+አንድ ማሳሰቢያ!+
የአውሬውን የ”Copyright” ጨዋታ መብት በመጠቀም ይህን ቻነል ለማዘጋት እየሠሩ ያሉ “ተዋሕዶ ነን” የሚሉ ዩቱበሮች፦
👉 ቻነል ፩፦ “Lule Quanquayenesh (ሉሌ ቋንቋዬ ነሽ)”
👉 Content removed by Lule Quanquayenesh (ሉሌ ቋንቋዬ ነሽ)
👉 ቪዲዮዎች፦
+ “ኢትዮጵያ ማለት ቤተክርስቲያን ናት ፤ እየታረዱላት ያሉትም የተዋሕዶ ልጆች ናቸው”
+ “የሰይጣን ምልክት 666 ነው ፥ የክርስቶስ የሆኑት ደግሞ ባንገታቸው ላይ ያለው ማሕተብ ነው”
👉 ቻነል ፪፦ Semayat/ ሰማያት
👉 ቪዲዮ፦ + “በዶክተሮች ሊፈታ የማይችለው ወረርሽኝ በጻድቁ ማእጠንት ይታጠናል | የማእጠንት ፀሎት በአሜሪካ”
Content removed by Semayat የደብረ ከርቤ ቅድስት ማርያም ወአቡነ ሀብተማርያም የማእጠንት ፀሎት በተወሰኑ የቨርጂንያ መንደሮችና
እንግዲህ እነዚህ ዩቱበሮች አውሬው ተነካባቸው መሰለን በምናቀርበው ነገር የተደሰቱ ሆነው አላገኘናቸውም። መልስ እንዲሰጡን ጊዜ ሰጥተናቸው ነበር።
ማንም የሜዲያ ሰው ነኝ ማለት በሚችልበትና መላው የሰው ልጅ በወረርሽኝ ጉዳይ በተጠመደበትና በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ወገን መቀራረብና መፈቃቀር በሚኖርበት በዚህ የጭንቀት ዘመን ነጋዴ እንጅ አንድ “ክርስቲያን ነኝ” የሚል አካል በጭራሽ “Copyright“ የተባለውን ዝባዝንኬ እንደ መሀመዳውያኑ መጠቀም የለበትም። በተለይ በፋሲካ ሰሞን፤ ያውም “ሰለጠነች” በምትባለዋ አሜሪካ እየኖሩ። የኛን ቪዲዮዎች ማንም መጠቀም ይችላል፤ እንዳውም ደስ ይለናል!
ልብ ብላችሁ ከሆነ እንደ ውቂያኖስ ሰፊ በሆነ የዩቱብ ቪዲዮዎች ዓለም “Copyright“ን በብዛት የሚጠቀሙት “ኢትዮጵያዊ ነን” የሚሉ ዩቱበሮች ናቸው። ታዲያ ይህ የስግብግብነት፣ የምቀኝነት፣ የክፋትና የጠላትነት መገለጫ አይደለምን? በ21ኛው ክፍለ ዘመን ፤ ምናልባትም ኢንተርኔት የሚባል ነገር በቅርቡ እልም ብሎ ሊጠፋ በተዘጋጀበት ወቅት በራስህ ወገን ላይ ይህን መሰል እቃ እቃ ጨዋታ መጫወቱ አያሳዝንምን? ሰው እንዲማርበት ነው፤ ““ኮፒራይት” ከ666ቱ ምልክቶች አንዱ ነው፤ የአውሬው ባሪያ ከመሆን ለመዳን ከዩቱብና ጓደኞቹ ገንዘብ አትቀበሉ” ለማለት ነው።
ይህ ቀላል ነገር ነው፤ ዋናው እና ትልቁ ተል ዕኳችን አውሬውን መታገል ነው፤ ሕዝባችንን የሚያሰቃይብንን፣ ሕፃናቱን የሚገድልብንን፣ ካህናትን የሚያስርና የሚገድልብንን፣ እናቶችን የሚያፈናቅልብንን የአውሬ ሥርዓት ማጋለጥ ነው፤ የተሰውትን ሰማዕታት ወገኖቻችንን ማስታወስ ነው።
ለማንኛውም ሌላው ቻነላችን እዚህ ይገኛል፦
+++ዘመነ ኢትዮጵያ+++
ከምስጋና ጋር