Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘ቋንቋ’

Seattle Metro Transit Workers Sue over Order to Limit Use of Ethiopic Amharic Language

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 25, 2023

🚌 የሰሜን አሜሪካዋ ዋሽንግተን ግዛት ሲያትል ከተማ ሜትሮ ትራንዚት (አውቶብስና ባቡር) ሰራተኞች የግዕዝ አማርኛን አጠቃቀም ለመገደብ በተሰጣቸው ትዕዛዝ ላይ ክስ/አቤቱታ አቀረቡ

💭 የአፍ መፍቻ ቋንቋችን በዲ.ኤን.ኤ አችን/በመቅኒያችን ውስጥ ነው ፣ ይህ በደማችን ውስጥ ነው፣ ባህላችን ይህ ነው!” አለ ገብረ ሥላሴ።

የሜትሮ ትራንዚት ሰራተኞች በግል ብቻ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸውን አማርኛን እንዲናገሩ ታዘዋል

ኢትዮጵያውያን በሲያትል ከተማ ዙሪያ እ.አ.አ ከ1960ዎቹ መጨረሻ እና ከ1970ዎቹ መጀመሪያ ጀምሮ ኖረዋል፤ ወደ ፲፪/12 የሚጠጉ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እና የትዳር ጓደኞቻቸው ወደ አሜሪካ በመምጣት ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ በማሰብ የኮሌጅ ዲግሪ አግኝተዋል። ያ በ1974 የሀገሪቱ ንጉሠ ነገሥት ከስልጣን ሲወርዱ ኢትዮጵያ የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ስለገባች፤ በውጭ የሚገኙት ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች እና የከተማ አስተዳደር ባለሙያዎቹ ወደ መጡበት ወደ ኢትዮጵያ በመመለሱ ረገድ ‘እንታጎራለን’ የሚል ስጋት ስላደረባቸው እዚያው በሲያትል ቀርተዋል።

እ.ኤ.አ. በ1980 የወጣው የስደተኞች ህግ ከፀደቀ በኋላ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ከጦርነት፣ ከፖለቲካ ስደት፣ ሰፊ ድርቅ እና ረሃብ ሸሽተው በመጨረሻ በሲያትል ሜትሮፖሊታን አካባቢ እንደ ስደተኞች ሰፍረዋል።

በ2021 የሕዝብ ቆጠራ ቢሮ ግምት መሠረት ዛሬ፣ ወደ ሃያሁለት ሺህ/ 22,000 የሚጠጉ ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሲያትል አካባቢ ይኖራሉ። እ.ኤ.አ. በ2015 የወጣው የህዝብ ቆጠራ ቢሮ መረጃ ደግሞ አማርኛ የሚናገሩ ሰዎችን ቁጥር ወደ አስራ አራት ሺህ አምስት መቶ ሰባ አምስት/14,575 ያህሉ ሲሆን አርባ ስድስት በመቶ/46% ያህሉ ደግሞ እንግሊዘኛ የሚናገሩት “በጣም ጥሩ” ከሚለው ያነሰ ነው።

አቤቱታ አቅራቢዎቹ ኢትዮጵያውያን፤ “ብዙ ሐበሻ በሚኖርባት በሲያትል ከተማ አማርኛ ቋንቋ በመናገራቸው ብቻ እንደ “ሲጋራ አጫሽ” ቆሻሻ መቆጠራቸው አሳፋሪና ወራዳ የሆነ ተግባር ነው!”፤ ይላሉ።

ቀጥለውም፤ “የሲያትል ከተማ አሜሪካውያን ምስራቅ አፍሪካውያንን የሚያከብሩ አይመስለኝም፣ እንደማንኛውም ሰው ጠንክረን እንሰራለን ነገር ግን በቀኑ መጨረሻ ላይ ክብር አናገኝም፤ ይህ ጥሩ አይደለም!” ብለዋል አቶ ፍሰሃ።

የእኔ እይታ፤ ይህ ቀላል የሆነ ጉዳይ አይደለም። በርግጥ አማርኛ ቋንቋን የማይሰማ ባልደረባቸው በአቅራቢያቸው ካለ እንግሊዝኛ እንጂ አማርኛ መጠቀም የለባቸውም። ነገር ግን ሐበሾቹ እርስበርሳቸውም ሆነ አማርኛ ከሚናገር መንገደኛ/ ጎብኝ ጋር በአማርኛ ቢነጋገሩ በጭራሽ ሊተቹ ወይንም ሊወነጀሉ አይገባቸውም። እነርሱም እኮ ውጭ አገር በሥራ ቦታቸው እያሉ እርስበርሳቸው በእንግሊዝኛ፣ በጀርመንኛ፣ በፈረንሳይኛ ወዘተ ነው በየጊዜው የሚነጋገሩት። እኔ እስከ ሰባት ቋንቋዎችን እናገራለሁ፤ በየቀኑ ብዙ ከተለያዩ ሃገራት የመጡ እንግዶች፣ ደንበኞች ወይንም ቱሪስቶች ጋር በየቋንቋቸው የመነጋገር እድሉ አለኝ። አሰሪዎቼ በዚህ በጣም ደስተኞች ናቸው፤ እንዲያውም ተቋሙን ተወዳጅ አድርገውታል። ታዲያ የሲያትል ወገኖቻችን ከሜክሲኮ የመጣ አንድ ቱሪስት አውቶብስ ላይ ቢሳፈርና በስፓንኛ ቋንቋ ቢያናግሩት ምን ክፋት አለው? ከጥቅም ሌላ እንዴት ‘አድሏዊ’ ሊሆን ይችላል?

ጠለቅ ብለን ስናየው ጉዳዩ መንፈሳዊ ነው፤ አገራችን በአሁን ሰዓት እያካሄደች ያለውን መንፈሳዊ ውጊያ የሚያንጸባርቅ ነው። ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ እንዳወሳሁት፤ ሉሲፈራውያኑ ሮማውያን (ላቲን) በአክሱማዊቷ ኢትዮጵያ ላይ ጂሃዳቸውን ካወጁባቸው ምክኒያቶች አንዱ ቋንቋን የሚመለከት ነው። ሮማውያኑ ላቲን ባልሆኑ ቋንቋዎችና ፊደሎቻቸው ላይ ጦርነት ከከፈቱ ውለው አድረዋል።

ለምሳሌ በአውሮፓ እንኳን ጀርመናዊ የሆኑት የሰሜን አውሮፓ ሕዝቦች፤ ብሪታኒያውያን፣ ስካንዲናቪያውያን፣ አይስላንዳውያን ከ700 እስከ 1100 ክፍለ ዘመናት ድረስ)ላቲን ያልሆኑትንና፤ “ሩኒክ/ሩንኛ/Runic የተሰኙትን ጥንታዊ ፊደላት ነበር ሲጠቀሙ የነበሩት፤ ነገር ግን ሮማውያኑ ላቲኖች የካቶሊክን እምነት እያስፋፉ እግረ መንገዳቸውንም የላቲን ፊደላቸውን በሰሜን አውሮፓውያኑ ላይ አራገፉ። አሁን ከምስራቅ አውሮፓ ውጭ መላዋ አውሮፓ ቋንቋዎች ደሃ የሆነውን የላቲንን ፊደል ነው የሚገለገሉት። በምስራቅ አውሮፓም ዛሬ በዩክሬይን የሚካሄደው ጦርነት አንዱ ተልዕኮ በሲሪሊክ ፊደል የሚጻፈውን የዩክሬን ቋንቋን ወደ ላቲን መቀየር የሚለው ነው። ከሃያ ዓመታት በፊት በዩጎዝላቪያ ጦርነቱን ከከፈቱ በኋላ ነበር የዩጎዝላቪያ ብሔራዊ ቋንቋ የነበረውንና በሲሪሊክ ፊደላት ሲጻፍ የነበረውን የ’ስርፕስኮ-ህርባትስኪ/ሰርቦ-ክሮኤሺያን’ ቋንቋ በሰርቢያ እና በክሮኤሺያ(ህርባት (ከረባት ከክሮኤሺያ የመጣ ነው)) መካከል በመከፋፈል ኦርቶዶክስ ሰርቢያ በራሷ የሲሪሊክ ፊደላት ቋንቋውን መጻፉን ስትቀጥል ካቶሊክ ክሮኤሺያ ግን የላቲንን ፊደል መጠቀሙን መርጣለች።

በካውካስ ተራሮችም በአርሜኒያ እና በአዘርበጃን መካከል የሚታየው ግጭት መንስዔ እና ዒላማ ሃይማኖትና ቋንቋ ነው። በላቲን ቋንቋዋን የምትጽፈውና የቱርክ ሳተላይት የሆነችው ሙስሊም አዘርበጃን ላቲኑን ስትመርጥ አርሜኒያ ደግሞ በግዕዝ ፊደላት አነሳሽነት የተገኘውን የአርሜኒያ ፊደል ትጠቀማለች። ኢትዮጵያም፣ ሩሲያም፣ ዩክሬይንም፣ ሰርቢያም፣ አርሜኒያም ሁሉም የኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ሃገራት ናቸው።

ታዲያ አሁን በሮማውያኑ ላቲኖች ድጋፍ ፋሺስቱ ጋላ-ኦሮሞ አገዛዝ በኢትዮጵያ እያካሄደ ያለውና በዘር፣ በሃይማኖት፣ በባሕል፣ በቋንቋና በመላ ሕልውና ላይ ያተኮረው ጂሃድ አንዱ ዒላማ የግዕዝን ቋንቋ/ፊደላት አጥፍቶ ላቲንን ማንገስ ነው። የእነዚህ አረመኔዎች ዒላማዎች በዋናነት ‘አማራ’ ፣ ‘ትግሬ’ ፣ ‘ጉራጌ’ ፣ ጋሞ እና ‘ወላይታ’የተባሉት ነገዶች ሳይሆኑ ግዕዝ፣ ኢትዮጵያ እና ተዋሕዶ ክርስትናዋ ናቸው። ታዲያ እራሳቸውን ዛሬ፤ ‘አማራ’ ፣ ‘ትግሬ’ ፣ ‘ጉራጌ’ ፣ ጋሞ እና ‘ወላይታ’ እያሉ የሌለ ማንነትንና ምንነትን እንደ አዲስ ለመፍጠር የተነሳሱት ኢትዮጵያውያን በአክሱማዊው ኢትዮጵያዊነታቸው፣ በአጋዚያንነታቸው፣ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የመንፈስ ማንነታቸውና ምንነታቸውና በግዕዝ ፊደላት ባለቤትነታቸው በአንድ ላይ ተነስተው እስካልታገሉ ድረስ ከሃዲው ጠላት ጋላ-ኦሮሞ እና ላቲናውያኑ ፈጣሪዎቹ እየፈነጩበት፣ አፓርታዳዊ አድሎ እየፈጸሙበት፣ እያሳደዱትና እየገድሉት ይኖራሉ።

👉 የሚገርም ነው፤ ሩኒክ/ሩንኛ/Runic ፊደላትም አንዳንዶቹ የግዕዝን ፊደላት የመሳሰሉ ናቸው፤

💭 Metro Transit workers ordered to speak native language only in private

👉 Courtesy: The Seattle Times.

In spring 2021, King County Metro supervisor Daniel Fisseha asked his colleague, Berhanemeskal Gebreselassie, to print something for him from his computer. He made the request in Amharic; both men are originally from Ethiopia.

On May 5 that year, their boss, Riceda Stewart, called the two longtime employees into her office. She told them that she and her superior, Dennis Lock, had received a complaint from an operator, who reported feeling uncomfortable with their use of their native language. Stewart told them they were not “presenting and acting like a professional,” according to an investigation conducted by Metro’s Office of Equal Employment Opportunity. Going forward, if they wanted to speak Amharic, they should do so only in a private room, they were told.

RELATED Transit fare inspections are upheld by WA Supreme Court

That act was hostile and discriminatory, the EEO investigation concluded, creating “an atmosphere of inferiority, isolation and intimidation.” By implementing such a rule specifically targeted to two Amharic speakers, Metro was sending an “overt” message “that their national origin identities made people uncomfortable and were not appropriate in the workplace, statements that are subjectively and objectively offensive and discriminatory.”

The men, the report concluded, had grounds to sue.

With the damning EEO report in hand, the two men filed a lawsuit in King County Superior Court last month, asking for damages and attorney’s fees determined in court, and that Metro adopt policies against language discrimination. The case was recently reassigned to federal court, in the Western District of Washington.

“Our native language is in our DNA,” said Gebreselassie. “That’s our blood. That’s our culture.”

The basic arc of events is largely undisputed. Lawyers with the King County Prosecuting Attorney’s Office acknowledge that Fisseha and Gebreselassie were told they should “be more discreet and use a separate room when speaking in Amharic to each other” in response to a complaint.

RELATED Metro Transit worker whose video recording got King County deputies fired in 2015 alleges retaliation

Defendant Stewart and Lock also acknowledged to EEO investigators that they’d received the complaint and had told Fisseha and Gebreselassie to use a private room when speaking Amharic, although they disagree on who came up with the plan. Their focus, they said, was on making the operator feel more comfortable.

But in making that their goal, the two bosses failed to consider how it would make Fisseha and Gebreselassie feel.

“Mr. Lock and Ms. Stewart may very well have been thinking about [the complainant’s] comfort when they agreed to this course of action, but the comfort they wanted to provide was discriminatory against employees who speak a language other than English,” the EEO report concluded.

In a statement, Metro spokesperson Jeff Switzer said the agency works to build a healthy environment free from harassment or discrimination.

“It is not, nor has it ever been, Metro’s policy, practice or culture to require people to speak only English,” Switzer said. “We see this as a single, regrettable incident, rather than a rule, and we took swift steps to correct the behavior with the supervisors, including requiring appropriate King County training.”

Fisseha and Gebreselassie immigrated to the Seattle area from Ethiopia in the early 2000s, becoming American citizens several years later. Both started working for Metro as bus operators in 2008 before becoming supervisors — training and scheduling drivers — roughly 10 years after that.

Getting to that level is a source of pride, particularly for Gebreselassie. As an immigrant, he said he has a chip on his shoulder.

“We have to prove ourselves every day,” he said.

After the meeting, the two men requested that the policy be put into writing, which they never received. Shortly after, they filed a complaint with the EEO office.

Fisseha and Gebreselassie allege they were retaliated against for complaining — spurring them to take leaves of absence and later move to different departments with less desirable shifts, including overnight. In its response to the complaint in federal court, Metro denies any retaliation occurred and said the choice to move departments was the two men’s, pointing out that Fisseha returned to work under Stewart again in 2022.

Regardless, Fisseha and Gebreselassie said they were racked with anxiety following the interaction. Rumor spread among Metro’s diverse staff, giving workers pause whenever they slipped into their native languages.

“Sometimes you start talking and you have that feeling of, ‘Well now I have to always watch where I’m at’,” said Gebreselassie.

Ethiopians have lived in the Seattle region since the late 1960s and early 1970s, when about two dozen university students and their spouses came to the United States to earn college degrees with the intention of returning home. That changed with the deposition of the country’s emperor in 1974, sparking the Ethiopian Civil War and leaving Ethiopian students and urban professionals abroad stranded and fearful of returning.

With the passage of The Refugee Act of 1980, thousands of Ethiopians and Eritreans would ultimately settle in the Seattle metropolitan area as immigrants and refugees fleeing war, political persecution, widespread drought and famine.

Today, about 22,000 people of Ethiopian ancestry live in the Seattle area, according to 2021 Census Bureau estimates. Census Bureau data published in 2015 puts the number of people here who speak Amharic at home at about 14,575, with about 46% reporting they speak English less than “very well.”

With such a large population in Seattle, and presence within Metro, being treated like a “cigarette smoker” for using Amharic, was demeaning, the men said.

“I don’t think they respect East Africans,” said Fisseha. “We work hard like everybody else, but at the end of the day, we don’t get respect.”

______________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Life | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

በግእዝ ቋንቋ የምናደርገው ጸሎት በአማርኛ፣ በትግርኛ፣ በእንግሊዝኛና በሌሎች ቋንቋዎች ከምናደረገው ጸሎት የተሻለ ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 13, 2022

💭 በግእዝ ቋንቋ የምናደርገው ጸሎት በአማርኛ፣ በትግርኛ፣ በእንግሊዝኛና በሌሎች ቋንቋዎች ከምናደረገው ጸሎት የተሻለ ነው። ቃላቱን በትርጉም ደረጃ ባንረዳቸውም እንኳ የድምጽ አጠራሩ/አገላለጹ ግን ከየትኛውም ቋንቋ የላቀ መንፈሳዊነት ነው ያለው።

በአክሱማዊቷ ኢትዮጵያ ላይ የተከፈተው የዘር ማጥፋት ጦርነት አንዱ ዓላማ የግዕዝ ቋንቋን ሙሉ በሙሉ ማጥፋት ነው። አንዳንድ የትግራይ ሜዲያዎች ሰሞኑን በግዕዝ ፋንታ በጨፍጫፊዎቻችን እስማኤላውያን አረቦች ቋንቋ፤ በአረብኛ ዜናዎችን መስራት ጀምረዋል። ዋይ! ዋይ! ዋይ! ቀደም ሲል በኤርትራም እንዲህ ነበር የተደረገው። እንቁላል ቀስበቀስ በእግሩ ይሄዳል! ዓላማው በመጀመሪያ ኢትዮጵያዊነትን፣ ቀጥሎ የግዕዝ ቋንቋን በመጨረሻም ተዋሕዶ ክርስትናን በመንጠቅ የዲያብሎስ ልጅ ማድረግ ነው። እንግዲህ የዋቄዮ-አላህ ጭፍራው የምኒልክ ተልዕኮ እየተሳካ ነው ማለት ነው። ዛሬ ኢትዮጵያዊነታቸውን የተነጠቁት ክርስቲያን ‘ኤርትራውያን፤ “መርሃባ!፣ ምሽ አላህ! ፣ ሹክራል! ላ! ላ! ወዘተ” ሲሉ ይሰማሉ። አረብኛ፣ ኦሮምኛ፣ ሶማልኛ፣ ኪስዋሂሊ፣ ዮሩባ፣ የሰሜን አውሮፓ ቋንቋዎች ወዘተ ደግሞ በድምጽ፣ በአነጋገር፣ በአጻጻፍ፣ በአገባብ አጋንንታዊ ይዘቶች ያሏቸው ናቸው። ሱዳንና ግብጽም እኮ በዚህ መልክ ነበር ቀስበቀስ አረብ እና ሙስሊም የሆኑት። እግዚኦ! ከዚህ ዓይነት ውድቀት ያድነን! 😠😠😠 😢😢😢

በርግጥ ቋንቋን እግዚአብሔር አልፈጠረም፤ በቋንቋ መንግስተ ሰማያት አይገባም፡ ነገር ግን የመጀመሪያው አዳምም ለ ፯ ዓመታት በገነት ሳለ በፀሎት ሲተጋ የነበረውና ከሄዋን ጋር ይነጋገርበት የነበረው የመጀመሪያው ቋንቋ ግእዝ ስለሆነ እርስበርስ ለመግባባት እንችል ዘንድ ሁላችንም አሁን ግእዝ ቋንቋን ማወቅ ሊኖርብን ነው።”

አዎ! ዲያብሎስ በቋንቋ እርስበርሳችን ተጨፋጭፈን ኢትዮጵያዊውን የግዕዝ ቋንቋ፣ ፊደል ወይንም ልሳን እንድንከዳት ይሻል፤ ኢትዮጵያዊ ባልሆኑትና ምንም ዓይነት መንፈሳዊነት በሌለባቸው በእንግሊዝኛ፣ በአረብኛ ወይንም በኦሮምኛ ቋንቋዎች እየተነጋገርን መንፈሳችንን እንድናዳክም እየሠራ ነው። ታዲያ በፍጻሜ ዘመን፣ ለድሉ ጥቂት ሰዓት በቀረን በዚህ ወቅት ይህ አሳዛኝ ክስተት ከመከሰቱ በፊት ፈጥነን ግእዝ ቋንቋን መማር ይኖርብናል።

