Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘ትዳር’

እግዚሐርአብ-ሰርግ-እርግብ = ሰእርግብ | ቅዱስ ጋብቻ በተዋሕዶ ብቻ እንደሚገኝ እርግቦቹ መሠከሩ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 21, 2019

ይህን ባየንበት ወቅት የሁላችንም እምባ መጥቶ ነበር። ዛሬ ማክሰኞ ነው፤ እግዚአብሔር፦ የምድር አራዊትንና የሰማይ ወፎችን ሁሉ፦ ሕያው ነፍስ ላለውም ሁሉ ስም ያወጣላቸው ዘንድ ወደ አዳም አመጣቸው። እግዚአብሔር ሰኞ ማክሰኞ አዕዋፋትን አመጣለት፤ ነገር ግን ለአዳም እንደ እርሱ ያለ ረዳት አልተገኘለትም ነበርና አጭቶ፥ ወድዶ፥ ፈቅዶ እንዲገባበት ሔዋንን ከጎኑ አንዲት አጥንት ወስዶ ሴት አድርጎ ሠራለት። አዳምም፦ “ይህች አጥንት ከአጥንቴ ናት ፥ ሥጋም ከሥጋዬ ናት፤ እርስዋ ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል። ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፥ ከሚስቱም ይጣበቃል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።” ብሎ እግዚአብሔር የሰጠውን በጸጋ ተቀበለ።

አዳምና ሔዋን በጋብቻ አንድ አካል መሆናቸው፦ ሔዋን ከአዳም የጎን አጥንት በመፈጠሯ ብቻ አይደለም። አንድ ክብር በመውረስም ነው። ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ፦ “እናንተ ባሎች ሆይ ፥ ደካማ ፍጥረት ስለሆኑ ከሚስቶቻችሁ ጋር በማስተዋል አብራችሁ ኑሩ፤ ጸሎታችሁ እንዳይከለከል አብረው ደግሞ የሕይወትን ጸጋ እንደሚወርሱ አድረጋችሁ አክብሩ አቸው።” ያለው ለዚህ ነው። ፩ኛ ጴጥ ፫፥፯። ከዚህም ሌላ አንድነታቸው አንድ ልብስ በመልበስ ነው። ፈቃደ ሥጋቸው በጠ የቃቸው ጊዜም በግብር አንድ ይሆናሉ። ወንድ ቢወለድ ያንተ ነው፥ ሴት ብትወለድ ያንቺ ነው አይባባሉም። ሁለት ሆነው አንድ ልጅ ያስገኛሉ። አንድም፦ ከእናት ደም ፥ ከአባት ዘር ተከፍሎ አንድ ሰው ሁኖ ይወለዳል።

የጋብቻ ዓላማዎች ሦሰት ናቸው፦

የመጀመሪያው። “የሚመቸውን ረዳት እንፍጠርለት” እንዲል፦ ለመረዳዳት ነው። መረዳዳት ሲባልም በሥጋ ብቻ አይደለም በነፍስም ጭምር ነው። ለሥጋቸው በሥራ ሲረዳዱ ለነፍሳችው ደግሞ በጸሎት ይረዳዳሉ። ለምሳሌ፦ ይስሐቅ፦ ሚስቱ ርብቃ ለሃያ ዓመታት መክና ልጅ አልወለደችለትም ነበር። በዚህም ምክንያት ስለ ርብቃ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ ፥ እግዚአብሔርም ተለመነው፥ ርብቃም መንታ ፀነሰች ይላል። ዘፍ ፳፭ ፥፳፩። ሁለተኛው በፍትወተ ሥጋ ላለመቸገር ነው። ሦስተኛው ደግሞ፦ “ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው ፥እግዚአብሔርም ባረካቸው ፥እንዲህም አላቸው፦ ብዙ ተባዙ ፥ምድርንም ሙሉአት።” እንዲል፦ ዘር ለመተካት ነው። ዘፍ ፩፥፳፰። እነዚህም እንደ ሦስት ጉልቻዎች የሚቆጠሩ ናቸው።

አዎ! እግዚአብሔርን ስንቀርበው ፥ ይቀርበናል፤ ስንረቀው ይርቀናል። እግዚአብሔርን በቀረቡ ተዋሕዶዎች ዘንድ ፩ + = ፩ ሲሆኑ እግዚአብሔርን በራቁት በሌሎች ዘንድ ግን ፩ + = ፪ ናቸው። ስለዚህ ቅዱስ ጋብቻ በሌሎች ዘንድ የለም ለማለት ያስደፍራልበሌሎች ዘንድ ሁሉም ነገር ሂሳብ ነው፡ ዓለማዊ ነው፤ ከጋብቻ በፊት “መልአክ” የተባለ የትዳር ጓደኛ ከጋብቻ በኋላ “ሰይጣን” ይባላል። በመላው ዓለም እንደምናየው ወንዱ ወንድነቱን ሴቷ ሴትነቷን በማጣት ፍቅርአልቦች፣ አመጸኞች እና ጨካኞች ለልጆቻቸው ነፍስ የማይቆረቆሩ ግድየለሾች ይሆናሉ፤ ትዳራቸውም የሲዖል ነው። ይህ ክስተት ዛሬ “ለዘብተኞች”፣ “ፌሚኒስቶች” ፣ “ሰዶማውያን”፣ “መሀመዳውያን” በሚባሉት ዘንድ በደንብ እየተንጸባረቀ ይታያል።

ኢትዮጲያዊ ሲፋቀር አቤት ሲያምር ፥ ኢትዮጵያውያን በራሳቸው ጎዳና ሲራመዱ ሁሉም መዋደዱ! የምንጓዝበት መንገድ መንፈሳዊ ከሆነ በሁሉም በኩል ሰላም፣ ፍቅር፣ ብልጽግና እና ደስታ ሲነግሱ እናያለን፤ እርግቦቹ (መንፈስ ቅዱስ) እንደሚያሳዩን።

ታላቋ አገራችን ከተዋሕዶ ውጭ የሚገኙትን ትርኪምርኪ መጤ የምዕራባውያንን (ዔሳው)እና የአርቦችን(እስማኤል)አምልኮቶችን፣ ርዕዮተ-ዓለሞችንና ባሕሎችን አስገብታ መቀበል ስትጀምር ነው ፍቅር እየቀዘቀዘ፣ ሰላም እየጠፋባት፣ እንስሳቱ፣ አራዊቱ እና አዕዋፋት እየራቁባት፣ ድርቅ፣ ረሃብ እና በሽታ እየሰፈኑባት፤ ባጠቃላይ እያነሰችና እየወደቀች የመጣችው።

__________________

Posted in Ethiopia, Faith, Love | Tagged: , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ሙሽሪት ኢትዮጵያ ጠላትሽ ይንቀጥቀጥ ይሁን እያሪኮ፤ በነገድ በዘርም የእልፍነሽ አንቺኮ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 19, 2019

[ወደ ኤፌሶን ሰዎች ፭፥፲፱]

በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊም ቅኔ እርስ በርሳችሁ ተነጋገሩ፤ ለጌታ በልባችሁ ተቀኙና ዘምሩ”

__________________

Posted in Ethiopia, Faith, Love | Tagged: , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ሥርዓተ-ተክሊል | ያስደስታል የእኛ እምነታችን፤ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የጋብቻ ሥርዓታችን

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 18, 2019

__________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: