Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

 • June 2023
  M T W T F S S
   1234
  567891011
  12131415161718
  19202122232425
  2627282930  
 • Archives

 • Categories

 • Recent Posts

Posts Tagged ‘ተላላፊ በሽታዎችNGOs’

ቢጫ ወባ ብዙ ኢትዮጵያውያንን ገደለ | የእኅተ ማርያም ማስጠንቀቂያ ይህ ይሆን?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 7, 2018

አዎ! ብዙ የተጠነሰሰልን ነገር አለ! ይህ መጀመሪያው ነው፤ እነርሱ “ቢጫ ወባ ነው” ይሉታል።

እኅተ ማርያም ያቀረባቸው ሦስት ምልክቶች፦

 • + ዓይናችሁ ደም ይመስላል

 • + ጥፍራችሁ ወደ ቢጫነት ይቀየራል

 • + እንደ ሳሙና አረፋ ነገር ያስቀምጣችኋል

የዓለም የጤና ድርጅት መግለጫ፡ በሽታዉ በወላይታ አስቀድሞ በመነሳቱ ወደ መላው ኢትዮጵያ እንዳይዛመት ለመከላከል ነዉ ክትባቱን የመስጠቱ ዘመቻ የተጀመረዉ፤ ይለናል። በ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የሚመራው ይህ የዓለም የጤና ድርጅት መንግሥታዊ ካልሆኑ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ጋር በመተባበር የቢጫ ወባ ክትባት ዘመቻ በኢትዮጵያ ለማካሄድ ተዘጋጅቷል።  “የኢትዮጵያ ሕፃናት መከተብ አለባቸው፡ ይለናል ድርጅቱ።

አሁን 1.5 ሚሊየን የሚሆኑ የክትባት መርፌዎች ወደ ኢትዮጵያ ተልከዋል።

የአሜሪካው መከላከያ ሚንስትር፡ ፔንታጎን “አይፈለጉም” የሚላቸውን ሕዝቦች ለመዋጋት መርዛማ ትንኞችን ከላብራቶሪ ቀምሞ በማውጣት ላይ በሚገኝበት በእዚህ ዘመን፡ ክትባቱ የቢጫ ወባን ብቻ ለመከላከል የተዘጋጀ እንደማይሆን አሁን የታወቀ ነው።

ችግርምላሽ መፍትሔ / “Problem – Reaction – Solution” ብሎታል፡ ተንኮለኛው ፈላስፋ ጆርጅ ሄገል።

ደጋግሜ የምናገረው ነው፤ ዶ/ር አድሃኖምን የመረጡት ያለ ምክኒያት አይደለም። /ር ቴዎድሮስ አድሃኖምን የአለም ጤና ድርጅት ሃላፊ አርገው መሾማቸው በተለይ በኢትዮጵያውያን ላይ ያዘጋጁት ተንኮል ስላለ ነው።

ልክ ኡጋንዳዊቷን ወ/ሮ ዊኒ ቢያኒያምን የ “ኦክስፋም” መሪ (የዊኒ ማንዴላን ስም ይዛለች) አድርገው እንደሾሟት፤ ሊቀ ጳጳሳት ዴስሞንድ ቱቱን የዚሁ ድርጅት ልዩ አምባሳደር አድርገው እንደመረጧቸው፣ ወይም ኮፊ አናንን የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ እንደመረጧቸው፤ ዶ/ቴዎድሮስ አድሃኖምን የአለም ጤና ድርጅት ሃላፊ አድርገው መሾማቸው ያለምክኒያት እንደማይሆን መጠራጠር ግድ ነው።

______

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

በጥቁር ሕዝቦች ላይ ያነጣጠረው ‘ኢቦላ’ እንደገና አገርሽቷል | ዶ/ር ቴዎድሮስን ያለምክኒያት መርጠዋቸዋልን?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 18, 2018

ይህ መታየት ያለበት ቪዲዮ የሚያሳየን አረመኔዎቹ የምዕራቡ ዓለም “ሊቃውንት” እና ባለ ሃብቶች፡ አፍሪቃውያኑን እርስ በርስ በጦርነት ከማባላት አልፈው የአፍሪቃን ሕዝብ ቁጥር ለመቀነስ ኢቦላን፣ ኤች አይ ቪንና የመሳሰሉትን ቫይረሶች ላብራቶሪ ውስጥ ቀምመው እንዳሰራጯቸው ነው።

በዚህ ሳምንት ላይ ኢትዮጵያ ከፍተኛ የኢቦላ ቫይረስ ማስጠንቀቂያ ሰጥታለች።

ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የኢቦላ ቫይረስ እንደገና አገርሸቷል። ነገር ግን በሽታው መቼ እና እንዴት በድጋሚ ሊከሰት እንደቻለ የሚታወቅ ነገር የለም፤ ሁሉም ነገር “ድብቅ” ነው

የተጋረጠውን አደጋ እንዴት መከላከል ይቻል ይሆን?

በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሰሜን ምዕራብ አካባቢ የምትገኘው ቢኮሮ ከተማ የታየው የቫይረሱ ማገርሸት ከዚህ ቀድሞ የተከሰተውንና በምዕራብ አፍሪካ አስራ አንድ ሺህ ሰዎች ህይወት መቀጠፍን እንዲሁም ሃያ ስምንት ሺህ ሰዎች በቫይረሱ የተያዙበትን አስደንጋጭና አስፈሪ ጊዜ ያስታውሰናል።

ትናንትና ሚሊየን ሰው በሚኖርባት የኮንጎ ከተማ ቫይረሱ መዛመቱ ተወስቷል።

ልክ በዚህ ሰሞን ከዓመት በፊት /ር ቴዎድሮስ አድሃኖምን የአለም ጤና ድርጅት ሃላፊ አርገው መሾማቸው በአፍሪቃውያን ላይ ያዘጋጁት ተንኮል ስላለ ነው። ለምሳሌ፡ የ ዶ/ር ዴዎድሮስን መመረጥ ቶሎ ብለው ካወደሱት ቡድኖች መካከል ለህጋዊ ፅንስ የማስወረድ መብት ጠበቃ የቆሙ ድርጅቶች ይገኙበታል።

ይህን መረጃ እንመልከት፦

በሌላ በኩል፡ አውሮፕላኖች እንደ ኢቦላ የመሳሰሉ ቫይረሶችን በፈጠነ መልክ ለማሰራጨት አስተዋጽኦ ያበረክታሉ የሚለውን መረጃ ሳነብ፡ የታየኝ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ነው። ሁሌ የምጠይቀው፡ ከጥንት ጀምሮ፣ በማንኛውም የኢትዮጵያ መንግስታዊ መስተዳደር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያለምንም ተንኮልና መሰናክል እንዲያድግና እንዲስፋፋ መደረጉ ከምን የመጣ ይሆን? የሚለው ጥያቄ ነው።

ይህን መረጃ እንመልከት፦

______

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Health | Tagged: , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: