Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • May 2023
    M T W T F S S
    1234567
    891011121314
    15161718192021
    22232425262728
    293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘በኢትዮጵያ ላይ ሤራ’

ካሊፎርኒያ ሰዶም እና ገሞራ | በኢትዮጵያ ፀበላት ላይ ሤራ የሚጠነስሱት የ እነ ዊል ስሚዝ ቤቶች በእሳት ጋዩ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 12, 2018

ካሊፎርኒያ (ካሊፍ + ኦርኒያ) እየነደደች ነው። በህይወቴ እንደዚህ የመሰለ ነገር አይቼ አላውቅም

ከጥቂት ወራት በፊት ባቀረብኩት ቪዲዮ ላይ “የአርቲስት ዊል ስሚዝና ባለቤቱ ጄዳ የኢትዮጵያ ጉብኝት

ክቡሩን ፀብል ፍለጋ ወይስ ውሃ ለመጠጥ?“ የሚል ጥያቄ ጠይቄ ነበር። ሁሉም በእርዳታ ስም ወደ አገራችን እየገቡ ዲያብሎሳዊ ሥራዎቻቸውን አሁንም ቀጥለዋል።

በጣና ሐይቅ ያሉትን ብርቅ ገዳማት ለማዘጋት እምቦጩን ተከሉ፣ በላሊበላ መኻን ለሆኑ እህቶቻችን ለመጸንስ እንዲችሉ የሚረዳቸውን ኩሬ “ቢልሃርዝያ” አለበት በማለት አዘጉት፣ በትግራይ ደግሞ ፈውስ የሚሰጡትን ድንቅ ፀበላት በ ”ኮሌራ” አምጭ ባክቴሪያ በመበከል ብዛት ያላቸውን ወገኖቻችን ከገደሏቸው በኋላ ነዋሪው ጸበል እንዳይጠቀም ተደረገ…. እንግዲህ፡ ይህ ለአለፉት ጥቂት ወራት ብቻ መሆኑ ነው። እግዚአብሔር አያይም፥ የያዕቆብ አምላክ አያስተውልም እያሉ እኮ ነው።

ጊዜውን ጠብቆ ልክ በኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ዕለት የወጣ ዜና፤ የኛዎቹ ፀጥ ብለው ነበር፥ ርዕሱ ላይ እናተኩር፦

+ ‘Holy Water’ Blamed for Cholera Outbreak In Ethiopia

+ Cholera Outbreak ‘sparked By Holy Water’ as Deadly Disease Kills 10 And Infects 1,200

+ Cholera Outbreak Spread By Holy Water Leaves 10 Dead And 1,200 Infected

ታዋቂ የሆኑት የሆሊውድ አርቲስቶች እና የሉሲፈር አምባሳደሮች፤ የእነ ካርዴሺያኖች፣ ሊሊ ፓምፕ፣ ማርቲን ኢጊ አዛሊያ፣ ኬንዳል ጄነር ካትሊን ጄነር ዊል ስሚዝ ሌዲ ጋጋ (ስሞቻቸው ሁሉ ልክ እንደ ጣዖት አምላኪዎቹ፡ ዲያብሎሳዊ ቃና ያላቸው ናቸው) እና የሌሎችም መኖሪያ ቤቶች፡ “ ውልሴይ እሳት” የሚል ቅጽል ስም በተሰጠው በካሊፎርንያው የዱር እሳት በመጋየት ላይ ናቸው። እነዚህ ትዕቢተኞች በእሳት ቃጠሎው ሳቢያ ቤቶቻቸውን ለመልቀቅ ተገደዋል። ይቅመሷት፤ ማሊቡ የተባለውን መንደር የምድር ገነት ለማድረግ አልመው ነበርና። ዊልሴይ እሳት = ዊል = ዊሎው = ዊል ስሚዝ

አሁን ድሃዎቹም ኃብታሞችም እኩል ናቸው፤ ሁሉም ቤት አልባ ሆነዋል!

እነዚህ ቅብጥብጥ ሀብታም ሰዎች አሁን ለድሆች እና ለቤት አልባዎች የበለጠ ይቆረቆሩ ይሆናል የሚል ተስፋ አለኝ።

የመጭው ዘመን ምን እንደሚመስል እግዚአብሔር እያሳየን ነው።

ከዚህ አሰቃቂ ሁኔታ የምናገኘው ጥልቅ ትምህርት አለሰዶም እና ገሞራም ድራሻቸው እስኪጠፋ ተቃጥለዋል፤ የዘመናችን የሰዶማውያን መናኽሪያ የሆነችው ካሊፎርኒያም ዳግም ሎጥ ለቅቆ ከወጣ በኋላ በመሬት መንቀጥቀጥ ትናወጣለች፣ በእሳትም ትጋያለች።

ካሊፎርኒያ እና ሳዑዲ ባቢሎን ለምንገኝ ወገኖች፡ ዳግም ሎጥ ለመሆን ቶሎ ያብቃን።

______

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ግእዝ ኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ ሌላ አገር ሐይማኖታዊ/ መንፈሳዊ ቋንቋ ነው። የዓለም ህዝብ ተቀብሎታል፤ ከኢትዮጵያውያን በስተቀር”

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on July 7, 2017

ዛሬ: ..አ: 07/07/2017 ነው። ምስሉ ኩራታችን የሆነው አየር መንገዳችን ቦይንግ 777 ን ሲያበር ያሳያል።

በእግዚአብሔር አምላካችን ዘንድ አንድ ሐቅ ነው ያለችው፤ ወደድንም ጠላንም፡ አንድ ሐቅ ብቻ! ግዜ በእጃችን አይደለም ያለው፤ ለእኛ የተባለውን ነገር ሁሉ፣ የተሰጠነን ህልውና፣ የተረከብነውን ቅዱስ መንፈስ በመጠቀም ዛሬውኑ፣ አሁኑኑ ነው በሥራ ላይ ማወል የሚገባን። “ቆዩ፤ አሁን ሁኔታው አይፈቅድም ቀስ እንበል!„ እያሉ ከመቀመጫቸው መነሳት የማይሹትን አታላዮችና ሌላውንም እንዲያንቀላፋ የሚያደርጉት፣ በሌላው ላይ ብቻ ሳይሆን በራሳቸውም ላይ ነው ከባድ መዘዝ በማምጣት ላይ የሚገኙት። የራሳቸውን ቆሻሻ የቤት ሥራ ለመጪው ትውልድ አሳልፎ በመተው፡ በአሁኖቹ ህፃናት ላይ ሊሰረዝ የማይችሉ በደልና ኃጢአት ነው የሚፈጽሙት።

“ኢትዮጵያ አገራችን ተከባልች፣ ጠላቶቿ እራሳቸው በዘረጉት የጊዜ ጎዳና ላይ በመጓዝ አመቺ የሚሆነላቸውን አጋጣሚ በመጠበቅ ላይ ናቸው!፡” እያልኩ ላለፉት 15 ዓመታት ባቅሜ ያለማቋረጥ እጠቁም ዘንድ እግዚአብሔር ይገፋፋኝ ነበር። ሉሲፈራውያኑ ችግኞቻቸውን በየአገራቱ ተክለዋል፣ በተለይ በአገራችን፤ የክርስቶስንም ልጆች በግልጽ ለመዋጋት ቆርጠው ከተነሱ ውለው አድረዋል። ባሁኑ ሰዓትም ኢአማናያን ሰዶማውያኑን እና መሀመዳውያኑን እንደ መሳሪያ አድርገው በመጠቀም ላይ ይገኛሉ። አሁን ሁላችንም አካሄዳቸውን መከተል የምንችልበት ጊዜ ላይ ደርሰናል፤ ዓይን ያለው ፈጥኖ ይመልከት።

ባለፉት ጥቂት ወራት ብቻ ምን እንደሚሰሩ፡ ብሎም ማን እንደሆኑ ለመላው ዓለም በግልጽ ደፍረው ብዙውን ነገር እያሳዩን ነው። ካሳዩንም ሁኔታዎች መካከል የሚከተሉትን እንመልከት፤ ይህ ሁሉ ባጭር ጊዜ ውስጥ ነው የተከሰተው፦

  1. ታላቋ ብሪታኒያ ከአውሮፓው ህብረት ትወጣለች ብለው በፍጹም አልጠበቁም። brexitሬፈረንደም ውጤቱን ለመከለስ ያው እስካሁን በመታገል ላይ ናቸው

  2. የዶናልድ ትራምፕን ለፕሬዚደንትነት መብቃት ፈጽሞ አልጠበቁትም ነበር። ከተመረጡበት ቀን ጀምሮ በሳቸው እና ደጋፊዎቻቸው ላይ እየተካሄደ ያለው የጥቃት ዘመቻ በታሪክ ተወዳዳሪ አይኖረውም

  3. ኢትዮጵያውያን በአገር ቤትም በውጩም እርስበራሳቸው እንዲበጣበጡ፣ በህንድ ውቂያኖስ፣ በቀይ ባሕር፣ በሜዲተራንያን ባሕር፣ በቆሼበለንደን እና በካሌ ለሉሲፈር መስዋእት እንዲሆኑ ተደረጉ

  4. ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም የዓለም ጤና ድርጅት ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተመረጡ። አንድ ኢትዮጵያዊ እንደዚህ ዓለማቀፋዊ ተጽዕኖ ማድረግ በሚችል ድርጅት ውስጥ “ሰርጎ” መግባቱ፣ ከኢትዮጵያዊነት አንፃር፡ እሰይ! ትልቅ ነገር ነው! ለአገራችን የሚበጅ ነው! የሚያሰኝ ነው። ከስልጣን፣ ከታዋቂነት እና ከንዋይ ኃብት የበለጠ፡ በተለይ ለኢትዮጵያውያን፡ ሌላ እጅግ ትልቅ ነገር አለ። ዶ/ር ቴዎድሮስ ኢትዮጵያን የሚጠቅም እና እግዚአብሔር አምላኳን የሚያስደስት ሥራ ለመሥራት ይበቃሉን? ወደፊት የምናየው ነው። ለማንኛውም እንጸልይላቸው።

  5. ሊሲፈራውያኑ በአሜሪካ የሠሩትን ዓይነት ስህተት ላለመስራት፣ በፈረንሳይ ሰዶማዊውን ማክሮንን ፕሬዚደንት ለማድረግ በቁ

  6. በአየርላንድም ሰዶማዊውን የህንድ ስደተኛ በጠቅላይ ምኒስቴርነት አስቀመጡ

  7. በጀርመንም አንድ ሳምንት ብቻ በፈጀው ያልተጠበቀ ስብሰባ የሰዶማውያን “ጋብቻ” ሕጋዊ እንዲሆን በጥድፊያ አጸደቁት። ይህን መሰሉን ጉዳይ ሕዝቡ በሬፈረንደም መወስን ነበረበት።

  8. በኢትዮጵያም መንፈሳዊውን ኢትዮጵያኛ የግእዝ/አማርኛ ቋንቋ ለማጥፋት እንዲሁ በተጣደፈ መልክ ምክር ቤቱ ህግ እንዲያጸድቀ ተደረገ። ይህን መሰሉን ጉዳይ ሕዝቡ በሬፈረንደም መወስን ነበረበት።

  9. G20 አገራቱ መሪዎች ስብሰባ ከመጀመሩ ከሁለት ቀናት በፊት የአፍሪቃው ህብረት መሪዎች በአዲስ አበባ ተሰባሰቡ

እነዚህ እና ሌሎች ተመሳሳይ ጉዳዮችም በዚህ የሀምበርጉ የመሪዎች ስብሰባ ላ በሪፖርት መልክ ለውይይት እንደሚቀርቡ የሚያጠራጥር አይደለም። በነገራችን ላይ፡ ሀምበርግ ከተማ በተቃዋሚ ኃይሎች ብጥብጥ እየታወከችና እየነደደች ነው! እሳት! እሳት! እሳት!

