Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • March 2023
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    2728293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘ቁስቋም ማርያም’

ቁሱቋም ማርያም | በፋሺስቱ የኦሮሞ አገዛዝ የተገደሉት የወላይታ ብሔር ወጣቶች

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 15, 2021

💭 ያው የፋሺስቱ ኦሮሞ አገዛዝ ገና የሥልጣኑን ወንበር እንደተረከበ ነበር ኦሮሞ ያልሆኑትን ኢትዮጵያውያን አንድ በአንድ መጨፍጨፍ የጀመረው። እኛ በወቅቱ፤ “የግራኝን እባባዊ ዓይን ተመልከቱ! በጣም አደገኛ ሰው ነው ወዘተ” በማለት ቻነሎቻችን እስኪዘጉ ድረስ በተደጋጋሚ ስናስጠነቅቅ ነበር። ጭፍጨፋውን ከአንድ ኦሮሞ ካልሆነ ብሔር ወደሌላው ብሔር በሂደትና በማታለያ ስልት እየተሸጋገረ እየፈጸመ ዛሬ ወደ ትግራይ እና አማራ ክልሎች የተሸጋገረው።

አውሬው የበሻሻ ዲቃላ የግራኝ አብዮት አህመድ አሊ የባሌ ንግግር እንደ አንድ ትልቅ የዘርማጥፋት ጥሪ ተደርጎ በማስረጃነት መቅረብ ይኖርበታል። ከ እነ ለማ መገርሳ፣ ጃዋር እና ሽመልስ አብዲስ “ነፍጠኛን ሰባበረነዋል፣ የክርስቲያኑን አንገት በሜንጫ ነው የምንቆርጠው ወዘተ” ንግግር የከፋውና ዛሬ በደንብ ሲተገበር እያየነው ያለነው ይህን ነው፤፦

ኦሮሞ እስኪነቃ ነው እንጂ፣ እስኪነሳ ነው እንጂ ሲነሳ ሚዳቋ አትበላንም፤ እኛ ዝሆን ነን፤ እንሰብራለን፤ እንበላለን፤ እንገዛለን።” ሃሳብ አለን፤ ድርጅት አለን፤ ከአለም ጋር ግንኙነት አለን፤ ህዝባችን በስራ ያውቀናል፤ እኛም ህዝባችንን እናውቃለን፤ ሽማግሌዎቻችንን እናውቃለን፤ ተያይዘን መላውን አፍሪካን ለመለወጥ፣ ይሄ ዘመን የእኛ ስለሆነ፣ ይህን ዘመን የሰጠን አላህ በመሆኑ አሳልፈን ሰጥተን ዳግም ወደ ባርነት ለመመለስ አንፈልግም፤ ያ ደግሞ ተመልሶ አይመጣም። እጃችሁ የገባውን ነገር ጠብቁ፤ ቆጥቡ፤ አጠንክሩ፤ ጉድለት (ስህተት) ካለ ምከሩ። ያለበለዚያ ይህን ከጅ ካወጣን አጥር ውስጥ ተቀምጠው እንደሚያለቅሱት ዓይነት ለቅሶ ስለሚሆን፣ ከዚህ በኋላ ለኦሮሞ ለቅሶ የማይሆንለት ስለሆነ፣ ያገኘነውን ይዘን፣ የቀረውን ሞልተን፣ ወደ ፊት መሄድ እንድንችል”

በግልጽ ብሎናል።

💭 አረመኔው ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ ወደ ስልጣን መምጣቱን ተከትሎ በፋሺስቱ የኦሮሞ አገዛዝ የተካሄዱ ጭፍጨፋዎች፣ ግድያዎች፣ እገታቸው፣ ማፈናቀሎች፣ ቃጠሎዎችና ዝርፊያዎች፦

. ቡራዮ ላይ አራት መቶ የጋሞና የሌሎች ብሔር ተወላጆች ተጨፈጨፉ

. በዶዶላ የሰው ልጅ አካል ተቆራረጠ

. በአርባ ጉጉና በብኖ በደሌ የሰው ሬሳ ተጎተተ

. በሶማሌ ክልል ክርስቲያኖች ታረዱ

. በሲዳማ ዞን የሀይማኖት አባቶች ቤንዚን ተርከፍክፎ ተቃጠሉ

. በለገጣፎ በሰበታና በሰንዳፋ የንጹሃን ቤት በላያቸው ላይ ፈረሰ

. ፵፩/41 ዓብያተ ክርስቲያናት በኦሮሚያ ተቃጠሉ

. በርካታ መስጂድ ተቃጠለ

. ወለጋ ላይ 22 ባንክ ተዘረፈ

. ኦነግ በአጣዬ በካራ ቆሬና በኬሚሴ ንጹሃንን ጨፈጨፈ

፲፩. የአፋር አርሶ አደሮች በኡጋንዳ ታጣቂዎች ተረሸኑ

፲፪. /1 ሚሊዮን የጌድዮ ህዝብ ተፈናቀለ

፲፫. የአማራና የትግራይ ተወላጆች ከመስርያ ቤት እየተለቀሙተ ተባረሩ።

፲፬፣ ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ተገደለየአብን, የአማራ ወጣት እና የአማራ ተማሪ ማህበር አባላትና አመራሮች በግፍ በጅምላ ታሰሩ

፲፭. በአዲስ አበባ የወላይታ ተወላጆች በኦሮሞ ፖሊስ ተረሸኑ

፲፮. በቤንሻንጉል ክልል ንጹሃን በቀስት ተገደሉ

፲፯. ጎንደር ላይ ህጻናት ታግተው ተረሸኑ

፲፰. ፵፭/45 ሺህ የአማራ ተማሪዎች ከዩኒቨርሲቲ ተባረሩ

፲፱. አሳምነው ጽጌና ሰዓረ መኮንን ጨምሮ በርካታ የአማራና የትግራይ መሪዎች በኦነጉ አብይ ተረሸኑ

. በሐረርጌ የ ሁለት ወር አራስ ታረደች

፳፩. ወለጋ ላይ ፭/5 ተዋሕዶ ክርስቲያኖች በኦሮሞዎች ተገድለው ሬሳቸው ተቃጠለ

፳፪. ፹፮/86 ንጹሃን በአንድ ቀን ተጨፈጨፉ

፳፫. ፲፯ ሴት ተማሪዎች ከደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ታግተው እስከ አሁን ቁጥሩን እርግጠኛ መሆን ባይቻልም በርካታ ተማሪዎች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው ተሰምቷል

፪፬. ሻሸመኔ ላይ ሰው ተዘቅዝቆ ተሰቀለ

፳፭. የኦሮምያ ፖሊስ አዲስ አበባ ገብቶ ቤተክርስትያን በማፍረስ ሁለት ወጣቶች ገድሎ ፲፭/15 ወጣቶችን አቁስሏል

ይሄ ሁሉ የሆነው ራሱን ብልጽግና ብሎ በሚጠራው የኦሮሞው አውሬ ስብስብ ፓርቲ ነው። ይህ ከብዙ ግፎች በጥቂቱ ተጨፍልቆ የተጠቀሰ ነው።

ልብ በሉ ይህ ሁሉ ግፍና መከራ ተፈጽሞ አንድም ወንጀለኛ አልተያዘም፣ ለአንዱም ወንጀል ይቅርታ አልተጠየቀም፣ የሃዘን ቀን አልታወጀም። አረመኔው አብዮት አህመድ አሊ ኢትዮጵያን ያጠፋላቸውና እስላማዊቷን ኦሮሞ ኤሚራትን ይመስርትላቸው ዘንድ የተቀጠረ ጸረ-ጽዮን፣ ጸረ ኢትዮጵያና ጸረ ኦሮቶዶክስ አውሬ ነው።

👉 ይህ ከሦስት ዓመታት በፊት ልክ በዚህ ወቅት የቀረበ መረጃ ነው፤

✞✞✞አዲስ አበባ መስከረም ፱፡ ፪ሺ፲፩ ዓ.ም✞✞✞

የቁስቋም ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን አውደ ምህረት፤ ጸሎተ ፍትሃት በፋሺስቱ የኦሮሞ አገዛዝ ለተሰውት የወላይታ ብሔረሰብ ወንድሞቻችን።

በመስከረም ወር ላይ የኦሮሞ ሙስሊሞችን እንቅስቃሴ ለመቃወም በሰላማዊ መልክ በአደባባይ ወጥተው ከነበሩት ብዙ ወገኖቻችን መካከል ሁለት ወጣቶች መገደላቸው የሚታወስ ነው። ከዚህ ጋር በተያያዘ በ መስከረም ፱፡ ፪ሺ፲፩ ዓ.ም በታሪካዊው ቁስቋም ማርያም ቤተክርስቲያን አውደ ምህረት ላይ የወጣቶቹን ጸሎተ ፍትሀት እና ጸሎት በማከናወን አስፈላጊ የሆነውን ክብርም ተሰጥቷቸው ነበር።

የኀዘን ሥርዓቱ ላይም ብዙዎች ነጭ ለብሰው ይታያሉ።

በቁስቋም ማርያም ውሎዬ ይህን መሰሉ ታሪካዊ ነገር ይገጥመኛል ብዬ አላስብኩም ነበር፤ ቀደም ሲል ስለ ቀብር ሥርዓቱ ምንም የማውቀው ነገር አልነበረምና። ይህን እታዘብ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ ነው ወደዚህች ቅድስት ቦታ የመራኝ። ከቤተ ክርስቲያኗ ስወጣ፤ አንድ የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ የሆነ ሰው ወደ እኔ መጥቶ፤ “ለምንድን ነው ቪዲዮ ስትቀርጽ የነበረው?” ብሎ ሲጠይቀኝ፤ “እርስዎ ማን ነዎት?!” በማለት ሰውዬውን ዝም አሰኝቼው እንደነበር አስታውሳለሁ።

የሰማዕታቱ በረከታቸው ይደርብን!❖

_____________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ኀዳር ፮ ቁስቋም ማርያም፣ የቁስቋሟ ማርያም በምልጃዋ ትጠብቀን

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 15, 2018

ኀዳር ፮ ቀን እመቤታችን ወደ ግብጽ አገር ተሰዳ ስትመለስ ቁስቋም በምትባል አገር ገብታ ያረፈችበት በዓል ነው፡፡ ከገነት የተሰደደውን አዳም ወደ ገነት ለመመለስ ሲል ወልደ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከድንግል ማርያም ከአረጋዊው ዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ወደ ግብጽ ተሰደደ፡፡ ጌታችን ከ3 ዓመት ከ6 ወር የግብጽ ስደት በኋላ ወደ እስራኤል እንደሚመለስ አስቀድሞ ነቢየ ልኡል ሆሴዕ በትንቢት መነጽርነት ተመልክቶ “ልጄንም ከግብጽ ጠራሁት ” ብሎ ተናግሯል ሆሴ ፲፩፥፩

እንኳን አደረሰን!

ስለ መንበረ ንግስት ቁስቋም

ለእግዝአብሔር ካላቸው አክብሮትና ፍርሀት ለቤተ ክርስቲያንና በንግሥና ለሚያስተዳድሩት ህዝብ ካላቸው ፍቅር የተነሣ በህዝቡ “እምዬ” የሚል ስም የተሠጣቸው ንጉሠ ነገሥት አፄ ሚኒሊክ ከባለቤታቸው እቴጌ ጣይቱ ብጡል ጋር ሠራዊታቸውን አስከትለው ከእንጦጦ ቤተ መንግስታቸው ወደ ፍልውሃ እና ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ሲንቀሣቀሱ መንበረ ንግስት ቁስቋም ማርያም ቤተ ክርስቲያን በታነፀችበት ሥፍራ ላይ ድንኳናቸውን ተክለው ቆይታ ያደርጉበት ነበር፡፡

ከዕለታት አንድ ቀን እረፍት ባደረጉበት ሥፍራ እንቅልፍ ሸለብ ያደርጋቸውና አንዲት እጅግ የተዋበች ሴት ልጅ አዝላ በእቴጌ ጣይቱ አማሣል “ይህንን ቦታ ልቀቁልኝ፤ ቤቴን ልስራበት !!” ስትላቸው ያያሉ፡፡ ንጉሡም ከእንቅልፋቸው በመንቃት ያዩትን ሁሉ ለባለቤታቸው ለእቴጌ ጣይቱ ብጡል ይነግሯቸዋል፤ በመቀጠልም በእቴጌ ጣይቱ አምሣል ስለታየቻቸው በስምሽ ሆስፒታል ትሰሪበት ዘንድ ፈቅጄልሻለሁ ብለው ቦታውን ለእቴጌ ጣይቱ ይሰጧቸዋል፤ ከግዜ በኃላ ንጉሠ ነገሥት አፄ ምኒሊክ ስለታመሙ እቴጌ ጣይቱ ባለቤታቸውን ማስታመም ይጀምራሉ፤ አብረዋቸው አባታቸውን ያስታምሙ ለነበሩት ንግሥተ ነገሥት ዘውዲቱ አፄ ምኒሊክ ንጉሡ ያዩትን ራዕይና ሀኪም ቤቱን ለመስራት ያለመቻላቸውን ጭምር ይነግሯቸዋል፡፡ ከጥቂት ዓመታት በኃላ ንጉሠ ነገሥት አፄ ምኒሊክ አርፈው እቴጌ ጣይቱም እንጦጦ በቤተመንግስት ተቀምጠው ከእምዬ ምኒሊክ ጋር ያሣለፉትን ህይወት በማስታወስ አዲስ አበባን ቁልቁል እየተመለከቱ “ነበር እንዲህ ቅርብ ነው ወይ አሉ ይባላል !!” ብዙም ዓመት ሳይቆዩ እቴጌም ባለቤታቸውን ተከትለው አረፉ፡፡

ልጅ ኢያሱ መሪነቱን ይዘው በነበሩበት ሠዓት ከመኳንንቱ፤ መሳፍንቱ እና ሹማምንቱ ጋር በአስተዳደር ባለመግባባታቸው ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ሚኒሊክን ንግሥናቸውን እንዲረከቡ ሲደረግ ራስ ተፈሪ መኰንን አልጋወራሽነትን እንዲረከቡ ተደረገ፡፡ የንግሥና ህይወታቸውን ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ሚኒሊክ በመባል በትረ መንግስታቸውን ከተረከቡ በኃላ እቴጌ ጣይቱ የነገሯቸውን አስታውሰው፤ ዛሬ መንበረ ንግስት ቁስቋም ማርያም ቤተ ክርስቲያን በተተከለችበት ቦታ ላይ ሆስፒታሉን ለመሥራት የመሠረት ቁፋሮ ይጀመራል፡፡ በቁፋሮውም ወቅት አስደናቂ ነገር ይከሠታል፤ ይኽውም “ታቦተ ቁስቋም የሚል ፅሑፍ ያለበት የንግሥት እሌኒ የመዳብ ወንበር እና የብረት መስቀል” ይገኛል፡፡ ንግሥት እሌኒ የአፄ ዘርዓያቆብ እህት ሲሆኑ በ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበሩ ንግሥናቸውም በ1426 /ም እንደነበረ የኢትዮጵያ ታሪክ ያስረዳናል፡፡ የ492 ዓመት ዕድሜ ያለው ንብረት ከመሬት ተቀብሮ በጥበብ እግዚአብሔር ተጠብቆ ምንም ሳይበላሽ መገኘቱ ድንቅ የእግዝአብሔር ሥራን ያመላክተናል፡፡ በዚህም ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ተደንቀው ንዋየ ቅዱሣቱን መስቀል እና ሌሎቹንም የተገኙትን በታሪከ ነገሥታት በዓታ ለማርያም እንዲቀመጥ ያደርጋሉ፡፡ በቁፋሮው ግዜ በተገኘው ንዋየ ቅዱሣት ምክንያት ሥራው ወደ ተቋረጠው የሆስፒታል ቦታ በመሄድ ቤተክርስቲያን ይሠራ ዘንድ ሕዳር 6 ቀን 1918 .ም የመሠረት ድንጋይ አስቀመጡ፡፡ መቃኞውም በአስቸኳይ ይሠራ ዘንድ ለራስ ዳምጠው ትዕዛዝ ተሰጠ፡፡

በበጎ ሥራቸውና ካህናትን በመውደዳቸው ምክንያት ዘመነ ካህናት ተብሎ በሚጠራበት ግዜ በንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ሚኒሊክ ዘመነ ንግሥና በግብፃዊው ሊቀ ጳጳስ አቡነ ማቴዎስ ፍፃሜ ዘመን በሰሜን አዲስ አባባ ልዩ ስሙ እንጦጦ በተባለ ስፍራ በራስጌ ርዕሰ አድባራት እንጦጦ መንበረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም እና ደብረ ኃይል ቅዱስ ዑራኤል ወቅዱስ ኤልያስ በግርጌ ሀመረ ኖህ ቅድስት ኪዳነ ምህረት እና ቀጨኔ ደብረ ሠላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያንን አዋሣኝ አድርጋ በመሐል ባለ ልዩ ጉብታ (መሶብ) በምትመስል በግማሽ አዲስ አባባን ሊያሣይ በሚችል ቦታ ላይ መቅደስና ቅኔ ማህሌት ያለው መቃኞ ቤተክርስቲያን ሠርተው በትእዛዙ መሠረት አሠርተው ታቦተ ቁስቋም ማርያምንና ታቦተ መድኃኔዓለም እየሱስን ሌሎችንም ንዋየ ቅዱሳት በእጨጌ ተድላና በዓቃቤ ሠአት መምሬ አበበ ትዕዛዝ በንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ሚኒሊክ መኪና በካህናትና ዲያቆናት በምዕመናንና ምዕመናት ታጅቦ ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ እና ታላላቅ ሹማምንት በተገኙበት በግብፃዊው ሊቀ ጳጳስ አቡነ ማቴዎስ ባራኪነት ታቦŸ ኅዳር 6 ቀን 1919 .ም ገባች፡፡ ስያሜዋንም “መንበረ ንግሥት ቁስቋም ማርያም” ብለዋታል፤ የመጀመሪያው አስተዳዳሪም ቄስ ገበዝ ብሥራት ኃ/ማሪያም ነበሩ፡፡

______

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

በኢትዮጵያ ጠላቶች የተገደሉት ወጣቶች የቀብር ሥርዓት በቁስቋም ማርያም

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 11, 2018

በመስከረም ወር ላይ የኦሮሞ ሙስሊሞችን እንቅስቃሴ ለመቃወም በሰላማዊ መልክ በአደባባይ ወጥተው ከነበሩት ብዙ ወገኖቻችን መካከል ሁለት ወጣቶች መገደላቸው የሚታወስ ነው። ከዚህ ጋር በተያያዘ በ መስከረም ፱፡ ፪ሺ፲፩ ዓ.ም በታሪካዊው ቁስቋም ማርያም ቤተክርስቲያን አውደ ምህረት ላይ የወጣቶቹን ጸሎተ ፍትሀት እና ጸሎት በማከናወን አስፈላጊ የሆነውን ክብርም ተሰጥቷቸው ነበር።

የኀዘን ሥርዓቱ ላይም ብዙዎች ነጭ ለብሰው ይታያሉ።

በቁስቋም ማርያም ውሎዬ ይህን መሰሉ ታሪካዊ ነገር ይገጥመኛል ብዬ አላስብኩም ነበር፤ ቀደም ሲል ስለ ቀብር ሥርዓቱ ምንም የማውቀው ነገር አልነበረምና። ይህን እታዘብ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ ነው ወደዚህች ቅድስት ቦታ የመራኝ

በረከታቸው ይደርብን!

______

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: