ዳኛው ፈራጁ ሁሉን ነገር የሚያየው እርሱ ንጉሡ ክርስቶስ ብቻ ነው!
“በእግዚአብሔርም ቍጣ ቀን ብራቸውና ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም፤ እርሱም በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ፈጥኖ ይጨርሳቸዋልና ምድር ሁሉ በቅንዓቱ እሳት ትበላለች።”[ትንቢተ ሶፎንያስ.1፥18]
ባዕዳውያኑ የአገራችን ጠ
ላቶች ምንም ሳናደርጋቸው፤ ሳንደርስባቸው በሕዝባችን ላይ ያደረሱት በደል በዓይነቱ በጣም አስከፊ በመጠኑም እጅግ በጣም ከፍ ያለ ነው፡ ለሃሳብ እንኳ የሚያንገፈግፍ ነው። አንመኝላቸውም፡ ግን የፍትህ አምላክ፡ ኅያሉ ፈጣሪያችን መቅሰፍቱን ያወርድባቸዋል፤ ሌላ አማራጭም ያለ አይመስልም።
በመጪዎቹ የጾምና የጸሎት ቀናት እንድንድንና እንዲድኑ ልዩውን ጸሉት ልናደርስ ይገባናል። በማወቅም ሆነ ባለማወቅም በክህደታዊ መንገድ ከጠላቶች ጋር በመመሳጠርና በመተባበር ወንድሞቹን፣ እህቶቹን እንዲሁም ልጆቹን ለአውሬው አሳልፎ ለሚሰጠው “ኢትዮጵያዊ” ጊዜው ሳይረፍድ እንጸልይላቸው፤
ማንነታቸውን ክደው የክርስቶስ አምላክን ልብ ለሚያቆስሉት፡
-
ለተታለሉት የባዕዳውያን እምነት ተከታዮች ሁሉ እንዲድኑ ፀሎት እናድርስላቸው
-
የክርስቶስን ደናግልት ህፃናት ለባእዳዊ ሰዶማውያን ለሚያስረክቡት እንዲድኑ እንጸልይላቸው
-
የክርስቶስ ልጆች እንዳይበዙ የእህቶቻችንን ማሕፀን ለሚመርዙት ጨካኝ ውገኖች እንዲድኑ እንጸልይላቸው
-
በክርስቶስ ስም የተጠመቁትን እህቶቻችንን ለአረማውያኑ ጣኦት–አምላኪ ባዕዳን አሳልፈው ለሚሰጡት የዘመኑ ጂፋሮች እንዲድኑ እንጸልይላቸው
-
የክርስቶስን ገናናነትና ክብር ለመቀነስ የናዝሬትን፣ የደብረ ዘይትንና የመሳሰሉትን የኢትዮጵያ ቦታዎች ስም በዘፈቃድ ለሚቀይሩት ምስጋና–ቢሶች እንዲድኑ እንጸልይላቸው
-
ውጩ አገር ሆነው፡ ቸሩ እግዚአብሔር የሰጣቸውን ጸጋ ቸል በማለት እራሳቸውን በስንፍና የስድብና ጥላቻ ማዕበል ውስጥ ለከተቱና ወገናቸውንና ቅድስት ቤተክርስቲያናቸውን በድፍረትና በትዕቢት ለሚያዋርዱት እንዲድኑ ጸሎቱን እናድርስላቸው።
“ወላጆችም ስንኳ ወንድሞችም ዘመዶችም ወዳጆችም አሳልፈው ይሰጡአችኋል፥ ከእናንተም አንዳንዱን ይገድላሉ“[ሉቃስ 21:16]
ኒፈሌያዊ የደመና መጋረጃዎች ባገራችን ሰማያት ላይ ተዘርግተዋል፡ ነገር ግን የጽዮን ልጆች በእግዚአብሔር ብርኃን የተከበቡ፡ በፍቅሩ የታጠሩ ናቸውና የእርሱ ኃይል ይጠብቃቸዋል፡ የሚያሸነፋቸውም ኅይል የለም። የቃልኪዳኑ ልጆች ያሉበት ቦታ ሁሉ አምላካችን ስላለ ሁሉ ነገር ጥሩ ነው፡ ቸር ነው፤ በቤቱ ለዘላለም ለመኖር ተመርጠዋልና።
የቅዱሳን አምላክ ቸሩ እግዚአብሔር ነብዩ ዮናስን፡ ልክ እንደ ክርስቶስ፡ ሦስት ቀን እና ሦስት ሌሊት በአሣ ሆድ አሳድሮ ከክፉ ነገር ሁሉ ጠብቆ እንዳዳነው እኛንም ከመጥፎ ነገር ይከላከለን ከመቅሰፍት ይጠብቀን። አሜን!
ትንቢተ ዮናስ
ምዕራፍ አራት
የተናገረው ቃል ስላልተፈጸመ
ዮናስ ተቆጥቶ እያጕረመረመ
እንደዚህ እያለ ጸለየ ወደ አምላክ
እኔን መጀመሪያ ነነዌ ለመላክ
አስበህ ብታዘኝ ይህንኑ ዐውቄ
ወደ ተርሴስ ልሄድ ጠፋሁ ተደብቄ
ምሕረትህ የበዛ መሓሪና ታጋሽ
በደል የምትረሳ ከቍጣ ተመላሽ
የቍጣህን ያህል ምሕረትህ የጠና
መሆንክን ጥንቱንም እኔ ዐውቃለሁና
እኔን ግን ግደለኝ ልሙት ልቀበር
ሐሰት ተናግሬ የማይሆን ነገር
አልፈልግምና ቆሜ ለመኖር
ክከተማ ወጥቶ በምሥራቅ በኩል
ከወደ ዳር ሆኖ ነነነዌን ሊያስተውል
ምን እንደሚያገኛት ለማየት ዮናስ
ሠርቶ ተቀመጠ አንድ ትንሽ ዳስ
እግዜር በጥበቡ አንድ ቅል አብቅሎ
ቅሉም አደገና ከፍ ከፍ ብሎ
የዮናስ ራሱ እንዲያገኝ ጥላ
ለፀሓዩ ንዳድ ሆነለት ከለላ
በዚህ በቅል አገር ዮናስን ደስ አለው
እንዲህ ቶሎ ደርሶ ስላገለገለው
እግዜር በማግሥቱ ጧት በማለዳ
ቅል የሚበላ ትል ፈጣሪ አሰናዳ
ትሉ ቅሉን በልቶ በፍጥነት ደረቀ
ፀሓይ ወጣችና ግዜው በጣም ሞቀ
እግዜር አዘዘና ትኩስ ነፋስ መጣ
የሚከለልበት መጠጊያ ስላጣ
ቅሉ ደረቀና ንዳድ ቢያቃጥለው
ዮናስ ተበሳጭቶ ላምላክ እንዲህ አለው
እንደዚህስ ሆኜ ቆሜ ከምኖር
እባክህ ግደለኝ ልሙት ለቀበር
ደረቀብኝ ብለህ ይህን ቅል ለማጣት
እውን ይገባል ወይ ያንተ አሁን መቆጣት?
ብሎ እግዜር ቢጠይቅ መለሰ ዮናስ
በንዴቴ ብዛት እስክሞት ድረስ
አዎን ይገባኛል መናደድ መጤስ
እግዜርም መለሰ ለምን ጠፋ ስትል
ይህ ያልለፋህበት ያልደከምህበት ቅል
አንተ ስትናደድ ፈጥሬአት እኔማ ሳጠፋት ሳፈርሳት ነነዌን ከተማ
መቶ ሓያ ሺህ ነው የሕዝብዋ ብዛት
ለምን ትቆጣለህ እኔ ባዝንለት
ብሎ በምሳሌ ሲያስተምር ይቅርታ
ለዮናስ ነገረው የምሕረቱ ጌታ
ለእግዚአብሔር ቸርነት ምስጋና ይድረስ
ከክቡር አቶ ከበደ ሚካኤል የቅኔ አዝመራ ከሚለው የተወሰደ (1956)