ህልሜ ይህን ይመስላል፦
በቃሊት በኩል ሳልፍ መጀመሪያ የታየኝ ቤተክርስቲያን በኢትዮጵያ ቀለማት የተከበበው ጥንታዊው እና ክቡ የቤተክርስቲያን ህንጻ ነው። “ይህን ቤተክርስቲያን እንዴት እስካሁን አላውቀውም?” በማለት እራሴን በመጠየቅ ዘወር ስል ሌላ ቤተክርስቲያን ታየኝ፤ በቦታው ያለውን የቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ህንፃ ይመስላል፤ ነገር ግን እርሱም አዲስ ሆነበኝ እንዴት እስካሁን አላየሁትም? በማለት ተገርሜ በቤተክርስቲያኑ ግዙፍነትና ውበት እጅግ በይበልጥ ተደነቅኩ። “ካሜራ ይዤ መምጣት አለበኝ” እንዳልኩ ህልሙ አለቀ።
ይህን ቪዲዮ ሳዘጋጅ ባለፈው ዓመት ልክ በሁዳዴ ፆም መግቢያ፣ ረቡዕ፣ የካቲት ፯፣ ፪ሺ፲ ዓ.ም ላይ በቃልቲ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ድንገተኛ የእሳት አደጋ መድረሱን አስታወስኩ።
ይህ ህልም የታየኝ በአቡነ አረጋዊ ዕለት እና (የቆሼን አደጋ አስመልክቶ ቪዲዮዎች አቅርቤ ነበር)፣ በሁዳዴ ፆም ማብቂያ ላይ ነው… ምን ሊሆን ይችላል? ቅዳሜ የቅዱስ ገብርኤል ዕለት ነው…ሁሉም ለበጎ እንደሚሆን እርግጠኛ ነኝ!