Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘ቅድስት ሐና ማርያም’

ልደታ ለማርያም፡ “ኢያቄም እና ሐና ሰማይን ወለዱ!”

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 9, 2017

__

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

ቅድስት ሐና ማርያም ቤ/ክርስቲያንና ድንቅ ዛፎቿ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 19, 2013

በዛሬዋ የሐና ማርያም ዕለት አዲስ አበባ ነፋስ ስልክ ላፍቶ ስለምትገኛዋ ቅድስት ሐና ማርያም ይህችን ቪዲዮ በማቅረብ አንዳንድ ትዝታዎችን ልቀስቅስ። እንኳን አደረሰን!

የቅድስት ሐና ማርያም ቤተክርስቲያን በብዙዎቻችን ዘንድ በሚገባ የማትታወቅ፡ ነገር ግን፡ በእውነት፡ አዲስ አበባ ካየኋቸው ዓብያት ክርስቲያናት መካከል በጣም ከሚያማምሩት መካከል ልትመደብ የሚገባት ቆንጆ ቤተክርስቲያን ነች።

..አ በ1920ዎቹ አመታት በታላቋ ንግሥት ነገሥታችን ዘውዲቱ ዘመን የተገነባችው ይህች ቤተክርስቲያን ኮረብታማ በሆነ አቀማመጧ እጹብ ድንቅ የሆነ ቦታ ይዛለች። በዚያ ዘመን ከ100 ዓመታት በፊት፤ ማለትም አካባቢዋ ገና የገጠራማ ባሕርይ ይዛና በጫካ ብቻ ተከብባ በነበረችበት ዘመን ንግሥቲቷ የቅድስት ሐና ማርያምን ቤተክርስቲያን ሕንፃ መሠረት ሲያስቀምጡ፡ ወደፊት ይህች አካባቢ የአዲስ አበባ መኻል ከተማ ትሆናለችበማለት ትንቢት ተናግረው ነበር። እንዳሉትም፡ ቀስ በቅስ በማደግ ላይ የምትገኘው የሐና ማርያም አካባቢ እየሰፋች ለመጣችው የአዲስ አበባ ከተማችን ባሁኑ ጊዜ መኻከለኛ የሆነ አቀማመጥ አላት። ይህም በጣም የሚገርም ነው!

እዚህኛው ቪዲዮ ላይ በከፊል የሚታዬው የሐና ማርያም ቤተክርስቲያን አንጋፋ እና ጥንታዊ ዛፍ አካባቢ ሆኜ (በተከታዩ ቪዲዮ አቀርበዋለሁ) ራቅ ብሎ የሚገኘውን ጋራ ሸንተረር ስቃኝ ይሰማኝ የነበረው የመንፈስ መረጋጋትና ሰላም እጅግ በጣም ጥልቅ ነበር። ጸጥታውና መረጋጋቱ የከተማው ግርግርና ጫጫታ ከሚፈጥረው ሁከት በጣም ፈዋሽ ሆኖ ነው ያገኘሁት።

ቀጥሎ በእንግሊዝኛ የቀረበው ሳይንሳዊ ጥናት ዛፍን መጠጋት ወይም ማቀፍ አንድን ግለሰብ ጤናማ እንደሚያደርገው ባለመነጽሩ ሊቃውን ሳይቀሩ እንደሚመሰክሩ ነው የሚገልጸው። ታዲያ ዓብያተ ክርስቲያናቶቻችንና ገዳማቶቻችን በዛፎችና ልዩ ልዩ በሆኑ ዕፀዋት መከበባቸውና ምዕመናኑም እነርሱን በመጠጋት ከተፈጥሮና ከፈጣሪያቸው ጋር አንድ ለመሆን የጸሎት ጊዚያቸውን እዚያ በትጋት ማሳለፋቸው ኃይል ሰጪው የልዑል እግዚአብሔር ቅዱስ መንፈስ የት እንደሚገኝ በውል የሚያረጋግጥ አይደለምን?!

መንፈሳዊ ውድቀት ባራቆቷት፤መንፈሳዊው ጦርነት እየተጧጧፈ በመጣበት ዘመናችን እነዚህ ዓብያተክርስቲያናቶቻችንና ገዳማቶቻችን ከምናስበው በላይ ውድ የሆነ ሚና ይጫወታሉ ስለዚህ ልንጠብቃቸውና ልንንከባከባቸው ይገባናል።

Tree Hugging Makes Us Healthier

treehuggerIn a recently published book, Blinded by Science, the author Matthew Silverstone, proves scientifically that trees improve many health issues such as; mental illnesses, Attention Deficit Hyperactivity Disorder (ADHD), concentration levels, reaction times, depression and the ability to alleviate headaches.

Countless studies have shown that children show significant psychological and physiological effects in terms of their health and well being when they interact with plants. They demonstrate that children function better cognitively and emotionally in green environments and have more creative play in green areas.

A large public health report that investigated the association between green spaces and mental health concluded that “access to nature can significantly contribute to our mental capital and wellbeing”.

So what is it about nature that can have these significant effects? Up until now it has been thought to be the open green spaces that cause this effect. However, Matthew Silverstone, shows that it is nothing to do with this by proving scientifically that it is the vibrational properties of trees and plants that give us the health benefits and not the open green spaces.

The answer to how plants and trees affect us physiologically turns out to be very simple. It is all to do with the fact that everything vibrates, and different vibrations affect biological behaviours. It has been proven that if you drink a glass of water that has been treated with a 10Hz vibration your blood coagulation rates will change immediately on ingesting the treated water. It is the same with trees, when touching a tree its different vibrational pattern will affect various biological behaviours within your body.

This vibrational idea is backed up throughout the book by hundreds of scientific studies to provide overwhelming proof that tree hugging after all is not such a crazy idea. Not only is it good for our health but it can also save the Government a lot of money by offering an alternative form of treatment that is free.

One report concluded with the following: “safe, green spaces may be as effective as prescription drugs in treating some forms of mental illnesses”.

Wouldn’t it be nice to hear from now on that doctors treat some forms of illnesses by suggesting a walk in the park rather than taking a packet full of pills.

__

Posted in Ethiopia, Faith, Psychology | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: