Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • May 2023
    M T W T F S S
    1234567
    891011121314
    15161718192021
    22232425262728
    293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘ቅድስት ኪዳነምህረት’

ኪዳነ ምህረት | ስንቱ ቀስት አለፈ ስንቱ ሰንሰለት፡ መከታዬ ሆና የጌታዬ እናት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 22, 2020

ኪዳነ ምሕረት ስንል የምሕረት ቃልኪዳን ማለት ነው፡፡ በዚህ ውስጥም ምሕረት አድራጊው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን ምሕረት ተቀባይም መላው የአዳም ዘር ነው፡፡

እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በምድራዊ ቆይታዋ ዘውትር ወደ ክርስቶስ መካነ መቃብር ጎለጎታ እየወረደች ትፀልይ ነበር፡፡ ልጇ እና ወዳጇ ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያደረገችው ልመናና ፀሎት ተመልክቶና ሰምቶ የምህረት ቃል ኪዳን ገባለት ፡፡

እንኳን የእናቱን ፀሎት እና ልመና ቀርቶ ዘውትር በሀጥያት የምንዘፈቀውን እኛን ክፉዎቹን የሚሰማ አምላክ ስለ አንቺ ፣ ስለ እናቴ ክብርና ፀጋ ስል ይኸው ቃሌ ብሎ ቃልኪዳን አደረገ፡፡

« ከመረጥሁት ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ። … » መዝ, ፹፱ ፥፫ እንዲል መፅሐፉ፡፡

ስሟን ለሚጠሩ፣ በእርሷ አማላጅነት ለሚታመኑ በምድር በረከትን በሰማይ የዘለዓለም መንግስትን እንደሚወርሱ የምህረት እና የቸርነት ቃልኪዳን ሰጥቷታል ፡፡

ታላቁ መፅሐፍ እንዲህ ይላል፦

. . . ቀስቲቱም በደመና ትሆናለች፤ በእኔና በምድር ላይ በሚኖር ሥጋ ባለው በሕያው ነፍስ ሁሉ መካከል ያለውን የዘላለም ቃል ኪዳን ለማሰብ አያታለሁ። ኦሪት ዘፍ. ፱ :፲፮

በዚህም መሠረት ቃልኪዳኗን ምክንያት በማድረግ ኪዳነምሕረት እያልን እንጠራታለን!

እንኳን ለ ኪዳነ ምሕረትአደረሰን። የእመቤታችን ምህረት እና ረድዔት፤ በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን!

_____________________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

ውቡ መካነ ሕይወት የአቃቂ ቃሊቲ ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 24, 2020

፲፱፻፶፰ /1958 .ም ተመሠረተ። የቤተ ክርስቲያኑ አሠሪ/አስተካይ ወ/ሮ አቦነሽ አንበርብር ነበሩ

_____________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

ኪዳነ ምህረት | ስንቱ ቀስት አለፈ ስንቱ ሰንሰለት፡ መከታዬ ሆና የጌታዬ እናት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 22, 2019

_______________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: