Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘ቨርጂኒያ’

Ethiopian Immigrant Yelled ‘I Hate America!’ in Attempted Pentagon Attack

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 3, 2022

👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 😇 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ 👉 መድኃኔ ዓለም

💭 የአሜሪካ መከላከያ ሚንስትርን/ ፔንታጎንን ለማጥቃት የሞከረው ኢትዮጵያዊ ስደተኛ ታምራት ጥላሁን የኋላወርቅ፤ “አሜሪካን እጠላለሁ!” ሲል ጮኸ!

👹 አረመኔው ጋላኦሮሞ ግራኝ አብዮት፤ አክሱም ጽዮንን ስለምጠላት እንደ በሻሻ አድርጊያታለሁ፤ አሜሪካን ግን በጣም ስለምወዳት ሕይወቴን አሳልፌ ልሰጣት ዝግጁ ነኝ!”

😲 የተገለባበጠባት ዓለም! በጣም አሳዛኝና አስገራሚ ጊዜ ላይ እንገኛለን!

💭 An Ethiopian man admitted he was “trying to kill people” out of contempt for America during an attempted vehicle attack at the Pentagon Friday morning, according to court records obtained by The Post.

Tamirat Tilahun Yehualawork, 36, is accused of driving a large SUV through two access checkpoints and into a secure parking lot on the grounds of the Defense Department’s headquarters in Arlington, Va. before attempting to run down a Pentagon police officer, according to his arrest affidavit.

“The officer took cover, pointed his weapon at the vehicle, and began giving verbal commands that Yehualawork ignored,” a Pentagon Force Protection Agency special agent wrote in the document. “[He] then drove over a sidewalk and through grass towards the Pentagon Mall Entrance.”

Law enforcement eventually stopped Yehualawork by “pinning his Ford Expedition with their cruisers against a parked vehicle adjacent to the mall entrance,” according to the affidavit.

Yehualawork, who entered the US on a visa but whose “immigration status is unclear,” resisted arrest and was “forcibly removed” from his vehicle, the report said.

“While being advised of his Miranda Rights, Yehualawork yelled, ‘F–k America,’” the special agent wrote in the affidavit. “After acknowledging his rights, Yehualawork told officers, ‘I hate American [sic] and I was trying to kill people.’”

He now faces federal charges of “assaulting, resisting or impeding” law enforcement and criminal trespass, according to court documents.

Alexandria US District Judge William E. Fitzgerald on Tuesday denied Yehualawork bond, noting that the affidavit “indicate[s] the defendant poses an ongoing danger to the community by clear and convincing evidence.”

💭 The 2nd part:

  • Remembering 911 – The Pentagon Attack History
  • September 11—or Meskerem 1—is Ethiopian New Year’s Day

💭 Pentagon Mulls Using Elon Musk’s Rockets to Deploy Troops From Space

The U.S. Department of Defense (DoD) has been in discussions with Elon Musk’s SpaceX to potentially use rockets to rapidly deploy military personnel and cargo across the planet, documents reportedly show.

👉 Continue reading…

______________

Posted in Ethiopia, News/ዜና, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

በዶክተሮች ሊፈታ የማይችለው ወረርሽኝ በጻድቁ ማእጠንት ይታጠናል | የማእጠንት ፀሎት በአሜሪካ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 23, 2020

የደብረ ከርቤ ቅድስት ማርያም ወአቡነ ሃብተማርያም የማእጠንት ፀሎት በተወሰኑ የቨርጂንያ መንደሮችና ጎዳናዎች

[የዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ ፰፤]

ሰባተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ እኵል ሰዓት የሚያህል ዝምታ በሰማይ ሆነ

በእግዚአብሔርም ፊት የሚቆሙትን ሰባቱን መላእክት አየሁ፥ ሰባትም መለከት ተሰጣቸው

ሌላም መልአክ መጣና የወርቅ ጥና ይዞ በመሰዊያው አጠገብ ቆመ፤ በዙፋኑም ፊት ባለው በወርቅ መሰዊያ ላይ ለቅዱሳን ሁሉ ጸሎት እንዲጨምረው ብዙ ዕጣን ተሰጠው

የዕጣኑም ጢስ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር ከመልአኩ እጅ በእግዚአብሔር ፊት ወጣ

ሌላ የሚገርመው ነገር፤ ልክ እዚህ አካባቢ ነበር ባለፈው ጊዜ የሚከተለው የተከሰተው፦

_______________________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Health | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ይኸው ሰዓቱ ደርሶ አሜሪካ በአቡነ ሃብተማርያም ማዕጠንት እየታጠነች ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 23, 2020

[የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፳፥፲፮]

እንዲሁ ኋለኞች ፊተኞች፥ ፊተኞችም ኋለኞች ይሆናሉ፤ የተጠሩ ብዙዎች፥ የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸውና።

