Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

Posts Tagged ‘ሶማሌ’

የሳውዲው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር በጅጅጋው “ስኬታማ” ጂሃዳዊ ጭፍጨፋ አቶ አህመድን “እንኳን ደስ አለን!“ ለማለት አዲስ አበባ ገባ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 10, 2018

ያውልሽ እናት ኢትዮጵያ! በአላሙዲን የሚመራውና በምዕራባውያኑ ሉሲፈራውያን የተቀነባበረው ቅሌታማ ድራማ ከቀን ወደ ቀን ሞቅ ሞቅ እያለ መጥቷል። ግድየልም፤ ሁሉም ነገር ሆን ተብሎ የሚደረግ ነገር ስለሆነ ለጊዜው ይታዩንና እንወቃቸው።

[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፺፪፥፯]

ኃጢአተኞች እንደ ሣር ሲበቅሉ ዓመፃ የሚያደርጉ ሁሉ ሲለመልሙ፥ ለዘላለም ዓለም እንዲጠፋ ነው።

በእውነት ሁኔታው እራስ የሚያስነቀንቅ ነው። እኔ የአገራችን መሪ ብሆን ኖሮ ሃዘን ላይ ያሉትን እህቶቼንና ወንድሞቼን እቅፍ አድርጌ ለማስተዛዘን ወደ ጅጅጋ ፈጥኜ እሄድ ነበር።

______

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ክርስቲያኖችን ለማረድ ሆ! እያሉ ገቡ | አሁን መላው የጅጅጋ ክርስቲያን ‘በቤተክርስቲያናችን እንለቅ’ ብሎ ቅ/ሚካኤል ነው የሚያድረው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 8, 2018

አሁን በቤቱ የሚያድር ክርስቲያን የለም! እንደ ድንገት መጡባቸው፤ አብረዋቸው ሲበሉና ሲጠጡ የነበሩት መሀመዳውያን ጎረቤቶቻቸው ሆ! ብለው እንደ ድንገት መጡባቸው።

ዓለም አቀፍ የዜና ማሠራጫዎች፡ ለክርስቲያኖች ተቆርቋሪ ነንየሚሉትን ጨምሮ፡ በጅጅጋው የክርስቲያኖች ዕልቂት ላይ ሁሉም ፀጥ ብለዋል። ይታየን፡ በሚኒያፖሊስ ከተማ ያሉ ሶማሌዎች 30 ክርስቲያኖችን ቢገደሉና 10 ዓብያተክርስቲያናትን ቢያቃጠሉ ኖሮ የሰበር ዜናው ጋጋታ ለ7 ቀናት ያህል መሬት መንቀጥቀጥ በፈጠረ ነበር።

ግድ የለም፤ ለእኛ ሁሉንም አንድ በአንድ የሚቀርጸው አምላካችን በቂ ነውየእግዚአብሔር አትኩሮት ይበቃናል።

______

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ጂሃድ በጅጅጋ | ክርስቲያኖች ተገድለው አስከሬናቸው ተቃጥሏል፣ ስምንት ዓብያተክርስቲያናት በእሳት ጋይተዋል | ምነው ዝምታው?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 6, 2018

ክርስቲያን ወገኖቻችን እየተገደሉ፣ ዓብያተክርስቲያናት እየተቃጠሉ፤ መሀመዳውያኑ እና ደጋፊዎቻቸው አክሱም መስጊድ እንሥራ ይላሉ። ምን ያህል እግዚአብሔርን ቢንቁት ነው፤ እንዴት ቢደፍሩን ነው?!

ላለፉት ወራት፡ ሁሉም ነገር በደንብ የተቀነባበረ መሆኑን እና ጂሃዲስቶች ወደ አዲስ አበባ እንዲገቡ በይፋ ሲፈቀድላቸው፡ ጂሃዳዊ ጦርነት በግልጽ ለማወጅ መዘጋጀታቸውን ለመረዳት የማይችል የታወረ ብቻ ነው። የሕዝበ ክርስቲያኑ ዝምታ ያደንቁራል፤ ሞኝነቱ እራስ ያስነቀንቃል፤ ምነው ጃል?! እስከ መቼ እንዲህ እንታለላለን?

ሞባይል እያንዳንዱ ኪስ ውስጥ በሚገኝበት ዘመን ይህን ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት በቪዲዮ ቀርጾ ሊያሳየን የበቃ ሰው እንኳን አላየንም፤ አይ ጉዳችሁ የዜና ማሰራጫዎች፣ አይ ቅሌታችሁ ፖለቲከኞች እና የቤተክህነት አገልጋዮች!

ከጥቂት ሳምንታት በፊት የሚከተለው ቪዲዮ ላይ የሚታየው ጥቁር ሙስሊም ማንን ይመስላል? ብዬ ጠይቄ፤ እስካሁን የታየው ሰው የለም፤ ምን ያህል በመንፈስ ብንታወር ነው?!

በኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መምህር የሆነው ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በጅጅጋው ጥቃት 8 አብያተ ክርስቲያናት ላይ ጥቃት መፈጸሙን ገልጿል::

በሶማሊ ክልል ሰሞኑን የተሠራው ዘግናኝና አረመኔያዊ ሥራ ነው፡፡ ሰውን በቁሙ ማቃጠል ሴቶችን መድፈር መኪና ይዞ በየቤቱ እየዞሩ የሰው ንብረት መዝረፍ አብያተ ክርስቲያናትን ማቃጠል፡፡ ለመሆኑ መንግሥት የለም? አንድ ክልልስ ሥልጣኑ የሰው ዘርን እስከማጥፋት ድረስ ነው? ይህን መሰሉ ግፍ ዚያድባሬ ኢትዮጵያን የወረረ ጊዜ ነበር በምሥራቁ ክፍል የተፈጸመው ዚያድባሬ አለ ማለት ነው?” ያለው ዳንኤል ክብረት “የክልሉ ፕሬዚዳንት የልቡን ከሠራ በኀላ ትናንት ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን መጥቶ እንመካከር ሲል ነበር፡፡ ሰው ከተቃጠለ፡ ንብረት ከተዘረፈ፡ ቤተ ክርስቲያን ከተቃጠለ በኀላ የምን ምከከር ነው?” ብሏል::

አሁን በዚያ ክልል ስላለው ሕዝብ እንደ አዲስ ማሰብ አለብን፡፡ ሌላ መፍትሔም ማምጣት አለብን ከተቃጠለው ሕዝብ ይልቅ የአቃጣዩ አያያዝ በሚያስጨንቃቸው ሰዎች ሥር መኖር ከባድ ነው፡፡” ያለው ዳንኤል በሰሞኑ ግጭት የተጎዱ አብያተ ክርስቲያናትና ካህናት ዝርዝር የሚል መረጃ አውጥቷል

  1. + የዋርዴር ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ሲቃጠል ቄስ ያሬድ ኅቡዕ ተገደሉ፣

  2. + ቀብሪ ደኃር ደብረ መድኃኒት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ተቃጥላለች፡፡

  3. + ደጋሐቡር መካነ ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ሲቃጠል ቄስ ኪዳነ ማርያም ንብረቱ ተገድለዋል፡፡

  4. + በጅጅጋ የምሥራቀ ፀሐይ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ካቴድራል እና የደብረ ሰዋስው ገዳም የተቃጠሉ ሲሆን

    አባ ገብረ ማርያም አስፋው፣ መ/ር አብርሃም ጽጋቡ እና ሌላ አንድ ካህን ተገድለው አስከሬናቸው ተቃጥሏል፡፡

  5. + ጅጅጋ ቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን ተቃጥሏል

  6. + ጅጅጋ ቅዱስ ጊዮርጊስ ተቃጥሏል

  7. + ሽላቦ ቀራንዮ መድኃኒዓለም ቤተ ክርስቲን ተቃጥሏል

  8. + ጎዴ ቅዱስ ገብርኤል አጥሩ ተቃጥሏል

______

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith, Life | Tagged: , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ጂሃድ በጅጅጋ | የግራኝ አህመድ ልጆች፡ ክርስቲያኖችን ማደን ጀምረዋል፤ ሁለት የተዋሕዶ ዓብያተክርስቲያናትን አቃጥለዋል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 5, 2018

ሶማሌ ተብሎ በተሰየመው የኢትዮጵያ ክልል፡ በ ጅጅጋ ከተማ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ቁልፍ የከተማይቱን ተቋማት ለመቆጣጠር ጣልቃ መግባቱ ተገልጿል። የመከላከያ ስራዊቱ በጅጅጋ ከተማ ዝርፊያና ብሄርን ያማከለ ጥቃት በአንዳንድ አካባቢዎች በመታየቱ ነው ጣልቃ ለመግባት የወሰነው

ሶማሌ ሙስሊም ባልሆኑ ኢትዮጵያውያን ላይ፡ ልክ በግራኝ አህመድ ዘመን እንደነበረው፡ አሁንም አስከፊ የሆኑ ጥቃቶች ባለፉት ሰዓታት በመካሄድ ላይ ናቸው።

ሮይተርስ እንደዘገበው፡ ሁለት የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ዓብያተ ክርስቲያናት ተቃጥለዋል

ውድቀታችንን የሚመኙልን ሉሲፈራውያኑ ይህን መሰሉን ዜና ቶሎ ለማቅረብ የሚቀድማቸው የለም።

ይህን መሰሉን ጂሃዳዊ ጥቃት ታዛቢዎች ለዘመናት ስንጠብቀው የነበረ ነው። ልክ በግራኝ አህመድ ጊዜ እንደነበረው አሁንም ሶማሌዎችን እየቀሰቀሰች፣ እያበረታታችና እየደገፈች ያለቸው ፀረክርስቶስ ቱርክ ናት። ይህን አንዳንዶቻችን በተደጋጋሚ ተናግረናል። ቱርኮችና ሶማሌዎች በጣም ልዩ የሆነ “ ፍየላዊ ፍቅር” እንዳላቸው፡ ቱርክ አሁንም ጦሯን በሶማሊያ ማስፈሯ ከተንኮለኞቹ አውሮፓውያኖች በስጦታ መልክ የምታገኘውን ገንዘብ ወደ ሶማሊያ ማጉረፏ ብቻ በቂ ማስረጃ ነው። ቱርኮችና ሶማሌዎች ይህን “ልዩ ፍየላዊ ፍቅር” እርስበርስ ሲለዋወጡ ለመታዘብ ዚህና በሌሎች ብዙዎች ድህረ ገጾች ላይ ያሉትን አንዳንድ ዘገባዎች እናንብብ

ቱርክ (ጎግ ማጎግ) በግዛቷ የሚገኙትን ክርስቲያኖች ሙልጭ አድርጋ ካጠፋች በኋላ አሁን በቆጵሮስ፣ ሶሪያ እና ኢራቅ ቀስበቀስ የክርስቶስን ተከታዮች በሱኒ ቱርክ እና አረብ ሙስሊሞች በመተካት ላይ ናት፤ ዓለም በዚህ ጉዳይ ላይ ጸጥ ብሏል። ኢትዮጵያንም በምዕራባውያኑ ፈቃደኝነት እንደዚሁ ቀስበቀስ በመክበብና በኢንቨስትመንት መንገድም ሰርጎ ገብ ድርጊቶችን በመፈጸም ላይ ናት። አሁን በሱዳን እና በሶማሊያ “የግራኝ አህመድ ኮማንዶዎችን” በማቋቋም ላይ ናት።

+ በእውነት እነዚህን ፀረክርስቶስ የዲያብሎስ አርበኞች አቅፈን እየኖርን፡ ሰላም፣ ፍቅርና ደስታን መመኘት ይገባናልን?

+ መሀመዳውያኑ ሶማሌዎች የተሰጣቸውን ግዛት ከክርስቲያኖች ለማጽዳት አሁን መነሳሳታቸው ያለምክኒያት ነውን?

+ መሀመዳውያኑ አሁን አንድ ነገር ሳያዩ “መስጊድ በአክሱም ይሠራልን!“ እያሉ መለፈፍ መጀመራቸው በአጋጣሚ ይመስለናልን?

ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ ንቁ፡ እንንቃ!

______

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: