Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘ቬችተርስባህ’

ፍራንክፈርት | አንድ ዘረኛ ጀርመን ከመኪና ወርዶ በኢትዮጵያዊው ላይ ሽጉጡን ተኮሰበት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on July 23, 2019

ፍራንክፈርት ከተማ አቅራቢያ በምትገኘው ቬችተርስባህ መንደር አምሳ አምስት አመት የሞላው ጀርመናዊ መኪናውን አቁሞ መንገድ ላይ ወዳየው የሃያ ስድስት ዓመቱ ኢትዮጵያዊ (ኤርትራ) በማምራት ሽጉጡን አውጥቶ በመተኮስ ከፉኛ አቆሰለው። ኢትዮጵያዊው ወዲያው ወደ ሆስፒታል ተወስዶ ከሞት ሊተርፍ ችሏል (እንኳን አዳነው!)። ከድርጊቱ በኋላ ተኳሹ ጀርመናዊ እርሱን በራሱ ሽጉጥ ገድሏል። የድርጊቱ መንስዔ ዘረኝነት እንደሆነ እና ጀርመናዊውም እራሱን ከማጥፋቱ በፊት በመጀመሪያ ቆዳው ጠቆር ያለ ሰው መንገድ ላይ ፈልጎ በማግኘት ለመግደል አቅዶ እነደነበር መርማሪዎች ካገኙት የሰውየው ጽሑፍ ለመረዳት እንደበቁ ገልጸዋል።

ግን አየን፤ በጀርመን ሃገር አንድ ሰው መንገድ ላይ ሲገደል ፖሊስም ሜዲያውም ለጉዳዩ ትልቅ ቦታ ይሰጠዋል። ስለዚህ ጉዳይ ሁሉም ብሔራዊ ሜዲያዎች ሪፖርት አቅርበዋል። ለምሳሌ እዚህ በአሜሪካ ሰው በየመንገዱ መግደል የተለመደ ስለሆነ ብዙ ባይወራ አይገርመንም፤ እሁድ ዕለት ዋሽንግተን ከተማ በሚገኝ አንድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ጥቁር አሜሪካውያን ገብተው በምዕመናኑ ላይ ተኩስ እንደከፈቱባቸው ሰምተናል፤ ጉዳዩ ግን ብዙ ትኩረት አልተሰጠውም።

ወደ ሃገራችን ስንመለስ በሲዳማ ክፍለ ሃገር በተዋሕዶ ልጆች ላይ የተካሄደው ጂሃዳዊ ዘርተኮር ጭፍጨፋ እስካሁን የመንግስትን፣ የገዳይ አልአብይን፣ የሜዲያውን እንዲሁም የቤተ ክህነትን አትኩሮት ሊያገኝ አልቻለም። ሁሉም እስካሁን ጭጭ ብለዋልለምን? ወገን እያለቀ ተረጋጉ!?„

ጀርመኖች አብዛኞች አሁንም በብዙ ነገሮች ጥሩ ሰዎች ናቸው፤ ነገር ግን፤ ለመለወጥ ትንሽ ነገር ነው የሚበቃቸው ስለዚህ ሁኔታዎች፡ ቀስበቀስ እየተቀየሩ ነው። ለዚህም ብዙ ምኪኒያቶች አሉ፤ እርግማን ለሜርከል ይድረስና፡ በቅድሚያ ተጠያቂው ሥልጣኑን የያዘው እርጉሙ ኢስታብሊሽመንት/ አመራሩ ነው።

እግዚአብሔርን እየከዳ የመጣው የምዕራቡ አለም እራሱ በፈጠረው ችግር ከባድ ሁኔታ ላይ ወድቋል። ጀርመን ስንል አንድ የሆነች ጀርመን የለችም የተክፋፈለች እንጅ፣ ብሪታኒያ ስንል አንድ የሆነች ብሪታኒያ የለችም የተከፋፈለች እንጅ፣ አሜሪካ ስንል ፥ አንድ የሆነች አሜሪካ የለችም የተከፋፈለች እንጅ። እነዚህ በጎሳ አንድነን የሚሉ ሃገራት እኛን ከፋፈለው ለመግዛት ሲታገሉ እነርሱ እራሳቸው ተከፋፈልው በመውደቅ ላይ ናቸው። ይህን አንድ ወጥ በሆነው የሶማሊያ ሕዝብ ዘንድም አይተነዋል።

የኢሉሚናቲዎቹ ገረድ አንጌላ ሜርከል ከ አራት ዓመታት በፊት መስከረም ወር ላይ በሚሊየን የሚቆጠሩ በጥባጭ መሀመዳውያንን ወደ ጀርመን ጋብዛ ስታመጣቸው በሃገሪቱ ህውከት እና ሽብር ለመፍጠር፣ ሕብረተሰቡን አስቆጥቶ በውጭ ዝርያ ባላቸው ነዋሪዎች ላይ ለማነሳሳት ታስቦ እንደሆነ በጊዜው ጠቁመን ነበር። በተለይ ቆዳቸው ጠቆር ያለ ነዋሪዎች በቅድሚያ ጥቃት እንደሚፈጸምባቸው ግልጽ ነበር። ያው አሁን እያየነው ነው፤ ገና መጀመሩ ነው።

በጣም የሚያሳዝነው፤ እነዚህ ሉሲፈራውያን በሃገሮቻችን የሃገራችንን አየር እየሳብን፣ ፀሐይዋን እየሞቅን፣ ጤናማ የሆኑትን ምግቦች እየተመገብን፣ በየአብያተ ክርስትያናቱ እየተሳለምንና በፀበል እየተጠመቀን ከሕዝባችን ጋር በሰላም መኖር እንዳንችል ሃገር ወዳድ የሆኑትን መሪዎቻችን በመበከልና በመግደል እነርሱ የሚፈልጓቸውን መሪዎች መረጥው ሥልጣን ላይ በማስቀመጥ እንዲህ በስደት ጠፍተን እንድንቀር ይገፋፉናል። ያሳዝናል!

__________________

Posted in Ethiopia, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: