Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘ቢሸፍቱ’

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዚህ መልክ ነው ተከስክሶ ሊሆን የሚችለው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 11, 2019

በጣም ያሳዝናል፤ በሰንበት ዕለት እረፍት ነሳን። ኢትዮጵያ ውስጥ ይህን የመሰለ አስከፊ አደጋ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ ሲደረስ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው – በሰባ ዓመስት ዓመት ታሪኩ። ረዳት ፓይለቱ አህመድ ይባላል፤ ዘመነ አህመድ እርግማን እና መጥፎ ዕድል በአገራችን ላይ እያመጣ ነው፤ ይህን በአጭር ጊዜ ውስጥ እያየን ነው።

____________

Posted in Ethiopia, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የሚገርም ነው | የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሊከሰከስ ሰዓታት ሲቀሩት እኅተ ማርያም ይህን አስደናቂ ታሪኳን አጫውታን ነበር

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 11, 2019

እስከ መጨረሻው እንከታተላትና ከዛሬው አሳዛኝ አደጋ ጋር በማገናኘት ነገሮችን እንገምግም። በ እኔ በኩል በትይዩነት የታየኝ አንድ ትልቅ መንፈሳዊ የሆነ ክስተት አለ፤ በሚቀጥለው ቪዲዮ አቀርበዋለሁ።

____________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

በተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ውስጥ የነበሩት መንገደኞች ዜግነት ዝርዝር | ነፍስ ይማር

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 10, 2019

የተዘመነ ዝርዝር

  • + 32 ኬኒያውያን

  • + 18 ካናዳውያን

  • + 9 ኢትዮጵያውያን

  • + 8 ቻይናውያን

  • + 8 ጣልያኖች

  • + 8 አሜሪካውያን

  • + 7 ብሪታኒያውያን

  • + 7 ፈረንሳውያን

  • + 6 ግብጻውያን

  • + 5 ጀርመናውያን

  • + 4 የተባበሩት መንግሥታት ፓስፖርት ያላቸው

  • + 4 ህንዳውያን

  • + 4 ስሎቫካውያን (የብሔራዊ ፓርቲው ምክትል ሚስትና ሁለት ልጆች)

  • + 3 ሩሲያውያን

  • + 3 ስዊድናውያን

  • + 2 ሞሮኳውያን

  • + 2 ስፔንያውያን

  • + 2 ፖላንዳውያን

  • + 2 እስራኤላውያን

  • + 2 ያልታወቁ

  • + 1 ቤልጂማዊ

  • + 1 ኡጋንዳዊ

  • + 1 ሩዋንዳዊ

  • + 1 የመናዊ

  • + 1 ሰርብያዊ

  • + 1 ኖርዊያዊ

  • + 1 ሱዳናዊ

  • + 1 ሶማሊያዊ (የሶማሌ ጠቅላይ ሚንስትር ረዳት)

  • + 1 ጂቡቲያዊ

  • + 1 ሳውዲያዊ

  • + 1 ቶጓዊ

  • + 1 ሞዛምቢካዊ

  • + 1 አየርላንዳዊ

  • + 1 ናይጀሪያዊ

  • + 1 ኔፓላዊ

  • + 1 ኢንዶኔዢያዊ

  • + 1 ሞዛምቢካዊ

  • + 1 ኖርዌያዊ

ነፍሳቸውን ይማርላቸው!

በሌላ በኩል በጣም የሚገርመው፤ ማን ወደ አገራችን/ አፍሪቃ እይገባ እንደሆነ የሚያሳየውን ይህን መረጃ ማየታችን ነው! 35 ሃገራት ዜጎች፤ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያም የሚታይ ክስተት ነው፤ ይገርማል።

____________

Posted in Ethiopia, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , | 1 Comment »

የክርስቶስን “ደብረዘይት” “ቢሸፍቱ” በሚል መጠሪያ የለወጡት ጣዖት-አምላኪዎች ለዲያብሎስ አምላካቸው መስዋዕት አበርክተዋል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 3, 2016

ደብረ ዘይት = ደብረ ዘይት በሚል ርዕስ ከሦስት ዓመት በፊት ያቀረብኩት ይህ ጽሑፍ፡ በቀድሞዋ ደብረዘይት በሰንበት እለት ለተከሰተው አሳዛኝ እልቂት ትንቢታዊነት ነበረው ማለት ነው

Re-posted from April 6, 2013

debrezeytከሦስት ዓመታት በፊት ከአራት ሰዎች ጋር ሆኜ ከ አዲስ አበባ ወደ ደብረ ዘይት ከተማ በመጓዝ ላይ ነበርኩ። ቃሊቲን አለፍ እንዳልን፡ መኪናዋን ቤንዚንና ዘይት ሞላናት። እግረ መንገዳችንንም ብርቱካን እንዲሁም አብረውን ለነበሩት አክስታችን ቅቤ ገዝተን ጉዟችንን ቀጠልን። በመኻልም እኔና አክስታችን ብርቱካን እየላጠን ለሾፌሩና ለወንድማችን ማካፈል ጀመርን። አክስታችን ለሾፌሩ፡ ይህችን ብርቱካን እንካ ላጉርስህ” ሲሉ፡ ሾፌራችንም ” ኧረኧረየርስዎ እጅ ቅቤ ነክቷል፡ ባይሆን የእርሱ ቤንዚንና ዘይት ቢነካውም ቅቤ ከነካው የቤንዚኑ ይሻለኛል፡ እርሱ ያጕርሰኝ!” ብሎ፡ አሳቀን፤ አስገረመን።

መጠሪያ ስሞቻችን፣ የክርስትና ስሞቻችን ወይም ክርስቲያናዊ የሆኑ የቦታ ስሞችን የሚሰጠው መንፈስ ቅዱስ ነው። የእግዚአብሔር አምላክን ገናናነት ለማሳወቅ፡ ለእርሱ ክብር ለመስጠት የምንሰይማቸው ቦታዎች ወይም ከተሞች በርሱ ዘንድ ከፍተኛ ትርጕም አላቸው፤ ለኛም ሰላምን፣ ጽድቅንና በረከትን ያመጡልናል። ሶማሊያዎች እስከ ናዝሬት ከተማ ድረስ ያለው ግዛት የኛ ነው በማለት በህልማቸው የነደፉትን ካርታ ጥገኝነቱን ለሰጣቸው እንግዳ ተቀባይ የአዲስ አበባ ነዋሪ በድፍረት/በንቀት ያሳያሉ። ይህን በቅርብ ሆኜ ለመታዘብ በቅቻለሁ። ለመሆኑ በፊት ጂጂጋ ደርሰው ናዝሬት” ዘው ለማለት ያቃታቸው ለምን ይመስለናል? “ናዝሬት” “እየሩሳሌም፡ የእነዚህ ቦታዎች መጠሪያ ሁልጊዜ የጦርነት ወኔያቸውን ይቀሰቅሰዋል፡ ለምንመልሱን ሁላችንም እናውቀዋለን።

ታዲያ ሁለት ሺህ ዓመታት በሞሉት የክርስትና ታሪካችን፡ ብዛት ያላቸው ምሳሌዎችን ለማየት እየበቃን፡ እንደ ደብረ ዘይት” የመሳሰሉትን የቦታ መጠሪያዎች በዘፈቃድ ለመለወጥ የሚሹ ግለሰቦች በምን ተዓምር አሁን ሊመጡብን ቻሉ? ከተራራው በረሃውን፥ ከቅቤው ቤንዚኑን፥ ከደብረ ዘይት የመኪና ዘይትን የሚመርጥ ትውልድ፡ የመቅሰፍት ምንጭ አይሆንብንምንመቼም ለክርስቶስ ጥላቻ ያላቸው፣ ጸረክርስቶስ የሉሲፈር ፈቃደኛ ወኪሎች ካልሆኑ በቀር እዚህ ድረስ ሊያደርሳቸው የሚችል ሌላ ነገር ሊኖር ይችላልንአይመስለኝምይህ እንደ ቀላል ነገር ተደርጎ መታየት ያለበት ጉዳይ አይደለም፡ ምክኒያቱም በግለሰቦቹ ላይ ሊመጣባቸው የሚችለው ፍርድ ልክ መንፈስ ቅዱስን የሚያስቀይሙት ግለሰቦች ከሚመጣባቸው ኃይለኛ ፍርድ የሚለይ አይሆንምና፤ የመንፈስ ቅዱስን ክብር ደፍረዋልና!

ደብረ ዘይት

ደብረ ዘይት በግእዝ ልሣን ደብረዘይት ማለት የወይራ ተራራ ማለት ነው። ቦታው ከኢየሩሳሌም በስተምስራቅ የሚገኝ የወይራ ዛፍ የበዛበት ተራራ ሲሆን ስሙም ከወይራ ዛፉ:-ደብረ ዘይት (የወይራ ዛፍ ተራራበመሰኘት ተገኝቷል። በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ደብረ ዘይት በዓል ሆኖ የሚከበርበት ምክንያት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረዘይት ተራራ ላይ ሳለ ለቅዱሳን ደቀመዛሙርቱ ስለ ዓለም ፍጻሜ እና ስለ ዳግም ምጽአቱ ስላስተማራቸዉ በጌታችን ትምህርት መሰረት ነገረ ምጽአቱን (የመምጣቱን ነገርእንድናስታዉስ ወይም እያሰብን እንድንዘጋጅ ለማድረግ ነዉ።

በዚያ ልማድ መሠረት ጌታችን ዓለምን ለማሳለፍ ደግሞ የሚመጣበትን ምልክትና ጠቋሚ ነገር ምን ምን እንደሆነ፣ እርሱ ከመምጣቱ በፊት በዓለም ላይ ምን፥ ምን እንደሚደረግና ምን እንደሚታይ ለደቀመዛሙርቱ የነገራቸው በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ተቀምጦ ነው። (ማቴ. 241-51) ስለ ዓለም ሁሉ ቤዛ ለመሆን በሚሰቀልበት ቀን ዋዜማ ማለት በትልቁ ሐሙስ (ጸሎተ ሐሙስበለበሰው ሥጋ የጸለየው ከደብረ ዘይት ጋር ተያይዞ በሚገኘው ቦታ በጌተሴማኒ ነበር። (ማቴ. 2636) በኃላ ከሙታን ተለይቶ ከተነሣ በኋላም ለደቀመዛሙርቱ እንዲነግሩ ሲልካቸው፥ “ሂዱና ወደ ገሊላ ይቀድማችኋል፥ በዚያም ታዩኛላችሁ ብላችሁ ንገሩአቸው፥” ብሎ የላካቸው በደብረ ዘይት ገሊላ ተብላ ትጠራ ወደ ነበረችው ቦታ ነው። (ማቴ. 289) ገሊላውያን ወደ ኤየሩሳሌም ሲመጡ በደብረ ዘይት ያርፍ ነበርና እነሱ ሲያርፉባት የነበረችው ቦታ ገሊላ እየተባለች ትጠራ ነበር። መድኃኔዓለም ክርስቶስ የድኅነት ሥራ ፈጽሞ ወደ ሰማይ ያረገው ከዚህ ተራራ ተነሥቶ ነው። (ሐዋ. 112) ቀደም ብሎም የሆሳእናው የመድኃኔዓለም አስደናቂ ጉዞ የተጀመረው ከደብረ ዘይት ሥር ነበር። (ማቴ. 211-16)

ወስብሓት ለእግዚአብሔር

__

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: