እንዲህ የመሰለ ነገር አያለሁ ብዬ አስቤም አልሜውም አላውቅ፤ በጣም የሚያስገርም፣ ለማመን የሚያስቸግር ዘመን ላይ ነን። በእውነት ለታዛቢዎች ድንቅ የሆነ ዘመን ነው።
አብዛኞቹ ጀርመናውያን (85%) እና – ከሉሲፈራውያኑ መሀመዳውያና ግራኝ ደጋፊዎቻቸው በቀር – መላው ዓለም የሚጠላት አንጌላ ኤልዛቤል ሜርከል፡ ከሥልጣን አልወርድም ብላ ዙፋኗን ሙጭጭ አድርጋ ይዛለች – የሚገርም እኮ ነው – ሙጋቤ እንኳን ወርዷል።
ጀርመን ተከፋፍላ በነበረችበት ዘመን፤ (ከ 1989 ዓ.ም በፊት) የምሥራቅ ጀርመን ኮሙኒስት ፓርቲ አባል የነበረችው አንጌላ ሜርከል እ.አ.አ በ 2005 ዓ.ም ፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ለቻንስለርነት ስትመረጥ – በወቅቱ እዚያ ነበርኩ – ምን እንደሆነ አላውቅም ሂትለር ሆና ነበር የታየችኝ። ለጓደኞቼ ሳወሳላቸው ይስቁ እንደነበርም በደንብ አስታውሳለሁ።
ጀርመን ዋና ከተማዋን እ.አ.አ በ1991 ዓ.ም ከቦን ወደ በርሊን ለማዘዋወር ተሰጥቶ የነበረውን ውሳኔ ከተቃወሙት መካከል አንዱ እኔ ነበርኩ።
በርሊን የፀረ–ክርስቶሱ መቀመጫ ከሆኑት ከተሞች መካከል አንዷ ነች። ራዕይ ዮሐንስ ላይ ከተጠቀሱት ሰባት ዓብያተ ክርስቲያናት (ሁሉም ያሁኗ ቱርክ ውስጥ ነው የሚገኙት) መካከል አንዷ፤ ፐርጋሞን ናት፤ ይህችም የሰይጣን ዙፋን የሚገኝባት ቦታ እንደሆነች ቅዱስ ዮሐንስ ጠቁሞናል።
ታዲያ ከ ፐርጋሞን የተወሰደው የሰይጣን ኃውልት አሁን የሚገኘው በበርሊን ከተማ ነው። እነ ሂትለር፣ ቡሽ፣ ኦባማና ሂላሪ ክሊንተን ሁሉም ይህን ኃውልት ለመሳለም ወደ በርሊን ጎራ ብለው ነበር። ለሂላሪ ብቻ ነው ሥልጣኑ ያልተሳካው፣ በዚህም ያው እስካሁን ጋኔናዊ ለቅሶዋን ምርር ብላ ታለቅሳለች፤ ጋኔን መሸነፍ አይወድምና። ወይዘሮ አንጌላ ሜርከልም ከዚሁ ኃውልት ፊት ለፊት ነው የምትኖረው፤ ለዚህም ይመስላል ይህ ሁሉ ጉድ ተከላካይ በሌላቸው ጀርመናውያን ህፃናትና ሴቶች ላይ ተፈጽሞና ሁሉም ውረጅ እያላት ከሥልጣን ለመውረድ እስካሁን ፈቃደኝነት ያላሳየቸው።