ይህን ሳይ የሚሰማኝ፤ “እግዚአብሔር እኛ ኢትዮጵያውያንን በመላው ዓለም በስደትም ሆነ በሌላ አጋጣሚ ከአገራችን አውጥቶ የሚልከን በርገር እየበላን በከንቱ እንድናውደለድል ሳይሆን እንደዚህ እጣኑን እያጨስን መንፈሳዊ ውጊያውን እንድንመራለት፣ ከጠፉት ጋር አብረን እንድንጠፋ ሳይሆን፣ ሁሉም እንዲድን መድኃኒቱን እንድናሳይ ነው።” የሚለው ነው። በእውነት ነው የምለው፤ እኛ ኢትዮጵያውያን በከንቱ ሌላውን ለመምሰል ብንታገልም ምናልባት 90% መንፈሳውያን ሰዎች ነን።

እንግዲህ ያውልሽ አሜሪካ፤ ግብጻውያን አውሮፕላን አብርረው ከሰማይጠቀስ ፎቆችሽ ጋር በማላተም ሦስት ሺህ ዜጎችሽን ገደሉብሽ፣ ፕሬዝደንትሽ ለጉብኝት ወደ ግብጽ ሲመጡ በንቀት ጫማቸውን ወረወሩባቸውዛሬ የከዳሻቸው ኢትዮጵያውያን የተዋሕዶ ልጆች ግን መቅሰፍቱ ሁሉ ከምድርሽ እንዲርቅ ክቡር እጣኑን ከደመናው ጋር አዋሐዱልሽ። ይህን ውለታ አትርሺ፤ አሜሪካ!

የፃድቁ አባታችን አቡነ ሃብተማርያም ቃል ኪዳናቸው ይጠብቀን የመጣውን መቅሰፍት ከአገራቸን ኢትዬጵያና ከመላው ዓለም ይሰውርልን!

መምህር ዘመድኩን እንዳካፈለን፦

መፍትሄው እግዚአብሔር ብቻ ነው።

ጭንቅ ውስጥ በገባችው አሜሪካ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በየአደባባዩ፣ በየመንደሩ፣ እየዞረች የጻድቁ አቡነ ሀብተ ማርያምን ዕጣን እንድታጥን ተጠይቃ ይኸው ቃሏን አክብራ በጻድቁ አቡነ ኃብተ ማርያም ጸሎት ምድሪቱን እያጠነች ነው።

ዛሬ መጋቢት ፲፫ / ፲፪ /13/2012 .(Mar.22/2020)

በአሜሪካን ሀገር በሀገሩ ሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 5:00 PM ላይ በኸረንደን ቨርጂንያ 2472 Centreville Rd.Herndon, VA 20171 የደብረ ከርቤ ቅድስት ማርያም ወአቡነ ሀብተማርያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ካህናቱ የጻድቁ የአቡነ ሀብተ ማርያም ሥዕላቸው ተይዞ

በኸረንደን፣

በረስተን፣

በቻንትሊን፣

በእስትርሊንግና በሌሎችም ከተሞች የሚገኙ አደባባዮችና አውራ ጎዳናዎች በማጠን ላይ ይገኛሉ።

ለዚሁ የአሜሪካን ከተሞችና መንደሮች የማዕጠንት አገልግሎት

መልአከ ሰላም ቀሲስ ሰሎሞን

መጋቤ ካህናት መ/ር ቀሲስ ዮናስ ፍቅረ

ሊቀ ስዩማን መ/ር ቀሲስ ኢዮብ ደመቀ

ሊቀ ልሳናት መ/ር ቀሲስ ጌቱ ተገኑ

ሊቀ ማዕምራን መ/ር ዮሐንስ ለማ

ሊቀ ትጉሀን ዲ/ን አብርሐም ቶማስ

ሊቀ ዲያቆን ገረመው ተዘጋጅተው አገልግሎቱን ጀምረዋል።

አሜሪካ ደንግጣለች። ቤተ ጸሎቶች በሙሉ ተዘግተዋል። የመኪና መንገድ አውራ ጎዳናዎች ሁሉ ጭር ብለዋል። ነገር ግን በእኒህ ሞት ባጠላባቸው የአሜሪካ ጎዳናዎች ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናት አባቶቻችን ጸሎት እንዲያደርጉ የአሜሪካ መንግሥት ፈቅዶላቸዋል። በእውነት ከዚህ ውጪ ሌላ አማራጭ የለም። ይሄ ምልክት ነው። ወደድንም ጠላንም መጪው ዘመን የኦርቶዶክስ ነው። ኦርቶዶክሳዊነት የዓለሙ ሁሉ ሃይማኖት ይሆናል። ሰዎች ሁሉ ወደ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ እምነት ይተምማሉ። የኢትዮጵያ ሃይማኖት የዓለም ሃይማኖት ይሆናል የሚባለው የአበው የትንቢት ቃል በቅርቡ ፍጻሜውን ያገኛል።

ከኢትዮጵያ ውጪ ብቸኛው የጻድቁ አቡነ ሃብተ ማርያም ታቦት የሚገኘውም እዚሁ ቦታ ነው። በቦታውም ብዙ ህሙማን እየተፈወሱ መካኖች መወልዳቸው ብዙዎችን ሲያስደንቅ መኖሩም ተነግሯል። በእውነት መንክር እግዚአብሔር በላዕለ ቅዱሳኒሁእግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው፤ የእስራኤል አምላክ እርሱ ኃይልን ብርታትንም ለሕዝቡ ይሰጣል “(መዝሙረ ዳዊት 68:35)

በጻድቁ ዜና ገድል (ገድለ አቡነ ሀብተማርያም ገጽ.117) ላይ ተጽፎና ተመዝግቦ እንደምናገኘው ልዑል እግዚአብሔር ለጻድቁ በሰጣቸው ቃል ኪዳን መሰረት ስማቸው፣ በተጠራበት፣ ማዕጠንታቸው በታጠነበት፣ ዜና ገድላቸው በተነበበትና ባለበት፣ ጠበላቸው በተረጨበት ሥፍራ ፭ቱ መቅሰፍታት ማለትም :-

፩ኛ.መብረቅ

፪ኛ.ቸነፈር

፫ኛ.የረኀብ ጦር

፬ኛ.ወረርሽኝና

፭ኛ.ሰደድ እሳትና የመሳሰሉት ቦታ የላቸውም። ዜና ገድላቸው እንደሚነግረን በአንድ ወቅት ቅዱስ አባታችን ጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ልጆቻቸው በእነዚህ ፭ቱ መቅሰፍታት እንዳይጠቁና እንዳይጎዱ ጻድቁ አቡነ ሀብተማርያምን በቃል ኪዳናቸው ልጆቻቸውን እንዲጠብቁላቸው ሲማጸኑዋቸው የጻድቁ የአቡነ ሀብተማርያም መልስ የነበረው “ወዳጄ ተክለሃይማኖት ሆይ፤ በእኔ ስም ልጆችህና ወዳጆችህ በቃል ኪዳኔ የሚድኑ ከሆነ ይሁን ብለው ቃል እንደገቡላቸው ተመዝግቧል። ይህ ቃል ኪዳን ደግሞ ዘመን ተሻጋሪና ጊዜ የማይሽረው ነው። በእውነት ያለ ሀሰት። እንጠቀምበት።

በኢትዮጵያም በትናንትናው ዕለት የቃሌ አቡነ ሃብተማርያም ገዳም ካህናት አዲስ አበባ ቃሌ አከባቢ ሲያጥኑ መዋላቸው ተዘግቧል። ትናንት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የዐድዋውን ዘማች ታቦተ ጊዮርጊስን ይዛ ማዕጠንቱን ብታካሂድ ወረርሽኙ ድራሹ ይጠፋል በማለት ያሳሰብኩትም ማሳሰቢያዬም መልስ አግኝቷል። የአራዳ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን መጋቢት 20 ታቦቱን ይዘው ሊወጡ ነው። የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከትም መጋቢት 13 በአዲስ አበባም የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራትም በጋራ ከንጋቱ 12 ሰዓት ላይ አዲስ አበባን እንዲያጥኑ መመሪያ ተላልፏል።

በጣልያን ሊቀጳጳሱን ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስን አናግሬያለሁ። የጣልያን መንግሥት ፈቃድ ለመስጠት ፈቃደኛ ከሆነ እኛ ዝግጁ ነን ብለዋል። የጀርመኑን ሊቀጳጳስ ብፁዕ ዲዮናስዮስንም እንዲሁ አግኝቼ አውርተናል። ፈቃዱ ከመንግሥት ካለ እኛ ዝግጁ ነን።

____________________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Health | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ኢትዮጵያን አትንኳት | በአሜሪካዋ ቨርጂኒያ ግዛት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታወጀ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 16, 2020

በሃገረ ኢትዮጵያ በተዋሕዶ ዜጎቿ ላይ እየተካሄደ ያለው የጥቃትና የግድያ ዘመቻ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ በአሜሪካ፣ አውሮፓ እና አረብ ሃገራት አበረታችነት እንደሆነ እያየነው ነው። በጅማ፣ ጅጅጋ፣ ሐረርጌ፣ ናዝሬት፣ ከሚሴ፣ ነገሌ፣ ሆሣእና፣ ደምቢዶሎ ወዘተ እየተሠራ ያለው ግፍና በደል በእስማኤላውያኑ አረብ ሙስሊሞች እና በዔሳውያኑ/ኤዶማውያኑ ምዕራባውያን ፕሮቴስታንቶች የሚደገፍ ነው።

በእነዚህ የዲያብሎስ ልጆች ላይ ምንም ዓይነት እርምጃ እንዳንወስድ ተኮላሽተናል፤ ነገር ግን የበቀል አምላክ እግዚአብሔር ዝም አይልም፤ እነዚህ ሃገራት አንድ በአንድ በእሳት እንደሚጠረጉ አብረን እንታዘባለን።

ከዚህ በፊት ይህን ቪዲዮ አቅርበን ነበር

፲፪ / / ፲፪ ቅዱስ ሚካኤል ዕለት በአሜሪካዋ ቪርጂኒያ ግዛት የተከሰተው ተዓምር ነው። በዋሽንግተን ዲ.ሲ እና አካባቢዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በየአብያተክርስቲያናቱ ቅዱስ ሚካኤልን ሲያወድሱና ሲማጸኑ በአቅራቢያቸው በሚገኝ አንድ መንገድ ላይ የተተከለው ግዙፍ የኢሬቻ ዛፍ መኪና ላይ ወድቆ ተጓዦቹ ለአርባ አምስት ደቂቃ ያህል ከመኪናቸው መውጣት አልቻሉም ነበር። እንደሚታወቀው ጂኒ ጃዋር በዚሁ መንገድ በኩል አድርጎ ነበር ቤተዘዳ ወደተባለው መንደር የሚያመራው። ይህ ዛፍ ለጂኒ ጃዋር ተዘጋጅቶለት ይሆን?

በእነዚሁ ቀናት እስክንድር ነጋ ወደ ዋሽንግተን እና ቪርጂኒያ ተጉዞ ነበር። ከዚህ በተጨማሪ ብዙ ኢትዮጵያውያን የድንግል ማርያም መቀነት ቀለማት ያረፉበትን የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ በመያዝ የጂኒ ጃዋርን እባባዊ እንቅስቃሴ ተከታትለውት ነበር። ጂኒ ጃዋር በመጀመሪያ ዋሽንግተን በሚገኝ አንድ የፊልጲናውያን ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ከቄሮ አጋንንት አጋሮቹ ጋር መሰባሰብ አቅዶ ነበር፤ ነገር ግን በኢትዮጵያውያኑ ተጽዕኖ ይህ አልተሳካለትም። ቤተ ሳይዳ የሚገኝ አንድ የጴንጤ መናፍቃን ቸርች ግን በሩን ጂኒው ለመክፈት ፈቃደኛ ስለነበር ወደዚያ አመራ። ተመሳሳይ ላባ ያላቸው ወፎች አንድ ላይ ይበራሉ!

ይህ ሁሉ የሆነው አሜሪካ ዋንኛ የሃገሪቱ ክብረ በዓል የሆነውን “የምስጋና ዕለት” / “Thanksgiving“ ለማክበር በምትዘጋጅበት ዋዜማ ነው። ይህ በዓል የኛዎቹ ጣዖተኞች የሚያከብሩት ዓይነት ኢሬቻ ነው፤ ይህ በዓል በአሜሪካም ሆነ በኢትዮጵያ በጭራሽ መከበር የለበትም። ምክኒያቱም በአሜሪካ ከአውሮፓ የመጡት ነጮች “አሜሪካን ህንዶች” ተብለው የሚታወቁትን ቀደምት የአሜሪካ ነዋሪዎችን በመጨፍጨፍ መሬታቸውን በመውረሳቸው አምላካቸውን የሚያመሰግኑበት በዓል ስለሆነ ነው። በኢትዮጵያም “ኦሮሞ” የተባሉት መጤዎች በተመሳሳይ ሁኔታ ከታንዛኒያ አካባቢ በመፍለስ ሃያ የሚጠጉ ቀደምት የኢትዮጵያን ነገዶችን በመጨፍጨፍ ምድራቸውን በመውረሳቸው ለዋቄዮአላህ “ዋቄኒ” እያሉ ምስጋናቸውን የሚሰጡበት እርኩስ በዓል ስለሆነ ነው። …”

አሁን በዚሁ የቨርጂኒያ ግዛት፡ ሰኞ በጥምቀት ዕለት፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታወጇል። በዚሁ ዕለት፡ ልክ እንደ ደምቢዶሎው “የታጠቁ ሚሊሻዎች/ሽፍቶች የቨርጂኒያ ካፒቶልን ለማጥቃት አቅደዋል ተብሏል።

የቨርጂኒያ ግዛት መሪዎች ስጋት ስላደረባቸው ስለሽፍቶች ማንነት ትክክለኛ ዝርዝር ለመስጠት ፈቃደኛ ባይሆኑም ፣ ነገር ግን ከክልሉ ውጭ የሚመጡና ትጥቅ ለመፍታት ፈቃደኞች ይልሆኑ ቡድኖች የቨርጂኒያ ግዛት መስተዳደር ካፒቶልን በጉልበት ለማጥቃት እንዳቀዱ ተናግረዋል። በሚቀጥለው ሰኞ ትጥቅ የማስፈታት ሕግን ለመደገፍ የሚሰበሰቡትን ቡድኖች በመቃወም ሚሊሻዎቹ / ሽፍቶቹ አመፅ እያቀዱ ናቸው ሲሉ ተደምጠዋል።

በየዋህና ንጹሐኑ በኢትዮጵያ ህፃናት፣ አረጋውያን፣ ሴቶችና ተማሪዎች ላይ በሚያስቆጣ መልክ ግፍና ወንጀል ሲፈጽሙባቸው የኢትዮጵያ አምላክ እግዚአብሔር ለዘላለም ዝምታውን የሚቀጥል ይመስለናል? አይቀጥልም፤ ፈጠነም ዘገይም የእግዚአብሔር ፍርድና ቁጣ በእነዚህ አመጸኞች ላይ ይሆናል።

በደንቢዶሎ የታገቱት እህቶቻችን ጥምቀትን ጫካ ውስጥ ከአውሬ ጋር ነው የሚያሳልፉት? ታዝበናል፡ ከስም ዝርዝሩ ኦሮሞ እንደሌለ ግልጽ ነው፡ ምናልባት ኦሮሞ ያልሆነ እስላም ሊኖር ይችላል ብላችሁ ለምታሰቡ ከመካከላቸው አንድም የታገት እስላም የለም። እስኪ እራሳችንን እንጠይቅ ከእህቶቻችን ጋር አብረው የሚማሩት ኦሮሞዎቹና ሙስሊሞቹ ተማሪ ጓደኞቻቸውትምህርታቸውን ያለእነሱ በሰላም ቀጥለዋል። በአንድ ጤናማ ዓለም ሁሉም ተማሪዎች ወይ ወደ ዩኒቨርሲቲ ከመሄድ ይቆጠቡ ነበር፤ ወይም ለታገቱት ተማሪዎች የድጋፍ ድምጻቸውን ያሰሙ ነበር። ግን ይህ አይሆኑም ምክኒያቱም ኦሮሚያ በሃገረ ኢትዮጵያ የሲዖል ተምሳሊት ለመሆን የበቃ እርኩስ ምድር ነውና።

ላለፉት ሁለት ዓመታት ይህ ሁሉ ግፍ ሲሰራ ቤተክርስቲያንና ምዕመናኗ ምንም አለማድረጋቸውን ያየውና በዚህም የደፋፈረው አውሬው አብዮት አህመድ ሥልጣን ላይ ገና ሁለት ዓመት ሳይሞላው እንደ ፈርዖን እራሱን እንደ አምላክ ማድረግ ጀምሯል(እየታየ ነው)፤ ምናልባት አሁን ለበዓል እኔ አስፈታኋቸው፤ ስለዚህ ስሜን ጥሩ፣ አጨብጭቡልኝ፣ ውደዱኝ፣ ምረጡኝ፣ አንግሡኝሊለን አቅዶ ይሆናል ተማሪዎቹን ያሳገታቸው።

ጦርነቱን በእግዚአብሔር አምላክ ላይ በመስቀሉ ላይ ቀስበቀስም በሰባቱ ምስጢረ ቤተክርስቲያን ላይ መሆኑን እየተከታተልነው ነው። ጥምቀት ከእግዚአብሔር ዳግም የምንወለድበት ምሥጢር ስለሆነ አሁን በጥምቀት ላይ ጦርነት ከፍተዋል። ቀጥሎም በቍርባን እና ተክሊል ላይ ይሆናል።

ለማንኛውም፤ የጥምቀት በዓልን በ666ቱ ተቋም ዩኔስኮ ከመዘገቡ በኋላ ሆን ተብሎ በዓሉ በደቡቡ የኢትዮጵያ ክፍል በነፃነት እንዳይከበር በአሜሪካና አረቢያ ግን እንዲከበር በማድረግ ያው በሃገራቸው አልቻሉም!” እያሉ ይሳለቁብናል። ግን፡ ቀስ በቀስ ሃገራችንን ብቻ ሳይሆን ተዋሕዶ ሃይማኖታችንንም ለመንጠቅ ከፍተኛ ሤራ መጠንሰሱን እያየን ነውን? አገራችንና ሃይማኖታችንን በምስር ወጥ ለመለወጥ ዝግኙና ፈቃደኞች ነንን? እንግዲያውማ እባቡ አብዮት አህመድብልጽግናብሎ መጥቶላችኋል። ከማን ጋር ነን? ከእግዚአብሔር ጋር ወይስ ከቄሳር ጋር?

የሚከተለውን ጽሑፍ ያቀበለን መምህር ዘመድኩን በቀለ ነው

የበዓለ ጥምቀት አከባበር ዝግጅት በኢትዮጵያና በአሜሪካ ልብ ብላችሁ ተመልከቱልኝማ።

ሀ፥ በኢትዮጵያ ፦

በደቡብ ኢትዮጵያ በሆሣዕና ከተማ የጥምቀት በዓል የማክበሪያ ስፍራውን ፕሮቴስታንቱ ወርሰውታል። የገበያ ሥፍራ፣ የቆሻሻ መጣያና የአውቶቡስ መነሃሪያ አድርገው የከተራ ሥፍራውን ከልክለዋል። ምን አባህ ታመጣለህ ተብለናል። የሚመጣውን አብሮ ማየት ነው። የከተማው አስተዳዳር ጴንጤዎቹ የምን ዩኔስኮ ነው፣ የምን ጥምቀት ነው ብለው ለአህያ ማቆሚያ ፓርኪንግ 5 ሺ ካሬ መሬት ፈቅደዋል። ለኦርቶዶክሳውያን ይሄም አይገባችሁም ተብለዋል። ዮናታን አክሊሉ መቶ ሺ ካሬ፣ ፓስተር እስራኤል ዳንሳም እንዲሁ በነፃ ተሰጥቷቸዋል። ኦርቶዶክስ ግን የራሷን ያላትን መሬት ዐይኗ እያየ ነጥቀዋታል።

በዚያው በደቡብ ኢትዮጵያ በመሎለሃ ከተማ የበዓለ ጥመቀቱን ማክበሪያ ሥፍራውን አሁንም የጌታ ልጆች ፕሮቴስታንቱ ባለሥልጣናት ጊዜ ሰጠን ብለው ወታደር አሰማርተው በቀን ብርሃን በአደባባይ መሬቷን ነጥቀው ወርሰዋል። ካህናቱን ደብድበው፣ ምዕማናንን ቀጥቅጠው ከወኅኒ ወርውረዋል። ዚስ ኢዝ ኢትዮጵያ አለ ኢዩ ጩፋ።

በአርሲ ነገሌም በቅርቡ የሆነውንም በዓይናችን አይተናል። መስቀሉን ነቅለው እንዲነሳ ሲያደርጉ አይተናል። አሁን በባሌ ለበዓለ ጥምቀቱ ምንጣፍ ማንጠፍ፣ አዲስ አበባ ጫፍ በሱሉልታ፣ በዝዋይ፣ በናዝሬትና በአጠቃላይ በኦሮሚያ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ መያዝና መስቀል ማውለብለብም ባልተጻፈ ዐዋጅና ባልተነገረ ሕግ በይፋ ተከልክሏል። ሞተን ነው ቆመን ነው እያሉ ነው። ፕሮቴስታንት ኦሮሞ ቄሮዎችና የወሃቢያ እስላም ቄሮዎች።

ቀውሲ በላይና አህመዲን ጀበል በሊቀመንበራቸው በጃዋር ትእዛዝ ኦሮሚያ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ከታየ ሞተን ነው ቆመን እያሉ እየፎከሩ ነው። ኦርቶዶክሳውያኑ ኦሮሞዎችና ዐማራ፣ ትግሬ፣ ደቡብ ሁሉ እስቲ የሚሆነው ጊዜው ይድረስ እያሉ ነው። ሀረር ለጥር ሥላሴ ባንዲራው ሲዘረጋ፣ ሱልታ ልጥር ሥላሴ ከሐረር ተፈናቅለው ሱሉልታ እንዲሰፍሩ የተደረጉ እስላም ቄሮዎች ደብሩን አስፈራርተው ሰንደቅ ዓላማው እንዳይውለበለብ እንዳይሰቀልም አድርገዋል። [ የዘንድሮ ጥመቀት በተለይ በኦሮሚያ ከበድ የሚል ይመስላል። ]

ሁ ፥ በአማሪካ ፦

ይህን ሁሉ ዓይተው፣ በዓለ ጥምቀት በትውልድ ሃገሩ በኢትዮጵያ በገዛ ልጆቹ እንዲህ ፍዳውን ሲያይ አይተው፣ ተመልክተውም ከዚያ ራቅ ባለ ሥፍራ፣ በሰዶምና ገሞራ ምድር፣ በአህዛብ ምድር፣ በኢአማንያን ሀገር ደግሞ ሞተረኛ ተመድቦለት፣ በሰረገላ በሊሞዚን በፈረሰኛ ታጅቦ፣ ዐውራ ጎዳናዎች ተዘግተው፣ የየሀገሩ የየከተማዎቹ ከንቲባዎች በተገኙበት፣ የነጮቹ፣ የዐረቦቹ፣ የሩቅ ምስራቅና የጥቁሮቹ የመገናኛ ብዙሃን በተገኙበት በታልቅ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓትና ድምቀት ሲከበር ስታይ በእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ ትደመማለህ።

ይሄን ማስታወቂያ ሳየው ገረመኝ። በሀገረ አሜሪካ እንዲህ በይፋ በዓለ ጥምቀትን እንዴት ኢትዮጵያውያኑ እንደሚያከብሩትና ከወዲሁ ዕቅድ አውጥተው በይፋ እንዴት እንደሚያውጁ ተመልከተሉኝማ። ቄሮ የለ ቀሬ፣ ወሃቢይ የለ ሰለፊ፣ ነፃነት ብቻ። ሰንደቅ ዓላማው ከፍ፣ ዝማሬው፣ ወዳሴው፣ ሥርዓተ አምልኮውና ሥርዓተ ቅዳሴው ከፍከፍ ይላል።

በዋሽንግተንና አካባቢው በሜሪ ላንድ ( ሀገረ ማርያም) የምትኖሩ ምዕመናን ፏ ብላችሁ፣ እንቁጣጣሽ መስላችሁ፣ ጅንስና ሚኒስከርታችሁን ወዲያ ጥላችሁ፣ በሀገር ባህል ልብሱ፣ በጃኖ፣ በኩታው፣ በእጀጠባቡ ጀነን ኮራ ብላችሁ አማሪካን የትራንፕን ከተማ በአረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ዓላማ፣ በዝማሬው፣ በከበሮ፣ በእልልታ አናውጧት። ማዕጠንቱ ይታጠን፣ መስቀሉ ይወጣ አጋንንቱን ይቀጥቅጥ፣ ይቀደስ፣ ወረቡ፣ ዝማሜው፣ ሽብሸባው ይታይ ይፈጸም።

በኢትዮጵያ ደግሞ በተቃራኒው ነው። በዓለ ጥምቀትን እንዴት እንደምታከብር፣ እንዴት እንደምትዘምር፣ ምን መልበስ፣ ምን መያዝ እንዳለብህ ቄሮ የተባለ የወሃቢያ እስላም ሠራዊት ሊያዝህና ሊያስፈራራህ ይሞክራል። አዲስ አበባ መርካቶ ተክለሃይማኖቶች ገራሚ ዝግጅት እያደረጉ ነው። አንዳንድ አድባራትም እንዲሁ። የተከልሃይማኖት ልጆች የሚሠሩትን ለማስቆም የወሃቢይ እስላሞቹ ሆያ ሆዬ ቢዘፍኑም የተክልዬ ልጆች ግን መስሚያችን ጥጥ ነው ብለው ዝግጅታቸውን ቀጥለዋል። አብነት አደባባዩ በሰንደቅ ዓላማው አሸብርቋል። ደምቋልም።

______________________________

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የግዮን ሆቴል መደርመሱን ስሰማ ወዲያው የታየኝ የኢሬቻ ጋኔን ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 4, 2019

ይህ ጋኔን ከመስቀል አደባባይ እስከ ቪርጂኒያ እና ሜነሶታ ድረስ ተበትኖ ይታያል። ባለፈው ሳምንት ላይ በቨርጂኒያ ግዛት የኢሬቻ ዛፍ መደርመሱን እናስታውሳለን።

ፀረኢትዮጵያ የክርስቶስ ተቃዋሚው ኢሬቻ በዓል በመስቀል አደባባይ፣ በቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን እና በግዮን(አባይ)ሆቴል ዙሪያ በምትገኘው ትንሽ ወንዝ ነበር የመቅሰፍት ችግኝ ተከላውን የጀመረው። ለበዓሉ ሲባል ወንዙ ዙሪያውን ተከልሎ ነበር።

ታዲያ አሁን ቪዲዮው ላይ የሚታየው የግዮን ሆቴል አዳራሽ መደርመሱ ሊገርመን ይችላልን፤ እነዚህ ከሃዲ የሰይጣን ልጆች አገርንስ እየደረመሷት አይደለምን?

የፕሬዚደንት ትራምፕ ልጅ ባል ያሬድ ኩሽነር አዲስ አበባ ገብቷል። ሸለመጥማጣው ሰውዬ በግዮን/ አባይ ጉዳይ ግብጽን ወክሎ እንደሚከራከር አያጠራጥርም።

ባለፈው ዓመት ሚስቱ ኢትዮጵያን ስትጎበኝ ይህን ጽፌ ነበር፦ “በዓለማችን ላይ ከሚታዩት የክርስቶስ ተቃዋሚ ግለሰቦች መካከል ይመደባል ብዬ የማምነው ሰው የኢቫንካ ትራምፕ ባለቤት ያሬድ ኩሽነር ነው። የሚገርም ነው፡ የዚህ ቀፋፊ ሰው ቢሮ የሚገኘው በ ኒው ዮርክ ከተማ “666 Fifth Avenue/ 5ኛው ጎዳናላይ ነው።”

ከሁለት ሳምንታት በፊት ደግሞ የኒው ዮርኩን ግድያ በማስመልከት ይህን ጽሁፍ አቅርቤ ነበር፦

በጣም ይረብሻል፡ ያሳዝናል! ክፉ ግዜ ነው! የሕፃኗ አሟማት እጅግ በጣም ይሰቀጥጣል። ኤይይይ..… አገዳደሉ ኦሮሚያ በተባለው የተረገመ ክልል ሰሞኑን ከተፈጸሙት ጭካኔ የተሞላባቸው ድርጊቶች ጋር በጣም ይመሳሰላል።

ወደ ኒው ዮርክ እርኩስ መንፈስ እየገባ እንደሆነ በእነዚህ ቪዲዮውች በኩል ባለፉት ቀናት ለመጠቆም ሞከሬ ነበር። ፕሬዚደንት ትራምፕ በተወለዱባት ከተማ ይህ አሰቃቂ ድርጊት ተፈጸመ። አሁን በዋሽንግተን የሚኖሩት ፕሬዚደንቱ ኒው ዮርክ ከተማን እንደሚለቁ ሰሞኑን አስታውቀው ነበር። የአቶ ዮናታን ቤተሰብ በሞቱበት ዕለት ፕሬዚደንት ትራምፕ ከገዳይ አብይ መንግስት ልዑካን ጋር በአባይ ጉዳይ ላይ ሲወያዩ ነበር። የአቶ ዮናታን ሲት ልጅ ስም፦ “አባይነሽ”። ኤይይይ!

ግዮን – አባይ – አብይ

ብልጽግና + የግብጽ ቀለማት

ብልጽግና = ግብጽ = ብልግና

በአዲስ አበባ የተሰቀሉትን የግብጽ/ኦሮሞ ባንዲራዎች የማቃጠያው ጊዜ አሁን ነው !!!

[መጽሐፈ መክብብ ምዕራፍ ፫፥፩፡፰]

ለሁሉም ነገር ጊዜ አለው፤ ከሰማይ በታች ለሚከናወነው ለማንኛውም ነገር ወቅት አለው፤ ለመወለድ ጊዜ አለው፤ ለመሞትም ጊዜ አለው፤ ለመትከል ጊዜ አለው፤ ለመንቀልም ጊዜ አለው፤ ለመግደል ጊዜ አለው፤ ለማዳንም ጊዜ አለው፤ ለማፍረስ ጊዜ አለው፤ ለመገንባትም ጊዜ አለው፤ ለማልቀስ ጊዜ አለው፤ ለመሣቅም ጊዜ አለው፤ ለሐዘን ጊዜ አለው፤ ለጭፈራም ጊዜ አለው፤ ድንጋይ ለመጣል ጊዜ አለው፤ ድንጋይ ለመሰብሰብም ጊዜ አለው፤ ለመተቃቀፍ ጊዜ አለው፤ ለመለያየትም ጊዜ አለው፤ ለመፈለግ ጊዜ አለው፤ ለመተው ጊዜ አለው፤ ለማስቀመጥ ጊዜ አለው፤ አውጥቶ ለመጣልም ጊዜ አለው፤ ለመቅደድ ጊዜ አለው፤ ለመስፋትም ጊዜ አለው፤ ለዝምታ ጊዜ አለው፤ ለመናገርም ጊዜ አለው፤ ለመውደድ ጊዜ አለው፤ ለመጥላትም ጊዜ አለው፤ ለጦርነት ጊዜ አለው፤ ለሰላምም ጊዜ አለው።

________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , | 1 Comment »

ተዓምር በአሜሪካ | ኃይለኛ የእሳት ቃጠሎ በደረሰበት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ መጽሐፍ ቅዱሶች እና መስቀሎች ብቻ ተርፈዋል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 5, 2019

ከትናንትና ወዲያ እሑድ ምዕራብ ቨርጅኒያ በሚገኘው አንድ የ ቤተ ክርስቲያን ሕንፃ ላይ መንስዔው ባልታወቀ ኃይለኛ እሳት ሁሉም ነገር አመድ ሆኖ ሲወድም በውስጡ የነበሩት መስቀሎች እና ብዙ መጽሐፍ ቅዱሶች ምንም ሳይሆኑ ተርፈዋል።

እኩለ ሌሊት ላይ የተቀሰቀሰው እሳ ቤተ ክርስቲያኑን ሙሉ በሙሉ ለማውደም ተቃርቦ ነበር በቦታው ተገኘተው የነበሩት የእሳት አደጋ መከላከያ ሰራተኞች በማግሥቱ ጠዋት ላይ የፈራረሰው ሕንጻ ውስጥ ሲገቡ ተዓምር የሆነ ነገር ገጠማቸው፤ ከመስቀሎቹና መጽሐፍ ቅዱሶቹ መካከል አንዱም አልተቃጠለም፤ በዚህም ዓይናቸውን ማመን ነበር ያቃታቸው፤ ምክኒያቱም የእሳቱ ኃይለኛነት ምንም ነገር የማያተርፍ ነበርና፤ የእሳት ቃጠሎ በጣም ኃይለኛ ከመሆኑ የተነሳ ከቅርብ ሆነው ለመዋጋት እንዳልተቻላቸውና ባንድ ወቅት ከህንጻው ወደ ኋላ መመለስ እንደነበረባቸው ገልጸዋል።

_________

Posted in Curiosity, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: