ወገኖቼ፡ እጅግ በጣም የከፋ ግፍ በሃገራችን እየተፈጸመ ነው። ኦሮሚያ በተባለው ሲዖል በናዚዎች ጊዜ እንኳን ታይቶና ተሰምቶ በማይታወቅ መልክና እጅግ ዘግናኝ በሆነ የግድያ ዘመቻ ወገኖቻችን አካላቸው ተቆራርጦ፣ ተጠብሶና ተሰቅሎ እየታየ እንደሆነ ምንጮች ጠቁመዋል። ባካችሁ ወገኖች እያንዳንዷን ነገር መዝግቡልን፣ ቅረጹልን!
በሌላ በኩል የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ከፍተኛ አመራሮች አቶ እስክንድር ነጋ እና አቶ ስንታየሁ ቸኮል መታሰራቸው የሚታወስ ነው ነገር ግን በአሁን ሰአት ከፍተኛ ድብደባ እና እንግልት እየደረሰባቸው ነው። ከውስጥ የወጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ለ ሁለት ቀናት ምንም አይነት ምግብ እንዳልቀረበለት እና በረሀብም ጭምር እየቀጡት ነው። ልብ በሉ፦ እንድ እምነስቲ “የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ነን” የሚሉት ግብዝ ድርጅቶች ጸጥ ብለዋል። ኢትዮጵያውያን የሚፈተኑበት ወቅት አሁን ነው!
“…ጦርነት ውስጥ እንገባለን!” ብሏል እኮ ገዳይ አብይ አስቀድሞ። እስካሁን የተናገራቸውን ጽንፈኛ ንግግሮች ሁሉ በተግባር ላይ እያዋላቸው ነው። ከጀግናው ኢንጂነር ስመኘው እስከ ጽንፈኛው አጫሉ ሁሉንም የገደላቸው ዐቢይ አህመድ አሊ ነው። 100%! እርግጠኛ ነኝ።
የበሻሻ ቆሻሻን የባሌ ንግግር እናስታውስ፦
“ኦሮሞ እስኪነቃ ነው እንጂ፣ እስኪነሳ ነው እንጂ ሲነሳ ሚዳቋ አትበላንም፤ እኛ ዝሆን ነን፤ እንሰብራለን፤ እንበላለን፤ እንገዛለን። ሃሳብ አለን፤ ድርጅት አለን፤ ከአለም ጋር ግንኙነት አለን፤ ህዝባችን በስራ ያውቀናል፤ እኛም ህዝባችንን እናውቃለን፤ ሽማግሌዎቻችንን እናውቃለን፤ ተያይዘን መላውን አፍሪካን ለመለወጥ፣ ይሄ ዘመን የእኛ ስለሆነ፣ ይህን ዘመን የሰጠን እግዝያብሄር በመሆኑ አሳልፈን ሰጥተን ዳግም ወደ ባርነት ለመመለስ አንፈልግም፤ ያ ደግሞ ተመልሶ አይመጣም። እጃችሁ የገባውን ነገር ጠብቁ፤ ቆጥቡ፤ አጠንክሩ፤ ጉድለት (ስህተት) ካለ ምከሩ። ያለበለዚያ ይህን ከጅ ካወጣን አጥር ውስጥ ተቀምጠው እንደሚያለቅሱት ዓይነት ለቅሶ ስለሚሆን፣ ከዚህ በኋላ ለኦሮሞ ለቅሶ የማይሆንለት ስለሆነ፣ ያገኘነውን ይዘን፣ የቀረውን ሞልተን፣ ወደ ፊት መሄድ እንድንችል”