በትናንትናው ዕለት በአንድ የናይሮቢ ሆቴል ውስጥ በሙስሊም ሶማሌ አጥፍቶ ጠፊዎች ከተገደሉት 21 ሰዎች መካከል አሜሪካዊው ጄሰን ሽፒንድለር አንዱ ሆኖ ተገኝቷል። ሽፒንድለር በኢትዮጵያ አዲስ አመት መግቢያ ላይ፡ እ.አ.አ በ መስከረም 11/ 2001 ዓ.ም (Sept 11, 2001) በኒው ዮርኩ የዓለም ንግድ ማዕከል ከደረሰው አስከፊ ጥቃት የተረፈ ግለሰብ ነበር።
በጣም የሚያሳዝንና የሚገርም የሕይወት እጣ ነው።
የዚህ አሳዛኝ አጋጣሚ መከሰት ከኢትዮጵያ ጋር የሚያያዝበት ሁኔታ አለ። ይህን የሶማሌዎች ዘመቻ አስመልክቶ በሚቀጥሉት ቀናት ሌላ ቪድዮ ለማቅረብ እሞክራለሁ።