Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • May 2023
    M T W T F S S
    1234567
    891011121314
    15161718192021
    22232425262728
    293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘ትንሣኤ’

Happy Pascha! The Orthodox Easter Holy Fire From Jerusalem to The World

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 16, 2023

❖❖❖ ብሩክ ፋሲካ! የኦርቶዶክስ ፋሲካ ቅዱስ እሳት ከኢየሩሳሌም ወደ ዓለም ❖❖❖

በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም በቀራንዮ ጎልጎታ የጌታ መካነ መቃብር በሚገኝበት ቅዱስ ቤተክርስትያን ውስጥ እያንዳንዱ የምስራቅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቀዳሚት በዛሬው የሥዑር / ቅዱስ ቅዳሜ ዕለት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በኢየሱስ መቃብር ዙሪያ በተዓምር የሚወርደውን“ነበልባል” ለመመልከት ይሰበሰባሉ፡፡

የእግዚአብሔር እጅግ አስደናቂ ከሆኑት ተዓምራት ውስጥ አንዱ ይህ በቀዳሚት ሥዑር በኢየሩሳሌም በጌታችን መካነ መቃብር ላይ የሚወርደው የተባረከ/ቅዱስ እሳት ነው።

የምስራቅ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ይህ የትንሳኤ ጉልህ ምልክት ነው ብለው ያምናሉ።

ይህ ዋና ከሆኑት የምስራቅ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ተዓምራት መካከል አንዱ ነው። ይህ ተዓምር ላለፉት ፲፻፪፻/1,200 ዓመታት በየዓመቱ እየተከሰተ እንደሆነ ይታመናል።

ሥነ ሥርዓቱ የሚጀምረው በግሪክ ኦርቶዶክስ ፓትርያርክ (ወይም በሌላ የኦርቶዶክስ ሊቀ ጳጳስ) በቤተክርስቲያኑ ውስጥ ወደ ክርስቶስ ባዶ መካነ መቃብር ወርዶ ልዩ ጸሎቶችን በማንበብ ነው። ኦርቶዶክስ ያልሆነ ክርስቲያን ደግሞ ፓትርያርኩ ሻማዎቹን ለማብራት የሚጠቀሙባቸው የነዳጅ ዘይት መብራቶች በውስጣቸው እንዳይቃጠሉ ለማድረግ መቃብር (አነስተኛ መቃብር ዙሪያ ያለውን ትንሽ መዋቅር) እንደሚመረምሩ ተገልጻል ፡፡

ከመቃብሩ በላይ እና በዙሪያው በተከበበች ቤተክርስቲያን ውስጥ ፣ ምዕመናን በአንድ ድምፅ “ኪራላይሶን”(እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ!)ያሰማሉ፡፡ ቆይታው ረጅም ወይም አጭር ሊሆን ይችላል ግን ውሎ አድሮ ፓትርያርኩ ለብቻቸው በሚጸልዩበት መቃብር ላይ እንደሚታዩ ይነገራል ፡፡ ከዛም ፓትርያርኩ ከዚህ ተዓምራዊ ነበልባል ሻማዎቹን በማቀጣጠል ደወሎችን እየደወሉ በምዕመናኑ መካከል ተገኝተው እሳቱን ወደ ሌሎች ቀሳውስት ያስተላልፋሉ፡፡ በዚህ ወቅት ጨለማ የነበረው የቤተ ክርስቲያን ሕንፃ በተዓምራዊው የተባረክ/ ቅዱስ እሳት ያበራል፡፡

ለመጀመሪያዎቹ በርካታ ደቂቃዎች እሳቱ ይቀጣጠላል ነገር ግን አይባላም ፡፡ በዚህን ጊዜ ፣ ብዙ ምዕመናን ፊታቸውን እና እጆቻቸውን ሳይቃጠሉና ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸው በእሳቱ ነበልባል ውስጥ ይታጠባሉ፡፡ እሳቱ ከሻማ ወደ ሻማ ከተላለፈ በኋላ በሩቅ በሰፊው እንዲሰራጭ በመብራት ሳጥን ውስጥ ይቀመጣል፡፡

🔥 Holy Fire 🔥

🔥 Thousands of Christians throng Jerusalem for the traditional Holy Fire rite ahead of the Orthodox Easter, despite a security clampdown in the holy city.

