Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘በኣል’

አረጋዊው አሜሪካዊ | ዋ! ለአሜሪካ መቅሰፍቱን እንዳታመጡ ግብረ-ሰዶማዊያንን ወደ ኢትዮጵያ አትላኩ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 11, 2019

አዎ! የእነዚህ የዲያብሎስ ልጆች ተልዕኮ ስጋና ደምን ብሎም ነፍስን መስረቅ ነው።

አዎ! የእነዚህ የዲያብሎስ ልጆች ተልዕኮ ስጋና ደምን ብሎም ነፍስን መስረቅ ነው። የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ፀረግብረሰዶማዊ ድምጻቸውን ከፍ ሲያደርጉ በመላው ዓለም ተደማጭነትን አትርፈዋል። ሰሞኑን የተከሰተው ነገር የሚያስተምረን ትልቅ ትምህርት ቢኖር፡ ኢትዮጵያውያን በአንድ ልብ ሲቆጡ ዓለም እንደምትንቀጠቀጥ ነው። ከመንግስታቱ እና ደጋፊዎቻቸው በቀር በመላው ዓለም ድጋፍ ያገኘንበት ተግባር ነው። ከመንግስት አንጠብቅ፤ ጉዳዩ በሕዝቡና ቤተክርስቲያኑ እጅ መግባት አለበት። ጉዳዩ የአዲስ አበባን ጴንጤ ከንቲባ አይመለከትም፤ ወገን አትታለል። ከሦስት ዓመታት በፊት ታቅዶ የነበረውን የግብረሰዶማዊነት ተቃውሞ ሰልፍን አሁን ነው ማዘጋጀት የሚኖርብን፤ አሥር ሚሊየን ኢትዮጵያውያን በመስቀል አደባባይ ዙሪያ ድምጻቸውን ማሰማት ይኖርባቸዋል፤ ያኔ ነው ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን በጤናማው ዓለም ዘንድ አክብሮት እና አድናቆትን በይበልጥ ለማትረፍ የሚበቁት። በመላው ዓለም የፀረግብረሰዶማዊነት ዘመቻ ለመምራት የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ታሪካዊ ዕድል ያላት አሁን ነው።

ኢትዮጵያን አናሰርቃት! የማርያም መቀነታችንን (ሰንደቅ አላማ) እናስመልሳት!

__________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የፕሬዚደንት ትራምፕ መንግስት የአሜሪካ ኤምባሲዎች የግብረ-ሰዶማውያንን ሰንደቅ ዓላማ እንዳይሰቅሉ አዘዘ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 9, 2019

በእስራኤል፣ ጀርመን፣ ብራዚል እና ላትቪያ የሚገኙት የአሜሪካ ኢምባሲዎች የሰዶማውያኑን ሰንደቅ ዓላማ ለመስቀል ፈቃድ እንዲሰጣቸው ጠይቀው ነበር።

ይህ ጥሩ ውሳኔ ነው፤ ነገር ግን፡ ሴት ልጃቸውን በቅርቡ ወደ አዲስ አበባ ልከው የነበሩት ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ፡ በአንድ በኩል፡ ልክ እንደ ወስላታው ባራክ ሁሴን ኦባማ፡ ይህ የሰኔ ወር የግብረሰዶማውያን ወር እንዲሆን ድጋፋቸውን ይሰጣሉ፥ በሌላ በኩል ደግሞ ኤምባሲዎች ሰንደቅ ዓላማውን እንዳይሰቅሉ ያዛሉ፤ ይህ የሚያሳየን ፖለቲከኞች የሰይጣን ተከታዮቹንም ክርስቲያኖቹንም ማስቀየም እንደማይፈልጉ ዲፕሎማሲዊ የሆነውን መንገድ መከተላቸውን ነው።

ይህ ነገር ሰሞኑን በኢትዮጵያ ከሚካሄደው ሤራ ጋር የተያያዘ ነው። በዚህ አጋጣሚ መጠየቅ ያለብን፤ ዶ/ር አብዮት አህመድ ስልጣን ላይ እንደወጣ የዴንማርክና ፊንላንድ ኤምባሲዎች የሰዶማውያኑን ሰንድቅ ዓላማ አዲስ አበባ ላይ እንዲሰቅሉ ማን ነው የፈቀደላቸው? ይህን ከላሊበላ ጉዳይ ጋር በማያያዝ ዶ/ር አህመድን አፋጣችሁ ጠይቁት፤ እስካሁን ለምን በጉዳዩ ላይ ጸጥ አለ? ጸጥታውን ከቀጠለና ተገቢውን እርምጃ የማይወስድ ከሆነ አገራችን የመጀመሪያውን የግብረሰዶማዊእስላማውያን መንግስት መስርታለች ማለት ነው ፥ ሃይማኖታቸው ሰይጣናዊነት፣ አማልክታቸውም በኣልና ሞሎክ ናቸው ማለት ነው። አቤት ጉዳቸው!

[ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ ፴፪፥፴፭]

ይሁዳን ወደ ኃጢአት እንዲያገቡት፥ ይህንን ርኵሰት ያደርጉ ዘንድ፥ እኔ ያላዘዝሁትንና በልቤ ያላሰብሁትን ነገር፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ለሞሎክ በእሳት ያሳልፉ ዘንድ በሄኖም ልጅ ሸለቆ ውስጥ ያሉትን የበኣልን የኮረብታውን መስገጃዎች ሠሩ።

[ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ ፯፥፱፡፲፩]

ትሰርቃላችሁ፥ ትገድላላችሁ፥ ታመነዝራላችሁ፥ በሐሰትም ትምላላችሁ፥ ለበኣልም ታጥናላችሁ፥ የማታውቋቸውንም እንግዶች አማልክት ትከተላላችሁ መጣችሁም፥ ስሜም በተጠራበት በዚህ ቤት በፊቴ ቆማችሁ። ይህን አስጸያፊ የሆነ ነገርን ሁሉ አላደረግንም አላችሁ። ይህስ ስሜ የተጠራበት ቤት በዓይናችሁ የሌቦች ዋሻ ሆኖአልን? እነሆ፥ እኔ አይቻለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።

__________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ከሶሪያ በኋላ | ሮማውያኑ ሉሲፈራውያን በኢትዮጵያ ላይ ከባድ ሴራ እየጠነሰሱ ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 3, 2017

[1 ዜና መዋዕል 12:32]

ዘመኑን የተረዱና እስራኤላውያንም ምን ማድረግ እንደሚገባቸው የተገነዘቡ የይሳኮር ሰዎች ሁለት መቶ አለቆች፤ በእነርሱም ሥር ሆነው የሚታዘዙ ዘመዶቻቸው

ምንም በአጋጣሚ ወይም በድንገት የሚከሰት ነገር የለም። ነገሮች ሁሉ እርስበርስ የተገናኙ ናቸው። እያንዳንዱ ሀሳብ ቃል እና ድርጊት በማይታየው የኃይል ድር ላይ በየቦታው ተጽእኖ ይፈጥራል። እንደ፡ ጥሩ ወይም መጥፎ፣ ጤና ወይም በሽታ፣ ደስታ ወይም ሃዘን፣ ፍቅር ወይም ጥላቻ፣ ብርሃን ወይም ጨለማ የመሳሰሉት ተቃራኒ ጥንዶች፡ ተቃራኒ ውጤት ያላቸው የሚመስሉትን ምርጫዎችን ወይም ሁኔታዎችን ይፈጥሩልናል። ምንም እንኳን በጥንድዮሽ ግዛት ውስጥ መንቀሳቀስ እንደሌለብን ብናውቅም፣ እነዚህ ተቃራኒ ሁኔታዎች መኖራቸውን ልንክድ ግን አንችልም። ዋናው ቁምነገር ምርጫችን ነው፤ ወይ ቅዱሱን ወይ ርኩሱን ነው መያዝ የምንችለው፤ ወይ እግዚአብሔር ለሰጠን ለጥሩው፣ ለጤናማው፣ ለደስተኛው፣ ለአፍቃሪውና ብርሃናማው ዓለም እንታገላለን ወይም ለተቃራኒው የዲያብሎስ ዓለም እጃችንን እንሰጣለን፤ ሌላ ምርጫ ሊኖረን አይችልም።

ሰይጣን በትእቢቱ ምክንያት ከገነት ከመባረሩ በፊት የንጋት ልጅ፣ ብርሃን ያዥ ይባል ነበር፣ [ትንቢተ ኢሳይያስ 1412] ይህ ማዕረጉ መገፈፉ ግን ለተከታዮቹ አልተዋጠላቸውም፣ አሁንም ድረስ እውቀት ይሠጣል፣ “ብርሃኑን ይዞ ነው ከገነት የወጣው” ብለው ያስተምራሉ፡፡ ይህም ሉሲፈራዊነት ይባላል።

ለተቃራኒው የዲያብሎስ የጨለማ ዓለም እራሳቸውን አሳልፈው የሰጡት እነዚህ ኃይሎች (ሉሲፈራውያን) የተሰጣቸው ጊዜና ኃይል ውሱን በመሆኑ ተልዕኮዎቻቸውንና ሥራዎቻቸውን በደንብ አድርገው ያውቃሉ፤ እያንዳንዷ ዕለት የትግልና የፍልሚያ ዕለት መሆኗንም ይገነዘባሉ። እግዚአብሔርን በመካዳቸው ትግላቸው ሁልጊዜ ከእግዚአብሔር ልጆች ጋር ነው፤ ተጣድፈዋል፤ ፍልሚያውንም ከመቼውም በላይ በማጧጧፍ ላይ ይገኛሉ።

እነዚህ ሉሲፈራውያን ሥራዎቻቸውን በተግባር ላይ የሚያውሉበት ጊዜና ቦታ እንዲሁ በአጋጣሚ ሳይሆን፡ በጥንቃቄ ተመረጦና አስፈላጊውን ውጤት ሊያመጣ እንዲችል ተደርጎ ነው።

እንደምሳሌ ብንወስድ፡ ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ አቅርቤዋለሁ፤ መስከረም ፩፤ የኢትዮጵያ አገራችን አዲስ ዓመት፣ የብዙ ቅዱሳን የልደት ዕለት ነው። ይህ ዕለት በሉሲፈራውያኑ ዘንድ ለሽብር መመረጡ ያለምክኒያት አልነበረም።

ባለፈው የብርሃነ ትንሳኤ በዓል ዕለታችንም ጸረክርስቶሱ የቱርክ መንግስት ቁልፍ የሆነ ሕዝባዊ ሬፈረንደም ለማካሄድ መምረጡ፡ አውሬው ከጉድጉዱ እየወጣ፡ እንዲሁም ኃይልና ድፍረትንም እያገኘ መሆኑን ለማሳየት በማሰብ ነበር።

ርኩስ የሆነው የሰይጣን ቀን መቁጠሪያ

ሚያዚያ 23 (May 1) ይህ ዕለት ከቀጰዶቅያ አገር (በአሁኒቷ ቱርክ ግዛት ሥር ነው የሚገኘው) የሆነው የኢትዮጵያ ጠባቂ የሰማዕቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ በዓለ እረፍት ዓመታዊ የመታሰቢያ በዓል ነው። ይህን ዕለት የእግዚአብሔር ልጆች ከጥንት ጊዜ ጀምረን ሲያስቡት፤ ሉሲፈራውያኑ ደግሞ፤ በቅርብ ጊዜ “ሜይ ደይ” ወይም “ዓለም አቀፍ የሠራተኞች ቀን” ብለው ሰይመውታል። ሌላ ብዙ የማይታወቀው፤ እ..አ ከ April 30 (ሚያዚያ ፪፳ / May 1 ሚያዚያ ፳፫) እስከ May 6 (ሚያዝያ ፳፰) ድረስ ያሉት ቀናት (የቅዱሳን ዕለታት ጊዮርጊስ፣ ተክለ ሃይማኖት፣ መርቆርዮስ፣ ዮሴፍ፣ መድኃኔዓለም እና አማኑኤል (6) የሚውሉበት) ከጥንት ጀምሮ በሉሲፈራውያኑ ዘንድ በጣም ኃይለኛ የሆኑ ቀኖች ናቸው። እነዚህ ቀናት የ “ቤልታኔ በዓል” የሚል ስያሜ ተሰጥቷቸዋል። እነዚህ ቀኖች ሉሲፈራውያኑ በይበልጥ በጨለማ ቁጥጥር ሥር የሚገኙበትና ጨለማን ተገን አድርገው ርኩስ ተግባር የሚፈጽሙባቸው ርጉም ቀናት ናቸው።

እነዚህ ጥንታዊ ቀኖች በሉሲፈራውያኑ በአጋጣሚ የተመረጡ አልነበሩም፤ በጣም ኃይለኛ የሆኑ ቀናት በመሆናቸው እንጂ።

ከጥንት ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በ April 30 (ሚያዚያ ፪፳ / May 1 ሚያዚያ ፳፫) እና May 6 (ሚያዝያ ፳፰) ያሉት ቀናት ቀንዳማው ፍየል ባፎሜትን የሚያመልኩት ሉሲፈራውያን አምልኮታችውን፣ መሠዊያዎችን የሚሠሩበት እና ሰብዓዊ መሥዋዕት የሚያቀርቡባቸው ቀናት ናቸው።

ሶርያ እስክ ኢትዮጵያ ፡ ቁልፍ በሆኑ ቦታዎች ምን እየተካሄደ እንደሆነ እንመልከት። ሊሲፈራውያኑ ሰብዓዊ ስሜት ለማነሳሳት፣ ደም ለመፋሰስና ሞትን ለመፍጠር ግልጽ የሆኑ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ይገኛሉ፦

1. ሴቶችን እንደ እንስሳት የትምትቆጥርዋ ሳዑዲ አራቢያ በተባበሩት መንግሥታት የሴቶች መብት አስከባሪ ኮሚቴ ውስጥ በሉሲፈራውያኑ ተመርጣለች። ለ እግዚአብሔር ፍጥረታት ግድ የሌላቸውን፣ በተለይ በእስራኤላውያንና ኢትዮጵያውያን ላይ እጅግ በጣም ከፍተኛ የሆነ ጥላቻ ያላቸውን ሰነፍ አረቦችን ስልጣን ላይ በማስቀመጥ ቁልፍ ዓለም አቀፋዊ ድርጅቶችን እንዲመሩ እየተደረጉ ነው። ከእነዚህም አንዱ የዮርዳኖሱ አረብ፡…. የተባበሩት መንግሥታት ሰብዓዊ መብቶች አስከባሪ ድርጅት አለቃ አል=ሁሴን ኢትዮጵያውያንን ለማስጠንቀቅ ወደ ኢትዮጵያ ተጉዟል። እስከ ነገ ይቆያል። ወቸውጉድ፡ እሳት እና ውሃ፡ አረብ እና የሰብዓዊ መብት!

2. በፈረንጆቹ ቅዱስ ጊዮርጊስ ዕለት፡ በ 23 Apr 2017፡ በፈረንሳይ የመጀመሪያው ዙር የፕሬዚደንታዊ ምርጫ ተካሄደ። አሁን ደግሞ ሲፈራውያኑ ይህን ርኩስ ተግባር በሚያገባድዱበት ማግስት፡ በ 6 Apr 2017፡ ፈረንሳይ ፕሬዚደንቷን ትመርጣለች፤ ይህም በአጋጣሚ አይደለም። ልክ በመላው አውሮፓ እንደሚታየው ምርጫው በኮሌራና በወረርሽኝ መካከል ነው። የሚመረጠው ግን ማክሮን የተባለውና የጸረክርስቶሱ ርኩስ መንፈስ ያደረበት አውሬ እንደሚሆን የሚያጠራጥር አይደለም። በ25 ዓመት እድሜ የምትበልጠውን አስተማሪውን “አግብቷል” የተባለው ማክሮን ሰዶማዊ መሆኑ አፍንጫው ይናገራል። ጂቡቲን ከኢትዮጵያ የሰረቀችው ፈረንሳይ በመጪው ጊዜ ዋና የሽብር ፈጣሪዎች መናኽሪያ ትሆናለች

3. የተባበሩት መንግሥታትን፣ አውሮፓን እና አሜሪካን የሚመሩት ሮማውያን (ቫቲካን) ናቸው። የቫቲካን ጳጳሶች የምድራችን ቀዳሚ የክርስቲያኖች ሃገር የሆነችው ኢትዮጵያን አንዴም ጎብኝተው አያውቁም፤ ለዚህም ታላቅ ምስጢር አለ፡ በቅርቡ ይገለጥልናል። አድርባዩ የሮማው ጳጳስ ፍራንሲስ ባለፈው አርብ ወደ ግብጽ አምርተው ነበር። ግብጽን የጎበኙት በሙስሊሞች ከሚበደሉት ግብጻውያን ክርስቲያን ወንድሞቻችንና እህቶቻችንን ጎን ለመቆም ወይም እነርሱን ለማበረታታት ሳይሆን በሮማውያን ቁጥጥር ስር ለሚገኘው ዲያብሎሳዊ የአረብ ግብጻውያን መንግስት ድጋፍ ለመስጠት ነው። ቀደም ሲል ወደ ግብጽ ከማምራታቸው በፊት ፓፓስ ፍራንሲስ አንድ አስገራሚ የሆነ ንግግር አሰምተው ነበር፦

With a heart full of joy and gratitude,” said Pope Francis, “I will soon visit your beloved country, the Cradle of Civilization, the Gift of the Nile, Land of the Sun and Hospitality

ደስታ እና ምስጋና በተሞላው ልቤ እኔ በቅርቡ የሥልጣኔ ምንጭ, የአባይ ስጦታ, የፀሐይ እና የእንግዳ ተቀባዮች ምድር ውዲቷን አገራችሁን እጎበኛለሁ…“

አባይ ስጦታ (አዎ! ግሪኮችም እንዲህ ይሉ ነበር) ሥልጣኔ ምንጭ እና የፀሐይ ምድር። እምም.. አይገርምም? እንደሚታወቀው ግብፃውያን “አሞፅ ራ” የተባለውን የፀሐይ አምላክ ያመልኩ ነበር፡ አሁን ደግሞ “አላህ” የተባለውን የጨረቃ አምላክን ያመልካሉ፤ እነዚህ አማልክት የጌቶች ጌታ እና የነገስታት ንጉሥ የሆነው እግዚአብሔር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አይደለም። ጳጳስ ፍራንሲስ እባቡን የግብጽ ሸህ ጥምጥም አድርገው ሲያቅፉት፤ “ወቸው ጉድ! ለፓትርያርክ ታዋድሮስ ይህን ያህል ሞቅታ አላሳዩም፡ አይ ቫቲካን ሁለት‘! (እዚህ አንብቡት)“ አልኩ።

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ቤል (አራሜይክ) ወይምበኣል የሐሰት አማልክት አምልኮ፡ እንዲሁም ስለ ኤልዛቤል እና ጥንቆላዊ ልምዶቿ በግልጽ ያስጠነቅቀናል።

ከግብፅ ምድርም ያወጣቸውን የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ተዉ፥ በዙሪያቸውም ካሉት ከአሕዛብ አማልክት ሌሎችን አማልክት ተከተሉ፥ ሰገዱላቸውም፤ እግዚአብሔርንም አስቈጡ።

13፤ እግዚአብሔርንም ትተው በኣልንና አስታሮትን አመለኩ[መጽሐፈ መሣፍንት 2: 1213]

በባቢሎንም ውስጥ ቤልን እቀጣለሁ የዋጠውንም ከአፉ አስተፋዋለሁ፤ አሕዛብም ከዚያ ወዲያ ወደ እርሱ አይሰበሰቡም፥ የባቢሎንም ቅጥር ይወድቃል። [ትንቢተ ኤርምያስ 5144]

የሚገርም ነው! አንዳንድ ሰዎች፡ ቫቲካን የእስልምና እምነት መስራች መሆንዋን ይጠቁሙናል። እንደ ኢንሳይክሎፒዲያ ስለሀይማኖት ዘገባአላህ ” የመጀመሪያ የኢስላም ስም ሲሆን ስያሜውን ያገኘው ከባቢሎናውያን “ቤል(በኣል) ነው ይለናል::

አላህ” እሱ የጨረቃ አምላክ ነው:: ከጸሀይ አምላክ ጋር ተጋብቶ አንድ ላይ በመሆን ሶስት የአማልክ ወልደዋል:: እነዚህ ሶስቱ አማልክት ባንድ ላይ ሲጠሩ አላህ ይባላሉ:: እነዚያ ሶስት አማልክት አልላት : አልዩዛ እና ማናት ይባላሉ:: ለዚህም ነው የማጭድ ቅርጽ ያለውን ጨረቃ እና ኮከብ የሚጠቀሙት።

ለማንኛውም፡ አገራችንን፣ ጥንታዊ እምነታችን እና ቅዱሱን የአባይ ውሃ በሚመለከት ግብጻውያን ብቻ ሳይሆኑ፣ ሁሉም በሮማውያን ሥር ያሉት ሉሲፈራውያን አገሮች ተጨንቀዋል። የቫቲካን ሰዎች በታሪክ ከገዳይ አረቦች ጋር በመተባበር ይሰሩ እንደነበር የሚታወቅ ነው፤ ፀረኢትዮጵያ ዘመቻዎችም በታሪክ አጋጣሚ ተደጋግመው ተከስተዋል። ታላቁ የኢትዮጵያ የኅዳሴ ግድብ ግንባታ የሚያከናውነው የጣሊያኑ ሳሊኒ ኩባንያ መሆኑ ይከነክነኝ ነበር፤ ኩባንያው በኢትዮጵያ ላይ በተጠነሰሰው ሴራ ምን ዓይነት ሚና እንደሚጫወት ባላውቅም፤ ግን የአባይ ጉዳይ ግብጽን ብቻ ሳይሆን፡ ወንዛችን የሚነካቸውን መላውን የሚዲቴራንያን ባሕር አገራት፡ ጣሊያንን ጨምሮ፡ በጥልቅና በጥብቅ የሚመለከት ጉዳይ ነው።

ትንቢት ዳንኤል 11÷ 4 ጋር በተያያዘ ሮማውያን በኢትዮጵያ ላይ ከባድ ሴራ እየጠነሰሱ ነው ይሉናል።
አይሁዱ የ ዩቱብ ሰባኪ Steven Ben-DeNoon ምን እንደሚሉ እናዳምጥ፦

__

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: