የዱባዩ መሪ መሐመድ ራሺድ አል ማክቱም ተሠውራ የነበረችው ሴት ልጁን ላቲፋ አል ማክቱምን ከ ህንዷ ከተማ ከጎዓ ጠልፎ ወደ ዱባይ አምጥቷታል፤ አሁን የትና እንዴት እንዳለች የሚታወቅ ነገር የለም።
ይህ የአሜሪካ ዜግነት ያለው የቀድሞ የፈረንሳይ ምስጢራዊ የስለላ ድርጅት መኮንን እሷን ከዱባይ ለማምለጥ በምታደርገው ትግል ላይ ከፍተኛ እርዳታ ያደረገ ግለሰብ ነው።
ላለፉት ወራት ላቲፋና ጓደኛዋ ከዚህ የፈረንሳይ መኮንን ጋር በአንድ ጀልባ በህንዷ ጎአ ተደብቀው ይኖሩ ነበር።
ለ16 አመታት ያህል የእስራት፣ ኢ–ሰብዓዊ ጥቃትና ስቃይ ሰለባዎች ለመሆን የበቃችው ልዕልት ላቲፋ ወደ አሜሪካ ለመሄድ እና ጥገኝነት ለመጠየቅ ነበር ዓላማዋ።