ይህ ሥራ በጣም በጎ ነገር ነው፤ እንዲያውም አዲስ አበባ ዙሪያዋን በመስቀል ብትከበብ ነዋሪዎቿ ከብዙ መዓት ይድናሉ፤ በአቡነ ኃብተማርያም ገዳምም መሠራት ይኖርበታል።
ነገር ግን ዛሬ በአላጋጮችና ድራማ ሠሪዎች ተከብበናልና “ይህ ዜና በአዲስ ዓመት መግቢያ ላይ እንዲሁም በደመራና መስቀል ወቅት ከመውጣቱ ጀርባ ማን/ ምን ይኖር ይሆን?” የሚለውን ጥያቄ ከመጠየቅ መቆጠብ የለብንም። መቼስ ማጭበርበርና ማታለል ሙያው አድርጎ የያዘው የአውሬው አገዛዝ ቤተ ክርስቲያንን ለመፈታተን እና ለመተናኮል የማይቆፍረው ጉድጓድ የለምና።
ምናልባት፦
👉 የቆፋፈረውን የመስቀል አደባባይ ጉዳይ ለማረሳሳትና ህዝበ ክርስቲያኑን ለመደለል ይሆን?
👉 በጣም ሚስጢራዊ የሆነውን እና መስቀል አደባባይ እና ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን የሚገኙበትን አካባቢ ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር አቅዶ ይሆን?
👉 የመስቀል አደባባይን “አንድነት ወይንም ኢሬቻ አደባባይ” ብሎ ለመሰየም ዕቅድ ስላለው ይሆን?
👉 ከ “ሸገር ፕሮጀክት፣ እንጦጦ ፓርክ ቅብርጥሴ” ጋርስ የሚያገናኘው ምን ነገር ይኖራል?
ለማንኛውም በሚቀጥሉት ቀናት የምናየው ይሆናል። የአውሬው አገዛዝ ካድሬዎችና ወኪሎች ተዋሕዷውያንን አወናብዶ ወደካምፑ ለማምጣት የተለያዩ ቅስቀሳዎችን ሲያደርጉ የምንሰማበት አጋጣሚ ይኖራል።
________________________