራኤል፣ ዐረቦች፣ አውሮፓ እና አሜሪካ የተፃፈውን በእምነቶቻቸው ፍሬነት የተጠቃለለውን የረዥም ዘመናት ሕይወት ታሪካቸውን ተመልክተናል፤ ቀጥሎ ደግሞ የእምነቶቻቸውን ማንነት ገላጭ የሆኑትን ዐረፍተ ነገሮ (ሐረጎችን) ሰፋ አድርገን እንመለከታለን።
የዐረቦች ሠራዊት አለቃ የሚሆነው፦ “ተመልሶም ሃይማኖታቸውን (ክርስትናን) ከካዱት ሰዎች ጋር (ከዐረቦች ጋር)ይወዳጃል። ሠራዊቱም ቤተመቅደሱንና አካባቢውን ያረክሳሉ፤(የድንጋዩ ጉልላት መስጊድ) የዘወትር መሥዋዕትም እንዳቀርብ ያደርጋሉ፤ አሰቃቂና አስጸያፊ የሆነ ርኩስ ነገር እንዲቆምበት ያደርጋሉ። ንጉሡም (ኢየሩሳሌምን የያዘው የዐረቦች ሠራዊት አለቃም)ቀደም ብለው ሃይማኖታቸውን (ኦርቶዶክስ ተዋህዶን)የካዱትን ሁሉ (አውሮፓውያንን)በማታለል የእነርሱን ድጋፍ ያገኛል።” ዳን. 11፥30-32)የኢትዮጵያ መ.ቅ.ማህበር መ.ቅ።
“ቅዱስ ቃል ኪዳን (አዲስ ኪዳንን)የተውት ሰዎች፤” “ቅዱስን ቃል ኪዳን (አዲስ ኪዳንን)የሚበድሉት፤” በሚሉት ፍሬ ሐረጎች የዕረቦችና አውሮፓውያን እምነቶች፡ ማለትም የእስልምናና የካቶሊክ–ፕሮቴስታንት ምንነት ተገልጿል።
ዐረቦች ሙስሊሞች የጌታ ኢየሱስን የእግዚአብሔር ልጅነት፣ አምላክነቱንና አዳኝነቱን፤ ከውኃና ከመንፈስ ዳግም ልደትንና ሙታን ትንሳኤውን መተዋቸውና አለመቀበላቸውም በግልጽ የታወቀ ነገር ስለሆነ የሚያነጋግር አይደለም። ትኩረት የሚሰጠው ስለፈረንጆች፤ ካቶሊክ–ፕሮቴስታንት “ቃል ኪዳኑን የሚበድሉ ሰዎች” ተብሎ ስለ መሠረተ እምነቶቻቸው የተጻፈላቸው ቃል ነው።
በደል፦ ክፋትን በማድረግ ማመፅ፡ ከእግዚአብሔር ትዕዛዝ ከፍርድም ፈቀቅ ማለት። ዳን 9፥5። በዚህ መሠረት የአዲስ ኪዳንን መበደል። በክርስትና ሃይማኖት ላይ ማመፅ፥ ትዕዛዛትን መጣል፤ ክፋትን ማድረግ፤ ሕግን መቃወም።
አዎ! ንጉሡ የተባለው ኢየሩሳሌምን የሚይዛት የዐረቦች ሠራዊት አለቃ “ቀደም ብለው ሃይማኖታቸውን የካዱትን ሁሉ፡” ማለትም፡ “ቃል ኪዳኑን የሚበድሉትን፡” አውሮፓ–አሜሪካን በማታለል ለርኩሱ ጥፋት ጦርነት የእነርሱን ድጋፍ ያገኛል፡ ያስታቸዋልም።
ዐረቦቹ ምዕራባውያኑን እንዴት እያታለሏቸው እንደሆነ የዛሬው የዓለማችን ሁኔታ በግልጽ ያሳየናል። ምዕራባውያኑ፡ ዐረብና እስላም በሆኑት አገሮች ከፍተኛ የገንዘብና የሰው ሕይወት መስዋዕት በማድረግ ላይ ናቸው። ሙስሊሞቹ ምዕራባውያኑ ላይ የሽብር ፈጣሪነት ተግባር በፈጸሙ ቁጥር፡ ምዕራብውያኑ ወደ ዐረቦቹ አገሮች በመግባት ትርፍ ለሌለው የብድር መላሽነት ተግባር ይጋበዛሉ፡ አገሮቻቸውንም ለሙስሊሞቹ ይከፍታሉ። በኢራቅና አፍጋኒስታን፡ እንዲሁም በሰሜን አፍሪቃ የወጣው ወጭ በጣም ብዙ ነበር፤ በሙስሊሞቹ ሽብር ፈጣሪዎች ጥቃት በተካሄደባት በኒውዮርክ ከተማም፡ ሰማይ ጠቀሶቹ ህንፃዎች በፈራረሱበት ቦታ ላይ መስጊድ ለመሥራት ዝግጁ መሆናቸውን ማሳወቃቸው ምን ያህል ግራ እንደተጋቡና እንደተታለሉ ነው የሚያሳየው። እዚህ ላይ ልብ ልንል የሚገባን፤ ግጭቶች በበዙባቸው በመካከለኛው ምስራቅ አገሮች፤ አንድም የአረብ ማህበረሰብ (አረብ ሊግ)አባል ወታደር ወደ ጦር ሜዳ አለመላኩን ነው። ሊቢያ፤ ግብጽ፤ ቱኒዚያ፤ የመን፤ ሶማሊያና ሶሪያ ሁሉም የዐረብ ሊግ አባላት አገሮች ናቸው። ነገር ግን የዐረብ ሊግ ወይም መንግሥታቱ ወደነዚህ አገሮች የገንዘብና ቁሳቁስ ድጎማ ከማደረግ በቀር ወታደሮቻቸውን(ፀጥታ አስከባሪዎችን)ለመላክ ፈቃደኞች አይደሉም። ሳውዲ አረቢያም ወደ ባሕሬን ሠራዊቷን ስትልክ ቀጥተኛ የወታደራዊ ፍጥጫ ባለመኖሩ፡ ቢኖርም ከሺያ እስላሟ ኢራን ብቻ ሊሆን እንደሚችልና እሷም ለጦርነት አሁን ዝግጁ እንዳልሆነች በመገንዘብ ነበር።
ቀደም ብለው ሃይማኖታቸውን ኦርቶዶክስ ተዋህዶን የካዱት ሁሉ የተባሉት አውሮፓ–አሜሪካ ተታለው የዐረቡ ሠራዊት ለሚያስነሳው ርኩስ ጥፋት ድጋፍ የሚሄዱት እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አጻጻፍ መንፈስ ንጉሡን (እየሩሳሌምእን የያዘውን የዐረቦችን ሠራዊት አለቃ)ለመወገን ሳይሆን፡ ትክክለኛ ታሪኩ በተቃራኒነት ነው። ዳሩ ግን ንጉሡ የተባለው ወይም የዐረቦች ሠራዊትና ሃይማኖታቸውን የካዱት ሁሉ የተባሉት አውሮፓውያን በተቃራኒነት ጦርነት ቢያካሂዱም ሁለቱም ወገኖች አንድ የርኩስ ጥፋት ዓላማ ጦርነት ስለሚያካሂዱ አጠቃላይ ታሪኩን ከሥር ከመሠረቱ በግልጥ ላልተረዱና ለተምታታባቸው፡ ተባባሪዎች ናቸው የሚለው ሃሳብ ያስኬዳል። እንደተገለጸው ግን ሃይማኖታቸውን የካዱት ለንጉሡ ተቃራኒዎች ሳሉ ርኩሱን ጥፋት ለማካሄድ ግን ደጋፊዎቹ ተባባሪዎቹ ናቸው። አንድ የጥፋት መንፈስ ነውና። ወደ ርኩስ ጥፋት የሚዘምተውን የምዕራቡን ወገን (መሪ) ዳን.8፥25 ላይም “በመታለሉ ተንኮል በእጁ ያከናውናል፤ በልቡ ይታበያል።” ይለዋል።
አንድ መስተዋል ያለበት ትልቅ ምስጢር፦ የእነዚህ ሁለት ወገኖች፡ ማለትም የዐረቦችና የፈረንጆች፥ አጠቃላይ ሕይወት ታሪክ በዋና ዋና ነጥቦች ጠቅለል ተደርጎ ይታያል። በሰዎች ቋንቋ፡ ፖለቲካም ሃይማኖትም ይበሉት ይህ ጽሁፍ ግን የዐረቦችን ከባቢሎኑ ናቡከደነፆር፤ የፈረንጆችን ከግሪኩ እስክንድር መንግሥታት ጀምሮ እስከ መጨረሻው ዘመን ፍሬአቸው ድረስ ባጭሩ የቀረበው በሃማኖት ነው።
ይህን ሁሉ ነገር ስለ እነርሱ እንደሚናገር ብዙዎቻችን አላስተዋልነውም፤ ዓለማችንም አስፈላጊውን ትኩረት አልሰጠችውም። እነርሱ ግን ምድሪቷን የምንቆጣጠር፤ ዓለሙን የምንሰብክ እስራኤል እኛ ነን ይላሉ። “የሚሉሽን በሰማሽ ገበያም ባልወጣሽ፤” ይላል ያገራችን ሰው። ራስን ትንሽ ቅንጣት ታህል እንኳ አለማወቅ እጅግ የሚያሳዝን ነገር ነው። “ከሀብትህም ሁሉ ማስተዋልን አትርፍ።” ምሳሌ 4፥7።
ነገር ግን ይህን ሁሉ መመልከት ያለብን በአብዛኛው፣ በዋንኛነት ወይም በአመዛኙ ነው እንጂ በአውሮፓውያንም ሆነ በሌሎች ሕዝቦች ዉስጥ እጅግ ሩህሩህና ለሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ለተፈጥሮ ሁሉ የሚቆረቆሩ ሕይወታቸውን ሳይቀር የሚሰው ብዙ ሰዎች እንዳሉ ግልጽ ነው።
ነገር ግን እነዚህ ‘ልዩ‘ የሆኑት የእግዚአብሔር ሰዎች በተለይ እኛን አፍሪቃውያኑን በሚመለከት ጉዳይ ብዙም ሚና አይጫወቱም፤ ከኛ ጋር ግንኙነት ያላቸው እኛን ለመቆጣጠር፡ ባሪያ ለማድረግ ብሎም ለማጥፋት የሚፈልጉት የአውሬው ኃይሎች ናቸው። ሲያስፈልጋቸው የኤድሱንና የኢቦላውን ቫይረስ፤ ሲያሰኛቸው ረሃቡን፣ የማጥፊያ ክትባቱንና የርስበርስ ጦርነቱን ይልኩብናል። ይህን ሁሉ ጉድ የዓለም ማሕበረሰብ እንዴት ዝም ብሎ እንደሚያልፈው እጅግ በጣም የሚገርምና የሚያሳዝን ነገር ነው።
ከዚህ ጋር በተያያዘ እየተካሄደ ያለው ጦርነት በይበልጥ በክርስትና እምነት ላይ ነው ትኩረቱን ያደረገው። የአውሮፓን የበላይነት በምድር ላይ ለማስፋፋት ሲባል የክርስትና እምነትን ለማጥፋት ዘመቻ ውስጥ የሚሳተፉት፡ ልባቸውን ለአውሮፓ–አሜሪካና ዐረቦች ዓላማ የሚሰጡት ወገኖች ሁሉ የአውሬው አገልጋይ እንደሆኑ ተደርገው ነው የሚቆጠሩት። አውሮፓውያኑ–አሜሪካኑ ከሙስሊሞቹ ዐረቦች ጋር በመተባበር በክርስቲያን ሕዝቦች ላይ የሚያካሂዱትን ዘመቻ፤ በግብጽ፤ በኢራቅ፤ በሶሪያ በግልጽ የምንታዘበው ነው።
በሶሪያ በ አላዊ እስላም መንግሥታዊ መስተዳደርና “ደፈጣ ተዋጊዎች” በሚባሉት የሱኒ እስላም አክራሪዎች መካከል የሚካሄደው ጦርነት ወደ አሌፖ ከተማ መዘዋወሩ ያለ ምክኒያት አይደለም። አሌፖ ጥንታዊ የክርስቲያኖች ከተማ ናት። በዚህች ከተማ 47 ጥንታውያን ዓብያተክርስቲያናት አሉ፤ አሁን ግን በጦርነቱ ሳቢያ በቦምብ ለመፈራረስ ይበቃሉ፤ በዚህም የዲያብሎስ አርበኞች ዓላማቸውን ከግብ ያደርሳሉ። ከ100 ዓመታት በፊት፡ እ.አ.አ በ1860 ዓ.ም በአሌፖና አካባቢዋ ተካሂዶ በነበረው የድሩዝ ሙስሊሞች ጸረ–ክርስቲያን ዘመቻ እስከ 20.000 የሚጠጉ ክርስቲያኖች ተጨፍጭፈዋል። በዚያን ጊዜም ቢሆን ምዕራባውያኑ ከቱርክና ዐረብ ሙስሊሞች ጋር በመተባበር ነበር ክርስቲያኖችን በመካከለኛው ምስራቅ እንዲሁም በኢትዮጵያ ሲጨፈጭፉ የነበሩት። በዓፄ ዮሐንስ ዘመነ መንግሥት ኢትዮጵያን ወረርው የነበሩትን የግብጽና ቱርክ ሠራዊቶች በሰው ኃይልና በጦር መሣሪያ ሲደግፉ የነበሩት እንግሊዛውያንና አሜሪካውያን እንደነበሩ ስንገነዘብ እጅግ በጣም እያዘንን ነው፤ ክርስቲያን ነን የሚሉ ኃያላን አገሮች ከእስላም አገሮች ጋር በመተባበር ሌላዋን ድሃ የክርስቲያኖች አገር፤ ኢትዮጵያን ለመጨፍጨፍ ሲበቁ። እነዚህ ከታሪክ ለመማር ፈቃደኞች ያልሆኑት ምዕራባውያን በሁለተኛው የዓለም ጦርነትም ይህን ትልቅ ስህተት ደግመውታል፤ አሁንም እየደገሙት ነው። ባሁኑ ሰዓት ልዩ የውትድርና ውል ከአሜሪካ ጋር ለማድረግ የበቁትና በጣም የረቀቁትን የጦር መሣሪያዎች ከአሜሪካ ለማግኘት ዕድል ያገኙት፤ ከኔቶ ዓባላት ሌላ፤ ግብጽ፣ ፓኪስታንና አፍጋኒስታን ናቸው።
የሚቀጥለው የዚህ አውሬ ሠራዊት ዒላማም የመጨረሻዋ የክርስትና ትልቅ ምሽግ የሆነችው ኢትዮጵያ እንደሆነች መገንዘብ ይኖርብናል።
የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይጠብቅልን!
በ PDF ለማንበብ እዚች ይጫኑ EndTimesConstellation
______________________________________