Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘ቸርች’

የወደቀው መልአክ በናይጄሪያ? | ተወርዋሪ ኮከብ በመናፍቃን ቸርቾች ላይ ወደቀ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 31, 2020

የንጋት ልጅ አጥቢያ ኮከብ/ሉሲፈር ኩሬ በ አኩሬ?

ባለፈው ቅዳሜ በደቡብ ምዕራብ ናይጀሪያ አኩሬ ከተማ ከሰማይ ወረደ የተባለ ተወርዋሪ ኮከብ ወይም ሚትዮራይትስ /ሜትዮሮይድስ ቸርቾችንና መቶ የሚሆኑ ቤቶችን ማፈራረሱ ታውቋል። በቦታው ከፍተኛ የፍንዳታ ድምጽ ተሰምቶና ጥልቅ የሆነ አዲስ ኩሬ ተገኝቶም ነበር። ምንም እንኳን አንዳንዶች፡ የአገረገዢውን ጨምሮ፡ ይህን ኃይለኛ ፍንዳታ የፈጠረው በጭነት መኪና የተወሰደ ቦምብ ነው ቢሉም ቅሉ በይፋ ግን፡ ባለሙያዎች አሁን እንዳረጋገጡትም፡ የ 43 ዲግሪዎች አንግል የሚሸፍን ስፍራ ላይ ኩሬ የሠራ ሜትዮሮይድስ / ሚትዮራይትስ ወይም ተወርዋሪ ኮከብ ነው።

በሰማይ ላይ የሚመላለሱ ልዩ ልዩ የሰማይ ሠራዊት ከዋክብት ተወርዋሪ ኮከብ ወይንም ሚትዮራይትስ/ ሜትዮሮይድስ የሚባሉት የሚባሉት ድንጋያማ አለቶች የኮሜትና አስትሮይዶች ቅሪቶች ናቸው። ኮሜትም አስትሮይድም ግዙፍ አለቶች ናቸው። እነዚህ አካላት ወደ መሬት ወይም ወደ ሌላ አካል ቀረብ ሲሉ እየተሰባበሩ፣ እየተሰባበሩ ይመጡና፤ መሬት በፀሐይ ዙሪያ ስትሽከረከር እነርሱን ስለምትስብ፣ ወደመሬት እየመጡ ብዙዎቹ ተቃጥለው ያልቃሉ።

የሚገርም ነው፤ ባለፈው ዓመት ላይ በዚህችው አኩሬ ከተማ የአንድ ዓመት ህፃን ልጅ በማምለኪያው ቦታ ተቀብሯል በሚል ያልተጣራ ወሬ ሰልፈኞች ሌላ የመናፍቃን ቸርች አቃጥለው ነበር ። ህፃኑ በቸርች ውስጥ ከእናቱ ጋር የታየው ከወር በፊት ሲሆን፤ ከቸርቹ ሳይወጣም በዚያው የውሃ ሽታ ሆኖ ቀርቶ ነበር።

___________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: