ሰሞኑን አባ ዘ–ወንጌልን በተመለከተ አንዳንድ ሕልሞች ይታዮኝ ነበር። ሕልሞቹን ለማስታወስ እየታገልኩ ነው። አባታችን የጠቆሙን ነገሮች ሁሉ አንድ በአንድ በመፈጸም ላይ ናቸው።
አባታችን አባ ዘ–ወንጌል በአንድ ወቅት እንዲህ ብለውን ነበር፦
“ኢትዮጵያን በዚህ ወቅት እያስተዳደሯት ያሉት ጠላቶቿ ናቸው!”
አዎ! አውሬው ጦርነቱን አስቀድሞ በማካሄድ ላይ ያለው የቤተ ክርስቲያን በር በሆኑት በሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ላይ ነው፦
፩. ምሥጢረ ጥምቀት
፪. ምሥጢረ ሜሮን
፫. ምሥጢረ ቁርባን
፬. ምሥጢረ ክህነት
፭. ምሥጢረ ተክሊል
፮. ምሥጢረ ንስሐ
፯. ምሥጢረ ቀንዲል
መጀመሪያ በቁርባን(ሕብስትና ወይን / ስጋውና ደሙ) ፣ ቀጥሎም በጥምቀት ላይ ነው የዘመቱት። በኢትዮጵያ የእንጀራና ዳቦ መጋገር ባሕል ባልተለመደ መልክ የአሕዛብ ዳቦ ቤቶች በብዛት እየተከፍቱና በየትምህርት ቤቱ ለሕፃናቱ ዳቦና ማርማላታ እያጎረሷቸው መሆናቸውን እንዲሁም ዓብያተ ክርስቲያናት ባሕረ ጥምቀትን በመነጠቅ ላይ መሆናቸውን በግልጽ እያየነው ነው። የሰው ልጅ ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ እንደማይችል ምቀኛው ጠላታችን ዲያብሎስ አጠንቅቆ ያውቃልና።