ግእዝ የእግዚአብሔር ቋንቋ ነው ተብሎ በትዉፊት ይነገራል ❖

ትውፊታዊ ታሪኩ

ግእዝ የእግዚአብሔር ቋንቋ ነው ተብሎ በትዉፊት ይነገራል። ፍጥረታት በሐሌዎ’ በነቢብና በግብር የተፈጠሩ ሲሆን በተለይ ነቢቡ (ንግግሩ) ግእዝ ነበር ብለዉ የሚከራከሩና የራሳቸውን ማስረጃ የሚያቀርቡ ሊቃውንት አሉ። ግእዝ የመጀመሪያ ቋንቋ ነው ስንል አዳም ማለት ያማረ የተዋበ ማለት ሲሆን አባቶቻችን በመንፈስ ቅዱስ እየተመሩ ከጻፏቸው መጻሕፍት እና ሌሎች ድርሰቶች ተነስተን ቅዱስ ገብርኤል “ንቁም በበህላዌነ” ብሎ ሠራዊተ መላእክትን ያረጋጋው በግእዝ ነው፤ አዳምም ለ ፯ ዓመታት በገነት ሳለ በፀሎት ሲተጋ የነበረውና ከሄዋን ጋር ይነጋገርበት የነበረው ቋንቋ በግእዝ ነው በማለት ቋንቋውን የመላእክትም የሰውም መግባቢያ ያደርጉታል።

ግእዝ የአዳምና ሔዋን (የተፈጥሮ ቋንቋ) የመጀመሪያው መነጋገሪያ ልሳን መኾኑ ለማረጋገጥ ከሚያቀርቧቸው ፲ ምክኒያቶች መካከል

፩ኛ. የ ”ግእዝ” የጥሬ ዘሩ ቃል ትርጉም፡ “መጀመሪያ”, “ነፃ” እና “የጥንት ተፈጥሮ ጠባይ ወይም ባህሪይ” ማለት መኾኑ

፪ኛ. የእያንዳንዱ ፊደል የመጀመሪያ ቅርጽ አፍ ሳያስከፍት በድን በኾነው በተፈጥሮ ድምፅ ብቻ የሚነገር መኾኑ

፫ኛ. የፊደሉ መነሻ “አ” “አዳም” በሚል ቃል በወንድና ሴት ጾታ ለተፈጠሩት ለመጀመሪያዎቹ ሰዎች መጠሪያ መኾኑ

፬ኛ. በሰባት ብዛት የሚወሰን ቁጥር፤ የመለኮታዊ ሥራ ምሥጢር እንዳለበት ስለሚታመን፤ እያንዳንዱ ፊደል፤ በሰባት ስሞች ድምጾችና መልኮች ተለይቶ የሚታወቅና የሚነገር መኾኑ

፭ኛ. ሌሎቹ የሰዎች ቋንቋዎችና ፊደሎቻቸው በተናጋሪዎቻቸው ሕዝቦች ወይም ጎሣዎች ስም ለምሳሌ፤ ዐማርኛ፤ በዐምሓሮች፤ ትግርኛ በትግሬዎች፣ ኦሮምኛ በኦሮሞዎች፣ ሶማልኛ በሶማሌዎች፣ ዕብራይስጥ በዕብራዊያን፤ ዐረብኛ በዓረቦች፣ እንግሊዝኛ በእንግሊዞች፣ ቻይንኛ በቻይኖች ስም ሲጠሩ “ግዕዝ” ግን በራሱ ብቻ የሚጠራ መኾኑ

፮ኛ. በ ”አ” ጀምሮ በ “ኦ” የሚፈጸም ፊደል ያለው እርሱ፤ ግእዝ ብቻ ከመኾኑ ጋር “አልፋና ኦሜጋ፤ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ” ብሎ፡ ኃላ “ኢየሱስ ክርስቶስ” ተብሎ፤ ራሱን በሰውነት የገለጸው “እግዚአብሔር” በዚህ ስሙ የታወቀበትና አምልኮቱ የሚፈጸምበት ቋንቋና ፊደል ኾኖ በሕያውነት እስከዛሬ መቀጠሉ

፯ኛ. በምድር ላይ የሚኖሩ የሰው ልጆች ኹሉ፡ ተወልደው በሕፃንነታቸው መናገር በሚጀምሩበት ጊዜ ቋንቋቸውና ፊዲፈላቸው የተለያዩ ሲኾኑ፤ አፋቸውን መፍታት አባቶቻቸውናና እናቶቻቸውንም ለይተው መጥራት የሚጀምሩበት “አባባ”፤ “እማማ!” የሚባሉት ቃላት “አብ አብ አብ”፤ “እም እም እም” የተባሉት፤ ትርጉማቸው፡ “አባት አባት አባት”፡ “እናት እናት እናት” የኾነውን ቀጥታ የግእዙን ቃላት መኾኑ ናቸው።

፰ኛ. «ግእዝ» የሚለው ቃል እራሱ አንደኛ፣ የመጀመሪያ ማለት ነው። የሰው ልጅ የመጀመሪያ የሆነው ቋንቋ “አንደኛ” ቢባል ይስማማዋል።

፱ኛ. የዚህ ቋንቋ የመጀመሪያው ተናጋሪ ሰው አዳም ነው። የዚህ ሰው ስም በቋንቋው ትርጉም ሊኖረው ይገባል። በግእዝ «አዳም» ማለት ያማረ ማለት ነው።

፲ኛ. ሌላው ነገር የግእዝ ፊደላት ከአምላክ የተገኙ ናቸው ለዚህም የአዳም ሶስተኛ ትውልድ የሆነው ሄኖስ በሰማይ ገበታ እንዳያቸው አባቶች ይናገራሉ።

አማርኛ ቋንቋ ከግእዝ ያገኛቸውን በሙሉ ይዞ ሌሎች ፯ ፊደላትን በመጨመር ግእዝ ፳፮ ሲሆን አማርኛ ደግሞ ፴፫ ነው “ቨ”ን ሳይጨምር ማለት ነው።

የግእዝን ፊደሎች ትርጉም ስንመለከት

ሀ፦ ብሂል ሀልዎቱ ለአብ እምቅድመ ዓለም ፥ የአብ አኗኗሩ ከዓለም በፊት ነው

ለ ፦ ብሂል ለብሰ ሥጋ እምድንግል ፥ ክርስቶስ ከድንግል ሥጋን ለበሰ

ሐ ፦ ብሂል ሐመ ወሞተ ፥ ስለኛ ታመመና ሞተ

መ፦ ብሂል መንክር ግብሩ ለእግዚአብሔር ፥ የእግዚአብሔር ሥራው ድንቅ ነው

ሠ ፦ ብሂል ሠረቀ በሥጋ ፥ በሥጋ ተገለጠ

ረ ፦ ብሂል ረግዓት ምድር በቃሉ ፥ ምድር በቃሉ ረጋች

ሰ ፦ ብሂል ሰብአ ኮነ እግዚእነ ፥ ጌታችን ሰው ሆነ

ቀ ፦ ብሂል ቀዳሚሁ ቃል ፥ ቃል መጀመሪያ ነበር

በ ፦ ብሂል በትሕትናሁ ወረደ ፥ ጌታችን በትሕትናው ወደኛ ወረደ

ተ ፦ ብሂል ተሰብአ ወተሰገወ ፥ ጌታችን ሰው ሆነ

ኀ ፦ ብሂል ኀያል እግዚአብሔር ፥ እግዚአብሔር ኀያል ነው

ነ ፦ ብሂል ነስአ ደዌነ ወጾረ ሕማመነ ፥ መከራችንን ያዘልን ሕመማችንን ተሸከመልን

አ ፦ ብሂል አእኵቶ ወእሴብሖ ለእግዚአብሔር ፥ እግዚአብሔርን ፈፅሜ አመሰግነዋለሁ

ከ ፦ ብሂል ከሃሊ እግዚአብሔር ፥ ጌታችን ቻይ ነው

ወ ፦ ብሂል ወረደ እምሰማይ ፥ ጌታ ከሰማይ ወረደ

ዐ ፦ ብሂል ዐርገ ሰማያተ ፥ ወደ ሰማይ ዐረገ

ዘ ፦ ብሂል ዘኵሎ ይእኅዝ እግዚአብሔር ፥ ጌታ ሁሉን የሚይዝ

የ ፦ ብሂል የማነ እግዚአብሔር ገብረት ኃይለ ፥ የጌታ ቀኝ እጅ ኃይልን ታደርጋለች

ገ ፦ ብሂል ገብረ ሰማያተ በጥበቡ ፥ ጌታ በጥበቡ ሰማያትን ሠራ

ጠ ፦ ብሂል ጣዕሙ ወታእምሩ ከመ ኄር እግዚአብሔር ፥ ጌታ ቸር እንደሆነ ቅመሱና ዕወቁ

ጰ ፦ ብሂል ጰራቅሊጦስ መንፈሰ ጽድቅ ፥ ጰራቅሊጦስ እውነተኛ መንፈስ ቅዱስ ነው

ጸ ፦ ብሂል ጸጋ ወክብር ተውህበ ለነ ፥ ጸጋ እና በረከት ተሰጠን

ፀ ፦ ብሂል ፀሐይ ጸልመት በጊዜ ስቅለቱ ለእግዚእነ ፥ ጌታ በተሰቀለ ጊዜ ፀሐይ ጨለመች

ፈ ፦ ብሂል ፈጠረ ሰማየ ወምድረ ፥ ጌታ ሰማይ እና ምድርን ፈጠረ

ፐ ፦ ብሂል ፓፓኤል ስሙ ለአምላክ ፥ ፓፓኤል የአምላክ ህቡዕ ስም

ትርጉማቸዉ ይሄን ይመስላል።

ስለዚህ ግእዝ የአዳም ቋንቋ ነው የሚለው መላምት የበለጠ ጥንካሬ አለው

አባቶቻችን በመንፈስ ቅዱስ እየተመሩ ከጻፏቸው መጻሕፍት እና ሌሎች ድርሰቶች ተነስተን ፍቺውን ስንመለከት ደግሞ ግእዝ (የዜማ ስም፥ ግእዝ፣ እዝል እና አራራይ። የፊደል ስም ሀ ፦ ግእዝ ሁ ፥ ካዕብ ሂ ፥ ሳልስ …… ) በመጽሐፍ ቅዱስ ዘፍ 11 ፥ ፮ ላይ እግዚአብሔርም አለ ” እነሆ እነርሱ አንድ ወገን ናቸው ለሁሉም አንድ ቋንቋ አላቸው” ይላል።

______________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

በሃገራችን ስልጣኑን የያዙት ባዕዳኑ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊነት በተለይ በግዕዝ ቋንቋ ላይ ነው ጦርነት የሚያካሂዱት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 12, 2019

ጦርነቱ በሌሎች “ኩሽቲክ” በተባሉት ቋንቋዎች ላይ አይደለም

ከቀናት በፊት በአፍሪቃ እና አፍሪቃውያን ላይ ትኩረት ባደረገ (Afrocentric) በአንድ ጉባኤ ላይ ተገኝቼ ነበር። የጉባኤው አዘጋጆችና ተሳታፊዎች በብዛት ጥቁር አሜሪካውያን ነበሩ። ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያን ሃብታም ታሪክ፣ ባሕልና ቋንቋ የሚያዳንቁ ድርሰቶች ቀርበው ሳይ ከፍተኛ ኩራት ተሰምቶኝ ነበር። አጋጣሚውን በመጠቀም ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነትን በማስመልከት በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ምን እየተካሄደ ስላለው የጎሳ እብደት ለጉባኤው ተሳታፊዎች ሳወሳላቸው ሁሉም በመገረም እራሳቸውን ይነቀንቁ ነበር። ስለ ኢትዮጵያ ቋንቋና ጽሑፍ፣ ስለ ተዋሕዶ እምነትና ነጮቹ ድብና አጋዘን እያደኑ በሚኖሩበት ዘመን ስለተገነቡት ዓብያተ ክርስቲያናት ብዙ ካወሳሁ በኋላ፤ ዛሬ “ኦሮሞ ነን” የሚሉ የኢትዮጵያውናን እና የጥቁር ሕዝቦች ጠላቶች ከአፍሪቃውያን ኩራት ከግዕዝ ይልቅ የአውሮፓውያኑን ፊደል በመውሰድ ፀረኢትዮጵያ እና ፀረኢትዮጵያውያን የሆኑ የጥላቻ መጽሐፍትንና ትረካዎችን አሳፋሪና ፋሽስታዊ በሆነ መልክ ለማተም መብቃታቸውን ገለጽኩ። የሚገርም ነው፤ አብዛኛዎቹ የጉባኤው ተካፋዮች ይህ መረጃ አልነበራቸው፤ እጅግ በጣም ነበር ያሳፈራቸው። “በ2019 .ም እንዲህ ዓይነት ቅሌት? 500 ዓመታት በፊት የተከሰተውን የባርነት ዘመን አስታወሰን” እያሉ በጥልቁ በማዘን ጉዳዩን በቅርብ ለመከታተል ቃል ገብተው ነበር።

አዎ! “ኦሮሞ ነን” የሚሉት ብልሹ ልሂቃን እጅግ በጣም አሳፋሪና በዝምታ የማይታለፍ ምሑራዊ ቀውስ ውስጥ መግባታቸው መታወቅ አለበት፤ አካሄዳቸው ልክ እንደ ጣልያን ፋሺስቶች፣ እንደ ጀርመን ናዚዎች፣ እንደ ሩዋንዳ ሁቱ እና ሰሜን ሱዳን እብዶች መሆኑን እያየን ነውና እንደ እስካሁኑ ሳንለሳለስ ቆንጠንጥ ብለን ልንዋጋቸው ይገባል። እስኪ እናስበው፤ ከአንድ ቢሊየን በላይ ቁጥር ላላቸው “ጥቁር” ሕዝቦች ኩራት የሚሆነውን ኢትዮጵያኛ ጽሑፍን፣ ባሕልንና ሃይማኖትን ለመዋጋት የኢትዮጵያን ጡት ለዘመናት ጠብተው ያደጉት ውርንጭሎች ደፋ ቀና ሲሉ።

ኢትዮጵያ ከሰማንያ በላይ ቋንቋዎች የሚነገሩባት ሃገር ነች። የእነዚህ ሁሉ ቋንቋዎች ተናጋሪዎች መብታቸው ተጠብቆ ቋንቋቸውን ያለምንም ገደብ እንዲናገሩ ያው እስከ ዛሬ ድረስ እንዲናገሩ የከለከላቸው የሰሜን መንግስት ወይም ሥርዓት የለም። ይህን መሰሉ መብትለጋሽነት፣ ዜጎች የማንነታቸው መገለጫ የሆኑትን ቋንቋዎችና ባሕሎች ጠብቀው እንዲኖሩ የሚያስችላቸው መብት በምዕራቡም ሆነ በአረብ ቱርክ ዓለም የለም፤ እነዚህ ሃገራት የአናሳ ብሔር ቋንቋዎችንና ባሕሎችን ባጭር ጊዜ ውስጥ ሊያጠፉ ችለዋል። በአሜሪካ ቀይህንዳውያን ቋንቋዎቻቸውን አጥተዋል። አብዛኞቹ ነጭ አሜሪካውያን የጀርመን ዝርያ ያላቸው ሲሆኑ ጀርመንኛ ቋንቋቸውንም በእንግሊዝኛ እንዲተኩ ተገድደዋል። በቱርክ ሁሉም ነዋሪ ከቱርክኛ በቀር ሌላ ቋንቋ እንዳይነገር ተደርጓል፤ ሠላሳ ሚሊየን የሚጠጉ የቱርክ ኩርዶች እንኳን እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ቋንቋቸውን መንገድ ላይ እንዳይናገሩ፣ በትምህርት ቤትና መንግስት ተቋማት እንዳይናገሩ ተደርገው ነበር። በአረቡ ዓለም ደግሞ ከአረብኛ ቋንቋ በቀር ሌሎች ብዙ የአገራቱ ቋንቋዎች ሙልጭ ብለው እንዲጠፉ ተደርገዋል።

በኢትዮጵያ ሃገራችን ግን በከፍተኛ ደረጃ ብቸኛ ጥቃት የደረሰበት ቋንቋ የኢትዮጵያ የሆነው የግዕዝ ቋንቋ ነው። በውጭ ሃገራት ተጽዕኖ እና በኢትዮጵያውያኑ ደካማነት ላለፉት መቶ ዓመታት በግዕዝ ቋንቋ ላይ አሳፋሪና ቅሌታማ የሆነ ጦርነት ተካሂዷል። ለምን? ተብሎ ቢጠየቅ፤ ግዕዝ የሰው ልጅ የመጀመሪያ ቋንቋ ስለሆነ እንዲሁም በመንፈሳዊ ኃይሉ ከማንኛውም የዓለማችን ቋንቋ(ከትግርኛ እና አማርኛ ሳይቀር)በጣም የላቀና ኃብታም የሆነ ድንቅ ቋንቋ በመሆኑ ነው። ቀናተኛው ዲያብሎስ የግዕዝን ቋንቋ አጥፍቶ ደካማ በሆኑ የራሱ ቋንቋዎች ለመተከታት ፍላጎት ስላለው ነው።

የአዲሲቷ ኢትዮጵያ መሪዎች ነን” እያሉ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊነት ላይ የሚያላግጡ ግብዞች ሆኑ እርሷን ለማጥፋት የተሰለፉ የተለያዩ ቡድኖችና ድርጅቶች እንዲሁም መንግሥታትና ተቋማት እንዲሁም ግለሰቦች ዛሬ ነገ ሳይሉ በእዉነተኛ ንስሐ ለእግዚአብሔር እጃቸዉን ቢሰጡና ወደማንነታቸዉ ወይንም ወደ ኢትዮጵያዊነታቸዉ ቢመለሱ ነው የሚበጃቸዉ።

ግዕዝ ሊጠፋ አይችልም፤ የእግዚአብሔር የሆነው ነገር ሁሉ አይጠፋም፤ ሊጠፋም አይችልም። ግዕዝ ይለምልም!

_________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , | Leave a Comment »

‘ቦብ’ ሙስሊሞችን አዋረዳቸው | ከሁሉ ቀድማ ጎረቤቶቿን የሚያስቀና ሥልጣኔ የፈጠረች ክርስቲያን ኢትዮጵያ ናት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 9, 2019

በሃይድ ፓርክ የ ‘መተንፈሻ መናፈሻ’ ይህን ድንቅ ትምህርት የሰጠን ጀግናው የሃይድ ፓርክ ክርስቲያን “ቦብ” ነው። በዚህ ትምህርቱ እስልምና የዓረብን ባሕል ማስፋፊያ መሣሪያ እንደሆነ፤ ለዚህም የግብጽ ኮፕቶች፣ ኑብያውያን እና ደቡብ ሱዳናውያን በምሳሌነት እንደሚቀርቡ ያስተምረናል።

የግብጽ ኮፕቶች እና ኑብያውያን ባሕላቸውንና ቋንቋቸውን ተግባራዊ እንዳያደርጉና የዓረብን ቋንቋ እና ባሕል እንዲከተከሉ ተገድደዋል። (በግብጽ አገር ኮፕትኛ ቋንቋን የተናገረ ምላሱ ይቆረጥ እንደነበር ታሪክ ያስተምረናል፤ ያውም በገዛ አገራቸው።

እስኪ እንደምሳሌ ወስደን አለባበስን በሚመለከት እራሳችንን እንጠይቅ፦ ለሴት ሙስሊም ወገኖቻችን ዋናው ቁምነገር ሰውነታቸውና ጸጉራቸው እንዳይታይ በልብስ መከለል ከሆነ የሚሸፈኑበትን ሂጃብ የሀገራቸውን ነጠላ ወይም ኩታ ቀሚሳቸውንም የሐበሻ ቀሚስ ማድረግ ሲችሉ የኢትዮጵያ የሆነውን ልብስ ወርውረው በመጣል የሚጠቀሙት ከላይ እስከ ታች የዓረብን ልብስ ነው። ይህ ምንን ያሳያል? አዎ! ለማንነታቸው ያላቸው ግምትና ጥላቻ ከፍተኛ መሆኑ ነው። እነዚህ ወገኖች ወደዱም ጠሉም በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ለገዛ ሀገራቸው እሴቶች ጠላቶች ሆነዋል። እንግዲህ እስልምናን ሲቀበሉ ከልብሳቸው እስከ ቋንቋቸው ሁለነገራቸውን የዓረብ ለማድረግ መርጠዋል ማለት ነው።

የቦብ ሐተታ የሚያስተምረን፡ እስልምናን መቀበል ማለት የዓረብ ባሪያ ሎሌ ባንዳ መሆን ማለት እንደሆነ ነው፤ ይህም በመላው ዓለም በግልጽ የሚታይ ክስተት ነው፤ ሃይድ ፓርክን ጨምሮ።

ዓረቦች እንዲጠበቅላቸው የሚፈልጉት የራሳቸው ማንነት እንዳላቸው ሁሉ እኛም ኢትዮጵያውያን ከነሱ የተሻለ እንዲጠበቅልን የምንፈልገው ማንነት አለን። የራስን ጥሎ የዓረብን መያዝ ማለት የውዴታ ባርነት ነው። የገዛ ማንነትን መካድ ነው። ችግሩ ወገኖቻችን ይሄንን አለመረዳታቸው ብቻ ሳይሆን ለመረዳት አለመሞከራቸውና አለመፈለጋቸውም ነው።

በተለይ፡ በአሁን ሰዓት በቅናትና ምቀኝነት መንፈስ በተዋሕዶ ክርስትና ላይ ለተነሱት የጎረቤት ሃገራት ጠላቶቻችን፣ ለምዕራባውያን የክርስቶስ ተቃዋሚዎች እና ለዋቄዮ አላህ ልጆች ይህ ትልቅ ትምህርት ነው።

_________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

አባ ተስፋ ሥላሴ ሞገስ | “ ከ A – Z ያሉ የላቲን ፊደላት ሁሉም ከኢትዮጵያዉያን የተወሰዱ ናቸዉ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 26, 2019

አባቶች ለእኛ ትውልድ ከባድ ኃላፊነት በማስረከብ ትተውን እየሄዱ ነው።

ሉሲፈራውያኑ መጀመሪያ ቋንቋችንን ቀጥሎ ጤፋችንና ውሃችንን ከዚያ ደግሞ ሃይማኖታችንን አንድ ባንድ ሊነጥቁን ዳር ዳር እያሉ ነው። ታዲያ አባቶች እንዳያዝኑብን፣ እግዚአብሔርም እንዳይቀየመን የተሰጠንን ተወዳዳሪ የሌለው ትልቅ ፀጋና ኅብት የመከላከል ግዴታ አለብንና ወለም ዘለም ሳንል ቀበቷችንን ጠበቅ አድርገን እንዝመት።

ከሃዲዎቹ “ኦሮሞ ነን” ባዮች ቅራሬውን ላቲን መምረጣቸው ምን ያህል እግዚአብሔርን እና አባቶቻችንን እንደሚያስቀይም መገመት አያዳግትም።

_________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , | Leave a Comment »

ምዕመናኑን ፀጥ ያሰኘ ስብከት | ቋንቋን ለምን እንደ ሃይማኖት እንጠቀማለን? ከሆነማ ሁላችንም በግእዝ መነጋገር አለብን

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 15, 2018

ቋንቋን እግዚአብሔር አልፈጠረም፤ በቋንቋ መንግስተ ሰማያት አይገባም፡ ነገር ግን የመጀመሪያው አዳምም ለ ፯ ዓመታት በገነት ሳለ በፀሎት ሲተጋ የነበረውና ከሄዋን ጋር ይነጋገርበት የነበረው የመጀመሪያው ቋንቋ ግእዝ ስለሆነ እርስበርስ ለመግባባት እንችል ዘንድ ሁላችንም አሁን ግእዝ ቋንቋን ማወቅ ሊኖርብን ነው።”

ቃለ ሕይወት ያሰማልን፡ አባታችን! (የካሜራዬን ባትሪ መለወጥ ነበረብኝና ሁሉም ስብከታቸው አልተካተተም፡ ይቅርታ!)

አዎ! ዲያብሎስ በቋንቋ እርስበርሳችን እንድንጨፋጨፍና በእንግሊዝኛ ወይም በአረብኛ እንድንነጋገር ከማስገደዱ በፊት ፈጥነን ግእዝ ቋንቋን መማር አለብን።

ግእዝ የእግዚአብሔር ቋንቋ ነው ተብሎ በትዉፊት ይነገራል

ትውፊታዊ ታሪኩ

ግእዝ የእግዚአብሔር ቋንቋ ነው ተብሎ በትዉፊት ይነገራል። ፍጥረታት በሐሌዎበነቢብና በግብር የተፈጠሩ ሲሆን በተለይ ነቢቡ (ንግግሩ) ግእዝ ነበር ብለዉ የሚከራከሩና የራሳቸውን ማስረጃ የሚያቀርቡ ሊቃውንት አሉ። ግእዝ የመጀመሪያ ቋንቋ ነው ስንል አዳም ማለት ያማረ የተዋበ ማለት ሲሆን አባቶቻችን በመንፈስ ቅዱስ እየተመሩ ከጻፏቸው መጻሕፍት እና ሌሎች ድርሰቶች ተነስተን ቅዱስ ገብርኤል “ንቁም በበህላዌነ” ብሎ ሠራዊተ መላእክትን ያረጋጋው በግእዝ ነው፤ አዳምም ለ ፯ ዓመታት በገነት ሳለ በፀሎት ሲተጋ የነበረውና ከሄዋን ጋር ይነጋገርበት የነበረው ቋንቋ በግእዝ ነው በማለት ቋንቋውን የመላእክትም የሰውም መግባቢያ ያደርጉታል።

ግእዝ የአዳምና ሔዋን (የተፈጥሮ ቋንቋ) የመጀመሪያው መነጋገሪያ ልሳን መኾኑ ለማረጋገጥ ከሚያቀርቧቸው ፲ ምክኒያቶች መካከል

፩ኛ. ”ግእዝ” የጥሬ ዘሩ ቃል ትርጉም፡ “መጀመሪያ”, “ነፃ” እና “የጥንት ተፈጥሮ ጠባይ ወይም ባህሪይ” ማለት መኾኑ

፪ኛ. የእያንዳንዱ ፊደል የመጀመሪያ ቅርጽ አፍ ሳያስከፍት በድን በኾነው በተፈጥሮ ድምፅ ብቻ የሚነገር መኾኑ

፫ኛ. የፊደሉ መነሻ “አ” “አዳም” በሚል ቃል በወንድና ሴት ጾታ ለተፈጠሩት ለመጀመሪያዎቹ ሰዎች መጠሪያ መኾኑ

፬ኛ. በሰባት ብዛት የሚወሰን ቁጥር፤ የመለኮታዊ ሥራ ምሥጢር እንዳለበት ስለሚታመን፤ እያንዳንዱ ፊደል፤ በሰባት ስሞች ድምጾችና መልኮች ተለይቶ የሚታወቅና የሚነገር መኾኑ

፭ኛ. ሌሎቹ የሰዎች ቋንቋዎችና ፊደሎቻቸው በተናጋሪዎቻቸው ሕዝቦች ወይም ጎሣዎች ስም ለምሳሌ፤ ዐማርኛ፤ በዐምሓሮች፤ ትግርኛ በትግሬዎች፣ ኦሮምኛ በኦሮሞዎች፣ ሶማልኛ በሶማሌዎች፣ ዕብራይስጥ በዕብራዊያን፤ ዐረብኛ በዓረቦች፣ እንግሊዝኛ በእንግሊዞች፣ ቻይንኛ በቻይኖች ስም ሲጠሩ “ግዕዝ” ግን በራሱ ብቻ የሚጠራ መኾኑ

፮ኛ. በ ”አ” ጀምሮ በ “ኦ” የሚፈጸም ፊደል ያለው እርሱ፤ ግእዝ ብቻ ከመኾኑ ጋር “አልፋና ኦሜጋ፤ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ” ብሎ፡ ኃላ “ኢየሱስ ክርስቶስ” ተብሎ፤ ራሱን በሰውነት የገለጸው “እግዚአብሔር” በዚህ ስሙ የታወቀበትና አምልኮቱ የሚፈጸምበት ቋንቋና ፊደል ኾኖ በሕያውነት እስከዛሬ መቀጠሉ

፯ኛ. በምድር ላይ የሚኖሩ የሰው ልጆች ኹሉ፡ ተወልደው በሕፃንነታቸው መናገር በሚጀምሩበት ጊዜ ቋንቋቸውና ፊዲፈላቸው የተለያዩ ሲኾኑ፤ አፋቸውን መፍታት አባቶቻቸውናና እናቶቻቸውንም ለይተው መጥራት የሚጀምሩበት “አባባ”፤ “እማማ!” የሚባሉት ቃላት “አብ አብ አብ”፤ “እም እም እም” የተባሉት፤ ትርጉማቸው፡ “አባት አባት አባት”፡ “እናት እናት እናት” የኾነውን ቀጥታ የግእዙን ቃላት መኾኑ ናቸው።

፰ኛ. «ግእዝ» የሚለው ቃል እራሱ አንደኛ፣ የመጀመሪያ ማለት ነው። የሰው ልጅ የመጀመሪያ የሆነው ቋንቋ አንደኛቢባል ይስማማዋል።

፱ኛ. የዚህ ቋንቋ የመጀመሪያው ተናጋሪ ሰው አዳም ነው። የዚህ ሰው ስም በቋንቋው ትርጉም ሊኖረው ይገባል። በግእዝ «አዳም» ማለት ያማረ ማለት ነው።

፲ኛ. ሌላው ነገር የግእዝ ፊደላት ከአምላክ የተገኙ ናቸው ለዚህም የአዳም ሶስተኛ ትውልድ የሆነው ሄኖስ በሰማይ ገበታ እንዳያቸው አባቶች ይናገራሉአማርኛ ቋንቋ ከግእዝ ያገኛቸውን በሙሉ ይዞ ሌሎች ፯ ፊደላትን በመጨመር ግእዝ ፳፮ ሲሆን አማርኛ ደግሞ ፴፫ ነው “ቨ”ን ሳይጨምር ማለት ነው፡፡

የግእዝን ፊደሎች ትርጉም ስንመለከት

ሀ፦ ብሂል ሀልዎቱ ለአብ እምቅድመ ዓለም ፥ የአብ አኗኗሩ ከዓለም በፊት ነው

ለ ፦ ብሂል ለብሰ ሥጋ እምድንግል ፥ ክርስቶስ ከድንግል ሥጋን ለበሰ

ሐ ፦ ብሂል ሐመ ወሞተ ፥ ስለኛ ታመመና ሞተ

መ፦ ብሂል መንክር ግብሩ ለእግዚአብሔር ፥ የእግዚአብሔር ሥራው ድንቅ ነው

ሠ ፦ ብሂል ሠረቀ በሥጋ ፥ በሥጋ ተገለጠ

ረ ፦ ብሂል ረግዓት ምድር በቃሉ ፥ ምድር በቃሉ ረጋች

ሰ ፦ ብሂል ሰብአ ኮነ እግዚእነ ፥ ጌታችን ሰው ሆነ

ቀ ፦ ብሂል ቀዳሚሁ ቃል ፥ ቃል መጀመሪያ ነበር

በ ፦ ብሂል በትሕትናሁ ወረደ ፥ ጌታችን በትሕትናው ወደኛ ወረደ

ተ ፦ ብሂል ተሰብአ ወተሰገወ ፥ ጌታችን ሰው ሆነ

ኀ ፦ ብሂል ኀያል እግዚአብሔር ፥ እግዚአብሔር ኀያል ነው

ነ ፦ ብሂል ነስአ ደዌነ ወጾረ ሕማመነ ፥ መከራችንን ያዘልን ሕመማችንን ተሸከመልን

አ ፦ ብሂል አእኵቶ ወእሴብሖ ለእግዚአብሔር ፥ እግዚአብሔርን ፈፅሜ አመሰግነዋለሁ

ከ ፦ ብሂል ከሃሊ እግዚአብሔር ፥ ጌታችን ቻይ ነው

ወ ፦ ብሂል ወረደ እምሰማይ ፥ ጌታ ከሰማይ ወረደ

ዐ ፦ ብሂል ዐርገ ሰማያተ ፥ ወደ ሰማይ ዐረገ

ዘ ፦ ብሂል ዘኵሎ ይእኅዝ እግዚአብሔር ፥ ጌታ ሁሉን የሚይዝ

የ ፦ ብሂል የማነ እግዚአብሔር ገብረት ኃይለ ፥ የጌታ ቀኝ እጅ ኃይልን ታደርጋለች

ገ ፦ ብሂል ገብረ ሰማያተ በጥበቡ ፥ ጌታ በጥበቡ ሰማያትን ሠራ

ጠ ፦ ብሂል ጣዕሙ ወታእምሩ ከመ ኄር እግዚአብሔር ፥ ጌታ ቸር እንደሆነ ቅመሱና ዕወቁ

ጰ ፦ ብሂል ጰራቅሊጦስ መንፈሰ ጽድቅ ፥ ጰራቅሊጦስ እውነተኛ መንፈስ ቅዱስ ነው

ጸ ፦ ብሂል ጸጋ ወክብር ተውህበ ለነ ፥ ጸጋ እና በረከት ተሰጠን

ፀ ፦ ብሂል ፀሐይ ጸልመት በጊዜ ስቅለቱ ለእግዚእነ ፥ ጌታ በተሰቀለ ጊዜ ፀሐይ ጨለመች

ፈ ፦ ብሂል ፈጠረ ሰማየ ወምድረ ፥ ጌታ ሰማይ እና ምድርን ፈጠረ

ፐ ፦ ብሂል ፓፓኤል ስሙ ለአምላክ ፥ ፓፓኤል የአምላክ ህቡዕ ስም

ትርጉማቸዉ ይሄን ይመስላል።

ስለዚህ ግእዝ የአዳም ቋንቋ ነው የሚለው መላምት የበለጠ ጥንካሬ አለው

______

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ቀጣፊው ፍየል Al Jazeera | “ኢትዮጵያውያን ህጻናት ከአማርኛ ይልቅ አረብኛ የተሻለ መናገር ጀምረዋል” ይለናል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 13, 2017

ከእኛ ከእራሳችን ጉያ ወጥቶ ልናስብበት የሚገባንን ጉዳይ ጠላታችን ይጠቁመናል። ልክ ባለፉት ሳምንታት ላይ፣ በሊቢያ የሚታየውን አንገፍጋፊ የባርነት ቅሌት ለመቃወም ለንደን ያሉ አፍሪቃውያን ሲወጡ ወኪላቸውና አፈቀላጢያቸው የነበረው አረቡ ግለሰብ እንደነበረው።

አልጀዚራ የሰጠን ማብራሪያ፦ የአረብ ሳተላይት ብዙ የህፃናት ፕሮግራምን በአረብኛ ስለሚያስተላልፍ ነው የሚል ነው

የተበላሸ ሰዓት በቀን ሁለቴ ትክክል ነው። አዎ! አልተሳሳቱም፤ ስይጣን ከሁሉም አቅጣጫ ነው በህጻናቶቻችንና በሴቶቻችን ላይ ጦረንቱን የከፈተባቸው። ኢትዮጵያን ቀስበቀስ፣ በማዝናናትና በጸጥታ እንደ ሱዳን ለማውደቅ ነው እነዚህ እርኩስ አረቦች እና እ/ንግሊዞች በመታገል ላይ ያሉት።

ፀሐይ” የሚለውን የህጻናት ፕሮግራም የባሃይ እስላሞች ነበር የሠሩት፤ እነርሱም እባባዊ ድብቅ መልዕክቶች ያዘሉትን ተንቀሳቃሽ ስዕሎች አዝናኝ በሆነ መልክ በማቅረብ ህጻናቶቻችን ቅንጭላት ውስጥ ለመግባት ሞክረዋል።

ቃና ቴሌቪዥን ሊዘጋ ነው የሚል ጭምጭምታ ሰሞኑን ሲወራ፡ በሉሲፈራውያኑ ዔሳውያን የምዕራቡ ግብዞች ደጋፊነት የተቋቋመው የእስማኤላውያኑ አልጀዚራ ከትናንትና ወዲያ ባወጣው ርዕስ ሥር የሚከተለውን አለ፦

የቃና ቲቪ መከፈት የሜዲያ ነፃነት መኖሩን ያመለክታልን?

በዚህም ጽሑፍ፦

  • ቃና የውጭ አገር ፊልሞችን በአማርኛ ተርጉሞ እንደሚያሳይ
  • ቃና በጣም ብዙ ተመልካቾች እንዳሉት
  • ቃና የኢትዮጵያውያን ባህል ለማሻሻል (ለመለወጥ) እንደሚሞክር
  • ቃና ከአፍጋኒስታን እንደሚተላለፍ
  • በአረብሳት ብዙ ፕሮግራሞች በአረብኛ እንደሚተላለፉ
  • ስለዚህ የኢትዮጵያ ህፃናት ከአማርኛ ይልቅ አረብኛ የተሻለ እንደሚናገሩ

አስቀምጦልናል።

ያው እንግዲህ፤ ዓላማቸው ምን እንደሆነ ዓይናችን ያያል፤ የሚፈልጉትንም ፊትለፊት በድፍረት እየነገሩን ነው።

አልጀዚራን ቢቢሲን እና ሲኤን ኤን የመሳሰሉትን የቴሊቪዝን ጣቢያዎች፣ አልፎ አልፎ ሞኒተር ለማድረግ ካልሆነ በቀር ከፍቼ የማየት ፍላጎት የለኝም፤ ድህረገጾቻቸው ውስጥ መግባት ካቆምኩ ብዙ ጊዜ ሆኖኛል፤ የተያያዘ ነገር ከሌለ።

ግን፤ ተንኮለኞቹ አልጀዚራና ቢቢሲ እንደ ኢትዮጵያ ክርስቲያናዊ በሆኑ ሕዝቦች ላይ መጥፎ አቋም እንዳላቸው የሚታወቅ ነው።

ለምሳሌ አልጀዚራ ለኦሮሞዎች እንታገላለን ለሚሉት ጡት ነካሽ ከሃዲዎች፡ መድረኩን መስጠቱ የሚገርመን ነገር አይደለም። ኦሮሞ የሚለው ኮድ እስላም ለማለት ነው፤ ልክ አማራ ወይም ትግሬ በሚሉት ኮድ ጀርባ በክርስቲያኖች ላይ ቀስታቸውን ማነጣጠራቸውን እንደሚደብቁት

ዋናው ዲያብሎሳዊ ዓላማቸውም ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊ የሆነውን ነገር ሁሉ ማጥፋት ነው።

የአልጀዚራ ጽሑፍ ላይ፦ ቃና ቲቪ “የመግባቢያ ቋንቋ” (ሊንጉዋ ፍራንካ) አማርኛ የውጭ ፊልሞችን እየቀረበ ለሁሉም ያቀርባል፣ ኢትዮጵያ ከ80 በላይ ቋንቋዎች የሚነገሩባት አገር ስለሆነች በአማርኛ ነው የሚግባቡት አለ። የተንኮለኛው እንግሊዛዊ መልዕክት ግን “የኢትዮጵያ ብሔሮች ከ25 ዓመታት በኋላ እነደ ቀደሙ እርስበርስ በአማርኛ መግባባት ስለማይችሉ አሁን እንግሊዝኛን እና አረብኛን የግድ መጠቀም ይኖርባቸዋል” ማለቱ ነው። አሁን ባይቻልም በመጪዎቹ ዓመታት።

አንድ ዓለም ሥርዓትን ለመመስረት የተፈቀደላቸው ቋንቋዎች፦

  • እንግሊዝኛ
  • ስፓኒኛ
  • ፈረንሳይኛ
  • ሩሲያውኛ
  • ቻይንኛ
  • አርብኛ

ብቻ ናቸው (ሁሉም የተባበሩት መንግስታት የመስሪያ ቋንቁዎች ናቸው)

ስለዚህ አንዱ ዓላማቸው፦

ኢትዮጵያኛውን ቋንቋ፡ ልክ ግእዝን ቀስበቀስ እንዳደከሙት፣ አማርኛውንም ቀስበቀስ አጥፍተው በእንግሊዝኛና አረብኛ መተካት ነው። ቀደም ሲል በአውሮፓውያን ግፊት ኦሮምኛ በላቲን እንዲጻፍ የተደረገውም በዚህ መንገድ አማርኛን ማጥቃት እንዲችል ነው።

በሴቶች እና በህፃናት ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት፦

ምዕራባውያኑ ዔሳውያኑ የሠሯቸውን ካርቱኖች በአረብኛ በማቅረብ ህፃናቶቻችንን ገና በልጅነታቸው ሲያጠምዱ ሴቶቻችንን ደግሞ በቱርክ ድራማ እየመረዙ ነው።

ቪዲዮው ላይ የሚታዩት ውብ መንፈሳውያን ህፃናት አያሳዝኑንምን? እነዚህ ንጹሕና የዋህ ህፃናት ምን ዓይነት ወደፊት እያዘጋጃችሁልን ነው? ለራስችሁ ብቻ አታስቡ የኛን ወደፊት አታበላሹብን የቤት ስራችሁን ስሩ፣ ተዋጉልን እንጂ! እያሉ እኮ ነው። ምን ዓይነት ጭካኔ ነው? መላዕክቶቻቸው እኮ ሁሉንም ይቀርጻሉ፤ ኧረ በኋላ እንዳይረግሙን!

እግዚአብሔር እነዚህን እስማኤላውያን እና ኤዶማውያን እርኩሶች ከአጠገባችን ያርቅልን፣ ውድቀታቸውንም ያፋጥንልን!

______

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Infos, Media & Journalism | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ግእዝ ኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ ሌላ አገር ሐይማኖታዊ/ መንፈሳዊ ቋንቋ ነው። የዓለም ህዝብ ተቀብሎታል፤ ከኢትዮጵያውያን በስተቀር”

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on July 7, 2017

ዛሬ: ..አ: 07/07/2017 ነው። ምስሉ ኩራታችን የሆነው አየር መንገዳችን ቦይንግ 777 ን ሲያበር ያሳያል።

በእግዚአብሔር አምላካችን ዘንድ አንድ ሐቅ ነው ያለችው፤ ወደድንም ጠላንም፡ አንድ ሐቅ ብቻ! ግዜ በእጃችን አይደለም ያለው፤ ለእኛ የተባለውን ነገር ሁሉ፣ የተሰጠነን ህልውና፣ የተረከብነውን ቅዱስ መንፈስ በመጠቀም ዛሬውኑ፣ አሁኑኑ ነው በሥራ ላይ ማወል የሚገባን። “ቆዩ፤ አሁን ሁኔታው አይፈቅድም ቀስ እንበል!„ እያሉ ከመቀመጫቸው መነሳት የማይሹትን አታላዮችና ሌላውንም እንዲያንቀላፋ የሚያደርጉት፣ በሌላው ላይ ብቻ ሳይሆን በራሳቸውም ላይ ነው ከባድ መዘዝ በማምጣት ላይ የሚገኙት። የራሳቸውን ቆሻሻ የቤት ሥራ ለመጪው ትውልድ አሳልፎ በመተው፡ በአሁኖቹ ህፃናት ላይ ሊሰረዝ የማይችሉ በደልና ኃጢአት ነው የሚፈጽሙት።

“ኢትዮጵያ አገራችን ተከባልች፣ ጠላቶቿ እራሳቸው በዘረጉት የጊዜ ጎዳና ላይ በመጓዝ አመቺ የሚሆነላቸውን አጋጣሚ በመጠበቅ ላይ ናቸው!፡” እያልኩ ላለፉት 15 ዓመታት ባቅሜ ያለማቋረጥ እጠቁም ዘንድ እግዚአብሔር ይገፋፋኝ ነበር። ሉሲፈራውያኑ ችግኞቻቸውን በየአገራቱ ተክለዋል፣ በተለይ በአገራችን፤ የክርስቶስንም ልጆች በግልጽ ለመዋጋት ቆርጠው ከተነሱ ውለው አድረዋል። ባሁኑ ሰዓትም ኢአማናያን ሰዶማውያኑን እና መሀመዳውያኑን እንደ መሳሪያ አድርገው በመጠቀም ላይ ይገኛሉ። አሁን ሁላችንም አካሄዳቸውን መከተል የምንችልበት ጊዜ ላይ ደርሰናል፤ ዓይን ያለው ፈጥኖ ይመልከት።

ባለፉት ጥቂት ወራት ብቻ ምን እንደሚሰሩ፡ ብሎም ማን እንደሆኑ ለመላው ዓለም በግልጽ ደፍረው ብዙውን ነገር እያሳዩን ነው። ካሳዩንም ሁኔታዎች መካከል የሚከተሉትን እንመልከት፤ ይህ ሁሉ ባጭር ጊዜ ውስጥ ነው የተከሰተው፦

  1. ታላቋ ብሪታኒያ ከአውሮፓው ህብረት ትወጣለች ብለው በፍጹም አልጠበቁም። brexitሬፈረንደም ውጤቱን ለመከለስ ያው እስካሁን በመታገል ላይ ናቸው

  2. የዶናልድ ትራምፕን ለፕሬዚደንትነት መብቃት ፈጽሞ አልጠበቁትም ነበር። ከተመረጡበት ቀን ጀምሮ በሳቸው እና ደጋፊዎቻቸው ላይ እየተካሄደ ያለው የጥቃት ዘመቻ በታሪክ ተወዳዳሪ አይኖረውም

  3. ኢትዮጵያውያን በአገር ቤትም በውጩም እርስበራሳቸው እንዲበጣበጡ፣ በህንድ ውቂያኖስ፣ በቀይ ባሕር፣ በሜዲተራንያን ባሕር፣ በቆሼበለንደን እና በካሌ ለሉሲፈር መስዋእት እንዲሆኑ ተደረጉ

  4. ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም የዓለም ጤና ድርጅት ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተመረጡ። አንድ ኢትዮጵያዊ እንደዚህ ዓለማቀፋዊ ተጽዕኖ ማድረግ በሚችል ድርጅት ውስጥ “ሰርጎ” መግባቱ፣ ከኢትዮጵያዊነት አንፃር፡ እሰይ! ትልቅ ነገር ነው! ለአገራችን የሚበጅ ነው! የሚያሰኝ ነው። ከስልጣን፣ ከታዋቂነት እና ከንዋይ ኃብት የበለጠ፡ በተለይ ለኢትዮጵያውያን፡ ሌላ እጅግ ትልቅ ነገር አለ። ዶ/ር ቴዎድሮስ ኢትዮጵያን የሚጠቅም እና እግዚአብሔር አምላኳን የሚያስደስት ሥራ ለመሥራት ይበቃሉን? ወደፊት የምናየው ነው። ለማንኛውም እንጸልይላቸው።

  5. ሊሲፈራውያኑ በአሜሪካ የሠሩትን ዓይነት ስህተት ላለመስራት፣ በፈረንሳይ ሰዶማዊውን ማክሮንን ፕሬዚደንት ለማድረግ በቁ

  6. በአየርላንድም ሰዶማዊውን የህንድ ስደተኛ በጠቅላይ ምኒስቴርነት አስቀመጡ

  7. በጀርመንም አንድ ሳምንት ብቻ በፈጀው ያልተጠበቀ ስብሰባ የሰዶማውያን “ጋብቻ” ሕጋዊ እንዲሆን በጥድፊያ አጸደቁት። ይህን መሰሉን ጉዳይ ሕዝቡ በሬፈረንደም መወስን ነበረበት።

  8. በኢትዮጵያም መንፈሳዊውን ኢትዮጵያኛ የግእዝ/አማርኛ ቋንቋ ለማጥፋት እንዲሁ በተጣደፈ መልክ ምክር ቤቱ ህግ እንዲያጸድቀ ተደረገ። ይህን መሰሉን ጉዳይ ሕዝቡ በሬፈረንደም መወስን ነበረበት።

  9. G20 አገራቱ መሪዎች ስብሰባ ከመጀመሩ ከሁለት ቀናት በፊት የአፍሪቃው ህብረት መሪዎች በአዲስ አበባ ተሰባሰቡ

እነዚህ እና ሌሎች ተመሳሳይ ጉዳዮችም በዚህ የሀምበርጉ የመሪዎች ስብሰባ ላ በሪፖርት መልክ ለውይይት እንደሚቀርቡ የሚያጠራጥር አይደለም። በነገራችን ላይ፡ ሀምበርግ ከተማ በተቃዋሚ ኃይሎች ብጥብጥ እየታወከችና እየነደደች ነው! እሳት! እሳት! እሳት!

አፍሪቃ ዋና የመወያያ ርዕስ እንደሆነች ቀደም ሲል ተጠቁሟል። ብዙ የአፍሪቃ አገሮች መሪዎች በስብሰባው እንዲሳተፉ ቢደረግም፤ አፍሪቃን በዋናነት የሚወክሉት ግን ደቡብ አፍሪቃዊውና ባለ አራት ሚስቱ (ሰዶማዊ) ያዕቆብ ዙማ ናቸው።

የሳጥናኤል ጎል ኢትዮጵያ

በእኛ አቆጣጠር በ 2007 .ላይ ታታሪው ወንድማችን ፍስሐ ያዜ ካሳ ሳጥናኤል ጎል ኢትዮጵያ” የሚለውን ድንቅ መፅሐፍ ጽፎልናል።የዚህ መፅሐፍ ትኩረት ስለ አዲሱ የምድር መንግስት ምስረታ ብቻ ሳይሆን፤ የፍፃሜው ጦርነት ምን እንደሚመስል፣ኢትዮጵያም ከፍፃሜው ጦርነት ጋ በተያያዘ የተለየ ትኩረት እንደተደረገባት፣ ዘንዶውን በኒውክሌር እናግዛለን፤ እግዚአብሔርንና መላዕክቱንም እናሸንፋለን!ብለው የኃያላን አገራት መሪዎችና የቫቲካን ቤተክርስቲያን የሚዝቱበትና የሚዘጋጁበት፤ ጦርነቱም በዋናነት ኢትዮጵያ ላይ እንደሚሆን፤ጎላቸውም ኢትዮጵያ እንደሆነች ይገልፃል። የዓለማችን ታላላቅ የሚባሉ ገለባ አገራትና መሪዎች ከዚህ በኋላ ትልቁ የቤት ስራቸው ኢትዮጵያ ላይ እንደሆነ በማስረጃ እያስደገፈ ተንትኖታል፡፡

ለዛሬው የሚከተለውን ከመጽሐፉ ጠቅሼ አቅርቤዋለሁ፦

በቅርቡ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የታሪክ ዲፓርትመንትን ሊዘጋ ነው ሲባል ሰማሁና በጣም ተገረምኩ። እንዴት? ታሪክ ከታጠፈ ጂኦግራፊም ቀረ ማለት ነው። እሱ ቀረ ማለት ደግሞ አገር አገርነቷ የሚታወቀው በምን ሊሆን ነው። እሱ ቀረ ማለት ደግሞ አገር አገርነቷ የሚታወቀው በምን ሊሆን ነው? ብዬ ራሴን ጠየቅሁ። የዲፓርትመንቱ ሃላፊዎች ለምን አደጋ እንዳንዣበበበት ሲጠየቁ “በዘርፉ የሚመረቁ ተእማሪዎች ስራ እያጡ ተቸገርን፣ 70/30 ፕሮግራም፣ ወዘተ…„ የሚል የናቴ መቀነት አደናቀፈኝ ዓይነት ምክንያት ሲሰጡ ሰማሁና ግርም እንዳለኝ ተውኩት። የታሪክ ትምህርትን ያጠፋች አገር ካለች ብየ ኢንተርኔት ላይ አጣራሁ። ይኖራል ብዬ ማሰቤ ራሱ የሚገርም ነው። የለም! ስራ ስላለ ስለሌለ ነው እንዴ ታሪክ ማወቅና መማር ማስተማር ያስፈለገው? ምን ማለት ይሆን? እያልኩ ሳይገባኝ አለሁ። ጭራሽ ኢትዮጵያ ታሪክን ማስቀረት? አሜሪካ እንኳ የሶስት መቶ ዓመት ታሪክ ይዛ ልዩ ትኩረት የሰጠችው ዲፓርትመንት ነው። ጭራሽ ኢትዮጵያ? ታሪክን ማስቀረት ማለት ምን ማለት መሰለህቀጣዩን ትውልድ አገርም ታሪክም ንብረትም ማንነትም ምንም ምንም የለህም ማለት ነው። መነሻም መድረሻም የሌላቸው ከንቱ ትውልዶች ናችሁ! ማለት ነው! ቀጥተኛ ትርጉሙ ይሄ ነው። ቀጣዩን ትውል ምን እያሉት መሰለህየግዛታችሁ ስፋት አይታወቅም። አባቶቻችሁም አልተናገሩም እንደማለት ነው! ደግነቱ ቀጣይ ትውልድ የሚባል ነገር…„

አሁንማ ግልጽ ሆነ! ለምን እንደዚያ እንደተደረገም አውቅነ! ይሄ ብቻ ሳይሆን ይህ በተባለ ማግስት በታሪካዊው ቤተ መፃህፍት የነበሩትን ታሪካዊ ሰነዶች በሙሉ ቦታ ጠበበ በሚል ተልካሻና አስቂኝ ምክንያት ለሲቅ እቃ መጠቅለያነት ይውሉ ዘንድ ጠርገው አወጡና አጫርተው ሸጧቸው። ግራ ገብቶኝ ነበር። ግን ግልፅ ሆነ። ለካስትልቅ የዛፍ ግንድን ሲገዘግዙ ሲገዘግዙ ቆይተው፤ ግዝገዛው ሲያልቅ ግንድስ ብሎ መውደቁ ነው። ገዝጋዡም ስራውን አጠናቆ ላቡን እየጠራረገ እፎይ ብሎ አረፈ። ተገንድሶ የወደቀውን ግንድ ገዝጋዡ ተሸክሞ የመሄድ ግዴታ የለበትም። ለሸክም የተዘጋጁ ሊሎች ሰራተኞች ይኖራሉ። የቀረውን ግፋፎና ቅጠላ ቅጠል የሚጋፋና አካባቢውን የሚያፀዱም ተዘጋጅተዋል፤ ስራው ግን ተጠናቋል!„

በጣም ያሳዝናል! ግዝገዛውን አውቅ ነበር። ይሄኛውን ግን አልሰማሁም፤ አዝናለሁ”

አሁን ነው እንዲያ የሆነው። አንድ ተማሪ አልተቀበሉም። በማግስቱ ግን አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የቻይንኛን ቋንቋ በመደበኛ ፕሮግራም በዲግሪ መርሀ ግብር ማስተማር ጀመረ። የራሳችንን ትተን ቻይንኛ እየተማርን ነው። ቻይና ደግሞ በተመሳሳይ አማርኛ ቋንቋን ሶስተኛ ቋንቋዋ አድርጋ አገሯ ላይ እያስተማረች ነው። ሌሎች የG20 አገራትም እንደ ቻይና አማርኛንና ግእዝን ሶስተኛ ቋንቁ አድርገው በዲግሪ እያስተማሩ ነው። እስከ ፒ...ዲ ድረስ እያስተማሩ ነው። ይህን ነገር በዜና ሳይ ያው ከልማቱ ጋር በተገናኘ ይሆናል ብዬ አስቤ ነበር። አሁን ነው ጅልነቴ የገባኝ። ለካስ ታዘው ነው። ስለዚህ እኛ የነሱን መማር ጀመርንእውነት ለንግዱ፣ ለልማቱ፣ ለምናምኑ ቻይንኛን መልመድ እዚህ ድረስ አስፈልጎ ነው? ከዚህ ወዲያ ውድቀት አለ? ከዚህ ወዲያ ሴራ አለ? ሌቦች ናቸው! እኛም እልል ብለን እንቀበላቸዋለን!

አንድ ተረት ልናገር፦ ሰሜን ሸዋ አካባቢ አንዲት እብድ ነበረች አሉ። ይቺ ታዋቂ እብድ በአንድ ቅዳሜ ማለዳ ላይ ትነሳና፣ “ዛሬ ገበያ እንዳትሄዱ ቤት ይቃጠላል። ገበያ እንዳትሄዱ ቤት ይቃጠላል። እያለች ስትለፍፍ አረፈደች። የቀዬው ሰዎች ግን፤ “ዛሬ ደግሞ ይቺ እብድ በጠዋት ተነሳባት” እያሉ አሽሟጠጧት። ቀኑ የገባያ ቀን ነውና የእብዷን ልፍለፋ ከምንም ሳይቆጥሩ ልብ ብለውም ሳይሰሙ ጎጆ ቤታቸውን ዘጋግተው ወደ ገበያ ሄዱ። አጅሪት ደግሞ ቀዬው ጭር ማለቱን ስታይ፤ እሳት በችቦ ትለኩስና ያንን ሁሉ ጎጆ ቤት ታቃጥለዋለች። ሁሉንም ቤት አንድዳ ዞር ትላለች። ያገሬው ህዝብ ገበያ ውሉ ሲመጣ መንደሩ እንዳለ ተቃጥሏል። በዚህ ጊዜ ያች እብድ ተመልሳ መጣችና፤ “ነግረናል ቤት ይቃጠላል ብለናል፤ ነግረናል ቤት ይቃጠላል ብለናል” እያለች ትናገር ጀመር። አሁንም ከዚህ ቀደም ጥቂት ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያ ታሪክ እየተዘረፈ ነው፤ ታሪኩም አፈ ታሪክ አይደለም፤ ከ3ሺ ዓመትም ይበልጣል፤ ነጮችንም አትመኑ እያሉ ስድብ ቢጤም እያካተቱ ለመግለፅ ሞክረው ነበር። ይገሬው ጎሳ መሪዎች ግን ፈፈፋውን ልብ አላሉም፤ ወደ ጎን ሊሉት ሞከሩ። አሁን እኔ እነሱን ብሆን ኖሮ እንደዚያች እብድ፤ “ነግረናል ቤት ይቃጠላል ብለናል” እያልኩ በየአደባባዩ እለፍፍ ነበር”

የሚያሳዝን ነው!“

አለም (ዲያብሎስ) “ማየት ማመን ነው” ይለናል | እግዚአብሔር ደግሞ “ማመን ማየት ነው” ብሎ ያስተምረናል

It’s 07/07/17 | G20 Summit Embarrassment: Germany’s Merkel Bows To Saudi Arabian State Minister


______

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: