የ CBS TVዋ እህታችን ታዋቂውን የቅርጫት ኳስ ተጫዋች፡ ሻኪል ኦኒልን እና የሥራ ባልደረባዋን በበርበሬ በመቃጠል/ባለመቃጠል ሩጫ ረታቻቸው፤ ጎበዝ፡ እህታችን! አገርሽንም እግረ-መንገድሽን ማስተዋወቅሽ ደስ ይላል። በርበሬ ለዘላለም ይኑር!
በርበሬው አጨሰኝ…!
በ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)
ያግድም አግድም ሔጄ ብዙ ተመክሬ አልሰማም ሰላልኩኝ፤
በእናቴ ምድጃ ቁልቁል ተደፍቼ በርበሬ ታጠንኩኝ፤
በዐይኖቼ እያነባሁ ባ‘ፌ እያስነጠስኩኝ“
እንደምንም ብዬ እናቴን በመሓል እንዲህ ስል ጠየ‘ኩኝ!
‘አባዬ ልጅ ሳይኾን በ‘ድሜ እየበለጠን፤
ምን አጥፍቶ ይኾን ሲጋራ የሚታጠን…?’
ብዬ ብጠይቃት፥
ፀጉሬን ጨምድዳ ደፍቃኝ ወደ ጭሱ፤
“ዝም ብለህ ታጠን ለየት ይላል የሱ፤
ከሕሊናው ዓለም ሲጣላ ከራሱ፤
ገላጋይ አ‘ቶ ነው ባ‘ፉ እና ባፍንጫው የሚወጣው ጭሱ፤
እናት እና አባቱ እንዳንተ በጊዜ ቢያጥ‘ኑት በበርበሬ፤
ብርቅ አይኾንም ነበር ለትንባሆ ዛሬ!
ዛሬም ያንተን ጥጋብ ልክ ካላገባው የበርበሬ ጭሱ፤
ትንሽ ከፍ ስትል ትብሳለህ ከ‘ሱ!፤
ቶሎ ካልተዘጋ የአመል በራፍህ፤
ይገባል ሲጋራ በመሀል ጣትህ፤“
አለችና እናቴ ደግማ ወደጭሱ አንዴ ብትመልሰኝ፤
የወደፊቱን ሱስ ነቅሎ እያስነጠሰኝ፤ ሲጋራ እንዳላጨስ በርበሬው አጨሰኝ!!