❖ Every Orthodox Holy Saturday in Jerusalem’s Church of the Holy Sepulcher, thousands gather to witness a flame “miraculously” appearing in the tomb of Jesus.

Orthodox Christians believe it’s a potent symbol of the resurrection.

It’s the Church’s most important miracle. And it’s believed to have been happening annually for the past 1,200 years.

The ritual begins with the Greek Orthodox Patriarch of Jerusalem (or another Orthodox archbishop), descending into the empty tomb of Christ within the church and reciting special prayers. A non-Orthodox Christian is also said to examine the edicule (a small structure surrounding the tomb) to make sure no oil lamps have been left burning inside that the patriarch could use to light his candles.

In the crowded church above the tomb and surrounding the edicule, the faithful chant with one voice “Kyrie eleison” (Lord, have mercy). The wait might be long or short but eventually a light is said to appear in the tomb where the patriarch has been praying alone. He then lights his candles from this miraculous flame and, accompanied by the pealing of bells, emerges to spread the fire among the crowd. The oncedark church becomes illuminated by the miraculous Holy Fire.

It is said that for the first several minutes the fire burns, but does not consume. During this time, many of the faithful bathe their faces and hands in the flame, apparently without being harmed. The flame is passed from candle to candle and then placed in lanterns so that it can be spread far and wide.

______________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የሞት ኃይልን ሰብሮ ተነስቷል የትንሣኤው ጌታ | ሲኦል ተሻረልን ጌታችን ተነስቷል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 16, 2023

❖❖❖[፩ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች ምዕራፍ ፬፥፲፬]❖❖❖

“ኢየሱስ እንደ ሞተና እንደ ተነሣ ካመንን፥ እንዲሁም በኢየሱስ ያንቀላፉቱን እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ያመጣቸዋልና።”

✞✞✞

ተነስቷል

ወተንሥአ እንበል ………..

ትንሣኤው ልዩ ነው ………..

የመከራ ቀንበር ከእኛ አርቆልናል

✞✞✞እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው አደረሰን!✞✞✞

ጽዮናውያን ለሆኑ ኢትዮጵያውያን ሁሉ በጎ ዘመን እየመጣ ነው።

______________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

Psychologist Dr. Jordan Peterson on the Crucifixion of Christ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 14, 2023

✞✞✞ Day 6: Trial, Crucifixion, Death, and Burial on Good Friday

❖ የቪዲዮው ምስል ላይ ከጌታችን ጎን ደመናው የኢትዮጵያን ቅርጽ ሠርቶ ይታያል (የመጀመሪያው) ልክ እሱን የመሰለ ቅርጽ በትናንትናው የጸሎተ ሐሙስ ዕለት የዕጣን ማጬሻዬ ላይ ታይቶኝ ነበር። አጋጣሚ ሳገኝ አቀርበዋለሁ። ተዓምር ነው!

Friday’s events are recorded in Matthew 27:1-62, Mark 15:1-47, Luke 22:63, Luke 23:56, and John 18:28, John 19:37.

In the early morning hours, as Jesus’ trial was getting underway, Peter denied knowing his Master three times before the rooster crowed.

Good Friday is the most difficult day of Passion Week. Christ’s journey turned treacherous and acutely painful in these final hours leading to his death.

According to Scripture, Judas Iscariot, the disciple who had betrayed Jesus, was overcome with remorse and hanged himself early Friday morning.

Meanwhile, before the third hour (9 a.m.), Jesus endured the shame of false accusations, condemnation, mockery, beatings, and abandonment. After multiple unlawful trials, He was sentenced to death by crucifixion, one of the most horrible and disgraceful methods of capital punishment known at the time.

Before Christ was led away, soldiers spit on him, tormented and mocked him, and pierced him with a crown of thorns. Then Jesus carried His cross part of the way to Calvary and then a man named Simon was compelled to carry it the rest of the way. At Calvary, Jesus was again mocked and insulted as Roman soldiers nailed Him to the wooden cross.

Jesus spoke seven powerful statements from the cross, including “Father, forgive them, for they do not know what they are doing” (Luke 23:34, NIV), “Father, into your hands I commit my spirit” (Luke 23:46, NIV), and His last words were, “It is finished” (John 19:30).

Then, about the ninth hour (3 p.m.), Jesus breathed his last breath and died.

By 6 p.m. Friday evening, Nicodemus and Joseph of Arimathea took Jesus’ body down from the cross and lay it in a tomb.

______________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የሞት ኃይልን ሰብሮ ተነስቷል | ሲኦል ተሻረልን ጌታችን ተነስቷል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 24, 2022

✞✞✞

ተነስቷል

ወተንሥአ እንበል ………..

ትንሣኤው ልዩ ነው ………..

የመከራ ቀንበር ከእኛ አርቆልናል

እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው አደረሰን!

ጽዮናውያን ለሆኑ ኢትዮጵያውያን ሁሉ በጎ ዘመን እየመጣ ነው።

😇 በዚህ የተቀደሰ ሣምንት የገጠመኝን በአጭሩ ላውሳው፤

ባለፈው የፀሎተ ኃሙስ ዕለት ብዙ ፈተና ገጥሞኝ ነበር፤ በሕልሜ አንዲት የማላውቃትና አይቻት የማልውቃት ሴት ስታሽኮረምመኝና ስትስመኝ አፌ በጥራጥሬ ሞላና ጥራጥሬውን እየተፋሁ፤ ለምንድን ነው የምትስሚኝ፤ ይኽ እኮ የጾም ጊዜ ነው፤ ተገቢ አይደለም!” ብዬ ሄድኩ። ዛሬ ደግሞ፤ ከሁለት ሰዓታት በፊት ወደቤቴ ላመራ ስል መንገድ ላይ ያልተለመደ መንገድ ተክትዬና ሳልዘጋጅበት ወደማዘወትርባት የቅዱስ ዮሴፍ ጸሎት ቤት አመራሁ። እዚያም ሌላ ሰው አልነበረም፤ ጸሎት አድርሼ ስጨረስም አንዱ ወንበር ላይ የገንዘብ ቦርሳ አየሁና፤ ስልክ ቁጥሬን ለመተው ወረቅት ሳወጣ፤ ግን እኮ ዝምብሎ የተጣለ ቦርሳ ሊሆን ይችላል እስኪ ልክፈተውበማለት ስከፍተው ሦስት የክሬዲት ካርዶች፣ የጤና ዋስታና ካርዳ፣ የመንጃ ፈቃድ፣ እስከ መቶ ዩሮ የሚጠጉ ብሮች ወዘተ. አገኘሁ። የመንጃ ፈቃዱን ስከፍተው አድራሻና የብሎንዷን ሴት ፎቶ አየሁት። ወዲያውም፤ እንዴ ምናልባት በሕልሜ ያየኋት ሴት ትሆን እንዴ? ዋው!” ብዬ በመገረም፤ ሴትይዋ ወደምትኖርበት ቤት አመራሁ። ደወሏን ስደውል ውሾች አስቀድመው መጮኽ ጀመሩ፤ ከዚያም ሴትየዋ ወጣች፤ በሃያ ስምንት እና ሰላሳ ዓመት ዕድሜ አካባቢ ያለች ሴት ትሆናለች። ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ፤ ዛሬ ጠዋት ምን ጠፍቶብዎታል?” ስላት፤ አንተ ማንነህ? ምንም አልጠፋብኝም!” አለችኝ፤ እርግጠኛ መስላ። እኔም፤ ዛሬ በቅዱስ ዮሴፍ ጸልቶ ቤት ነበሩን?” ስላት፤ አዎ!” አለችኝ፤ ያኔ ቦርሳዋን ከኪሴ አውጥቼ ሳሳያት፤ በመገረምና በመደሰት፤ ትልቁን ቦርሳየን አልፈተሽኩትም! እግዚአብሔር ይስጥህ፣ ባክህ ግባ ቡና ጠጥተህ ሂድ…” አለችኝና ሃምሳ ዩሮ ገደማ አውጥታ፤ ባክህ ይህን ውሰድ፣ ከፈልግክም ለተቸገሩ ስጥልኝበማለት ልትሰጠኝ ስትሞከር፤ ኧረ በጭራሽ፤ ዛሬ የትን ሣኤ ክብረ በዓል ስለሆነ፤ ለኔ የጠፋብዎትን አምጥቼ ከመስጠት በላይ የበለጠ ስጦታ የለም፤ የቅዱስ ዮሴፍ ሥራ ነው! አይሆንምስላት እምባ እየተናነቃት ጥምጥም አድርጋ አቀፈችኝና ጉንጮቼን ሳመቻቸው። እኔም፤ ይህን ቀን ያስታውሱት፤ ከሰባት ዓመታት በፊትም መንገድ ላይ ገንዘብና ክሬዲት ካርዶች፣ መታወቂያ የነበረው ቦርሳ በጌታችን ልደት ዋዜማ አግኝቼ፤ ያኔም ለጠፋባት ሴት እንደ ገና አባት ይቁጠሩኝ፤ ለኔም ለርስዎም ትልቅ ስጦታ ነው ገንዘብ አልቀበልም ብያት ነበርስላት በድጋሚ አቀፈችኝና ተሰነባብተን ተለያየን።

በዚህ ስጦታ እጅግ በጣም ነው ደስ የተሰኘሁት፤ መጭው ጊዜ በመከራና ስቃይ ላይ ላሉት አባቶቼና እናቶቼ፣ ወንድሞቼና እኅቶቼ ብሩኽ እንደሚሆን ጥሩ ስሜት ይሰማኛል። እነዚህ ገጠመኞች ትልቅ ምልክቶች ናቸው። ጽዮናውያንን በድጋሚ የማስጠነቅቀው ግን በተደጋጋሚ ከባድ የሆኑ ስሕተቶችን የሠሩት ሕወሓቶች ዛሬም በግትርነት በሰፊው በማስተዋወቅ ላይ ያሉትን (ወዮላችሁ!) የሉሲፈርን/ቻይናን ባንዲራ እንዲያስወግዱት ነው። ይኽ ሳይውል ሳያደር መወጣት ያለባቸው ግዴታቸው ነው!

✞✞✞ No CROSS No CROWN – ያለህመም ማግኘት የለም ፥ ያለ መስቀል ፣ አክሊል የለም! ✞✞✞

______________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

Psychologist Dr. Jordan Peterson on the Crucifixion of Christ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 22, 2022

✞✞✞ Day 6: Trial, Crucifixion, Death, and Burial on Good Friday

Friday’s events are recorded in Matthew 27:1-62, Mark 15:1-47, Luke 22:63, Luke 23:56, and John 18:28, John 19:37.

In the early morning hours, as Jesus’ trial was getting underway, Peter denied knowing his Master three times before the rooster crowed.

Good Friday is the most difficult day of Passion Week. Christ’s journey turned treacherous and acutely painful in these final hours leading to his death.

According to Scripture, Judas Iscariot, the disciple who had betrayed Jesus, was overcome with remorse and hanged himself early Friday morning.

Meanwhile, before the third hour (9 a.m.), Jesus endured the shame of false accusations, condemnation, mockery, beatings, and abandonment. After multiple unlawful trials, He was sentenced to death by crucifixion, one of the most horrible and disgraceful methods of capital punishment known at the time.

Before Christ was led away, soldiers spit on him, tormented and mocked him, and pierced him with a crown of thorns. Then Jesus carried His cross part of the way to Calvary and then a man named Simon was compelled to carry it the rest of the way. At Calvary, Jesus was again mocked and insulted as Roman soldiers nailed Him to the wooden cross.

Jesus spoke seven powerful statements from the cross, including “Father, forgive them, for they do not know what they are doing” (Luke 23:34, NIV), “Father, into your hands I commit my spirit” (Luke 23:46, NIV), and His last words were, “It is finished” (John 19:30).

Then, about the ninth hour (3 p.m.), Jesus breathed his last breath and died.

By 6 p.m. Friday evening, Nicodemus and Joseph of Arimathea took Jesus’ body down from the cross and lay it in a tomb.

______________

Posted in Ethiopia, Faith, Psychology, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

Good Friday Crucifixion | ዓርብ ስቅለት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 22, 2022

✞✞✞ ዓርብ ስቅለት (የድኅነት ቀን) –የዕዳ ደብዳቤያችን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ለመጨረሻ ጊዜ የተደመሰሰበት፤ ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ የወጣንበት ዕለት✞✞✞

ዓርብ ስቅለት የዕዳ ደብዳቤያችን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ለመጨረሻ ጊዜ የተደመሰሰበት፤ ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ የወጣንበት ዕለት ስለኾነ ‹የድኅነት ቀን› ይባላል፡፡ ጌታችን ከተያዘባት ሰዓት አንሥቶ አይሁድ ከቀያፋ ወደ ሐና፣ ከሐና ወደ ቀያፋ ሲያመላልሱት አደሩ፡፡ ሲነጋ ከቀያፋ ወደ ጲላጦስ አደባባይ አስረው ወሰዱት (ማቴ. ፳፯፥፩-፶፯)፡፡ አይሁድ ይህን አጥፍቶአል የሚሉት ነጥብ ሳይኖራቸው ነውና ጌታችንን ለፍርድ ያቀረቡት ጲላጦሰ እነርሱ ወደ ተሰባሰቡበት ቦታ ወጥቶ “ይህን ሰው ወደ እኔ ያመጣችሁበት በደል ምንድን ነው?” ሲል በጠየቃቸው ጊዜ በቂ ምላሽ አላቀረቡም፡፡

ዓርብ ስቅለት የዕዳ ደብዳቤያችን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ለመጨረሻ ጊዜ የተደመሰሰበት፤ ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ የወጣንበት ዕለት ስለኾነ ‹የድኅነት ቀን› ይባላል፡፡ ጌታችን ከተያዘባት ሰዓት አንሥቶ አይሁድ ከቀያፋ ወደ ሐና፣ ከሐና ወደ ቀያፋ ሲያመላልሱት አደሩ፡፡ ሲነጋ ከቀያፋ ወደ ጲላጦስ አደባባይ አስረው ወሰዱት (ማቴ. ፳፯፥፩-፶፯)፡፡ አይሁድ ይህን አጥፍቶአል የሚሉት ነጥብ ሳይኖራቸው ነውና ጌታችንን ለፍርድ ያቀረቡት ጲላጦሰ እነርሱ ወደ ተሰባሰቡበት ቦታ ወጥቶ “ይህን ሰው ወደ እኔ ያመጣችሁበት በደል ምንድን ነው?” ሲል በጠየቃቸው ጊዜ በቂ ምላሽ አላቀረቡም፡፡

“ክፉ የሠራ ባይኾንስ ወደ አንተ ባላመጣነውም ነበር” በሚል የሸፍጥ ቃል ሲያጕረመርሙ ጲላጦስ መልሶ “እኔ ምንም ጥፋት አላገኘሁበትም፤ እናንተወስዳችሁ እንደ ሕጋችሁ ፍረዱበት፤” አላቸው፡፡ አይሁድም ኦሪት “ኢትቅትል ብእሴ ጻድቀ ወኀጥአ ኢታኅዩ፤ ጻድቅን ሰው አትግደል፤ ኀጥኡንምከፍርድአታድን፤” ትላለችና “እኛስ ማንንም ልንገድል አልተፈቀደልንም፤” ብለዋል (ዮሐ. ፲፰፥፳፰-፴፩)፡፡ ይኸውም መንፈስ ቅዱስ “በሕጋችን ጻድቀ ባሕርይ ክርስቶስን መግደል አይገባንም ሙሉ በሙሉ ጥፋተኞችነን፤” ሲያሰኛቸው ነው፡፡ በኋላም እርሱ ሞቶ ዓለም ይድን ዘንድዳ ምድር መጥቷልና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያለ ጥፋቱ ሞት ተፈረደበት፡፡ ስለዚህም ገርፈው ሰቀሉት፡፡

ልክ አሁን የሕማማተ መስቀልን ፀሎት አንብቤ እንደጨረስኩ፤ ከጎረቤቴ ሕንጻ ጣራ ላይ ፲፫ ርግቦች ተነስተው በዙሪያዬ አንድ ጊዜና በአንድ ላይ ጅው ብለው በመብረር የተነሱበት ጣራ ላይ ተመልሰው አረፉ። ተገርሜ በመመሰጥ፤ “ምን የሚሉኝ ነገር ሊኖር ይችላል?” የሚለውን ጥያቄ ጠየቅኩ። ፲፫/13ቱ ሕማማተ መስቀል?

______________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ጸሎተ ሐሙስ | “ይህ ሥጋዬ ነው፤ ይህ ደሜ ነው” | ወገኔ ሆይ! የዳንኸውና ልጅነትን ያገኘኸው በክርስቶስ ሞትና ደም ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 20, 2022

❖❖❖ ጌታችን በጸሎተ ሐሙስ | ሌባን እንደምትይዙ በሰይፍና በጎመድ ልትይዙኝ መጣችሁን? ❖❖❖

ከኅፅበተ እግር በኋላ ሊይዙት ወደ እርሱ የመጡትን የካህናት አለቆችን፣ የቤተ መቅደስ ሹሞችንና ሽማግሌዎችን ጌታችን እንዲህ ብሏቸዋል፤ ሌባን እንደምትይዙ በሰይፍና በጎመድ ልትይዙኝ መጣችሁን? ዘወትር ከእናንተ ጋር በቤተ መቅደስ ስኖር እጃችሁን እንኳ አልዘረጋችሁብኝም፤ ነገር ግን ጊዜያችሁ ይህ ነው፡፡ የጨለማው አበጋዝም ሥልጣኑ ይህ ነው፤” (ሉቃ. ፳፪፥፶፪፶፫)

👉 የሰሙነ ሕማማት ሐሙስ ፮ ስያሜዎች

  • ፩. ሕጽበተ እግር ይባላል
  • ፪. የጸሎት ሐሙስ ይባላል
  • ፫. የምስጢር ቀንም ይባላል
  • ፬. የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል
  • ፭. የነጻነት ሐሙስ ይባላል
  • ፮. አረንጓዴው ሐሙስ ይባላል

______________

Posted in Ethiopia, Faith, Saints/ቅዱሳን, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

From Holy Thursday / The Last Supper to Easter Sunday | The Jesus Film

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 20, 2022

❖❖❖ Holy Week – Day 5: Passover and Last Supper on Maundy Thursday ❖❖❖

Holy Week takes a somber turn on Thursday.

From Bethany, Jesus sent Peter and John ahead to the Upper Room in Jerusalem to make the preparations for the Passover Feast. That evening after sunset, Jesus washed the feet of his disciples as they prepared to share in the Passover. By performing this humble act of service, Jesus demonstrated by example how believers should love one another. Today, many churches practice foot-washing ceremonies as a part of their Maundy Thursday services.

Then, Jesus shared the feast of Passover with his disciples, saying:

“I have been very eager to eat this Passover meal with you before my suffering begins. For I tell you now that I won’t eat this meal again until its meaning is fulfilled in the Kingdom of God.” (Luke 22:15-16, NLT)

As the Lamb of God, Jesus was about to fulfill the meaning of Passover by giving his body to be broken and his blood to be shed in sacrifice, freeing us from sin and death. During this Last Supper, Jesus established the Lord’s Supper, or Communion, instructing his followers to continually remember his sacrifice by sharing in the elements of bread and wine (Luke 22:19-20).

Later, Jesus and the disciples left the Upper Room and went to the Garden of Gethsemane, where Jesus prayed in agony to God the Father. Luke’s Gospel says that “his sweat became like great drops of blood falling down to the ground” (Luke 22:44, ESV).

Late that evening in Gethsemane, Jesus was betrayed with a kiss by Judas Iscariot and arrested by the Sanhedrin. He was taken to the home of Caiaphas, the High Priest, where the whole council had gathered to begin making their case against Jesus.

Meanwhile, in the early morning hours, as Jesus’ trial was getting underway, Peter denied knowing his Master three times before the rooster crowed.

Thursday’s events are recorded in Matthew 26:17–75, Mark 14:12-72, Luke 22:7-62, and John 13:1-38.

______________

Posted in Ethiopia, Faith, Saints/ቅዱሳን, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የናዝሬትን ሕፃናት ለምን ሄዳችሁ ብለው ገደሏቸው ፥ እስክንድርን ለምን ሄድክ ብለው አሠሩት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 25, 2020

ወደ ቤተ ክርስቲያን አትሂዱ! ለእኛ ተውልን! እናፍርሳት ፥ ድኾችን አትጎብኙ! እኛን አትረብሹን! እናፈናቅላቸው!

ነጥብጣቦቹን እናገገናኛቸው… “አትሂዱ ብያችሁ አልነበረም! የኔን ትዕዛዝ መፈጸም ነበረባችሁ ፤ በጣም አስቆጥታችሁኛል” አለ ወሮበላው ፈርዖን። የጌታችን ትንሣኤ በጣም ረብሾታል፣ ለፍርድ የሚመጣው የይሑዳው አንበሣም በጣም አስበርግጎታል ፥ በሳምንት ውስጥ ስንት ጉድ አሳየን! አገራችን በታሪኳ አይታ የማታውቀውን አረመኔያዊ የሆነ ሥራቸውን እስከ መቼ ድረስ ይቀጥሉበት ይሆን?

____________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የግራኝ ጂሃድ በኮልፌ ቀራንዮ | “በገዛ ሀገራችን መሄጃ አጣን! የ፲፭ ቀን አራስ ሆኜ ቤቴን እላዬ ላይ አፈረሱብኝ”

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 23, 2020

ኮረመዳን ቫይረስ” ሲጀምር እንዲህ ነው፤ ጊዜውን ጠብቀው ጂሃዳዊ ገጽታቸውን እያሳዩን ነው ፤ በትንሣኤ ሕፃናት የተዋሕዶ ልጆችን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ መርዘው ገደሏቸው፤ አሁን ደግሞ ጌታችን በቀራንዮ የተሰቀለብትን ዕለት ባሰብን በሳምንቱ የድኸ ክርስቲያኖችን ቤት ጨለማን ተገን አድርገው በሌሊት ያፈርሳሉ።

ኢትዮጵያ ሃገሬ፡ ቆላማዎቹ ሃጋራውያን ስጋዊ ፍጥረታት ፈነጩብሽ፣ አላገጡብሽ፣ አረከሱሽ፤ ፈጣሪሽ እሳቱን ያውረድባቸው! ዘር ማንዘራቸው ከምድርሽ በእሳት ይጠራርጋቸው!

+++ምድረ ቀራንዮ+++

  • ምድረ ቀራንዮ ምድረ ጎልጎታ
  • መድኃኒት ክርስቶስ በአንቺ ተንገላታ
  • የዓለም መድኃኒት በአንቺ ተንገላታ።
  • መስክሪ አንቺ ምድር ግዑዚቷ ስፍራ
  • መድኃኒት ክርስቶስ ያየብሽ መከራ
  • ደሙ እንደ ውኃ ሲፈስ በመስቀሉ ላይ
  • ፀሐይ ከለከለች ለመስጠት ብርሃን
  • ለመሸፈን ብላ የአምላኳን ዕርቃን
  • ሁሉን ማድረግ ሲችል ሥልጣን ሲኖረው
  • በመስቀል ተሰቅሎ ፍቅሩን ገለጸው
  • በመስቀል ላይ ሆኖ ተጠማሁ እያለ
  • የእሾህ አክሊል ደፍቶ ቀራንዮ ዋለ
  • እጆቹና እግሮቹ በችንካር ተመትተው
  • ይቅርታ አደረገ ለዚህ ኃጢአታቸ
  • መከራን ሲቀበል በዚያች ምድር ላይ
  • ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን!

___________________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: