በቱርክ እና ግሪክ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀ ልክ በዮሐንስ ራእይ መጽሐፍ ውስጥ በተጠቀሱት የ፯/ 7ቱ አብያተ ክርስቲያናት አካባቢ መሆኑ እጅግ በጣም የሚያስገርምና ብዙ ነገር የሚናገር ነው። በግሪኳ ፍጥሞ (Patmos) ደሴት ነበር ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ የራእይን መጽሐፍ የፃፈው። በቱርክ ደግሞ በመንቀጥቀጡ ክፉኛ የተመታቸው ክፉኛ የተመታችው ስሚረነስ (Smyrna) ፯ቱ አብያተክርስቲያናት ከሚገኙባት ቦታዎች አንዷ ናት። ዛሬ ኢዝሚር ትባላለች። የክርስቶስ ተቃዋሚውና የሀሰተኛው ነብይ መሀመድ የልደት ቀን በሚከበርበት (መውሊድ) ዕለት መከሰቱ ደግሞ ያለምክኒያት አይደለም። ዋ! ዋ! ዋ!
[የዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ ፩፥፱]
“እኔ ወንድማችሁ የሆንሁ ከእናንተም ጋር አብሬ መከራውንና መንግሥቱን የኢየሱስ ክርስቶስንም ትዕግሥት የምካፈል ዮሐንስ ስለ እግዚአብሔር ቃልና ስለ ኢየሱስ ምስክር ፍጥሞ በምትባል ደሴት ነበርሁ።”
👉ከሦስት ሳምንታት በፊት እነዚህን ፯ ዓብያተክርስቲያናት በሚከተለው ጽሑፍ ማንሳቴን አሁን ስገነዘብ “ምን ይሆን?” እያልኩ በመገረም በመንቀጥቀጥ ላይ ነኝ።
አውሎ ንፋሱ “ኢዝሚር” ብለው የሰየሟትን የመጽሐፍ ቅዱሷን ሰምርኔስ ከተማ ነው ያጠቃት።
ስምርኔስን ኢዝሚር፣ ናዝሬትን አዳማ…የቦታ መጠሪያ ስሞችን እየቀያየሩ እግዚአብሔር ያልሰጣቸውን ቦታዎች ለሚወሩ ለክርስቶስ ተቃዋሚዎች፤ ዋ! ዋ! ዋ!
በዮሐንስ ራዕይ ላይ የተጠቀሱት ሰባቱ የእስያ አብያተ ክርስቲያናት ያለምክኒያት አይደለም ዛሬ “ቱርክ” በተባለቸው የክርስቶስ ተቃዋሚ ሃገር እንዲገኙ የተደረገው። ድንቅ ነው!
የቦታዎቹን ስም ልክ ናዝሬትን – አዳማ ፣ ደብረዘይትን – ቢሾፍቱ ብለው እንደሰየሙት እንደ እኛዎቹ የቱርክ ወኪሎች ወራሪዎቹ ቱርኮችም እግዚአብሔር የሰየማቸውን ቦታዎች እንደተለመድው እንዲህ በማለት ቀይረዋቸዋል፦
፩. ኤፌሶን – ሰልጁክ
፪. ሰምርኔስ – ኢዝሚር
፫. ጴርጋሞን – ቤርጋማ
፬. ትያጥሮን – አኪሳር
፭. ሰርዴስ – ሳርት
፮. ፊልድልፍያ – አላሸሂር
፯. ሎዶቅያ – ዴንዝሊ
_________________________