ከዚህ በፊትም በተመሳሳይ መልክ ጨረቃዋ ታይታኝ እንደነበረው፥ አሁን ደግሞ በቃና ዘገሊላ፣ በቅዱስ ሚካኤል ዕለት፣ በጥምቀት ማግስት፣ በጨረቃ ግርዶሽ ወቅት፤ ደም የለበሰችው ጨረቃ የኢትዮጵያን ቅርጽ ቁልጭ አድርጋ ታሳያለች።
ይህ አልበቃ ብሎ፣ በየጊዜው በጸበል ስጠመቅበት የነበረውን የቤቴን ምንጣፍ ሳነሳው ላሚኔቱ ወለል ላይ (እርጥበቱ አወፍሮታል) የኢትዮጵያ ቅርጽ ቁጭ ብላ ታየችኝ፤ ማመን እስኪያቅተኝ ድረስ፤ ምን ይሆን? አልኩ። ድንቅ ነው!
ለማንኛውም ከሰይጣን ጋር ተመሳጥራችሁ በእናት ኢትዮጵያ ላይ ሤራ የምትጠነስሱ የውስጥም የውጭም ጠላቶቿ የስልጣን ጊዚያችሁ እያለቀ ነው። ቅዱስ ሚካኤል በቅርቡ ጥልቁ ጉድጓድ ውስጥ ይከታችኋል!
ጨረቃዋ ዛሬም ደም ለብሳ ትታያለች!