Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

 • September 2022
  M T W T F S S
   1234
  567891011
  12131415161718
  19202122232425
  2627282930  
 • Archives

 • Categories

 • Recent Posts

Posts Tagged ‘ታከለ ኡማ’

ጂሃድ በ አዲስ | የግራኝ አህመድ ሠራዊት ተዋሕዶ ምዕመናንን ገደለ ቤተ ክርስቲያን አፈረሰ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 5, 2020

በአብዮት አህመድና ታከለ ኡማ ትዕዛዝ በጥቂቱ ሁለት የተዋሕዶ ልጆች በጥይት ተገድለዋል።

______________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የሰይፉ ቤት ተቃጠለ ሲባል ጥቁሩ ደመና ላይ የታዩኝ አብዮትና ታከለ ናቸው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 18, 2019

ሰይፉ ፋንታሁን በተማሪዎች መመረዝና በግዮን ሆቴል አዳራሽ መፍረስ ላይ መረጃ ለማቅረብ ሲሞክር ስሰማው፤ “እንዴ ምናልባት ሰውየው እየነቃ ይሆን? ወንጀለኞቹ የአዲስ አበባ ሜዲያዎች እንደሆኑ ለነዋሪው የእንቅልፍ ኪኒን ከመስጠት ሌላ ይህን ስለመሰለ ጉዳይ በጭራሽ አይዘግቡም” የሚል ስሜት ተሰምቶኝ ነበር።

የሰዶምና ገሞራ ውላጆች የዲያብሎስ የግብር ልጆች የሆኑት እነ ግራኝ አብዮትና ታከለ ኡማ ለብዙ ጭካኔ ለተሞላባቸው ድርጊቶች የተዘጋጁና ብቁ መሆናቸውን ተዓምረኛው ዘመነ ዮሐንስ እያሳየን ነው። የኢትዮጵያን ስም አዘውትረው በሚያነሱት አሐዱ 94.3 ኤፍ ኤም በተሰኘዉ ራዲዮ ጣቢያ ላይ ጠላተ ኢትዮጵያ የዋቄዮአላህ አርበኞች እያካሄዱ ያሉትን ጂሃድ እንመዝግበው።

የኢትዮጵያን ንብረት ለጠላቶቿ በማስረከብ ላይ ያሉት እነዚህ ወረበሎች እያንዳንዷን የአሠርቱ ቃላት ትዕዛዝን የጣሱ ከሃዲዎች፣ አታላዮች፣ ቀጣፊዎች፣ ሌቦችና ገዳዮች ናቸው። ስለዚህ ሰይፉን ከእነቤተሰቡ ለማቃጠል ቢሞክሩ የሚገርም ነገር አይደለም። እነ ኢንጂነር ስመኘውን በጠራራ ፀሐይ የገደለ ወንጀለኛ ይህን የመሰለ ጽንፈኛ ተግባር አንድም ሌሊት ሳይፈጽም ካደረ ዕረፍት የለውምና። እኅተ ማርያም “አብዮት አህመድ ቀን ሰው ሌሊት አውሬ ነው” ማለቷ ይህን ጽንፈኛ ተግባሩን ይጠቁመናል።

ሌባው ሰርቆ ከመሸሹ በፊት ቶሎ መያዝና ለፍርድ መቅረብ አለበት!

[የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ ፲፥፲]

ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም

________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የሞት ፍሬ በ ፍሬህይወት | ወገን፡ እነ ታከለ ልጆቻችሁን እየመረዙባችሁ ነው!!!

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 27, 2019

በአዲስ አበባ ልደታ ማርያም አቅራቢያ በሚገኘው ፍሬህይወት ቁጥር አንድ ትምህርት ቤት ዛሬ ኅዳር ፲፯ /፲፪ . በዕለተ ቅዱስ እስጢፋኖስ፡ ጠዋት ላይ ፳፭ ተማሪዎች እና መምህራን ላይ በተፈጠረው የጤና ዕክል ምክንያት ወደ ጥቁር አንበሳ እና ዘውዲቱ ሆስፒታሎች ተወስደዋል።

በኢትዮጵያውያን ሕፃናት ላይ የመርዝ ጂሃድ እንደሚካሄድ በተለይ ላለፉት ሰባት ዓመታት ሳስጠነቅቅ ነበር። “ልጆቻችሁ ከማን ጋር እንደሚበሉ ተከታተሉ፣ የልጆቻችሁን የምሳ እቃ ተቆጣጠሩ” እያልኩ፡ በመንገድ ላይ ሳይቀር እንደ እብድስለፈልፍ ነበር። ያየሁትን አይቻለሁና። ከአምስት ዓመታት በፊት ሊደበድቡኝ ሁላ የመጡ መንጋዎች ነበሩ። በቅርቡ እንኳን የታከለ ኡማ “ነፃ ምግብ” ፕሮግራም አደገኛ ሊሆን እንደሚችል ለመጠቆም ሞክሬ ነበር። ወገን፡ እነዚህ የዲያብሎስ የግብር ልጆች ባገኙት አጋጣሚ ከሁሉም አቅጣጫ ነው እያጠቁን ያሉት!

ከሁለት ዓመታት በፊት በቅዱስ ሩፋኤል ቤተክርስቲያን ያገኘኋቸው አንዲት እናት ታከለ ኡማ ከመጣበት በአምቦ ከተማ የተዋሕዶ ህፃናት እየተመረዙ እንደሆነ ጠቁመውኝ እንደነበር አስታውሳለሁ። በጣም ያሳዝናል፤ ሕዝባችን ለምን፣ በምን እና እንዴት እንደታመመ ውጭ ያለን ወገኖቹ ካላሳውቅነው በቀላሉ አያውቀውም፤ በመተት አስረውታል።

ለተጎዱት እግዚአብሔር ይድረስላቸው!

__________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , | 2 Comments »

አብዮት እና ታከለ ይሆኑ አቡነ መልከጼዴቅን በቅዱስ ሚካኤል ዕለት ከአዲስ አበባ ያባረሯቸው? ወንበሩን የኢሬቻ ዘመዳቸው ጠቅልለው ይይዙት ዘንድ?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 22, 2019

በዚህ ድንቅ ስብከታቸው(ሙሉውን በሌላ ጊዜ አቀርበዋለሁ) ምክኒያት ይሆን አቡነ መልከጼዴቅ የተባረሩት? ወይስ ሌላ ነገር አለ?

ከመፈንቅለ መንግስቱ ቀጥሎ አሁን መፈንቅለ ወንበር በቤተክርስቲያናችን ውስጥ እየተካሄደ ይሆን?

መጀመሪያ ላይ፤ ከአብዮት አህመድ ትውልድ ከተማ ከጂማ እና ከታከለ ገማ ትውልድ ከተማ ከ አንቦ ተባርረው ወደ አዲስ አበባ የመጡትንና በአዱሱ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ተጠልለው የነበሩትን የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ቤተከርስቲያኑን ለቀቅው እንዲወጡ ተደረጉ፤ ከዚያ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የፓትርያርኩ ረዳት የሆኑት ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ ከወንበራቸው እንዲነሱ ተደረጉ፤ ያውም በቅዱስ ሚካኤል ዕለት! ተማሪዎቹ የአዲሱ ሚካኤል ቤተክርስቲያንን ግቢ እንዲለቅቁ በከፍተኛ ባለስልጣን ትዕዛዙ እንደተሰጠ ተወርቶ ነበር። አሁን የፕሮፓጋንዳና ቅጥፈት አርቲስቶቹ አብዮት አህመድና ታከል ገማ፤ አቡነ መልኬ ጻዲቅ ናቸው ይህን ትዕዛዝ ሰጥተው የነበሩት፣ ከአዲስ አበባ መባረራቸውም ተገቢ ነውየሚል ተልካሻ ቅስቀሳ እንዲካሄድ እያደረጉ ነው።ውሻውን መጥፎ ስም ሰጥተህ ስቀለው / ‘Give the dog a bad name and hang him ይሉ የለ።

ቀደም ሲል አቡነ መልከጼዴቅ ለታከለ ገማ ገንዘብ ለመስጠት ፈቃደኛ ነበሩእየተባለ ሲነገር ነበር። በእውነት ይህን ለማድረግ ከወሰኑ ምክኒያታቸው ምን ይሆን? አብዮትና ታከለ ወንበራቸውን በመነቅነቅ ላይ እንደሆኑ ስላወቁ ይሆን? ወይስ ሌላ ነገር አለ? ለማንኛውም በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ ተደረገው የተሾሙት የአብዮት አህመድና የታገለ ገማ ኦሮሞ ወንድም መ/ር አባ ሞገስ ኃይለማርያም ናቸው። *(ሌላ ኃይለማርያም?!)

በሁሉም ቦታ መፈንቅለ ወንበር፣ መፈንቅለ ሥርዓት እየተካሄደ ነው። ከዓመታት በፊት በአዲስ አበባ አብያተ ክርስቲያናት ላይ የዋቄዮአላህን የጥፋት ዘመቻ ለመጀመር አሁን ለመስለም በመዘጋጀት ላይ የሚገኘውን ኢሬቻ በላይን የሃገረ ስብከቷ ስራ አስኪያጅ ማድረጋቸው የሚታወስ ነው። ዛሬም ዓይናችን እያየ ታሪክ ራሱን እየደገመ ይሆን? *(ሌላ ኢሬቻ በላይ?! )

በአብዮትና በታከለ እንዲሁም በአራት ኪሎ የጂሃድ ዋሻቸው ላይ ቅዱስ ሚካኤል እሳቱን ያውርድባቸው!

________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ችግኝ ተከላ፥ ታከለ ኡማ | ችግኙ የዋቄዮ-አላህ ማምለኪያ ዐፀድ መሆኑ ነውን?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 21, 2019

[ዘዳ ፲፮፡፳፩]

ከማናቸውም ዛፍ የማምለኪያ ዐፀድ አድርገህ አትትከል።

እኛ የኢየሱስ ክርስቶስ ልጆች ክቡር ሥጋውንና ቅዱስ ደሙን ተቀብለን ምድራዊና ሰማያዊ ክብር እያገኘን ስንኖር ፥ የዋቄዮ አላህ ልጆች ደግሞ በፈቃዳቸው ከእግዚአብሔርና ለእግዚአብሔር ያልሆነውን ችግኝ በመትከል ላይ ናቸው።

የማታለያ ድራማውን ዓይናችን እያየ በድፍረት ቀጥለውበታል። ይህን የችግኝ ተከላ እርኩስ መንፈሱ ሳይመራቸው ሆን ብለው በረመዳን ጊዜ ያለምክኒያት አልጀመሩትም። ዛፍ፡ የእግዚአብሔር ዛፍ፣ የሕይወት ዛፍ እስከሆነ ድረስ ጥሩ ነገር ነው፤ ነገር ግን ይህ ችግኝ ተከላ ለበጎ ነገር አይመስልም፤ የእግዚአብሔርን ልጆች እያፈናቀሉ ለዋቄዮ አላህ ዛፍ ይተክላሉ። ባንዲራቸው ላይ “ኦዳ” የተባለውን ዛፍ ማሳረፋቸውም አምላካቸው ማን እንደሆነ እየጠቆሙን ነው። ከሃዲዎች!

ወገን፤ ለልጆችህ ስትል ተነሳ! በጉ ከፍየሎች የሚለይበት ዘመን ላይ ደርሰናል፣ ጦርነት ላይ ነን፤ ሰላም ሳይኖር፤ ሰላም ሰላም አትበል!

እግዚአብሔር የሚጸየፈው ይህ የዛፍ አምልኮ በክርስቶስ ኢየሱስ ስም ከኢትዮጵያ ይነቀል፡ አሜን!!!

__________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: