Posts Tagged ‘ተላላፊ በሽታዎች’
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 24, 2020
VIDEO
የሉሲፈራውያኑ ሤራ፦
በትናንትናው ዕለት የዓለም ቍጥር ፩ ቴኒስ ተጫዋቹ ሰርቢያዊ ኮከብ “ኖቫክ ጆኮቪች” / Novak Djokovic “ በኮሮና ተይዟል” ተባለ። ኖቫክ ጆኮቪች አጥባቂ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን እና ፀረ– ክትባት አቋም ያለው ግለሰብ ነው። ፀረ – ክትባት / Anti-Vaxxer = No Vaccine.
👉 አሁን ወደ ስሙ ስንሄድ፦ Novak = No Vax – Djokovic = Djo Covid – NoVax Djokovid ( ኖ ቫክስ ጆኮቪድ )
ዋውው !
በድጋሚ የቀረበ
[ የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፳፬፥፯፡፰ ]
“ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና፥ ራብም ቸነፈርም የምድርም መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል፤ እነዚህም ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው ።”
ዶ / ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ገና እንደተመረጡ ዶ / ር ቴዎድሮስ አድሃኖምን የአለም ጤና ድርጅት ሃላፊ አርገው መሾማቸው በተለይ በኢትዮጵያውያን ላይ ያዘጋጁት ተንኮል ስላለ ነው።” ማለቴ ያለምክኒያት አይደለም።
ዲያብሎስ እላይ ከፍ አድርጎ ያወጣህና አሽቀንጥሮ ወደ ታች ይወረውርሃል። ታዋቂ፣ ዝነኛ፣ ሃብታም፣ ተሸላሚ ያደርግህና ጊዜህ ሲደርስ የለመደውን የደም ግብሩን “አምጣ !” ብሎ ይደፋሃል።
፳፬ / 24 ቁጥር ያረፈበትን ማልያ ለብሶ ሲጫወት የነበረው ዝነኛው ጥቁር አሜሪካዊ የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ኮቤ ብራያንት እና ሴት ልጁ ከወር በፊት ልክ በዚህ ዕለት በፈረንጆቹ 01/26/2020 ዓ . ም በሄሊኮፕተር አደጋ ተከስክሰው ለሉሲፈር ኢሉሚናቲዎች ተሰውተዋል።
አሁንማ የሚደብቁት ነገር የለም፤ ሃሳባቸውንና ዕቅዳቸውን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መልክ፣ ወደውም ሆነ ሳይወዱም፣ አውቀውም ሆነ ሳያውቁም ሁሉንም ነገር በቅደም ተከተሉ እያሳዩን ነው።
+++ “ ትንቢት ? ”+++
👉 ከአራት ዓመታት በፊት፡ እ . አ . አ በ 2016 ዓ . ም ላይ ኮቤ ብራያንት በሄሊኮፕተር ሲከሰከስ የሚያሳይ የካርቱን ፊልም “ኮሜዲ ሲንትራል” በተሰኘው የቴሌቪዥን ጣቢያ እንዲተላለፍ ተደረገ።
👉 እ . አ . አ . ጃንዋሪ 25 / 2020 ላይ ኮቤ ተከስክሶ ሊሞት አንድ ቀን ሲቀረው ሌቦርን ጀምስ የተሰኘው የሎስ ኤንገልስ ሌከርስ የቅርጫት ኳስ ኮከብ የኮቤ ብራያንትን የቅርጫት ኳስ ሬከርድ ሰበረው።
👉 በበነገታው እ . አ . አ ጃንዋሪ 26 / 2020 ዓ . ም ላይ ዝነኛው የቅርጫት ኳስ ተጨዋች ኮቤ ብርያንት፣ ሴት ልጁና ሌሎች ስምንት ሰዎችን ጨምሮ በካሊፎርኒያ ሄሊኮፕተር አደጋ ህይወታቸው አለፈ።
👉 ኮቤና ልጁ በሞቱበት በዚሁ ዕለት ቻይና በተቀሰቀሰው ኮሮና ቫይረስ 41 ሰዎች መሞታችውና 1300 ሰዎች መታመማቸው ታወቀ። በዚሁ ዕለት ኮቤ 41 ዓመቱ ልጁም የ 13 ዓመት ልጃገረድ ነበሩ።
👉 በቺካጎ ከተማ በተካሄደውና ለኮቤ መታሰቢያ እንዲሆን የተደረገው የሁሉም – ኮከብ የቅርጫት ኳስ ጨዋታ ላይ ድጋፍ ሰጭ / ስፖንሰር የነበረው ኩባንያ የሜክሲኮው ቢራ አምራች “ኮሮና / Corona ነበር”
👉 በዚሁ ሰሞን የኮሮና ቢራ ምናልባት ከቫይረሱ ጋር ይገናኝ ይሆናል በሚል ፍራቻ ብዙ ሰዎች ጉግል ላይ “የኮሮና ቢራ ቫይረስ ” የሚለውን ቃል ይፈልጋሉ።
👉 ኮቤ ብራያንት እና ልጁ C ORONA del mar / ኮሮና ዴል ማር በሚባለው የካሊፎርኒያ መንደር ተቀበሩ።
👉 ኮቪድ / Covid በዕብራይስጥ ቁንቋ ኮቤ /KOBE ይባላል
Covid = Corona Virus / ኰሮና ቫይረስ
በጉግል አስተርጓሚ Covid ን ወደ ዕብራይስጥ ተርጉሙትና ወደ እንግሊዝኛው መልሱት።
👉 ሌላው፦ ኮቤ ብራያንት ሊከሰከስ አስር ቀን ሲቀረው በ ኮቤ ( ጃፓን ) በ እ . አ . አ በጃንውሪ 16/17 /1995 ዓ . ም ኃይለኛ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ 7 ሺ ሰዎች ሞቱ። ባለፈው ወር በ 01.16/17.20 ላይ 25 ኛው ዓመት ( ኢዮቤልዮ ) ታስቦ ውሎ ነበር።
ባለፈው ዓመት በዚሁ በሎስ ኤንጀልስ የተገደለውና የሀበሻ ዝርያ የነበረበት ራፐር “ Nipsey Hussle / ኒፕሲ ሃስል”ም እንዲሁ ለዲያብሎስ የደም ግብር እንዲከፍል ነበር የተደረገው። በተለይ አንድ ኢትዮጵያዊ ከገደለው ሌላው ራፐር “ Snoop Dog / ስኑፕ ዶግ” እና በዘጠናዎቹ አጋማሽ ላይ ከተገደለው ከሌላው ራፐር “ Tupac Shakur / ቱፓክ ሻኩር“ ጋር በመንፈስ የተያያዘ አስገራሚ ጉዳይ ነው። 51.5% የሂፕ ሆፕ ሙዚቀኞች በግድያ ነው ህይወታቸው የምታለፈው። በሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ።
_____________ ________________________
Like this: Like Loading...
Posted in Conspiracies , Ethiopia , Health , Infos | Tagged: anti-Ethiopia Conspiracy , ሕዝብ ቁጥር ቅነሳ , ቅርጫት ኳስ , ተላላፊ በሽታዎች , ቻይና , ኢትዮጵያ , ኮሮና ቢራ , ኮሮናቫይረስ , ኮቤ , ኮቤ ብራያንት , ወረርሽኝ , የክርስቶስ ተቃዋሚ , ጃፓን , ፀረ-ኢትዮጵያ ሤራ , Corona Beer , Depopulation Agenda , Dr. Teodros Adhanom , Ethiopian Airlines , Kobe Bryant , WHO | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 22, 2020
እዚህ ይመልከቱ፦ https://www.bitchute.com/video/r15Aw4y681ma/
ኮሮና ጋኔን ናት ፥ ዘረኝነት ደግሞ የጋኔን አንዱ መገለጫ ነው፦
👉 ቢጫ ጥቁርን ይጠላል ነጭን ይወዳል
👉 ነጭ ቢጫን እና ጥቁርን ይጠላል
👉 ጥቁር ነጭን + ቢጫን ይወዳል
ሰሞኑን በጀርመን አገር ያሉ ምግብ ቤቶች የመንግስት የኮሮና ቫይረስ ክልከላዎችን አብቅተው እፎይ በማለት እንደገና እንዲከፈቱ ሲፈቀድላቸው፤ የአንድ ታዋቂ ምግብ ቤት ፈረንሳዊ ኮከብ ምግብ አዘጋጅ፡ “ቻይናዎችን እዚህ አንፈልግም !” በማለት ቢጫ ሰዎችን ወደ ሬስቶራንቱ እንዳይገቡ በመከልከሉና ብዙዎችን በማስቆጣቱ ከማዕረጉ ላይ አንድ ኮከብ ቀነሰ።
ቀደም ሲል በቻይና ብዙ ጥቁሮች የዘረኝነት አድሎና ጥቃት እየደረሰባቸው ነበር። በአን ወቅት አንዲት ቻይና የቆየች ኢትዮጵያዊት ዲፕሎማት ወደ ገበያ ማዕከል መግባት ስትከለከል አብራት የነበረችዋ ነጯ ሴት ግን መግባት ተፈቅዶላት እንደነበር አይተናል። ብዙም ሳይቆይ በዘመነ ኦሪት እግዚአብሔር አምላክ በኢትዮጵያዊቷ ሲፖራ ምክኒያት የነብዩ ሙሴንና አሮንን እህት ማርያምን በዘረኝነቷ ገጽሶ ለምጻም እንዳደረጋት በዘመነ ኮሮናም ቻይናውያን ኢትዮጵያዊቷን ዲፕሎማት በማግለላቸው ይመስላል ሁለት ቻይናውያን ዶክተሮቻቸው ከእንቅልፋቸው ሲነቁ ጠቁረው ተ ገኙ ፤ ኮሮና ሁሉንም ፩ ገጽታ ሰጠቻቸው ማለት ነው።
ኮሮና ሁሉንም ፩ አደረገቻቸው | ዘረኞቹ ቢጫ ቻይናውያን ጥቁሮች ሆነው ከእንቅልፋቸው ነቁ
በኮሮና ተጠቅተው የነበሩት ሁለት የቻይና ዶክተሮች ከማገገሚያ አልጋቸው ሲነቁ ቢጫው ቆዳቸው ሙሉ በሙሉ ጠቁሮባቸው ተገኘ።
እንግዲህ የእነዚህ ሁለት ዶክተሮች መጥቆር ሰሞኑን ቻይናውያን በጥቁር ሰዎች ላይ እያራገፉት ያለውን የዘረኝነትን ጋኔን “ዋ ! ዋ ! ዊ ! ዋ !” እያሉ እራሳቸውን በመስተዋት እንዲያዩት ረድቷቸው ይሆናል።
በጣም የሚገርም ዘመን እኮ ነው፡ ጃል ! ግን የዘረኝነትን ውጤቶች እያየን ነው ? ነጮቹ ቻይናን በኮሮና ቫይረስ ከበከሏት በኋላ ሌት ተቀን ይኮንኗታል ፥ ቻይና ግን በሚሊየን ለሚቆጠሩ ቻይናውያን የአገሮቻቸውን በሮች ብርግድ አድርገው በከፈቱላት ጥቁር አፍሪቃውያን ላይ የዘረኝነትን መርዝ ትተፋለች። ለነገሩማ የምዕራብ እና ምስራቅ ኢ – አማንያን ሁሉም አብረው በአንድነት እየሠሩ ነው። ሁሉም ጥቁር አፍሪቃውያንን ከአህጉራቸው አስወግደው በአፍሪቃ ወይ ነጭንና ቢጫን ብቻ ለማስፈር ይሠራሉ ወይም ደግሞ አፍሪቃ የዱር አራዊቶችና ማዕድኖች መኖሪያ ብቻ እንድትሆን ይሻሉ። የተገለባበጠባት እርኩስ ዓለም።
እግዚአብሐር አምላክ ከሦስት ሺህ ሦስት መቶ ዓመታት በፊት ያስተማረን ይህን ነበር፤ የሰው ልጅ ግን ተምሮ ለመለወጥ ሰንፏል።
[ ኦሪት ዘኍልቍ ምዕራፍ ፲፪፥ ]
፩ ሙሴም ኢትዮጵያይቱን አግብቶአልና ባገባት በኢትዮጵያይቱ ምክንያት ማርያምና አሮን በእርሱ ላይ ተናገሩ።
፪ እነርሱም። በውኑ እግዚአብሔር በሙሴ ብቻ ተናግሮአልን ? በእኛስ ደግሞ የተናገረ አይደለምን ? አሉ፤ እግዚአብሔርም ሰማ።
፫ ሙሴም በምድር ላይ ካሉት ሰዎች ሁሉ ይልቅ እጅግ ትሑት ሰው ነበረ።
፬ እግዚአብሔርም ወዲያው ሙሴንና አሮንን ማርያምንም። ሦስታችሁ ወደ መገኛኛው ድንኳን ውጡ ብሎ ተናገረ፤ ሦስቱም ወጡ።
፭ እግዚአብሔርም በደመና ዓምድ ወረደ፥ በድንኳኑም ደጃፍ ቆመ፤ አሮንንና ማርያምን ጠራ፥ ሁለቱም ወጡ።
፮ እርሱም። ቃሌን ስሙ፤ በመካከላችሁ ነቢይ ቢኖር፥ እኔ እግዚአብሔር በራእይ እገለጥለታለሁ፥ ወይም በሕልም እናገረዋለሁ።
፯ ባሪያዬ ሙሴ ግን እንዲህ አይደለም፤ እርሱ በቤቴ ሁሉ የታመነ ነው።
፰ እኔ አፍ ለአፍ በግልጥ እናገረዋለሁ፥ በምሳሌ አይደለም፤ የእግዚአብሔርንም መልክ ያያል፤ በባሪያዬ በሙሴ ላይ ትናገሩ ዘንድ ስለ ምን አልፈራችሁም ? አለ።
፱ እግዚአብሔርም ተቈጥቶባቸው ሄደ።
፲ ደመናውም ከድንኳኑ ተነሣ፤ እነሆም፥ ማርያም ለምጻም ሆነች፥ እንደ አመዳይም ነጭ ሆነች፤ አሮንም ማርያምን ተመለከተ፥ እነሆም፥ ለምጻም ሆና ነበር።
__________ ___________________
Like this: Like Loading...
Posted in Curiosity , Ethiopia , Faith , Health , Infos | Tagged: መጥቆር , ቢጫ , ተላላፊ በሽታዎች , ቻይና , ነጭ , አፍሪቃውያን , ኢትዮጵያ , ኮሮናቫይረስ , ወረርሽኝ , ዘረኝነት , የቆዳ ቀለም , ዶክተሮች , ጋኔን , ጥቁር , Black white yellow , China , Demons of Racism , Europe , skin Color | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 21, 2020
አውሬው ደንግጧል፣ ክትባቱን መርጦታል፣ ሳንሱር አብዝቷል፣ ቪዲዮውን ከዩቱብ አንስቶታል። ስለዚህ እዚህ ገብተው ይመልከቱ፦ https://www.bitchute.com/video/U1DNdhsltUWp/
“ዓለም ዛሬ 6.8 ቢሊዮን ሰዎች አሏት፡፡ ያ ወደ ዘጠኝ ቢሊዮን ያህል እየመራ ነው ፡፡ አሁን በአዳዲስ ክትባቶች ፣ የጤና እንክብካቤ እና የመራቢያ ጤና አገልግሎቶች ላይ ትልቅ ስራ የምንሰራ ከሆነ ምናልባት ምናልባት ቁጥሩን በ 10 ወይም በ 15 በመቶ ዝቅ ማድረግ እንችላለን፡፡” – ቢል ጌትስ
“The world today has 6.8 billion people. That’s heading up to about nine billion. Now if we do a really great job on new vaccines, health care & reproductive health services, we could LOWER that by perhaps 10 or 15 percent.” -Bill Gates
ዶ / ር ቴዎድሮስ አድሃኖምን ገና ሲመረጧቸው፤ “ያለ ምክኒያት አለመረጧቸውም !” ብለን ነበር። ኢትዮጵያን ለዚህ ዘመን በደንብ አዘጋጅተዋታል። አውሬው ሕዝቦቿን በነገድ ከከፋፈለ በኋላ በአውሬው መታወቂያና ፓስፖርት ላይ የነገድ ስም ብሎም የየትኛው እምነት ተከታይ እንደሆነ ቁልጭ ብሎ እንዲቀመጥ አድርጓል። ይህ ደግሞ በቀበሌ ሥርዓት የተዋቀሩትን የኢትዮጵያ ከተሞችና መንደሮች ዲያብሎሳዊ ሥራቸውን ለመስራት ትልቅ እድል ሰጥቷቸዋል። ለእነ አብዮት አህመድና ታከለ ኡማ የየትኛውን ነገድ / ብሔር ነዋሪዎች መከተብ፣ መመረዝና መግደል እንደሚችሉ በጣም አመቺ የሆነ ሁኔታ ፈጥሮላቸዋል።
የተማረው ያለተማረው ወገን ገዳዮቹን “መሪዎቹን” በማወደስ እድሜውን ሲገፋና በማይረቡ ነገሮች እርስበርስ እየተነታረክ ጊዜውን በከንቱ ሲያጠፋ፤ ገዳዮቹ “ልሂቃን” ግን እርሱንና ዘሩን ለማጥፋት ሌት ተቀን ተግተው በመስራት ላይ ናቸው። የአውሬ ምሣ የሆነው ሰጎን በድንጋጤ አንገቱን አሸዋ ውስጥ ይቀብራል፤ የዘመኑ ትውልድ ግን በግድየለሽነት አንተቱን አሸዋ ውስጥ ለመቅበር የሚፈልግ ይመስላል።
ከስምንት ዓመታት በፊት እነ ቢል ጌትስ በኢትዮጵያ ሴቶችና ሕፃናት ላይ ያነጣጠረ ዲያብሎሳዊ ዕቅድ እንዳላቸው በጦማሬ እንዲህ በማለት ጽፌ ነበ ር፦
“ወደ አገራችን በረቀቀ መልክና በድብቅ የገባው ይህ የፀረ–ህይወት እንቅስቃሴ ከ 1970 ዎቹ ዓመታት ጀምሮ በትጋት እየሠራ እንደሆነ ባለሙያዎች ይናገራሉ። ከኢትዮጵያ ሌላ፡ ይህ የቤተሰብ አጥፊ ፕላን በጥቁር አፍሪቃውያን ላይ ብቻ ነው እየተካሄደ ያለው። ከሦስት ወራት በፊት ለንደን ከተማ ውስጥ ይህን አስመልክቶ እን ቢል ጌትስ አዘጋጅተውት በነበረው ስብሰባ ላይ ተገኝተው የነበሩት ከሳሃራ በረሃ በታች የሚገኙት አፍሪቃ አገሮች ሲሆኑ፤ የሰሜን አፍሪቃና አረብ አገሮች ጭራሹን አልተሳተፉም። 85 ሚሊየን ሕዝብ የሚኖሩባት በረሃማዋ ግብጽ የሕዝብ ቁጥርሽን ቀንሽ የሚል ሃሳብ ቀርቦላት አይታወቅም፡ እንዲያውም ምዕራባውያኑ የእርዳታ ገንዘቡን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ በደስታ ይሰጧታል፤ የኢትዮጵያንም ውሃና አፈር በነፃ ታገኛለች፡ ጦረኛ የሆኑ ልጆችን መፈልፈሏንም ያለምንም ተቃውሞ ትቀጥልበታለች። ከ 1 ቢሊየን በላይ የሕዝብ ቁጥር ያላት ህንድ እንደ ዶፖ ፕሮቬራ የመሳሰሉትን የወሊድ መከላከያ መርፌዎች ከልክላለች ( እ . አ . አ በ 2002 ዓ . ም )
አዎ ! የዲያብሎስ ሠራዊት ኢትዮጵያውያንን በረሃብ፣ በበሽታና በእርስ በርስ ጦርነቶች እንዳሰበው / እንዳቀደው ለማጥፋት አልተቻለውም፤ ታዲያ አውሬው አሁን ውስጥ ሠርጎ በመግባት መርፌንና፤ (“ መድኃኒት” አልለውም ) መርዛማ‘ቅመሞችን‘በነፃ በማደል መጠራጠር የተሳነውን ወገናችንን ወደ ወጥመዱ ለማስገባት እየሞከረ ነው።
ወገን፤ እህቶቻችን፣ እናቶቻችን፣ ጓደኞቻችንና ሚስቶቻችን እንደ ዓይጥ ተቆጥረው የህክምና ሙከራ ሲደረግባቸው እያየን እንዴት ዝም እንላለን ? ይህን ይህን መሰሉን አስከፊ ሥራ ለማጋለጥ ካልተነሳሳን ከእንስሳ በምን ነው የምንሻለው ?
የሚከተሉትን መረጃዎች ለሚመለከታቸው ወገኖች ሁሉ በሚያስቆጣ መልክ የማስተላለፉ ተግባር የያንዳንዳችን ብሔራዊና ሰብዓዊ ግዴታ መሆን ይኖርበታል።
ለምሳሌ፤ በውጭ ኃይሎች ‘ግፊት‘ኢትዮጵያ ውስጥ ከተቋቋሙት ድርጅቶች መካከል “ DKT Ethiopia (DKT/E)” የተባለውን የፀረ–ህይወት ዘመቻ አራማጅ ድርጅት ብንመለከት፤ ሥራውና ዓላማው ምን እንደሆነ በደንብ ለመረዳት እንችላለን። ድርጅቱ የሚናገረው ሌላ …”
_________ _________________
Like this: Like Loading...
Posted in Conspiracies , Ethiopia , Faith , Health | Tagged: #የሕዝብ ቁጥር ቅነሳ #Vaccines , anti-Ethiopia Conspiracy , ቢል ጌትስ , ተላላፊ በሽታዎች , ቻይና , ክትባት , ኮሮናቫይረስ , ወረርሽኝ , ዶ/ር አድሃኖም , Bill Gates , Depopulation Agenda , Dr. Teodros Adhanom , Ethiopia , WHO | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 23, 2020
VIDEO
እነዚህ ሁለት የኒው ዮርክ ሴቶች ጉድ ! የሚያስበል መረጃ ሰጥተውናል፦
👉 የመጀመሪያዋ ሴት ለዶክተሩ“ማሽተትና መቅመስ ተስኖኛል” ስትለው፤ ዶክተሩ ፤ “ኮሮና አለብሽ” ብሎ ወደ ሆስፒታል ላካት።
👉 ሁለተኛዋ ትውልደ ዶሚኒካን ሪፓብሊክ የሆነችውና በኮቪድ 19 የተጠቃችው የ 49 ዓመቷ ባለትዳር በኒው ዮርክ ሆስፒታል ውስጥ ከመሞቷ በፊት የድምፅ መልእክት ትታ አርፋለች። ይህንም ያደረገችው ልክ ስትወጋ እንደምትሞት ስለታወቃት ነበር። እንደገለጸችውም ህመምተኞቹ ከሆስፒታል በፍጥነት እንዲወጡ እርሷና ሌሎች ህመምተኞች በገዳይ መርፌ ተወግተው ነበር።
እያለቀሰች የተወችው የድምጽ መልዕክት እንዳይሰማ ፌስቡክ፣ ትዊተርና ዩቱብ ከልክለውታል !
የኮሮናቫይቫይረስ ሕክምና፤ አደገኛ ገዳይ መርፌ ውስጥ የሚገቡ መድኃኒቶች የኮቪድ 19 /COVID-19 በሽተኞችን ሊረዱ ይችላሉ” ይላሉ ሐኪሞች።
ዋው !
👉 የክርስቶስ ተቃዋሚውን ዲያብሎሳዊ ሥራ እያየን ነው ?
👉 ጌታችን “ ማደንዘዣውን ” ሊጠጣው አልወደደም፤
[ የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፳፯፥፴፬ ]
“በሐሞት የተደባለቀ የወይን ጠጅ ሊጠጣ አቀረቡለት፤ ቀምሶም ሊጠጣው አልወደደም። ”
👉 እነዚህ ገዳዮች “እጃችሁን በሳሙና ታጠቡ” ለምን እንደሚሉንስ ?
[ የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፳፯፥ ፳፬ ]
“ጲላጦስም ሁከት እንዲጀመር እንጂ አንዳች እንዳይረባ ባየ ጊዜ፥ ውኃ አንሥቶ። እኔ ከዚህ ጻድቅ ሰው ደም ንጹሕ ነኝ፤ እናንተ ተጠንቀቁ ሲል በሕዝቡ ፊት እጁን ታጠበ። ”
_________ __________________
Like this: Like Loading...
Posted in Ethiopia , Health , Infos | Tagged: Antichrist , ተላላፊ በሽታዎች , ቸነፈር ወረርሽኝ , ኒው ዮርክ , ኢትዮጵያ , ክትባት ሤራ , ኮሮናቫይረስ , ዘመነ ኮሮና , የክርስቶስ ተቃዋሚው , ገዳይ መርፌ , Coronavirus , Evil , Flu , Lethal Injection , New York , Vaccine | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 22, 2020
VIDEO
ባጭሩ መንግስት የክርስቲያኖችን አንጎል ለመቀየር የጉንፋን ቫይረስን ፈጥሮ በመርፌ ይወጋቸዋል ! ወገኖቼ ተመልከቱልኝ ይህን ክፋትና አረመኔነት ! ታዲያ ይህን ለማድረግ አይደል ኮሮናን የፈጠሯት ?! መቼስ ይህን ቪዲዮ አይቶ ክትባት የሚከተብ ይኖራል ብዬ አልገምትም።
ቪዲዮው የተቀረፀበት ቀን ከአስራ አምስት ዓመታት በፊት እ . አ . አ በ 4/13/2005 ዓ . ም ነው፡፡ ይህ በአንድ የሳይንስ ሊቅ የቀረበ ማብራሪያ የተቀረጸው በዝነኛው የአሜሪካ መከላከያ ሚንስትር ( ፔንታጎን ) ሕንፃ አንድ አዳራሽ ውስጥ ነው፡፡ ይህ ሰው የወታደራዊ መለዮ በለበሱ የአዳራሹ ተሳታፊዎች ፊት ስለ አንጎል እና VMAT2 ተብሎ ስለሚጠራው ‘ ጂን ‘[ የዘር ቅንጣት ] መግለጫ ይሰጣል፡፡ “የኤምአርአይ የአንጎል ምርመራ” ምስሎችን እያሳየ ስለ ሃይማኖትና አጥባቂ ሃይማኖተኞች አንጎል ይናገራል፡፡
የቪኤምአይ 2 ን / VMAT2 የዘር ቅንጣትን በመከላከል / በማደናቀፍ ከጊዜ በኋላ የሰዎች አንጎል ከሃይማኖት የአንጎል መዋቅር ወደ ኢ – አማናይ አንጎል መዋቅር፤ እነርሱ እንደሚሉት “በሳይንሳዊ መልኩ እንዲዛወር ማድረግ ይቻላል… በመሠረቱ የሃይማኖተኛን አንጎል ሃይማኖታዊ ወዳልሆነ የአዕምሮ መዋቅር መለወጥ ይቻላል ብለው ያምናሉ፡፡
V MAT2 ሰዎች “የእግዚአብሔርን ጂን / የዘር ቅንጣት” ብለው ለሚጠሩት ሳይንሳዊ ስሙ ሳይሆን አይቀርም፡፡
በቪዲዮው ማብቂያ ላይ “ FunVax”(Vaccine for religious fundamentalists) በሚል መጠሪያ በ “ VMAT2 ጂን / የዘር ቅንጣት” ላይ ሙከራዎችን በማድረግና “የጉንፋን ቫይረስ”ፈጥረን ክትባቶችን በመውጋት አማኞችን ኢ – አማናይ ማድረግ ይቻላል የሚል አንድ ሀሳብ አቅርቧል፡፡ በይፋ እንደሚሉትም ይህን የምናደርገው “በመካከለኛው ምስራቅ ሰላም የመፍጠር ዓላማ ስላላቸው ነው”፡፡
ይህ እ . አ . አ በ 2005 ዓ . ም የተቀረጸ ቪዲዮ ነው። በእኔ በኩል እንኳ ይህን ጉዳይ አስመልክቶ ይህ ዓመተ ምህረት ቁልፍ ቦታ እንዳለው በጦማሬ ላይ በእንግሊዝኛው ያቀረብኳቸው አንዳንድ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ብዙ ነገሮች የተገለጹበት ተዓምረኛ የሆን ዓመተ ምህረት ነበር።
የእነዚህ “የሳይንስ ሊቅ” የተባሉ አረመኔዎች ዒላማ የክርስትና እምነት በተለይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት እንደሆነ ደጋግሜ አውስቸዋለሁ። ከዚህች ሃይማኖት ሌላው ከኢ – አማናይ ስለሚመደብ “አክራሪ ሃይማኖተኛ” ሲሉ በየቀኑ የሚያርደውን እስላም ወይም ሂንዱ ማለታቸው አይደለም። አካራሪ ሃይማኖተኛ እንደ ኢትዮጵያ ተዋሕዷውያን ያሉት አማኞች ናቸው። አዎ ! ስጋዊው ሰውነታችን ወይም ደማችን በጥንታዊነቱ በምድር ላይ ከቀሩት ጥንታውያን / የአዳም ዘር ከቀረባቸው ሁለት ሕዝቦች መካከል አንዱ ነው። ሌላው በደቡብ አፍሪቃና ናሚቢያ የሚገኘው “ሳን” የተባለው ሕዝብ ነው። እዚህ ያንብቡ ።
ከመንፈሣዊነት አንጻርም ተዋሕዶ ኢትዮጵያውያን ከአባታችን ሔኖክ ዘመን ጀምሮ ጥልቅ የሆነ የመንፈሣዊ ፀጋ ተሰጥቶን ያለን ሰዎች ነን።
ስለዚህ አረመኔዎቹ ሊቃውንት በኢትዮጵያውያን ደም እና “የእግዚአብሔር ጂን / የዘር ቅንጣቸው” ላይ ሙከራ ለማድረግ ብሎም ጥቃት ለመፈጸም በጣም ከፍተኛ የሆነ ሙያዊ የማወቅ ጉጉት ነው ያላቸው። ለዚህም ነው ደጋሜ “የኢትዮጵያ አባቶች ከሃገራችሁ አትውጡ ፤ ለህክምና ወደ ውጭ አትሂዱ” የምለው። እንኳን በእነርሱ በእኛ ላይ እንኳን ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ጥቃቶቻውን ይፈጽሙብናል። ይህን ድርጊት እስካልነቃንበትና በክርስቶስ ስምም “ሂዱ !” ብለን እስካላባርነናቸው ድረስ በየጎረቤቱ ያሰማሩት የዲያብሎስ ሠራዊት በእያንዳንዱ ተዋሕዶ ኢትዮጵያዊ ላይ ከሩቅም ከቅርብም ጥቃቱን ከመፈጸም ወደኋላ አይልም። እንዲያውም ቪዲዮው ላይ የቀረበው “የጉንፋን ቫይረስ” ሃሳብ የመጀመሪያው ደረጃ ነው ፤ በአሁኑ ሰዓት ያለው ቴክኖሎጂ ከምናስበው በላይ በጣም የረቀቀ የመጠቀ ነው። እንግዲህ ከአስራ አምስት ዓመት በፊት ስለ “ጉንፋን ቫይረስ / ኮሮና” ጠቁመውን ነበር ፤ ታዲያ ዛሬ ያዘጋጇቸውን እንደ 5 ጂ የማይክሮዌቭ ጨረር አፈንጣቂ የሆኑትን መሣሪያዎች በመጠቀም ይህን የጉንፋን ቫይረስ በአማኞች ዘንድ ለማሰራጨት እየሞከሩ ነው።
ውጤቱ የጠበቁትን ያህል ባይሆንም የማይጠነቀቁትና ስለጉዳዩ ብዙ እውቅና የሌላቸው ሰዎች፤ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ የዚህ ሙከራ ሰለባ ሲሆኑ ሁላችንም እያየነው ነው። አዎ ! በሃገር ቤትም በውጭም። በየማህበረሰባዊ ድህረ ገጹ ወገናችን ዋና ጠላቱ በሆኑትና “ሊቃውንት” በተባሉት በእነዚህ የሉሲፈር ደቀ መዛሙርት ላይ አንድ ሆኖ እንደመነሳት ጠላት በሰጠው ማንነት እርስበርሱ እንዲበላላ፣ ዛሬ የያዘውን አቋም ነገር ሲለውጥ ፣ ዛሬ የግራኝ አህመድ ተቃዋሚ ፣ ነገ ደጋፊ ፣ ዛሬ ተዋሕዶ ነገ ጴንጤና ኢ – አማናይ እንዲሆን እየተደረገ ነው። በተለይ ይህ አቋመ – ቢስነት የዚህ ሙከራ ውጤት እንደሆነ ተደርጎ ሊቆጠር ይገባል።
እህተ ማርያም “በአዲስ አበባ የሚገኙት የሃያላኑ ኤምባሲዎች ምድር ሥር ድብቅ ቤተ ሙከራዎችና መሣሪያዎች አላቸው” ስትል የነበረው ትክክል ነው። የአሜሪካ፣ የፈረንሳይ፣ የጀርምን፣ የብሪታኒያ፣ የሩሲያ እና የሌሎችም ኤምባሲዎች እንጦጦ ተራራ ሥር በጫካ የተሸፈኑ ታላላቅ መሬቶችን መያዛቸው ዝም ብሎ ይመስለናልን ? ግራኝ አህመድስ “የአንድነት ፓርክ” ብሎ በምኒሊክ ቤተ መንግስት እንዲሁም በጃን ሜዳ መስቀል አደባባይ ባጠቃላይ በታሪካዊዎቹ የአዲስ አበባ የክፍለ ከተማዋዎች ላይ ማተኮሩ ለበጎ ነገር ይመስለናልን ? ሽህ አላሙዲንስ ፍልውሃ አካባቢ ሸረተንን መገንባቱ፣ ጻድቁ አብርሐም ገዳም አካባቢ “የመዝናኛ ቦታ” እንዲሁም አራዳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፊት ለፊት ከእንጦጦ ተራራ ከፍ የሚል፤ ከጂዳ ሰማይ ጠቀስ ፎቅ ጋር በአየር የሚተያይ ሰማይ ጠቀስ ፎቅ ለመስራት ማቀዱስ ለኢትዮጵያ አስቦ ይመስለናልን ?
የሰውን ልጅ ሕልውና አደጋ ላይ የሚጥሉ 10 አስፈሪ ቴክኖሎጂዎች
VIDEO
__________ _________________
Like this: Like Loading...
Posted in Conspiracies , Curiosity , Ethiopia , Faith , Infos | Tagged: 5G Tower , Antichrist , Atheism , ተላላፊ በሽታዎች , ቸነፈር ወረርሽኝ , ኢትዮጵያ , ክትባት ሤራ , ኮሮናቫይረስ , ዘመነ ኮሮና , ፀረ-ክርስትና , Coronavirus , Evil , Flu , FunVax , Pentagon , UK , Vaccine | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 22, 2020
VIDEO
እስኪ ይታየን፤ ኢትዮጵያውያን በሃገራቸው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ይገደላሉ፣ ከቤታቸው ይፈናቀላሉ፣ ይሰደዳሉ ፥ በውጭ ሃገር ደግሞ በየአውሮፕላን ማረፊያው እየተጉላሉ የድርሱልን ጪኸት ያሰማሉ ፥ በሌላ በኩል ግን አብዮት አህመድ ለአረቦች፣ ለጃፓናውያንና ለአሜሪካውያን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላኖችን በፍጥነት ከች ያደርግላቸዋል።
ላለፉት ሁለት ዓመታት ይህን ያህል እየቀለደብህ ያለውን ይህን ህገ – ወጥ የወሮበሎች ስብስብ መንግስት የምትታገስ ደካማ ትውልድ አንቀላፋ፣ ገና ሌላ ጉድ ይጠብቀሃል። ደግሞ ትግሬ ስለሆነ በአቶ ተወልደ አሳብ፤ አቶ ተውለደ ገብረ ማርያም ይህን አውቆ ከሃላፊነቱ አስቀድሞ በፈቃዱ መውረድ ነበረበት። ሤራው ሆን ተብሎ የተጠነሰሰ ነው። በኢትዮጵያ አየር መንገድ እየታየ ላለው እራስን የመግደል አካሄድና ጥልቅ ውርደት ሙሉ ሃላፊነቱን የሚወስደው ግራኝ አህመድ አሊ ነው። ዛሬ የኢትዮጵያ አየር መንገድ CEO አብዮት አህመድ አሊ ነው። በዚህ ባልተለመደ የወረርሽኝ ዘመን በረራዎቹን መፍቀድና መላክ ፣ ማቆምና ማገድ የሚችለው እሱ ብቻ ነው። ከጃፓን እና አሜሪካ ፖለቲከኞች ጋር የሚያደርገው የስልክ ልውውጥም ለዚህ በቂ ማስረጃ ነው።
____________ _______________________
Like this: Like Loading...
Posted in Conspiracies , Ethiopia , Faith , Infos | Tagged: anti-Ethiopia Conspiracy , ተላላፊ በሽታዎች , ቻይና , ኢትዮጵያ , ኮሮናቫይረስ , ወረርሽኝ , የኢትዮጵያ አየር መንገድ , ዱባይ , ጃፓን , ፀረ-ኢትዮጵያ ሤራ , Dubai , Ethiopian Airlines , Japan | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 21, 2020
VIDEO
በኮሮና ተጠቅተው የነበሩት ሁለት የቻይና ዶክተሮች ከማገገሚያ አልጋቸው ሲነቁ ቢጫው ቆዳቸው ሙሉ በሙሉ ጠቁሮባቸው ተገኘ።
ኮሮና ጋኔን ናት ፥ ዘረኝነት የጋኔን አንዱ መገለጫ ነው !
እንግዲህ የእነዚህ ሁለት ዶክተሮች መጥቆር ሰሞኑን ቻይናውያን በጥቁር ሰዎች ላይ እያራገፉት ያለውን የዘረኝነትን ጋኔን “ዋ ! ዋ ! ዊ ! ዋ !” እያሉ እራሳቸውን በመስተዋት እንዲያዩት ይረዳቸው ይሆናል።
በጣም የሚገርም ዘመን እኮ ነው፡ ጃል ! ግን የዘረኝነትን ውጤቶች እያየን ነው ? ነጮቹ ቻይናን በኮሮና ቫይረስ ከበከሏት በኋላ ሌት ተቀን ይኮንኗታል ፥ ቻይና ግን በሚሊየን ለሚቆጠሩ ቻይናውያን የአገሮቻቸውን በሮች ብርግድ አድርገው የከፈቱትን ጥቁሮችን ታጠቃለች። ታዲያ የምዕራብ እና ምስራቅ ኢ – አህማንያን ሁሉም አብረው በአንድነት እየሠሩ እንደሆነ አይነግረንምን ? የተገለባበጠባት ዓለም።
እግዚአብሐር አምላክ ከሦስት ሺህ ሦስት መቶ ዓመታት በፊት ያስተማረን ይህን ነበር፤ የሰው ልጅ ግን ተምሮ ለመለወጥ ሰንፏል።
[ ኦሪት ዘኍልቍ ምዕራፍ ፲፪፥ ]
፩ ሙሴም ኢትዮጵያይቱን አግብቶአልና ባገባት በኢትዮጵያይቱ ምክንያት ማርያምና አሮን በእርሱ ላይ ተናገሩ።
፪ እነርሱም። በውኑ እግዚአብሔር በሙሴ ብቻ ተናግሮአልን ? በእኛስ ደግሞ የተናገረ አይደለምን ? አሉ፤ እግዚአብሔርም ሰማ።
፫ ሙሴም በምድር ላይ ካሉት ሰዎች ሁሉ ይልቅ እጅግ ትሑት ሰው ነበረ።
፬ እግዚአብሔርም ወዲያው ሙሴንና አሮንን ማርያምንም። ሦስታችሁ ወደ መገኛኛው ድንኳን ውጡ ብሎ ተናገረ፤ ሦስቱም ወጡ።
፭ እግዚአብሔርም በደመና ዓምድ ወረደ፥ በድንኳኑም ደጃፍ ቆመ፤ አሮንንና ማርያምን ጠራ፥ ሁለቱም ወጡ።
፮ እርሱም። ቃሌን ስሙ፤ በመካከላችሁ ነቢይ ቢኖር፥ እኔ እግዚአብሔር በራእይ እገለጥለታለሁ፥ ወይም በሕልም እናገረዋለሁ።
፯ ባሪያዬ ሙሴ ግን እንዲህ አይደለም፤ እርሱ በቤቴ ሁሉ የታመነ ነው።
፰ እኔ አፍ ለአፍ በግልጥ እናገረዋለሁ፥ በምሳሌ አይደለም፤ የእግዚአብሔርንም መልክ ያያል፤ በባሪያዬ በሙሴ ላይ ትናገሩ ዘንድ ስለ ምን አልፈራችሁም ? አለ።
፱ እግዚአብሔርም ተቈጥቶባቸው ሄደ።
፲ ደመናውም ከድንኳኑ ተነሣ፤ እነሆም፥ ማርያም ለምጻም ሆነች፥ እንደ አመዳይም ነጭ ሆነች፤ አሮንም ማርያምን ተመለከተ፥ እነሆም፥ ለምጻም ሆና ነበር።
_________ _________________
Like this: Like Loading...
Posted in Curiosity , Ethiopia , Faith , Health | Tagged: መጥቆር , ተላላፊ በሽታዎች , ቻይና , አፍሪቃውያን , ኢትዮጵያ , ኮሮናቫይረስ , ወረርሽኝ , ዘረኝነት , የቆዳ ቀለም , ዶክተሮች , ጋኔን , Black , Demons of Racism , Racism , skin Color | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 20, 2020
VIDEO
በማለት በካራስናያርስክ እና አብዛኛዎቹ ነዋሬዎቿ ሩሲያውያን በሆኑባት የዩክሬኗ ዶኔትስክ ከተማዎች በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሩሲያውያን በቤተ ክርስቲያን ለጸሎት፣ ለጸበልና መስቀሉን ለመሳም ተገኝተዋል።
እርር ይበሉና ምዕራባውያኑ በዚህ ተቆጥተዋል ! የእንግሊዙ ጋዜጣ “ደይሊ ሜይል” የሚከተለውን ጽፏል፦
„So much for social distancing! Orthodox Christians defy lockdown to go to Easter Services . “
“የምን ማሕበራዊ መራራቅ ! ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ለኮሮና የወጣውን እገዳ በመቃወም ለፋሲካ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሄዱ”
ዓይናቸውን በኦርቶዶክሱ ክርስቲያን ዓለም ላይ ጥለዋል… በኢትዮጵያን አስመልክቶ ይህው ጋዜጣ ያወጣውን በሚቀጥለው ቪዲዮ …
ሮማውያኑ ( ኢ – አማንያን ) ፣ ሂትለር ( ብሔራዊ ሶሻሊዝም ) እና ስታሊን ( ኮሙኒዝም ) የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን ሊያጠፉት ብዙ ሞከሩ፤ ግን አልተሳካላቸውም፤ ዛሬም የኮሮና ቫይረስ ሆነው መጥተዋል፤ ቤተ ክርስቲያንንም በመላው ዓለም በመፈታተን ላይ ናቸው።
___________ ______________________
Like this: Like Loading...
Posted in Ethiopia , Faith , Health , Infos | Tagged: ማሕበራዊ መራራቅ , ቤተ ክርስቲያን , ተላላፊ በሽታዎች , ትንሣኤ , ቸነፈር ወረርሽኝ , የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን , ፋሲካ , Church Visit , Corona Virus , Easter , Easter Services , Russian Orthodox Church | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 7, 2020
VIDEO
በብሪታኒያ ብቻ በጥቂቱ 20 ማማዎች ተገንድሰዋል
_________ __________________
Like this: Like Loading...
Posted in Conspiracies , Ethiopia , Health | Tagged: 5ጂ , 5G Tower , ማማዎች , ማይክሮዌቭ , ተላላፊ በሽታዎች , ተንቀሳቃሽ ስልክ , ቸነፈር ወረርሽኝ , አንቴናዎች , ኢትዮጵያ , ኮሮናቫይረስ , ዘመነ ኮሮና , ፀረ-ኢትዮጵያ ሤራ , Coronavirus , UK | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 7, 2020
VIDEO
___________ ________________________
Like this: Like Loading...
Posted in Curiosity , Ethiopia , Health | Tagged: 5ጂ , 5G Tower , ማማዎች , ማይክሮዌቭ , ተላላፊ በሽታዎች , ተንቀሳቃሽ ስልክ , ቸነፈር ወረርሽኝ , አንቴናዎች , ኢትዮጵያ , ኮሮናቫይረስ , ዘመነ ኮሮና , ፀረ-ኢትዮጵያ ሤራ , Coronavirus , UK | Leave a Comment »