ባለፈው ሳምንት፡ የካቶሊኮች ፋሲካ ዕለት፡ በተለያዩ የስሪ ላንካ ከተሞች እስከ ሦስት መቶ የሚጠጉ ክርስቲያኖችን ሙስሊሞች በመግደላቸው ነው አሁን ስሪ ላንካ ሙሉ የፊት ገጽታን የሚሸፍን ‘ሂጃብ‘ ‘ቡርካ‘ እና ‘ኒቃብ‘ ለማገድ የተገደደችው። ከአጥፍቶ ጠፊዎቹ መካከል ብዙ ሴቶች ይገኙበት እንደነበር ተገልጿል።
ልክ እንደ ኢትዮጵያ አገራችን በስሪ ላንካ ሴቶች እነዚህን አስቀያሚ ልብሶች መልበስ የጀመሩት ከ ሰላሳ ዓመታት በፊት ነበር። በኢራቅና ኩዌት መካከል የመጀመሪያ ገልፍ ጦርነት ሲጀምር ማለት ነው።
በዘመናችን ዓለም አቀፉ የጂሃድ እንቅስቃሴ የጀመረው በዚህ ወቅት ነበር። በአገራችን ግብጽ፣ ኢራቅ እና ሶሪያ የኤርትራን፣ ሱዳንን እና ሶማሊያን ጂሃዲስቶች በመርዳት ኢትዮጵያን ይበታትኑ ዘንድ ሁለተኛው ደረጃ ላይ አደረሷቸው፤ የመጀመሪያው፤ በፈረንሳይ አነሳሽነት ጂቡቲን አስመልክቶ ተካሂዷል፤ አሁን ደግሞ ሶማሌ፣ ኦሮሞ፣ ትግሬ እና አማራ ነን የሚሉትን ወገኖቻችን (Useful Idiots/ጠቃሚ ሞኞች) በብሔር እንዲደራጁና ለጦርነት እንዲነሳሱ በመቆስቆስ ኢትዮጵያን ለመጨረሻ ጊዜ እራሳቸው ይበታትንሏቸው ዘንድ እንደ አሻንጉሊት ሲጠቀሙባቸው ይታያሉ።
ግን ለጊዜው ነው፤ እያንዳንዱ ከሃዲ አሁኑኑ ስህተቱን ካላረመ እና ንስሐ ገብቶ ቶሎ ካልተመለስ ገሃነም እሳት ነው የሚጠበቀው! እየታየ ያለው ክህደት እና ንቀት የተሞላበት ተግባር እጅግ በጣም ትልቅ የሆነ ወንጀል ነውና።