በዝዋይ ሐመረ ኖህ ቅድስት ኪዳነ ምህረት ገዳም አባቶች በር ዘግተው ቅዳሴ ገቡ። ሥርዓተ ቅዳሴው አልቆ ሲወጡ ግን የሽመልስ አብዲሳ አዲሱ ምልምል ጦር ቤተ ክርስቲያኗ በራፍ ላይ ቆሞ ጠበቃቸው። ከመቅደስም ገብቶ እያዳፋ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ወሰዳቸው። አይነ ሥውር አረጋዊ ካህን፣ የገዳሟን አስተዳዳሪ ጨምሮ አሥራ አንድ አባቶችን ወደ ወኅኒ ወረወረ።
የናዝሬት ሕፃናት ግድያ ፣ የእስክንድር ነጋ እሥራት ፣ የዝዋይ አባቶች መታሠር…
…ነጠብጣቦቹን እናገናኛቸው…
የስቅለት ዕለት የማርያም መቀነት/ቀስተ ደመና፤ “አይዟችሁ! አትፍሩ! ወደ ቤተ ክርስቲያን ሂዱ!” ብላን ነበር።