Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘ቱርክ ቴሌቪዥን’

የፀረ-ክርስቶሷ ቱርክ TV አየር መንገዳችንን ሲያጣጥል፥ እንግሊዛውያኑ፤ “ከዓለም ምርጥ ከሆኑት አንዱ ነው” በማለት ተከላከሉት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 12, 2019

ባለፈው ዓመት ላይ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሠራተኛ “ኢትዮጵያና ቱርክ ጦርነት ይጀምራሉ” ማለቱ ትክክል ነው፤ ጀግና ብዬው ነበር። የክርስቶስ ተቃዋሚዋ ቱርክ የአገራችን ቀንደኛ የታሪክ ጠላት ናት፤ት ጫማ ሥር ቅዱስ መስቀሉን እያሳረፈች ወደ አገራችን ከምትልከው፣ ስኳሩን፣ ዱቄቱን፣ ዘይቱንና እንስሳቱን ከምትመርዝብን ከቱርክ ጋር የኢትዮጵያ መንገስት የሚያደረገው ጥብቅ መቀራረብ መወገዝ አለበት። የኢትዮጵያ አየር መንገድን በማጣጣል መንገደኞች ርካሹን የቱርክ አየር መንገድ ብቻ እንዲጠቀሙ ለማድረግ ነው፤ የቱርክ አየር መንገድ በየቀኑ ወደ አዲስ አበባ ይበራል።

ባለፈው ሣምንት ላይ፤ በአምስተርዳም የኢግዚቢሽን ማዕከል አንድ ቱርካዊ ወደ እኔ መጣና፤ “ከየት ነህ?“ አለኝ፤ “ከኢትዮጵያ” አልኩት። “ወደ ኢትዮጵያ መጓዝ እፈልግ ነበር፤ የማተሚያ መሳሪዎችን ለሚያመርት ድርጅት ነው የምሠራው፤ ሕዝቡ እንዴት ነው? ከእኛ ጋር መግባባት ይችላልን?“ አለኝ። እኔም፡ “አዎ! የኢትዮጵያ ሕዝብ እንግዳ ተቀባይ ነው፤ ለመስተንግዶ ማንንም አይለይም” አልኩት። ቀጠል አደረገና፡ “ሃይማኖታችሁስ ምንድን ነው?” አለ፤ እኔም “ኢትዮጵያ ውስጥ ሁሉም ሃይማኖት አለ፤ ክርስቲያኑ ይበዛል፤ ግን አይሁዱም፣ ሙስሊሙም፣ ኢአማኒውም…“ ስለው ፊቱ ተቀያየረና ዝምታ ውስጥ ገባ። እኔም በደንብ ስለማውቃቸው በልቤ ስቄ፤ “መልካሙን እመኝልሃለሁ ብዬ ቶሎ ተሰናበትኩት። የመጀመሪያው ወይም ሁለተኛው ጥያቂያቸው ሁሌ ሃይማኖትን የተመለከተ ነው፤ የሁሉም መሀመዳውያን!

_________

Posted in Conspiracies, Curiosity, Ethiopia | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: