ገና ያልተወራልትና ያልተሰማ ብዙ ጉድ እንደሚኖር አንጠራጠረ። ሰዉ በአገሩ እዴት ይህን ያህል ይሰቃያል? እስክ መቼ ነው ኢትዮጵያ የዲያብሎስ መፈንጫ የምትሆነው? ይሄን እርኩስ መንፈስንና መጥፎ ዕድልን ይዞ የመጣውን የወሮበሎች ስብስብ መንግስት በእሳት ሊጠርግ የሚችል አንድ ቆፍጣና አርበኛ እንኳ ይጥፋ? ቤተክሕነትስ ባለፈው ሳምትን መግለጫዋ ላይ ወጣት ሴት ምዕመናኗ እንዲህ እልም ብለው ሲጠፉ ጉዳዩን አስመልክቶ አንድም ቃል ትንፍሽ ያላሉበት ምክኒያት ምንድን ነው? የኢትዮጵያን ስም ለማጠለሸትና ኢትዮጵያውያን በጭካኔ ከአረቦች እንደማይተናነሱ ለማሳየት ሲባል በተዘጋጀው በዚህ ዲያብሎሳዊ አጀንዳ ላይ እንዴት ሁሉም አካል ተባባሪ ሊሆን ቻለ? እንደው ይህ ለቲዲ አፍሮ ኮንሰርት የሚወጣበት ወቅት ነውን? በሃገራችን እየተካሄደ ያለው ነገር ሁሉ እጅግ በጣም አሳዛኝና ደም የሚያፈላ ነው! ይህች እግዚአብሔር የሚያውቃት፣ እኛም የምናውቃት ኢትዮጵያ አይደለችምና እርስታችን ኢትዮጵያን በፍጥነት ከአውሬው መንጋጋ አውጥተን ልናስመልሳት ግድ ነው። እግዚአብሔር ይርዳን!