አብዛኛዎቹ ነዋሪዎቿ ሙስሊሞች በሆኑባት የሩሲያ አውቶኖማዊ ሪፑብሊክ በቼችኒያ ዋና ከተማ ነበር ይህ ፀረ–ክርስቲያናዊ ጥቃት ትናንትና የተሠነዘረው። በቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ውስጥ በምሽት አገልግሎት ወቅት 15 ክርስቲያኖች ጸሎት እያደረሱ ነበር። 4ቱ ሽብር ፈጣሪዎቹ ቤተክርስቲያን ውስጥ ገና ሳይገቡ ከጸጥታ አስከባሪዎች ጋር በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ከቤተክርስቲያን ውጭ ተገድለዋል። ሁለት ፖሊሶች እና አንድ ክርስቲያን በተጨማሪ ሞተዋል።
ነፍሳቸውን ይማርላቸው!
በሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አንድ የሚገርም ነገር አለ፦
ይኽውም በብዙ የሩሲያ ኦርቶዶክስ አብያተክርስቲያናት ህንፃ ላይ መስቀሉ፡ ከስሩ ያለውን ግማሽ ጨረቃ እንዲወጋው ተደርጎ ይሠራል፤ ክቡር መስቀሉ በእስላም ግማሽ ጨረቃ ላይ ተቸክሎ ይታያል።
ይሀም፦ ክርስትና እስልምናን ድል ያደርገዋል ማለት ነው
______