አፍሪቃ ዋና የመወያያ ርዕስ እንደሆነች ቀደም ሲል ተጠቁሟል። ብዙ የአፍሪቃ አገሮች መሪዎች በስብሰባው እንዲሳተፉ ቢደረግም፤ አፍሪቃን በዋናነት የሚወክሉት ግን ደቡብ አፍሪቃዊውና ባለ አራት ሚስቱ (ሰዶማዊ) ያዕቆብ ዙማ ናቸው።

የሳጥናኤል ጎል ኢትዮጵያ

በእኛ አቆጣጠር በ 2007 .ላይ ታታሪው ወንድማችን ፍስሐ ያዜ ካሳ ሳጥናኤል ጎል ኢትዮጵያ” የሚለውን ድንቅ መፅሐፍ ጽፎልናል።የዚህ መፅሐፍ ትኩረት ስለ አዲሱ የምድር መንግስት ምስረታ ብቻ ሳይሆን፤ የፍፃሜው ጦርነት ምን እንደሚመስል፣ኢትዮጵያም ከፍፃሜው ጦርነት ጋ በተያያዘ የተለየ ትኩረት እንደተደረገባት፣ ዘንዶውን በኒውክሌር እናግዛለን፤ እግዚአብሔርንና መላዕክቱንም እናሸንፋለን!ብለው የኃያላን አገራት መሪዎችና የቫቲካን ቤተክርስቲያን የሚዝቱበትና የሚዘጋጁበት፤ ጦርነቱም በዋናነት ኢትዮጵያ ላይ እንደሚሆን፤ጎላቸውም ኢትዮጵያ እንደሆነች ይገልፃል። የዓለማችን ታላላቅ የሚባሉ ገለባ አገራትና መሪዎች ከዚህ በኋላ ትልቁ የቤት ስራቸው ኢትዮጵያ ላይ እንደሆነ በማስረጃ እያስደገፈ ተንትኖታል፡፡

ለዛሬው የሚከተለውን ከመጽሐፉ ጠቅሼ አቅርቤዋለሁ፦

በቅርቡ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የታሪክ ዲፓርትመንትን ሊዘጋ ነው ሲባል ሰማሁና በጣም ተገረምኩ። እንዴት? ታሪክ ከታጠፈ ጂኦግራፊም ቀረ ማለት ነው። እሱ ቀረ ማለት ደግሞ አገር አገርነቷ የሚታወቀው በምን ሊሆን ነው። እሱ ቀረ ማለት ደግሞ አገር አገርነቷ የሚታወቀው በምን ሊሆን ነው? ብዬ ራሴን ጠየቅሁ። የዲፓርትመንቱ ሃላፊዎች ለምን አደጋ እንዳንዣበበበት ሲጠየቁ “በዘርፉ የሚመረቁ ተእማሪዎች ስራ እያጡ ተቸገርን፣ 70/30 ፕሮግራም፣ ወዘተ…„ የሚል የናቴ መቀነት አደናቀፈኝ ዓይነት ምክንያት ሲሰጡ ሰማሁና ግርም እንዳለኝ ተውኩት። የታሪክ ትምህርትን ያጠፋች አገር ካለች ብየ ኢንተርኔት ላይ አጣራሁ። ይኖራል ብዬ ማሰቤ ራሱ የሚገርም ነው። የለም! ስራ ስላለ ስለሌለ ነው እንዴ ታሪክ ማወቅና መማር ማስተማር ያስፈለገው? ምን ማለት ይሆን? እያልኩ ሳይገባኝ አለሁ። ጭራሽ ኢትዮጵያ ታሪክን ማስቀረት? አሜሪካ እንኳ የሶስት መቶ ዓመት ታሪክ ይዛ ልዩ ትኩረት የሰጠችው ዲፓርትመንት ነው። ጭራሽ ኢትዮጵያ? ታሪክን ማስቀረት ማለት ምን ማለት መሰለህቀጣዩን ትውልድ አገርም ታሪክም ንብረትም ማንነትም ምንም ምንም የለህም ማለት ነው። መነሻም መድረሻም የሌላቸው ከንቱ ትውልዶች ናችሁ! ማለት ነው! ቀጥተኛ ትርጉሙ ይሄ ነው። ቀጣዩን ትውል ምን እያሉት መሰለህየግዛታችሁ ስፋት አይታወቅም። አባቶቻችሁም አልተናገሩም እንደማለት ነው! ደግነቱ ቀጣይ ትውልድ የሚባል ነገር…„

አሁንማ ግልጽ ሆነ! ለምን እንደዚያ እንደተደረገም አውቅነ! ይሄ ብቻ ሳይሆን ይህ በተባለ ማግስት በታሪካዊው ቤተ መፃህፍት የነበሩትን ታሪካዊ ሰነዶች በሙሉ ቦታ ጠበበ በሚል ተልካሻና አስቂኝ ምክንያት ለሲቅ እቃ መጠቅለያነት ይውሉ ዘንድ ጠርገው አወጡና አጫርተው ሸጧቸው። ግራ ገብቶኝ ነበር። ግን ግልፅ ሆነ። ለካስትልቅ የዛፍ ግንድን ሲገዘግዙ ሲገዘግዙ ቆይተው፤ ግዝገዛው ሲያልቅ ግንድስ ብሎ መውደቁ ነው። ገዝጋዡም ስራውን አጠናቆ ላቡን እየጠራረገ እፎይ ብሎ አረፈ። ተገንድሶ የወደቀውን ግንድ ገዝጋዡ ተሸክሞ የመሄድ ግዴታ የለበትም። ለሸክም የተዘጋጁ ሊሎች ሰራተኞች ይኖራሉ። የቀረውን ግፋፎና ቅጠላ ቅጠል የሚጋፋና አካባቢውን የሚያፀዱም ተዘጋጅተዋል፤ ስራው ግን ተጠናቋል!„

በጣም ያሳዝናል! ግዝገዛውን አውቅ ነበር። ይሄኛውን ግን አልሰማሁም፤ አዝናለሁ”

አሁን ነው እንዲያ የሆነው። አንድ ተማሪ አልተቀበሉም። በማግስቱ ግን አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የቻይንኛን ቋንቋ በመደበኛ ፕሮግራም በዲግሪ መርሀ ግብር ማስተማር ጀመረ። የራሳችንን ትተን ቻይንኛ እየተማርን ነው። ቻይና ደግሞ በተመሳሳይ አማርኛ ቋንቋን ሶስተኛ ቋንቋዋ አድርጋ አገሯ ላይ እያስተማረች ነው። ሌሎች የG20 አገራትም እንደ ቻይና አማርኛንና ግእዝን ሶስተኛ ቋንቁ አድርገው በዲግሪ እያስተማሩ ነው። እስከ ፒ...ዲ ድረስ እያስተማሩ ነው። ይህን ነገር በዜና ሳይ ያው ከልማቱ ጋር በተገናኘ ይሆናል ብዬ አስቤ ነበር። አሁን ነው ጅልነቴ የገባኝ። ለካስ ታዘው ነው። ስለዚህ እኛ የነሱን መማር ጀመርንእውነት ለንግዱ፣ ለልማቱ፣ ለምናምኑ ቻይንኛን መልመድ እዚህ ድረስ አስፈልጎ ነው? ከዚህ ወዲያ ውድቀት አለ? ከዚህ ወዲያ ሴራ አለ? ሌቦች ናቸው! እኛም እልል ብለን እንቀበላቸዋለን!

አንድ ተረት ልናገር፦ ሰሜን ሸዋ አካባቢ አንዲት እብድ ነበረች አሉ። ይቺ ታዋቂ እብድ በአንድ ቅዳሜ ማለዳ ላይ ትነሳና፣ “ዛሬ ገበያ እንዳትሄዱ ቤት ይቃጠላል። ገበያ እንዳትሄዱ ቤት ይቃጠላል። እያለች ስትለፍፍ አረፈደች። የቀዬው ሰዎች ግን፤ “ዛሬ ደግሞ ይቺ እብድ በጠዋት ተነሳባት” እያሉ አሽሟጠጧት። ቀኑ የገባያ ቀን ነውና የእብዷን ልፍለፋ ከምንም ሳይቆጥሩ ልብ ብለውም ሳይሰሙ ጎጆ ቤታቸውን ዘጋግተው ወደ ገበያ ሄዱ። አጅሪት ደግሞ ቀዬው ጭር ማለቱን ስታይ፤ እሳት በችቦ ትለኩስና ያንን ሁሉ ጎጆ ቤት ታቃጥለዋለች። ሁሉንም ቤት አንድዳ ዞር ትላለች። ያገሬው ህዝብ ገበያ ውሉ ሲመጣ መንደሩ እንዳለ ተቃጥሏል። በዚህ ጊዜ ያች እብድ ተመልሳ መጣችና፤ “ነግረናል ቤት ይቃጠላል ብለናል፤ ነግረናል ቤት ይቃጠላል ብለናል” እያለች ትናገር ጀመር። አሁንም ከዚህ ቀደም ጥቂት ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያ ታሪክ እየተዘረፈ ነው፤ ታሪኩም አፈ ታሪክ አይደለም፤ ከ3ሺ ዓመትም ይበልጣል፤ ነጮችንም አትመኑ እያሉ ስድብ ቢጤም እያካተቱ ለመግለፅ ሞክረው ነበር። ይገሬው ጎሳ መሪዎች ግን ፈፈፋውን ልብ አላሉም፤ ወደ ጎን ሊሉት ሞከሩ። አሁን እኔ እነሱን ብሆን ኖሮ እንደዚያች እብድ፤ “ነግረናል ቤት ይቃጠላል ብለናል” እያልኩ በየአደባባዩ እለፍፍ ነበር”

የሚያሳዝን ነው!“

አለም (ዲያብሎስ) “ማየት ማመን ነው” ይለናል | እግዚአብሔር ደግሞ “ማመን ማየት ነው” ብሎ ያስተምረናል

It’s 07/07/17 | G20 Summit Embarrassment: Germany’s Merkel Bows To Saudi Arabian State Minister


______

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , | Leave a Comment »

“ከፍሬአቸው ታውቁአቸዋላችሁ” | ሙስሊሞች ክርስቶስን ሲሳደቡ ኢትዮጵያዊ ልጆቹን ሲያንገላቱ፣ ሲያንቋሽሹና ሲዝቱባቸው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 19, 2017

የባቢሎን ቤል ሃውልት በመካ

ሳዑዲ ባቢሎን የመጥፊያዋ ጊዜ ተቃርቧል፤ በጎቹን ኢትዮጵያውያንን በድጋሚ ያው ሂዱ! ውጡ! እያለች እንደ ከብት በመንዳት ላይ ናት። ወይ ጉዷ!

ወንድሞች እህቶች የኢትዮጵያ ልጆች፡ አይክፋችሁ፡ አይክፋን፡ እንዲያውም ደስ ይበላችሁ፡ ደስ ይበለን ቶሎ ውጡ፡ ከባቢሎን በፍጥነት አምልጡ!

ትንቢተ ኤርሚያስ 50

2 በአሕዛብ መካከል ተናገሩ አውሩም፥ ዓላማውንም አንሡ፤ አውሩ፥ አትደብቁ። ባቢሎን ተወሰደች፥ ቤል አፈረ፥ ሜሮዳክ ደነገጠ፤ ምስሎችዋ አፈሩ፥ ጣዖታትዋ ደነገጡ በሉ።

6 ሕዝቤ የጠፉ በጎች ሆነዋል፤ እረኞቻቸው አሳቱአቸው፥ በተራሮችም ላይ የተቅበዘበዙ አደረጉአቸው፤ ከተራራ ወደ ኮረብታ አለፉ፥ በረታቸውንም ረሱ።

7 ያገኙአቸው ሁሉ በሉአቸው፥ ጠላቶቻቸውም። በጽድቅ ማደሪያ በእግዚአብሔር ላይ፥ በአባቶቻቸው ተስፋ በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት ስለ ሠሩ እኛ አልበደልንም አሉ።

8 ከባቢሎን መካከል ሽሹ፥ ከከለዳውያንም ድር ውጡ፥ በመንጎችም ፊት እንደ አውራ ፍየሎች ሁኑ።

ርስቴን የምትበዘብዙ እናንተ ሆይ፥ ደስ ብሎአችኋልና፥ ሐሤትንም አድርጋችኋልና፥ በመስክ ላይም እንዳለች ጊደር ሆናችሁ ተቀናጥታችኋልና፥ እንደ ብርቱዎችም ፈረሶች አሽካክታችኋልና፥

12 እናታችሁ እጅግ ታፍራለች፥ የወለደቻችሁም ትጐሰቍላለች፤ እነሆ፥ በአሕዛብ መካከል ኋለኛይቱ ትሆናለች፤ ምድረ በዳና ደረቅ ምድር በረሀም ትሆናለች።

13 ከእግዚአብሔር ቍጣ የተነሣ ባድማ ትሆናለች እንጂ ሰው አይቀመጥባትም፤ በባቢሎንም በኩል የሚያልፍ ሁሉ ይደነቃል በመጣባትም መቅሠፍት ሁሉ ያፍዋጫል።

35 ሰይፍ በከለዳውያንና በባቢሎን በሚኖሩ ላይ፥ በአለቆችዋና በጥበበኞችዋ ላይ አለ፥ ይላል እግዚአብሔር።

36 ሰይፍ በሚጓደዱት ላይ አለ ሰነፎችም ይሆናሉ፥ ሰይፍም በኃያላኖችዋ ላይ አለ እነርሱም ይደነግጣሉ።

37 ሰይፍ በፈረሶቻቸውና በሰረገሎቻቸው ላይ በመካከልዋም ባሉት በልዩ በልዩ ሕዝብ ሁሉ ላይ አለ፥ እነርሱም እንደ ሴቶች ይሆናሉ፤ ሰይፍም በመዝገብዋ ላይ አለ ለብዝበዛም ይሆናል።

38 እርስዋ የተቀረጹ ምስሎች ምድር ናት፥ እነርሱም በጣዖታት ይመካሉና ድርቅ በውኆችዋ ላይ ይሆናል እነርሱም ይደርቃሉ።

የእፉኝት ምላስ


ትንቢተ ኤርሚያስ 50

24 ባቢሎን ሆይ፥ አጥምጄብሻለሁ አንቺም ሳታውቂ ተይዘሻል፤ ከእግዚአብሔር ጋር ስለ ተዋጋሽ ተገኝተሻል ተይዘሽማል።

27 ወይፈኖችዋን ሁሉ እረዱ፥ ወደ መታረድም ይውረዱ፤ ቀናቸው፥ የመጐብኘታቸው ጊዜ፥ ደርሶአልና ወዮላቸው!

28 የአምላካችንን የእግዚአብሔርን በቀል የመቅደሱንም በቀል በጽዮን ይነግሩ ዘንድ ሸሽተው ከባቢሎን አገር ያመለጡት ሰዎች ድምፅ ተሰምቶአል።

31 ትዕቢተኛው ሆይ፥ የመጐብኘትህ ጊዜ፥ ቀንህ ደርሶአልና እነሆ፥ በአንተ ላይ ነኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

32 ትዕቢተኛው ተሰናክሎ ይወድቃል የሚያነሣውም የለም፤ በከተሞቹም ውስጥ እሳት አነድዳለሁ፥ በዙሪያውም ያለውን ሁሉ ትበላለች።

ሰይጣን ተለቅቋል፤ ልጆቹም የልብልብ ብሏቸዋል፣ ደፋር፣ ጯሂ፣ ተናጋሪና ተሳዳቢ ሆነዋል። ጊዚያቸው ነው፤ የተሰጣቸውም ጊዜ በጣም አጭር ስለሆነ በየአቅጣጫው እያጠቁን ነው።

ክርስቲያን ኢትዮጵያችን የሚዋጓትን ሙስሊም ጠላቶቿን ፡ እጆቿን ዘርግታ ተቀበለቻቸው፣ ተርባና ተጠምታ፡ ካላት፣ ከለፋችበት አካፍላ በጉርሻ አበላቻቸው፣ ለሺህ ዓመታት ታግሳ፣ እራሷን ዝቅ አድርጋ፣ ላቧ ጠብ እስኪል እንደ ከባድ ሸክም ተሸከማ አሳደገጃጀቸው፣ ፈወሰቻቸው፣ አስተማረቻቸው። አሁን ጠገቡባት፣ ጠሏት፣ ከመካ መዲና መስጊድ አሳድዶ ከሚያወጣቸውና ኢሰብዓዊ በሆነ መልክ እየሰበሰበ ከጠረፋቸው ከአረብ ጋር እየተማከሩ ባገራችን ላይ መልሰው ሴራው ጠነሰሱባት፣ ወደ እግዚአብሔር በመምጣት ፋንታ› ይባስ ብለው አምላኳን በድፍረት አንቋሸሹባት፣ ልጆቹንም ይሳደባሉ ይገድላሉ

የእፉኝት ምላስ ያላት ይህች ሴት በክርስቶስና በድንግል ማርያም ላይ ኡ! ! የሚያሰኝ የብልግና ቃል የምትሰነዝረው የት ባገኘችው መረጃ ላይ በመመርኮዝ ይሆን? ወልድን የት ታውቀዋለችና? ቁራኗ ወይም ሃዲቷ ላይ ተጽፏልን? ሰይጣን ይህን ያህል ዘልቆ ደፍሮ አይጽፍም። ግን ቁራኑም ሃዲቱም ብልግናውን የጻፈው ስለራሷ መሀመድ ነው። መንፈስ አልባ ጭንቅላቷም ውስጥ ሊቀረጽ የሚችለው ይኽው ስለ መሀመድ የተጻፈው ብልግና ብቻ ነው የሚሆነው። ታዲያ የራሷን ጉድ አረብ አገር ሄዳ ስላወቀች በተዘዋዋሪ መንገድ በራሱ በመሀመድ ላይ እያላገጠች አይደለምን? መቼም ሙስሊሞች እንደተለመደው ነገሮችን ፕሮጀክት ማድረግ ይወዳሉና እራሳቸው እየገደሉ ሌላውን ገዳይ እንደሚሉት አሁንም የመሀመድን ጉድ ለክርስቶስ ይሰጣሉ፤ የራሷ አሮባት የሰው ታማስላለች እንዲሉ።

ሰይጣን ሳይቀር በጌታችን ላይ ይህን ያህል ደፍሮ እንደማይናገር እናውቃለን፤ ታዲያ እንደነዚህች ላሉት ብኩን ባለጌ ከሃዲ ሴቶች እግዚአብሔር ምን ዓይነት ፍርድ የሚሰጣቸው ይመስለናል?

እንቆጣለን፣ ዳዊትን እንደግማለን፤ ግን አንጥላቸው! ሆኖም፡ ብዙም አንቅረባቸው!

___

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ከሶሪያ በኋላ | ሮማውያኑ ሉሲፈራውያን በኢትዮጵያ ላይ ከባድ ሴራ እየጠነሰሱ ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 3, 2017

[1 ዜና መዋዕል 12:32]

ዘመኑን የተረዱና እስራኤላውያንም ምን ማድረግ እንደሚገባቸው የተገነዘቡ የይሳኮር ሰዎች ሁለት መቶ አለቆች፤ በእነርሱም ሥር ሆነው የሚታዘዙ ዘመዶቻቸው

ምንም በአጋጣሚ ወይም በድንገት የሚከሰት ነገር የለም። ነገሮች ሁሉ እርስበርስ የተገናኙ ናቸው። እያንዳንዱ ሀሳብ ቃል እና ድርጊት በማይታየው የኃይል ድር ላይ በየቦታው ተጽእኖ ይፈጥራል። እንደ፡ ጥሩ ወይም መጥፎ፣ ጤና ወይም በሽታ፣ ደስታ ወይም ሃዘን፣ ፍቅር ወይም ጥላቻ፣ ብርሃን ወይም ጨለማ የመሳሰሉት ተቃራኒ ጥንዶች፡ ተቃራኒ ውጤት ያላቸው የሚመስሉትን ምርጫዎችን ወይም ሁኔታዎችን ይፈጥሩልናል። ምንም እንኳን በጥንድዮሽ ግዛት ውስጥ መንቀሳቀስ እንደሌለብን ብናውቅም፣ እነዚህ ተቃራኒ ሁኔታዎች መኖራቸውን ልንክድ ግን አንችልም። ዋናው ቁምነገር ምርጫችን ነው፤ ወይ ቅዱሱን ወይ ርኩሱን ነው መያዝ የምንችለው፤ ወይ እግዚአብሔር ለሰጠን ለጥሩው፣ ለጤናማው፣ ለደስተኛው፣ ለአፍቃሪውና ብርሃናማው ዓለም እንታገላለን ወይም ለተቃራኒው የዲያብሎስ ዓለም እጃችንን እንሰጣለን፤ ሌላ ምርጫ ሊኖረን አይችልም።

ሰይጣን በትእቢቱ ምክንያት ከገነት ከመባረሩ በፊት የንጋት ልጅ፣ ብርሃን ያዥ ይባል ነበር፣ [ትንቢተ ኢሳይያስ 1412] ይህ ማዕረጉ መገፈፉ ግን ለተከታዮቹ አልተዋጠላቸውም፣ አሁንም ድረስ እውቀት ይሠጣል፣ “ብርሃኑን ይዞ ነው ከገነት የወጣው” ብለው ያስተምራሉ፡፡ ይህም ሉሲፈራዊነት ይባላል።

ለተቃራኒው የዲያብሎስ የጨለማ ዓለም እራሳቸውን አሳልፈው የሰጡት እነዚህ ኃይሎች (ሉሲፈራውያን) የተሰጣቸው ጊዜና ኃይል ውሱን በመሆኑ ተልዕኮዎቻቸውንና ሥራዎቻቸውን በደንብ አድርገው ያውቃሉ፤ እያንዳንዷ ዕለት የትግልና የፍልሚያ ዕለት መሆኗንም ይገነዘባሉ። እግዚአብሔርን በመካዳቸው ትግላቸው ሁልጊዜ ከእግዚአብሔር ልጆች ጋር ነው፤ ተጣድፈዋል፤ ፍልሚያውንም ከመቼውም በላይ በማጧጧፍ ላይ ይገኛሉ።

እነዚህ ሉሲፈራውያን ሥራዎቻቸውን በተግባር ላይ የሚያውሉበት ጊዜና ቦታ እንዲሁ በአጋጣሚ ሳይሆን፡ በጥንቃቄ ተመረጦና አስፈላጊውን ውጤት ሊያመጣ እንዲችል ተደርጎ ነው።

እንደምሳሌ ብንወስድ፡ ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ አቅርቤዋለሁ፤ መስከረም ፩፤ የኢትዮጵያ አገራችን አዲስ ዓመት፣ የብዙ ቅዱሳን የልደት ዕለት ነው። ይህ ዕለት በሉሲፈራውያኑ ዘንድ ለሽብር መመረጡ ያለምክኒያት አልነበረም።

ባለፈው የብርሃነ ትንሳኤ በዓል ዕለታችንም ጸረክርስቶሱ የቱርክ መንግስት ቁልፍ የሆነ ሕዝባዊ ሬፈረንደም ለማካሄድ መምረጡ፡ አውሬው ከጉድጉዱ እየወጣ፡ እንዲሁም ኃይልና ድፍረትንም እያገኘ መሆኑን ለማሳየት በማሰብ ነበር።

ርኩስ የሆነው የሰይጣን ቀን መቁጠሪያ

ሚያዚያ 23 (May 1) ይህ ዕለት ከቀጰዶቅያ አገር (በአሁኒቷ ቱርክ ግዛት ሥር ነው የሚገኘው) የሆነው የኢትዮጵያ ጠባቂ የሰማዕቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ በዓለ እረፍት ዓመታዊ የመታሰቢያ በዓል ነው። ይህን ዕለት የእግዚአብሔር ልጆች ከጥንት ጊዜ ጀምረን ሲያስቡት፤ ሉሲፈራውያኑ ደግሞ፤ በቅርብ ጊዜ “ሜይ ደይ” ወይም “ዓለም አቀፍ የሠራተኞች ቀን” ብለው ሰይመውታል። ሌላ ብዙ የማይታወቀው፤ እ..አ ከ April 30 (ሚያዚያ ፪፳ / May 1 ሚያዚያ ፳፫) እስከ May 6 (ሚያዝያ ፳፰) ድረስ ያሉት ቀናት (የቅዱሳን ዕለታት ጊዮርጊስ፣ ተክለ ሃይማኖት፣ መርቆርዮስ፣ ዮሴፍ፣ መድኃኔዓለም እና አማኑኤል (6) የሚውሉበት) ከጥንት ጀምሮ በሉሲፈራውያኑ ዘንድ በጣም ኃይለኛ የሆኑ ቀኖች ናቸው። እነዚህ ቀናት የ “ቤልታኔ በዓል” የሚል ስያሜ ተሰጥቷቸዋል። እነዚህ ቀኖች ሉሲፈራውያኑ በይበልጥ በጨለማ ቁጥጥር ሥር የሚገኙበትና ጨለማን ተገን አድርገው ርኩስ ተግባር የሚፈጽሙባቸው ርጉም ቀናት ናቸው።

እነዚህ ጥንታዊ ቀኖች በሉሲፈራውያኑ በአጋጣሚ የተመረጡ አልነበሩም፤ በጣም ኃይለኛ የሆኑ ቀናት በመሆናቸው እንጂ።

ከጥንት ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በ April 30 (ሚያዚያ ፪፳ / May 1 ሚያዚያ ፳፫) እና May 6 (ሚያዝያ ፳፰) ያሉት ቀናት ቀንዳማው ፍየል ባፎሜትን የሚያመልኩት ሉሲፈራውያን አምልኮታችውን፣ መሠዊያዎችን የሚሠሩበት እና ሰብዓዊ መሥዋዕት የሚያቀርቡባቸው ቀናት ናቸው።

ሶርያ እስክ ኢትዮጵያ ፡ ቁልፍ በሆኑ ቦታዎች ምን እየተካሄደ እንደሆነ እንመልከት። ሊሲፈራውያኑ ሰብዓዊ ስሜት ለማነሳሳት፣ ደም ለመፋሰስና ሞትን ለመፍጠር ግልጽ የሆኑ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ይገኛሉ፦

1. ሴቶችን እንደ እንስሳት የትምትቆጥርዋ ሳዑዲ አራቢያ በተባበሩት መንግሥታት የሴቶች መብት አስከባሪ ኮሚቴ ውስጥ በሉሲፈራውያኑ ተመርጣለች። ለ እግዚአብሔር ፍጥረታት ግድ የሌላቸውን፣ በተለይ በእስራኤላውያንና ኢትዮጵያውያን ላይ እጅግ በጣም ከፍተኛ የሆነ ጥላቻ ያላቸውን ሰነፍ አረቦችን ስልጣን ላይ በማስቀመጥ ቁልፍ ዓለም አቀፋዊ ድርጅቶችን እንዲመሩ እየተደረጉ ነው። ከእነዚህም አንዱ የዮርዳኖሱ አረብ፡…. የተባበሩት መንግሥታት ሰብዓዊ መብቶች አስከባሪ ድርጅት አለቃ አል=ሁሴን ኢትዮጵያውያንን ለማስጠንቀቅ ወደ ኢትዮጵያ ተጉዟል። እስከ ነገ ይቆያል። ወቸውጉድ፡ እሳት እና ውሃ፡ አረብ እና የሰብዓዊ መብት!

2. በፈረንጆቹ ቅዱስ ጊዮርጊስ ዕለት፡ በ 23 Apr 2017፡ በፈረንሳይ የመጀመሪያው ዙር የፕሬዚደንታዊ ምርጫ ተካሄደ። አሁን ደግሞ ሲፈራውያኑ ይህን ርኩስ ተግባር በሚያገባድዱበት ማግስት፡ በ 6 Apr 2017፡ ፈረንሳይ ፕሬዚደንቷን ትመርጣለች፤ ይህም በአጋጣሚ አይደለም። ልክ በመላው አውሮፓ እንደሚታየው ምርጫው በኮሌራና በወረርሽኝ መካከል ነው። የሚመረጠው ግን ማክሮን የተባለውና የጸረክርስቶሱ ርኩስ መንፈስ ያደረበት አውሬ እንደሚሆን የሚያጠራጥር አይደለም። በ25 ዓመት እድሜ የምትበልጠውን አስተማሪውን “አግብቷል” የተባለው ማክሮን ሰዶማዊ መሆኑ አፍንጫው ይናገራል። ጂቡቲን ከኢትዮጵያ የሰረቀችው ፈረንሳይ በመጪው ጊዜ ዋና የሽብር ፈጣሪዎች መናኽሪያ ትሆናለች

3. የተባበሩት መንግሥታትን፣ አውሮፓን እና አሜሪካን የሚመሩት ሮማውያን (ቫቲካን) ናቸው። የቫቲካን ጳጳሶች የምድራችን ቀዳሚ የክርስቲያኖች ሃገር የሆነችው ኢትዮጵያን አንዴም ጎብኝተው አያውቁም፤ ለዚህም ታላቅ ምስጢር አለ፡ በቅርቡ ይገለጥልናል። አድርባዩ የሮማው ጳጳስ ፍራንሲስ ባለፈው አርብ ወደ ግብጽ አምርተው ነበር። ግብጽን የጎበኙት በሙስሊሞች ከሚበደሉት ግብጻውያን ክርስቲያን ወንድሞቻችንና እህቶቻችንን ጎን ለመቆም ወይም እነርሱን ለማበረታታት ሳይሆን በሮማውያን ቁጥጥር ስር ለሚገኘው ዲያብሎሳዊ የአረብ ግብጻውያን መንግስት ድጋፍ ለመስጠት ነው። ቀደም ሲል ወደ ግብጽ ከማምራታቸው በፊት ፓፓስ ፍራንሲስ አንድ አስገራሚ የሆነ ንግግር አሰምተው ነበር፦

With a heart full of joy and gratitude,” said Pope Francis, “I will soon visit your beloved country, the Cradle of Civilization, the Gift of the Nile, Land of the Sun and Hospitality

ደስታ እና ምስጋና በተሞላው ልቤ እኔ በቅርቡ የሥልጣኔ ምንጭ, የአባይ ስጦታ, የፀሐይ እና የእንግዳ ተቀባዮች ምድር ውዲቷን አገራችሁን እጎበኛለሁ…“

አባይ ስጦታ (አዎ! ግሪኮችም እንዲህ ይሉ ነበር) ሥልጣኔ ምንጭ እና የፀሐይ ምድር። እምም.. አይገርምም? እንደሚታወቀው ግብፃውያን “አሞፅ ራ” የተባለውን የፀሐይ አምላክ ያመልኩ ነበር፡ አሁን ደግሞ “አላህ” የተባለውን የጨረቃ አምላክን ያመልካሉ፤ እነዚህ አማልክት የጌቶች ጌታ እና የነገስታት ንጉሥ የሆነው እግዚአብሔር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አይደለም። ጳጳስ ፍራንሲስ እባቡን የግብጽ ሸህ ጥምጥም አድርገው ሲያቅፉት፤ “ወቸው ጉድ! ለፓትርያርክ ታዋድሮስ ይህን ያህል ሞቅታ አላሳዩም፡ አይ ቫቲካን ሁለት‘! (እዚህ አንብቡት)“ አልኩ።

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ቤል (አራሜይክ) ወይምበኣል የሐሰት አማልክት አምልኮ፡ እንዲሁም ስለ ኤልዛቤል እና ጥንቆላዊ ልምዶቿ በግልጽ ያስጠነቅቀናል።

ከግብፅ ምድርም ያወጣቸውን የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ተዉ፥ በዙሪያቸውም ካሉት ከአሕዛብ አማልክት ሌሎችን አማልክት ተከተሉ፥ ሰገዱላቸውም፤ እግዚአብሔርንም አስቈጡ።

13፤ እግዚአብሔርንም ትተው በኣልንና አስታሮትን አመለኩ[መጽሐፈ መሣፍንት 2: 1213]

በባቢሎንም ውስጥ ቤልን እቀጣለሁ የዋጠውንም ከአፉ አስተፋዋለሁ፤ አሕዛብም ከዚያ ወዲያ ወደ እርሱ አይሰበሰቡም፥ የባቢሎንም ቅጥር ይወድቃል። [ትንቢተ ኤርምያስ 5144]

የሚገርም ነው! አንዳንድ ሰዎች፡ ቫቲካን የእስልምና እምነት መስራች መሆንዋን ይጠቁሙናል። እንደ ኢንሳይክሎፒዲያ ስለሀይማኖት ዘገባአላህ ” የመጀመሪያ የኢስላም ስም ሲሆን ስያሜውን ያገኘው ከባቢሎናውያን “ቤል(በኣል) ነው ይለናል::

አላህ” እሱ የጨረቃ አምላክ ነው:: ከጸሀይ አምላክ ጋር ተጋብቶ አንድ ላይ በመሆን ሶስት የአማልክ ወልደዋል:: እነዚህ ሶስቱ አማልክት ባንድ ላይ ሲጠሩ አላህ ይባላሉ:: እነዚያ ሶስት አማልክት አልላት : አልዩዛ እና ማናት ይባላሉ:: ለዚህም ነው የማጭድ ቅርጽ ያለውን ጨረቃ እና ኮከብ የሚጠቀሙት።

ለማንኛውም፡ አገራችንን፣ ጥንታዊ እምነታችን እና ቅዱሱን የአባይ ውሃ በሚመለከት ግብጻውያን ብቻ ሳይሆኑ፣ ሁሉም በሮማውያን ሥር ያሉት ሉሲፈራውያን አገሮች ተጨንቀዋል። የቫቲካን ሰዎች በታሪክ ከገዳይ አረቦች ጋር በመተባበር ይሰሩ እንደነበር የሚታወቅ ነው፤ ፀረኢትዮጵያ ዘመቻዎችም በታሪክ አጋጣሚ ተደጋግመው ተከስተዋል። ታላቁ የኢትዮጵያ የኅዳሴ ግድብ ግንባታ የሚያከናውነው የጣሊያኑ ሳሊኒ ኩባንያ መሆኑ ይከነክነኝ ነበር፤ ኩባንያው በኢትዮጵያ ላይ በተጠነሰሰው ሴራ ምን ዓይነት ሚና እንደሚጫወት ባላውቅም፤ ግን የአባይ ጉዳይ ግብጽን ብቻ ሳይሆን፡ ወንዛችን የሚነካቸውን መላውን የሚዲቴራንያን ባሕር አገራት፡ ጣሊያንን ጨምሮ፡ በጥልቅና በጥብቅ የሚመለከት ጉዳይ ነው።

ትንቢት ዳንኤል 11÷ 4 ጋር በተያያዘ ሮማውያን በኢትዮጵያ ላይ ከባድ ሴራ እየጠነሰሱ ነው ይሉናል።
አይሁዱ የ ዩቱብ ሰባኪ Steven Ben-DeNoon ምን እንደሚሉ እናዳምጥ፦

__

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , | Leave a Comment »

የሳጥናኤል ጎል ኢትዮጵያ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 4, 2016

... jun 3/ 2014 Belgium / European Union HQ / Brussels

G8 አገራት የመሪዎች ጉባኤ

በዚያችው ብራሰልስ ከተማ መለስ ዜናዊን ለመስዋዕትነት ተጠቅመውባቸው ይሆን?”

የሳጥናኤል ጎል ኢትዮጵያከሚለው የ ፍስሐ ያዜ ካሣ መጽሐፍ (2007) የተወሰደ

በእውነት፡ ይህን በመሳሰሉት መጻሕፍት ሕፃናቶቻች ትምህርት ቤት ሊማሩና ተኮትኩተው ሊያድጉ ይገባል!

ከሰላምታ፡ አክብሮትና ምስጋና ጋር

PDF ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

G8scoreCard

40ኛው የG 8 ዓመታዊ ስብሰባ ይካሄድ የነበረው ከ ጁን 4 እስከ 5 2014 ..አ ቢሆንም፤ መሪዎቹ ግን አንድ ቀን ቀደም ብለው የግል ዝግ ጉባኤያቸውን ያደረጉት ጁን 3 / 2014 ምሽት ላይ ነበር። ማረጋገጫ የሆነውን ልዩና ረቂቅ የሆነ የኤክስሬይ ምርመራቸውን ሁሉም በየጀርባቸው እየተጋደሙ አረጋገጡና ወደ ቀዩ ሚስጥራዊ አዳራሽ አቅንተው ቦታ ቦታቸውን ያዙ።

ተሰብሳቢዎቹ በጥቁር ሱፍና በቀይ ከረባት አጊጠዋል። የአሜሪካው ጥቁር ፕሬዚደንት ላፕቶፑዋን መድረኩ ላይ ባለችው የቁም ጠረጴዛ ላይ አስቀምጦ መድረኩን ለቀቀና ወደ መሰሎቹ ተሰብሳቢዎች አምርቶ ተቀመጠ። እንደተቀመጠም ከፍተኛ የሆነ ብርሀን ያለው መብራት ቦግ አለና አዳራሹን ሌላ ውበት ሰጠው።

በአንዳቸውም ላይ የመረበሽና የመደንገጥ ሁኔታ አይስተዋልም። ሁሉም በፈገግታ ፈክተዋል። የጉባኤውን መጀመር በጉጉት እየተጠባበቁ ያሉም ይመስላል።

መሪ ነው! የእያንዳንዱን ተሰብሳቢ አይምሮና አስተሳሰብ፤ ብሎም እቅድና የእውነት ተገዥነቱን ማጣራትና ማወቅ ይችላል። የሹማምንቱን ብቻም ሳይሆን የሁሉንም ተራ አባላት የአይምሮ ዳታ ማንበብ ይችላል። አንዴ አምነውበትና ተቀብለውት ራሳቸውን በፈቃደኝነት አሳልፈው ሰጥተውታልና፤ የመጣል፣ የማንሳት፣ የመግደልና የማዳን፤ እንዲሁም የማበልፀግ፤ በጥቅሉ ሁሉንም የማድረግ መብት የተጎናፀፈ ልዑል ነው! ለልጆቹ፣ ለወዳጆቹ፣ ለተከታዮቹ በግልፅ ቅልጭ ብሎ ይታያል። ጥበብን ይገልጣል! የሚሹትን ሁሉ በለጋስነት ይሰጣል! ታማኝነቱ እስከ ዘላለም ነው! ሁሉን በእጁ ይዟል! የያዘውን ለተከታዮቹ ይሰጣል! ባለ ድል ነው! ያሸንፋል! ልዑል ነው! በድል አድራጊነት ይነግሳል! የሰው ልጅ ሁሉ በደስታ ይገዛለታል!” የሚል አስገምጋሚ ድምፅ አዳራሹን ናጠው።

መሪዎቹ ገና መናገር እንደጀመረ ነበር ተነስተው በደስታ ማጨብጨብ የጀመሩት። አዳራሹ ውስጥ ከስምንቱ መሪዎች ውጪ ለጊዜው ማንም አልነበረም። ተናጋሪውም ከመሪዎቹ አንዱ አልነበረም። መድረኩ ላይም ማንም የለም። መሪዎቹ ግን ማን እየተናገረ እንዳለ ያወቁ ይመስላል። ግራ የመጋባት ሁኔታም አልተስተዋለባቸውም።

baphomet1

ክብር ለልዑሉ!” ሲል፤ መሪዎቹም በአንድ ድምጽ

አሜን!” ሲሉ ተደመጡ።

ክብር ለኃያሉ!”

አሜን!”

ክብር ለባለ ድል አብዮተኛችን!”

አሜን!”

ከወደ ጣራው በኩሉ ኮሽታ ድምፅ ሳያሰማ ስፍፍፍፍእያለ ወረደና በዝግታ መድረኩ ላይ እርፍፍፍአለ። ግዙፍ የሆነ ርዝመት አለው። ግዙፍ የሆነ ውፍረትም አለው። ያማረና የተዋበ የፊት ገፅታም አለው። በሰዎች አገላለፅ የወንድ ቆንጆ፣ ፀጉረ ዞማ፣ የሚያማልሉ አይኖች፣ ከበረዶ የነፁ ጥርሶች፣ እንጆሪ የመሰሉ ከናፍርቶች አሉት። ቅላቱና የፊቱ ልስላሴ ሊገልፁት የሚከብድ ነው። እንዲህ ሆኖ የሚታየው ግን ከአንገቱ በላይ ብቻ ነው።

ፊቱ የሰው ነው። ከአንገቱ በታች ሲታይም የሰው ቅርፅና የሰው የሰውነት ክፍሎችን ሁሉ ያካተተ ተክለ ቁመና ያለው ነው። ነገር ግን አጠቃላይ አቋሙና ግዝፈቱ ሰው እንዳልሆነ የሚያስታውቅ ነው። የቆመው እንደ ሰው በእግሮቹ ነው፤ ነገር ግን ሁለቱ እግሮቹ በጣም ወፋፍራምና አብረቅራቂ ቆዳ ያላቸው ዘንዶዎች ናቸው።

G8 አገራት መሪዎችም መጥቶ ከቆመባት ጊዜ ጀምሮ ነው ቆመው ማጨብጨብ፣ በአንዳች በሚያርገፈግፍ የደስታ ስሜት ውስጥ ሆነው መጮህ፣ እልልልልልል የሚል ዓይነት ድምፅ ማሰማትና በደስታ መዝለል የጀመሩት።

ሂደቱ በዚህ ዓይነት እንደቀጠለ በነበረ ጊዜም ይህ ምንነቱ ያልለየ ነገር በመጣበት አኳኋን፤ ኮሽታ ድምፅ ሳያሰሙ ሀይማኖታዊ ልብሳቸውን እንደለበሱና በአንድ እጃቸው የወርቅ መቋሚያቸውን እንደጨበጡ፤ ያንን ከእንቁና ከወርቅ የተሰራ የራስ አክሊላቸውን እንደደፉ በቀይ ካባ አጊጠው የቫቲካኑ ዋና ጳጳስ ከተፍ አሉ።

2016-09-04_164022

ጳጳሱ አንድ እጃቸውን አንስተው የተቀመጡ ምልክት አሳዩዋቸው። የG8 አገራት መሪዎችም በድንፋታ የታጀበ ምስጋናቸውን ደምድመው በየወንበሮቻቸው ቁጭ አሉ። የቫቲካኑ ጳጳስም ተሰብሳቢዎችን አስቀምጠው በተለየ ቋንቋና ለማንም ባልተሰማ ሹክሹክታ ለዚያ ቀድሟቸው ለመጣው ዘንዶ ለበስ ሰው ጎንበስ ብለው አነበነቡና እጅ ነስተው ቀና አሉ። ይህንን አድርገውም ሌላ ቃል ሳይናገሩ በመጡበት አኳኋን ወደ ላይ ተነሱና ተንሳፈው ሄዱ። ኮርኒሱና ጣራው ክፍትም ክድንም ሳይል እንዲሁ አሳለፈቸው። ጳጳሱ ከሄዱ በኋላ እንዲሁ ባረፈበት ቦታ እንደቆመ እንደ ሞዴሊስት ተገትሮ በልዩ ፈገግታ በጎንዮሽ ተሰብሳቢዎችን በማየት ብቻ ተወስኖ የነበረው ሰው መሳይ አካል በዝግታ መድረኩ ላይ መንጎማለል ጀመረ። ወዲያውም አስገምጋሚ ድምፅ ከአንደበቱ ወጣ። የሚናገረው በጠረአ እንግሊዝኛ ነው።

ክብር ለኃያሉ አባቴ!” ሲል በከባድ ድምጽ ጀመረ።

አሜን!” የሚል የጋራ ጩኸት አሰሙ።

ተናጋሪው መድረኩ ላይ ወዲያ ወዲህ ሲል ቆየና አዳራሹ በፀጥታ እንደተዋጠ በቄንጥ ሽክርክር አለና፤ ወደ ተሰብሳቢዎች ዞረ። ከዚያም እነዚያን የሚያማምሩና ሙሉ በሙሉ የሰው የመሰሉ ዓይኖቹን ለአፍታ ጨፈን አድርጎ ገለጣቸው። ይህን እንዳደረገ ልዩ አርማዉ የሆኑት ሁለት ጥቋቁር ወንዶች በግንባሩ ግራና ቀኝ በቅፅበት ወጡ።

በዚህም የተገረመ ተሰብሳቢ አልነበረምና የተለመደ ክስተት መሆኑን ለማወቅ ተቻለ።

የወደፊቷ ድንቅና አጓጊ አዲስ ዓለም ዜጎች እንኳን በደህና መጣችሁ!” ብሎ ሲጀምር፤ በተሰብሳቢዎች በኩል ያልተጠበቀ የማጉረምረም ድምፅ ተሰማ። ሁሉም፤ እንዴት ነው ዜጎች የምንባለው? ያልተለመደ አጠራር የሆነውስ ለምንድን ነው?” ዓየነት ማጉረምረም ነበር ያስደመጡት። እሱ ግን በደስታ የተዋጠ ፊቱን ለተሰብሳቢዎች እያሳየና በዘንዶ ቆዳ የተለበጡ የሚመስሉ ሁለት ረጃጅም እጆቹን ግራና ቀኝ እየዘረጋ፤ አትፍሩ የተለወጠ ነገር የለም። ዜጎች በሚል እንግዳ ስም የጠራኋችሁ በምክንያት ነው። የአዲሲቷ ዓለም ሹማምንት ያላልኩት ኃያል ጌታ ከሆነው ከአባቴ አዲስ መመሪያ ስለተቀበልኩ ነው። ይህ እንደ ቀድሞው አይነት የሆነ የእናንተን የሹማምንቱን ጉዳይ የሚመለከት ጉባኤ አይደለም። በናንተ ውስጥ ስላሉትና ወደፊትም በእናንተ አማካኝነት በጥቁር እሳት ተጠምቀው ዜጎቻቸው ስለሚሆኑት ስለሌሎች የአዲሲቷ ዓለም ዜጎች የሚመለከት ጉባኤ ስለሆነ ነው!” ሲል፤ የተሰብሳቢዎች ፈገግታ መለስ አለና እርጋታ ሰፈነ። እሱም ቀጠለ።

እንኳን ደስ ያላችሁ! የዘመኑን መቅረብ ከአባቴ ተረዳሁ! ዘመኑ ሲቃረብ ደግሞ የበለጠ ዘመናዊ ጥበብ ወደ እናንተ ትመጣለች። ዛሬም የተሰጣችሁን እሰጣችሁ ዘንድ መጣሁ! ያለ ውጣ ውረድ ዜጎቻችሁን የምትመለምሉበትና የምታጠምቁበት አዲስ መንገድ! የፍፃሜው መጀመሪያ እንዲሁም መደምደሚያ!” ዜማዊ ቅላፄን በተላበስ ድምፀት ነበር የሚናገረው።

nwo-money-changers-rape

ሁላችሁም በአንድነት ውጪያችሁን አብሩ!” አላቸው። ሁሉም በአንድነት ዓይኖቻቸውን ለስድስት ሴኮንድ ያህል ጨፍነው ቆዩና ገለጡ። ሲገልጡም የተለመዱት ጥቋቁርና ጥምዝ የሆኑ አጫጭር ቀንዶቻቸው በየግንባሮቻቸው ግራና ቀኝ ወጡ። በዚህ ባለመገረማቸውም ይህ ነገር ለነሱ የተለመደና አዲስ አለመሆኑን መረዳት ተቻለ። ሁሉም አባላት ውጪያቸውን በሚያበሩ ጊዜ ሁለቱ ትናንሽ ጥቁር ቀንዶች በግንባሮቻቸው ግራና ቀኝ ይበቅላሉ። ያልተለመደው አዲስ ነገር ቀጣዩ ትዕዛዝና ተግባር ነበር።

ቀጠለ፤ አሁን ደግሞ ውስጣችሁን ለማብራት ተመሳሳይ ነገር በእጥፍ አድርጉ!” ሲል፤ ታዳሚዎች ለአስራሁለት ሴኮንድ ያህል አይኖቻቸውን ጨፍነው ገለጡ። ሆኖም ያዩት አዲስ ነገር አልነበረም። ወዲያው ግን፤

እርስ በርሳችሁ ተያዩሲላቸውና ሲተያዩ፤ በጉጉት ይጠብቁት የነበረው ነገር በየግንባሮቻቸው ላይ ተፅፎባቸው ተፅፎባቸው አዩ። በአብረቅራቂ የኩል ቀለም 666 የሚል ምልክት ተፅፎባቸው ሲያዩ ማመን አቃታቸው።

አመስግኑ! አባቴን አመስግኑ!” ተባሉ።

አስገራሚ ነገር ነበር፤ የምድራችን ባለ ስልጣናት ሆነው ስንት ነገር ሲያደርጉና ሲከብሩ ባየ አያናችን እነዚህን ሰዎች አሁን ያሉበትን ሁኔታ መልሰን ስናይ ፍፁም የማይታመንና የሚዘገንኑ ሰዎች ሆነው ነው የምናገኛቸው። ልብሳቸውን አውልቀው ወለል ላይ እየተንከባለሉ በአንድ አይነት ድምፅ፣ በጋራ ረጅምና ከባድ አስገምጋሚ ጩኸት በተቀላቀለበት አንደበት መሳቅ፣ ማሽካካት ጀመሩ። ለረጅም ደቂቃዎችም ወደ መድረኩ ቀርበው ወለሉ ላይ እየተንከባለሉ አመሰገኑት።

ዘመኑ ደረስ! ሹመታችን መጣ! በጉን እናርዳለን! አንተም ኃያላችን ስልጣን ሰጠኸን! ለአሸናፊ አለቃችን! ንግስና ላንተ! ጌትነት ላንተ! የምድር ነብሶች ሁሉ ላንተ!…” በማለት እየተንከባለሉ አመስግነው አበቁና እርስ በርስ በደስታ ተቃቅፈው እየተሳሳሙ ወደየቦታቸው ተመለሱ።

አሁን የነካችሁት፣ የዳሰሳችሁት፤ የፈለጋችሁት ሁሉ የአዲሲቷ ዓለም ዜጋ ይሆናል፤ አባቴንም ያከብራል! የተሰጠውን ጥበብም ጌታውን ለማክበር ይጠቀምበታል! እናንተም በክብር ትሾማላችሁ! ሞትና መውጊያውን በትብብር እንነጥቃለን! ለዚህም ይረዳን ዘንድ ኃይሉ አባቴ ያለውን ጥበብ ሁሉ ይጠቀማል! ያንንም ለናንተ ይሰጣል! ክብር ለታላቁ አባቴ! ክብር ለአመፀኛው እውነተኛ አለቃየ! ሹመት ለአዲሲቷ ዓለም ንጉሰ ነገስት! ሃሃሃ ሃሃሃ ሃሃሃ ሃሃሃካካ ካካ ካካ ካካ ሃሃሃ ሃሃሃ…” ለጆሮ የሚሰቀጥጥ የጋራ ሳቅ

G20Members

አሁንሲል እንደገና ጀመረ። አሁን ሌሎችን የG20 አገራት መሪዎችን ሰብስቡና፤ ከስረ መሰረቱ ጀምሩና ሂደቱን፤ እንዲሁም ያማረ ሰልሚሆነው ፍፃሜና ጎል አብራሩላቸው፡ አንዳች ሙግት አይገጥማችሁም። ካሁን በኋላ ምንም ሚስጥርና ድብቅ ነገር የለም። ይህ ዘመን በአባቴ ተዋጅቷልና እንደገና ደስስስስስይበላችሁ! ሁሉም በእጃችን ሆኗልና ሐሴት አድርጉ! የተዋጀውን ዘመን ደጋግማችሁ ዋጁት! ጥሯቸውና አብስሯቸው! ያሸናፊ ልጆች ሆይ! የንጥቂያ ዘመን አሁን ነው! ንጥቂያ ይቅለልላችሁ፤ ብየ ባረክኋችሁ! የአዲሲቷን የኛን ዓለም ምስረታ ገንቡ! ጠንክራችሁ ስሩ። ጠንክራችሁም ተናጠቁ። የገንዘብ፣ የኢኮኖሚ፣ የጦር መሳሪያና፤ የቴክኖሎጂ የበላይነትን ተጎናጽፋችኋልና ማንም ሊያቆማችሁ እንደማይችል ተረድታችኋል። ምድር ካለችበት የጭለማ ተስፋ ወጥታ ወደ ዘላለማዊ ህልውናዋ መመለስ አለባት። ያኔያኔ አባቴ፣ እኔ፣ እናንተና የእናንተ ሹሞች ለዘላለም እንነግሳለንና ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ! ስለምታደርጉት ነገር አታስቡ! ስለምትጠየቁት ጥያቄ አትጨነቁ። እኔ በሁሉም ውስጥ አድሬ ማላሽ እሰጥላችኋለውና! ይላል ልዑላችን! ደግሞም ማንም መውጫን ማምለጫ የለውምና ደስ ይበላችሁ! ውድቀት ለሚታረደውና ለታረደው በግ! ድል ለአሸናፊዎች የአዲሲቷ ዓለም ንጉሰ ነገስትና ነገስታት!

ንግግሩ ሞቅ እያለ ሲሄድ እነዚያ የሰው አይኖቹ ወደ ደምነት ተለወጡ። ያ ያማረ የራስ ቅሉ በድንገት ሶስት ማዕዘን ቅርጽ ወዳለው የፒራሚድ ገጽታ ተለወጠ። ተናፍሎ ወደ ጀርባው የተደፋው ወርቃማው ፀጉሩም ብን ብሎ ጠፋና ማዕዘን መላጣ ሆነ። ከዚህ መላጣ ቅርፅ ውስጥም ሌሎች ሁለት ቀንዶች በቀሉ። ከአንገቱ በታች የነበረው ቅርፅ ግን አልተለዋወጠም ነበር። የሹመታችሁ ማረጋገጫ ተሰጣችሁ! አሁን የቀረ ነገር የለም! ትናፍቁት የነበረው ነገር ሁሉ ደረሰላችሁ! የአባቴና የአባታችሁ የድል ዘመን ደረሰ! አሁኑኑ አብስሯቸው ይህን ድንቅ ጥበብ ለግሱና በሀሴት አጥለቅልቋቸው! በድል አድራጊነት አሰማሯቸው! አመስግኑ! አመስግኑ! አመስግኑ! አመስግኑ! አመስግኑ! አመስግኑ!” ድምፁ በጣም እየጋለ እየጋለ ሄደ።

20 ዎቻችሁ ሁኑና በተመሳሳይ ስልጣን ሙሉ ሂደቱን አሳውቁ! እናንተም ተጨማሪውን መመሪያ ተቀበሉ። በነፃነት ተሞልታችሁ ሁሉንም ነገር እወቁ አሳውቁ! መነሻና መድረሻችሁን ልታውቁ ነውና ደስ ይበላችሁ! የመጨረሻዋና ተሸሽጋ የነበረችው ሚስጥርና ትዕዛዝ ዘመኗን ጠብቃ ከ አባቴ ዘንድ መጣች! ተገለች! ሐሴትም አደረግሁ! ክብር ለኃያሉ ልዑል!”

አሜን!”

አሜን!”

አሉ ተሰብሳቢዎቹ ሁሉ በጋራ። የአሜሪካውን ጥቁር መሪ ጨምሮ ሁሉም በላብ ተዘፍቀው ነበር።

ይህ ሰው መስሎ ስልጣን የያዘና አሜሪካን በፕሬዘዳንትነት እየመራ ያለውን ጥቁር መሪ አሁን ባለበት ሁኔታ ሌላ የማያውቅ ሰው ቢያየው ሊገጥመው የሚችለው ድንጋጤ እጅግ ከባድ እንደሚሆን ጥርጥር የለኝም። ያን ከባድ ድንጋጤ ግን ቀድሜ ልደነግጠውና ልጋፈጠው የቻልኩት እኔ ሆንኩ!

የምስጋናው ጪኸት ጋብ እንዳለና ተሰብሳቢዎችም እንደተቀመጡ የአሜሪካው መዐሩ ንግግር ማድረግ ጀመረ።

በድጋሚ እንኳን ደስ ያለን ማለት እፈልጋለሁ!” ሲል፤ የጋራ ጭብጨባ ተስተጋባለት፡ አሁን ውጪና ውስጣችን እናጥፋ!” ሲል ደግሞ ሁሉም አይኖቻቸውን ጨፍነው ገለጡ። እሱም ተመሳሳይ ነገር አደረገና የሁሉም ቀንዶች ወደ ውስጥ ጠለሙ። የቁጥር ምልክቱም ከግንባራቸው ጠለመና ነፃ ግንባር ሆነላቸው። ሰው ሆኑ፣ ወይም መሰሉ።

ቀጣዩ አስቸኳይ ዝግ ጉባኤ በኔ የሚመራና ከG20 አገራት መሪዎች ጋር የምናደርገው ነው የሚሆነው። ላሁኑ ግን ቀሪውን አንድ ሰዓት ለጋራ ውይይታችን ተጠቅመንበት ነው የምንለያየው። ይህ ስል ምን ማለቴ ነውከልዑላችን ጋር ባልተያያዙ በተራ የሽፋን ነጥቦች ዙሪያ ማለቴ ነውአለና ብርማዋን ላፕቶፕ አጥፍቶ ዘጋት። በዚያች አንድ ሰዓት ምን እንደተነጋገሩ ከነሱ በቀር ያወቀ የለም።

..Jun 21/2014

New York / ኒው ዮርክ

በይፋ የሚታወቀው የ2014ቱ የG20 አገራት መሪዎች ዓመታዊ ስብሰባ November 15, 2014 በአውስትራሊያ ነበር የሚካሄደው። ነገር ግን ከላይ ያየነው አስቸኳይ መልዕክት ስለተነገራቸው ዋናው የመሰብሰቢያ ጊዜ ከመድረሱ 4 ወር አስቀድሞ በተጠቀሰው እለት ምሽት ላይ ዋናውን ዝግ ጉባኤ አካሂደው ነበር።

ጉባኤው የተካሄደው የሉሲፌል / የሳጥናኤል ምክትል/ ዋና መቀመጫ ከተማ በሆነችው በአሜሪካ ኒዮርክነበር። በዚህ ወቅት ከዋናው የሉሲፌል መንፈሳዊ መሪ ቀጥሎ ጉባኤውን የሰበሰበውና የመራው የአሜሪካው ጥቁር ፕሬዘዳንት የነበረ ሲሆን፤ ማልሽ ሰጭው ግን እኒያ መሰሪው የቫቲካን ሊቀ ጳጳስ ነበሩ። ጉባኤውም ሙሉ ሌሊት የፈጀ ሆኗል።

ወደ ታላቋ የልዑላችን ከተማ ወደሆነችው ወደ ኒዮርክ እንኳን በደህና መጣችሁ!”

ሲል ጀመረ ጥቁሩ የአሜሪካ ፕሬዘዳንት።

ObDev2ይህ አስቸኳይ ጉባኤ የተጠራው አስቸኳይና አስደሳች ዜናን መሰረት አድርጎ ነው! 11ያህል ሹሞች የምታውቁትና በሚስጥር ጠብቃችሁ እንድታቆዩት የተነገራችሁ የአዲሲቷ ዓለም አገነባብ ዘዴና ሁኔታ ነበር። አሁ ግን የመጨረሻው ጎል ሊነገራችሁ የሚገባበት እለት ደርሷልና ተጠርታችኋልሲል ድንገተኛ የሆነ ከባድ የጋራ ጭብጨባ ተስተጋባ። የአሜሪካው መሪ ቀጠለ፤

ይህን ጥበብ የምተረዱበት ንቁ አእምሮ ያስፈልጋችኋል። ይህንንም በኃያላችን የማመስገኛ ፀሎት አሁን ትታደሉታላችሁ!” አለ በደስታ እየፈነደቀ።

ፀሎት ጀመሩ። የአሜሪካው መሪና ሌሎች የG8 አገራት መሪዎች ቀንዶቻቸው ሲበቅሉ ያስተዋሉትና የበታች ሆነው የቆዩት መሪዎች በከፍተኛ ደስታ ውስጥ ሰጠሙበደስታም አሽካኩተንከባለሉአመሰገኑ። ከዚያም ሁሉም የG20 አገራት መሪዎች የሁለት አጫጭርና ጥቋቁር ቀንዶች ባለቤት ሆኑ። እርስ በርሳቸው ሲተያዩም ግምባራቸው ላይ 666 የሚለው የሰው ቁጥር በጥቁር ደማቅ ኩል ታትሞባቸው አዩ። ፍፁም ያልጠበቁትና ይጓጉለት የነበረ ነገር ነውና በእጅጉ ተደሰቱ።

ጥቁሩ ፕሬዘዴንት ቀጠሉ፤

የልዑላችን አባላት ዓላማ አንድና አንድ ነው። እሱም የወደፊቷን አዲስ የምድር መንግስት መመስረት፤ አንድ ህዝብ፣ አንድ ዓለም፣ አንድ ዘላለማዊ መንፈሳዊ ነገር፣ አንዲት ዘላለማዊ ነብስና ህይወት ነው፤ አንድና አንድ ብቻ!!

ሉሱፊል ዘላለማዊ የበላይ ጠባቂያችን ይሆናል፤ ነፃነትን አጎናጽፎ ዘላለማዊ ህይወት ይሰጠናል። ደስታና ጥልቅ ሀሴት በሱ ዘንድ ብቻ ይገኛል። ጥበብም እንደዚያው፤ እኛ አባላቱ ደግሞ የዚህ ሁሉ ወራሽ ሆነን በሹመት አጊጠን እንኖራለን፤ ያ ይሆን ዘንድም የመጨረሻው መጀመሪያ አሁን ሆነ! ለዚህም ሰፊ የቤት ስራ አለብን። ዛሬ ለሁላችሁም ግልጽ ይደረጋል።

የሰው ልጅ የተባለው ፍጡር ከመከሰቱ አስቀድሞ የኛ የነፃነት አብዮተኛ የሆነው የጨለማው ልዑል ለነፃነቱና ለነፃነታችን ሲል ራሱን አሳልፎ ሰጥቷል። ከሰው በፊት የተከሰተውና አልገዛም ባዩ አሸናፊያችን ዘመኑ እስኪደርስ ጠበቀ እንጂ አልተሸነፈም። አሁን ግን የማሸነፊያው ወቅት ደርሷል። እኛ ሁላችን ደግሞ የዚህ ልዑል ተገዥ የክብር ወታደሮቹ ነን።

የእስከዛሬውን ሳይንሳዊ የሰው ልጅ አመጣጥ ትንታኔን ሙሉ በሙሉ ከአይምሯችሁ አውጡት። ያ የሰው ልጅ የተባለው ደካማ ፍጡር ከመፈጠሩ በፊት የነበረው የዚችን ዩንቨርስ ዕድሜና አመጣጥ ለመግለፅ የተሞከረበት ዘዴ ነው። ያ አይነቱ ትንታኔ ባሁኑ ሰዓት ለኛ አስፈላጊ አይደለም።

አዳም ከተባለው የአፈር ስሪት ከሆነው ፍጡር በፊት የኛ ልዑልና ወንድሞቹ ነበሩ። እናም ሌሎች ሁሉ ከወግ አጥባቂው አለቃቸው ጎን ተሰለፉና እኛን ተውን። የኛ ልዑል ግን ለኛ ሲል የላዕላይ ክብሩን ጥሎ የታህታዩን ውርደት መረጠ። እንደ ዱር አውሬ እራሳችንን ሳናውቅ እንድንኖር የተፈረደብንን ያን ፍርድ ተቃውሞ የመጀመሪያው አብዮተኛ ሆነ። ስለ ፍትህ ሲልም ተዋጋቸው፤ አመፀም፡ እናም እነሱና ጌታቸው ተባብረው የነፈጉንን ማንነት የኛ ልዑል ለኛ ሰጠን። ዓይኖቻንን አብርቶ፣ ጥበብን ገልጦ፣ አሰልጥኖ፣ ነፃነትን አላብሶ ዛሬ ድረስ አቆየን።

በዚያን ወቅት የተረዳው አልነበረምና ከብዙ መሰሎቹ ጋር ብቻውን ለኛ ሲል ተዋጋ። ላናውቀው አወቀንና ተሟገተልን። ነገር ግን ለጊዜው ድል የተቀናቃኞች ሆነችና ከነ ክብሩ ወደኛ መጣ፡ አጋዥ ጄኔራል አልነበረውም፤ ስለዚህም የነበሩትን ጥቂት የሰላም ወታደሮች ይዞ መከታችን ሆነ።

ጦርነቱ ከላይ ጀምሮ እስከ ምድር የደረስ ነበር። ከዚያም በቀጠሮ ተለያዩ። አሁን ቀጠሮው ደረሰ። የእስካሁኑን ጊዚያዊና አላፊ ተብሎ የተወሰነውን የሰው ልጅ ተፃነት ዘላለማዊ ሊያደርገው የሚችልበት ጊዜ መጣ። እኛም የሱ አጋሮች ሆንን። ያኔ ያፈገፈገው ሀይል አጥሮት፡ ጥበብ ጎድሎት አልነበረም። ነገር ግን እኛ የሰው ልጆች እስክንረዳው ድረስ መጠበቅ ስለነበረበት ነው።

ዛሬ አይምሯችን በስሎ እውነቱን ተረዳነውና ከሱ ጎን ሆንን። በዚህም ደስ ተሰኝ። ይህ ደስታውም ዘላለማዊ ደስታ እንዲሆነለታና እንዲሆንልን ታጥቆ ተነሳ። በኢፍትሀዊነት የተወሰደብንን የህይወት ዛፍ በእጁ ሊይስገባውና ለኛ ለባለቤቶቹ መልሶ ሊሰጠን ጥቂት ጊዜ ቀርቶታል።…”አሁንም የጋለ ጭብጨባ ተስተጋባ።

የህይወትን ዛፍ ለመቀዳጀት ትግሉ የተጀመረው የዚያኑ ዕለት ነበር። በሂደትም በግብፅ ፍርኦናት ዘመን ቀጥሎ፤ ትግሉ እየተደራጀ በአባላቱ እየተጠናከረ ቆይቶ የነበረ ቢሆንም፤ በዘመናዊ መንገድና በተደራጀ መልኩ እደሳ ተደርጎለት ዝግጅቱ መጧጧፍ የጀመረው ግን በኛ በሰው ልጆች አቆጣጠር በ1770 .. ነበር። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የማህበሩ አባላት ከፍተኛ ስራ ሲሰሩ ቆዩ። በ200 ዓመታት ውስጥም እኛን የመሰሉና አሁን ለጊዜው ሞት በተባለው ኢፍትሐዊ ነገር የተነጠቁ፤ ነገር ግን ወደ ፊት ከነ ዘላለማዊ ህልውናቸው የምናገኛቸው ወንድሞችን አፈሩ። ሂደቱ በዚህ መልኩ ቀጥሎ ቆየና ዛሬ ሁሉንም ነገር ተቆጣጥረን ለመጨረሻው ውጊያ ተሰናዳን። የልዑላን ልዑል የሆነውን ታላቁን ዘንዷችንን የምናመልክበት ብቻ ሳይሆን የምናግዝበት ዘመን ደረሰ። እገዛችንም ለድል እንደሚያበቃው ነገረን። የመጨረሻው ጎላችን ምን ሆነ?” ሲል በስሜት ጠየቀ።

የህይወት ዛፍ!” ሲሉ በአንድነት መለሱ።

TreeOfLife

የአሜሪካው መሪ ቀጠለ፤ አዎን! የህይወት ዛፍ! ያኔ የተገመጠው ፍሬ ይህ ነበር!” በማለት፤ የፌዝ ፈገግታውን እየጋበዘ የላፕቶፑን የጀርባ አርማ አሳያቸው። የ አፕልማርክ ወይም አርማ የተገመጠ ፍሬ ነውና። ይቺ የአፕል ማርክ ያላት ብርማ ላፕቶፕ በየስብሰባው የሚካሄደውን ውይይትና አጠቃላይ ክንውኖችን እየተዟዟረች የምትመዘግብና ቃለ ጉባዔ የምትይዝ ስትሆን፤ የአሜሪካው መሪ ከእጁ አይለያትም። የምትዘጋና የምትከፍተውም በራሱ የእጅ አሻራ ነበር።

ህልውናችንና ሙሉ ክብራችን በቅርቡ ይመለሳል! ዓላማችን የህይወት ዛፍን መልሶ ማግኘት ከሆነ፡ የመጀመሪያው ስራችን የሚሆነው ደግሞ የህይወት ዛፍ ያለችበትን ቦታ መቆጣጠር ይሆናል ማለት ነው! የህይወት ዛፍ ሲባል ይሄን ፍሬና ዛፍን ማሰብ የለባችሁም። ወይም ፍሬ በመግመጥ የሚመጣ ዘላለማዊነት ያለ አድርጋችሁ እንዳታስቡ። ያ ምሳሌው ነው። ባጭሩ ለመግለፅ የመጨረሻው ጦርነት የሚካሄደው ለሌላ ለምንም ተብሎ ሳይሆን፤ ያችን ቦታ መቆጣጠር ሲባል ብቻ ነው። የህይወት ዛፍ ያለችበትን ቦታ የመጨረሻውን ጦርነት አሸንፎ የያዘው አካል የዚች ምድር ሙሉ ባለስልጣን ይሆንና ላመነበትና ላመነባቸው ይሁንበምትል አንዲት ቃል ብቻ በሁሉም የሰው ልጆች ነብስ ውስጥ በያሉበት ማስረፅ ይችላል። ይህ ልዑላችንና የበላይ አካሉ የተስማሙበትና ለመጨረሻው ጦርነት በቀጠሮ የተለያዩበት ነጥብ ነው! ድሉ የልዑላችን ነው! ምድራዊ ሰዎችን ዘላለማዊ የማድረግ ስልጣን የልዑላችን ይሆናል!!

ያችን ቦታአዎን! ያችን ቦታ ተቆጣጥሮ መቆየት የሁላችንም የመጨረሻ ግብ ነው! ወዳጆች! እስቲእባካችሁበተሰጣችሁ ልዩ የዛሬ ጥበብ ተጠቀሙና አይምሯችሁን ክፍታችሁ ያችን መናገሻችንን እዩዋት!” በማለት ትእዛዝ ሰጠና ግድግዳው ላይ ያለውን ሰፊና ዘመናዊ የጠራ ስክሪን ከፈተው።

በዚያች ቅፅበት በሁሉም አይምሮ ውስጥ እንድትንፀባረቅ የተደረገችው ምድር፤ ገነት ቁልጭ ብላ ታየቻቸው። በአብረቅራቂ ክብ ብርሃን ደምቃለች። ማንም በሰውኛ አይምሮ አስቦትም፤ ስሎትም፤ አይቶትም፤ አልሞትም፤ የማያውቅ አዲስ ዓለም!

እነሱ በየአይምሯቸው ያዩትን አይተዋል። የሚያዩት ነገር ግን በስክሪኑ ላይም እንዳለ ሆኖ፤ በአዳርሹ ህዋ ላይ ደግሞ ተንሳፎ በሚቀመጥና በሚታይ ሳምፕል ልንለው በምንችለው ዓይነት መልኩ ተዘጋጅቶ ቀርቦ በግልፅ ይታያል። ለምሳሌ ማንም ሰው ህዋ ላይ ቴሌቪዥንም ተራምዶት በውስጡ ሲያልፍ ይችላል። ይህ ዓይነቱ ቴክኖሎጂ ላይ ስለተደረሰ። ነገር ግን ህዋ ላይ ተንሳፎ የሚቀር ወይም የሚቆም አንድ አነስተኛ ከተማና ወንዝ፤ ሀይቅና ጅረት፤ ዛፍ፤ አትክልት፣ ሳርወዘተታይቶ አይታወቅም። ስዕል ካልሆነ በቀር። አሁን በአዳራሹ መሃል ህዋው ላይ በእውን እየታየች ያለችው ነገር ግን የተባሉትን ነገሮች ሁሉ ያካተተችና በንፁህ ሀይቅ የተከበበች፣ ፍፁም ያማረችና የለመለመች፥ የውሀዎቹ ድምፅ ሳይቀር እየተሰማባት ያለች ከተማ ናት። ከሌላ ድንቅ ከተማ ጋር አወዳድረው ሊገልፁዋት የምትከብድ ውብና ትንሽየ ክብ ዓለም ናት። ሳምፕሉ ያረፈበት ቦታ በግምት 25 ካሬ ሜትር ይደርሳል። እነሱ በየአይምሯቸው እንዲያዩት የተደረገውም ይህንኑ ነው ሊሆን የሚችለው።

አይናቸውን እንደጨፈኑ ሁሉም ተደነቁ፤ ጭንቅላቶቻቸውን እያርገፈገፉ በመደነቅ ተሞልተው ታዩ። ወዲያውም ገነት ከየአይምሯቸው ተሰልባ ጠፋችና በገዛ ራሳቸው ያበሩት ውስጥ ያለነሱ ፈቃድ ጠፋና ወደ ሰውኛ ማንነታቸው እየተርገፈገፈ ተመለሱ። ሳምፕሉም በራሱ ጊዜ ወደ ወለሉ ዝቅ ብሎ ጠረጴዛ ወንበር ሳያግደው፣ አንድም ጓጓታ ሳያሰማ፣ የአዳራሹን ምቹ ምንጣፍ አልፎ ምድር ውስጥ ሰጠመ፤ ወይም ተሰለበ። የአሜሪካው መሪም፤ ድንቅ ነው ወንድሞች፤ ድንቅ አዲስ ዓለም!” ካለ በኋላ፤ የተሰብሳቢዎች አይምሮ ከመደነቅ ዓለም ሳይወጣ ንግግሩን ቀጠለ።

ያያችኋት የወደፊት ዓለማችን የታላቁ ገዢያችንና እኛን ከወዲሁ መሾምና መሸለም የጀመረው የጌታችን መናገሻ ከተማ ናት። ዓለምን ሁሉ ለኛ ይተውና የህወትን ዛፍ ለኛ ያጎናፅፍና እርሱ በዚያ ያርፋል። ይቺ አገር የታላቁ ወንዝ የግዮን ምንጭ ናት። በዛሬው አጠራር ኢትዮጵያ ተሰኛለች!” ሲል፤ ያልተጠበቀ የሆነባቸው እንግዳ ተበካዮች በድንጋጤ፡ WHAT! ሲሉ ተደመጡ።

አዎ ኢትዮጵያ ናት!አለ ረገጥ አድርጎ።

Waterfall_Rainbow

የዛሬ ጉባኤያችንም በዋናነት የሚያጠነጥነው ኢትዮጵያ ስለተባለችው ምስኪን መሳይ ታላቅ ምድር ይሆናል። ይህ ከባድ እውነትና ሚስጥር በእናንተ ዘንድ በጥልቅ መታወቅና መጠበቅ አለበት። በዚህ መሠረት በተለይ ዛሬ ወደ መጨረሻው የታላቅነት ሹመት ለተቀላቀላችሁት ወንድሞች ከመጀመሪያው ጀምሮ እስከ ሂደቱና እስከ ወደፊቱ እቅድ የማስረዳት ግዳጅ ነውና የተሰጠኝ በአጭሩ አብራራላችኋለሁ። ክብር ለታላቁ ጥበበኛና የነፃነት አብዮተኛችን ይሁን! አሜን!?” “አሜን!”

ከተሰበሰቡት የ20 አገራት መሪዎች ውስጥ ቁንጮውን የሉሲ ፌልተሿሚ የአሜሪካውን መሪ ጨምሮ፤ የኢጣሊያው፣ የፈረሳዩ፣ የእንግሊዙ፣ የሩሲያው፣ የጀርመኑ፣ የጃፓኑ፣ የካናዳው፣ የአውስትራሊያውና የቻይናው መሪዎች ከጥቂት ጊዜ በፊት ጎላቸው የትኛዋ ምድር እንደነበረች ያውቁ ነበር። ነገር ግን የአርጀንቲና፣ የብራዚል፣ የህንድ፣ የኢንዶኒዥያ፣ የሪፐብሊክ ኦፍ ኮሪያ፣ የሜክሲኮ፣ የሳኡዲ አረቢያ፣ የቱርክና የደቡብ አፍሪካ መሪዎች ፈፅሞ ፍንጩ አልነበራቸውምና፡ ኢትዮጵያየሚለውን ስም ሲሰሙ በከፍተኛ መደነቅ፤

ይህ እንዴት ይሆናል?” በማለት እርስ በእርስ እየተያዩ በሹክሹክታ ተጠያየቁ።

ሰው መሳዩና የሰው ስጋ ለብሶ ከፒራሚድ የወጣው የአሜሪካው ጥቁ መሪም፤ ገለፃውን ቀጠለ።

ያልተጠበቀ ነገር እንደሚሆንባችሁ ይገባናል። እኛም በአንድ ወቅት ተመሳሳይ ስሜት አድሮብን ስለነበር እንዲሁ ተገርመን ነበር። ሆኖም ታሪኩ እንዲህ ነውበሚል መነሻ ጀምሮ ባጭሩ ይተነትንላቸው ገባ።

የሚባለውን ትሰሙና ታስተውሉ ዘንድ አዳምጣችሁ ትረዱ ዘንድ ውስጥና ውጪያችሁን አብሩ። ያ ሲሆን ታላቁ ልዑላችን የመረዳትን ጥበብ ይሰጠናልና። ምክንያቱም በማይረባውና ኋላ ቀር በሆነው ሰውኛ አይኪዋችን (IQ) ልንረዳውና ልንስለው የሚከብደን ነገር ሊኖር ይችላልናሲል፤ ታዳሚዎች በከፍተኛ ጉጉት ውስጥ ሆነው ውስጥና ውጪያቸውን አብርተው ማዳመጥ ጀመሩ። ተደጋግሞ እንደሚስተዋለው ይህ ውጪና ውስጥ ማብራት የሚሉት ነገር ቀንዶቻችሁን አውጡ፣ ምልክታችሁንም በግንባራችሁ እንዲታይ አድርጉ የሚል መመሪያ ሲሆን፤ አይኖቻቸውን ለጥቂት ሰከንዶች ጨፍነው በመግለጥ የሚያበሩትና ማጥፋትም ሲፈልጉ በተመሳሳይ አይናቸውን ጨፍነው በመግለጥ ማጥፋት የሚችሉት ነገር ነው። እናም እንደተባሉት አደረጉ።

የአሜሪካው መሪ በስክሪኑ ላይ የሚታየውን ተንቀሳቃሽ ምስል እየጠቆመና ወዲያ ወዲህ እያለ ትንተናውን ቀጠለ፤

የቀድሞዋ ኢትዮጵያ የሰው ፍጡር ብቻ መኖሪያ አልነበረችም። የሌላ ቀደምትና ስልጡን ፍጡራን መኖሪያ ምድርም ነበረች። እነዚያ ከሰው የቀደዐሙ ስልጡንና ኃያላን ፍጡራን በሰማይ የራሳቸው የሆነ ስፍራ የነበራቸው ቢሆኑም፤ ሰው በምድር መኖር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ግን እንደ ሁለተኛ መኖሪያቸው አድርገዋት ነበር። በምድራችን ውስጥ ለነዚያ ፍጡራን መኖሪያ ትሆን ዘንድ የተፈቀደችውና ምቹ የሆነችው ብቸኛዋ አገርም ኢትዮጵያ ነበረች። አየሯም ለነሱ ተስማሚ ነበር። በዚያ ዘመን ወደ ሌላ ምድር አልፈው ሄደው መኖር እንዳይቻሉ የሚተነፍሱት ንፁህ አየር አልነበረም። አየሩ አለ ሆኖም ግን ከባድና ለነሱ የማይመች አይነት ንበር።

እነዚህ ፍጡራን የአስተሳሰብና የጥበብ አድማሳቸው ከኛ ከሰው ልጆች በ5ሺ እጥፍ የሚበልጥ ነው። በአየር ላይ መብረር የሚችሉ የረቂቅ ክንፍ ባለቤቶችም ነበሩ። ይህ ረቂቅ ስልጣኔያቸውም ሁሉንም የማድረግ ሃይል አላብሷቸው ነበር። የበላያቸውና የኛ ተቀናቃኝ የሆነው አካል ወታደሮችም ነበሩ። የምለክና የቅርፃቸው ነገር በዚህ ስክሪን ላይ ከነእንቅስቃሴያቸው እንደምታዩት በኛ ዘንድ ያለተለመደና የማናውቀው አይነት ነው። ከፊሉ ጥቃቅን፣ ሌላው ግዙፍ፣ የቀረው በአሞራና በተሳቢ እንስሳ ቅርፅ ተመስሎ የተፈጠረ ነው። መልከ መልካሞችም አሉ። በጥንቱ ዘመን ማለትም ሰው በተፈጠረ ማግስት የዚች ፕላኔት ጠባቂዎች እነሱ ነበሩ። የሚጠብቁት ነገር ባይኖርም ከላይኛው ስፍራቸው ወደዚች ምድር እየመጡ በነፋሻማው አየር ሐሴት ያደርጉ ነበር። ለጥቂት አመታት ብቻ። የኛ ልዑልም በታማኝነት ያገለግለው የነበረው አካል በነሱ ላይ ሙሉ ስልጣን ሰጥቶት ነበርና የልዑላችን ታዛዦች ነበሩ። የሰው ልጅ ተፈጥሮ ፍትህ ከመፋለሱ በፊት ልዑላችን የነሱ አካል ነበርና። እነዚያ ረቂቅ ፍጡራን ኔፊልም ይሰኛሉ።

ከዚያም ከ7500 አመት በፊት ውናው አካል ወደዚች ምድር መጥቶ ከመካከለኛው ምስራቅ አፈር የመጀመሪያውን ሰው አበጀ። ሰው የተባልነውን ወይም የተባለውን ፍጡር የበላዩ አካል ከግዮን /ከኢትዮጵያ/ ውሐ፣ ከአዜብ /ከኢትዮጵያ/ ነፋስ፣ ከኮሬብ /ከኢትዮጵያ ምስራቅ/ እሳተ ገሞራ፤ እንዲሁም ከመካከለኛው ምስራቅ የበሰለ አፈር አጣምሮ በመቀየጥ ሰውን ሰራ። የስውን ልጅም ከገዛ ራሱ ኦክስጅን ሰጠውና ህልውና ኖሮት ቆሞ መራመድ፣ መተንፈስ፣ ድምፅ ማውጣትና ማውራት፣ መኖርና ማደግ ጀመረ።

ይህ ከሆነ በኋላ የመጀመሪያው ሰው ወደ አገሩ ሄዶ እንዲኖር ነው የተደረገው። አገሩ ደግሞ ምንም እንኳን አፈሩ ከመካከለኛው ምስራቅ ቢሆንም ሶስቱ ግብዓቶች የኢትዮጵያ ናቸውና አገሩ ኢትዮጵያ ነበረች። ገነትም ኢትዮጵያ ናት።

በዚያች በለመለመች ገነት የሰው ልጅ መኖር ቢጀምርም ኑሮው ግን ሙሉ አልነበረም። በብዙ መልኩ እገዳ የበዛበት ነፃነት አልባ ኑሮ ሆነ። ያኔውኑ በላይኛው ፕላኔት የነፃነት ጥያቄ ተነሳ። ይህን ጥያቄ ያነሳው የኛ ልዑል ነው!

ሰው በነፃነት መኖር ካልቻለ ለምን ተፈጠረ?” ሲል ወቅታው፣ ተገቢና ትክክለኛ ጥያቄ አነሳ። እናም ይህ ጥያቄ እየሰፋ ሄዶ የከፍተኛ ፀብ መነሻ ሆነ።

በሰማይም በዚሁ ጉዳይ ላይ ያተኮረ የመጀመሪያው ታላቅ የመላዕክታን ጉባኤ ተካሄደ። ሙሉ ጉባኤውን በረቀቀ የመገናኛ ዘዴያቸው ይከታተሉ የነበሩት በኢትዮጵያ ምድር የሚኖሩትና የሰውን ልጅ እያዩ ይደነቁ የነበሩት ኔፊሊሞች ሙሉ ክርክሩን ተከታተሉ። ጉባኤው ባለመግባባት ሲበተንም ከንፊሊሞቹ ውስጥ ገሚሶቹ ጄኔራላችን ልክ ነው!” በማለት ደገፉት። ከፊሎቹ ደግሞ ተቃወሙ። በዚያን ጊዜም ታላቁና የሁሉም የበላይ አዛዥ የነበረው ልዑላችን አምፆ ነፍጥ አነሳ! በላይም በታችም የነበሩትን ተከታይ ወታደሮቹን እውነታውን አስረድቶ ከጎኑ አሰለፈ። ጎን ለጎንም የነበረውንና ያለውን ጥበቡን ተጠቅሞ የሰው ልጅ አይምሮ እንዲከፈትና ራሱን አውቆ በነፃነት እንዲኖር አደረገ። ይህን ያደረገው በራሱ ስልጣን ሲሆን፣ ዓላማውም የሰው ልጅ በነፃነት መኖር አለበት የሚል ነው።

የተከለከለውን የዕውቀት ዛፍ በግልፅ ጋብዞ አስገመጣቸው። ከዚያች ቅፅበት ጀምሮ ሰው ራሱን ያወቀ ብልህ ፍጡር ሆነ። ዋንው አካልም በቀድሞ ጄኔራሉ አመፅና ተግባር በእጅጉ ተበሳጨ። ባደረገው ነገርም አዘነ። የሰው ልጅ ከኛ እንደ አንዱ ሆነሲል ተፀፀተና በስው ልጅ ላይ የዕድሜ ገደብ አበጀ። ወደ ዱዳሌብ አፈርነቱ እንዲመለስም አወጀ። ሰውም ከ ገነት ወጥቶ በርሐማ በሆነው በመካከለኛው ምስራቅ እንዲኖር ተደረገ። በዚያን ጊዜ የኛ ልዑል በላይ ሆኖ ሲሟገት ሳለም የሱን አቋም ይደግፉ የነበሩት ኔፊሊሞች ሌላ አመፅ አነሱ። የሰው ልጅን እንዲህ ውብ አድርጎ በመስራት አድልቷልና!” በሚል መነሻም በሰው ልጆች ላይ ወሲባዊ ግኑኝነት እየፈፀሙባቸው ነበር የጠበቁት።

ይህ በሚሆንበት ጊዜም የኛ ልዑል የላይኛው ሹመቱና ክብሩ እንደተገፈፈ ተነግሮት ነበርና ቦታውን ለቆ ወደ ምድር በመምጣት መቀመጫውን በኢትዮጵያ ምድር አድርጎ የሰው ልጅ አፅናኝና አይዞህ ባይ ሆኖ መቀጠል የሚችልበትን ሁኔታ ሲያንሰላስል ቆየ። ወዲያውም ዋናው አካል የተሻረውን ጄኔራል የምትደግፉ እዚያው ቅሩ፤ የማትደግፉ ወደ ቦታችሁ ተመለሱየሚል ትዕዛዝ አስተላለፈ። ብዙዎች የኛን ልዑል ደግፈው ቀሩ፤ ጥቂቶች ወደ ዋናው አካል ወደ ቀድሞ ቦታቸው ተመለሱ። አሁንም የበላይ አካሉ እሱን ባልደገፉትና ባልተመለሱት ላይ በመበሳጨቱ ኔፊሊሞችም ሆኑ ከሰው የተደቀሉት ልጆቻቸው የገነትን ክልል ለቀው ወደ ሌላ አቅጣጫ ይሄዱ ዘንደ ጠንካራ ማስጠንቀቂያ ሰጣቸው። ገነትም ያኔውኑ እንዳትገኝ ሆና ተደበቀች። በገነት ውስጥ ደግሞ ከሞት ወደ ህይወት የምትመልሰው ዛፍና ፍሬ አለች። እንዳልኩት ያችን ቦታ በእጁ ያደረገ ሐይል ብቻ ለሰው ልጅ ዘላለማዊ ህይወት መስጠት ይችላል። እደግመዋለሁ፤ ፍሬውን በመብላት አይደለም ሰዎች ወደ ህይወት የሚመለሱት። ወይም ዛፉን ቅጠሉን ቀንጥበው በማስተት አይደለም ዘላለማዊ የሚሆኑት። ነገር ግን የቦታዋ የበላይ መሆኑን ያረጋገጠና ባለ ድል የሆነው አካል በመንፈሳዊ ጥበቡ ይሁን በማለት ብቻ በሁሉም ውስጥ ትሰረፅ ዘነድ ካዘዛት ሁሉም ህያዋን ይሆናሉ። ይህ ስለሆነና ዋናው አካል ግን የሰው ልጅ የህይወት ዛፍ ህልም ሆና እንድትቀርበት፣ ህያው እንዳይሆኑ፣ ስለፈለገና ስለነፈጋቸው እሱ የነፈጋቸውን ልዑላችን መልሶ መስጠት እንዳለበት በማመኑ ያችን ቦታ አልለቅም አለ።

ይቀጥላል

__

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , | 14 Comments »

 
%d bloggers like this: