Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • May 2023
    M T W T F S S
    1234567
    891011121314
    15161718192021
    22232425262728
    293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘ስመኘው በቀለ’

የቅዱስ መቃርስ ገዳም አስተዳዳሪ የሆኑት አባታችን በአሰቃቂ መልክ ተገደሉ | ልክ እንደ ወንድም ስመኘው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on July 31, 2018

በግብጻውያን ክርስቲያን ወገኖቻችን ዘንድ ተወዳጅ የሆኑትና የዝነኛው የአባ መቃርስ ገዳም – የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ እና የነብዩ ኤልሳዕ አጽሞች የተቀበሩበት ገዳም ነው – አስተዳዳሪ የሆኑት አባ ኤፒፋኒዮስ ባለፈው እሑድ ዕለት በካይሮ ሰሜን ምዕራብ በሚገኘው በዚህ በረሃ ገዳም ውስጥ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለው ተገኝተዋል። የአባ ኤፒፋኒዮስ አካል ተወጋግቶ፣ ደማቸው ፈስሶ እና አንጎላቻውም ከተፈረካከሰው ራስ ቅላቸው ወጥቶ ተገኝቷል።

እግዚአብሔር ነፍሳቸውን ከቅዱሳን ይደምርልን!

ዑራኤል + ጊዮርጊስ + ተክለ ሐይማኖት + መርቆሪዎስ

የአባይ ሤራ

ይህን ጭካኔ የተሞላበት ግድያ ከወንድማችን ስመኘው በቀለ አገዳደል ጋር የሚያገናኙት አንዳንድ ነገሮች አሉ፦

  • 1. ሁለቱም የተገደሉት ባንድ ወቅት ነው
  • 2. ሁለቱም ደማቸው ፈሶባቸዋል
  • 3. ሁለቱም ከአባይ ጋር የተያያዘ ሥራ ነበራቸው፤ ከአባይ ወንዝ እየጠጡም ኖረዋል
  • 4. ሁለቱም የተገደሉት በ መሀመዳውያን ሳጥናኤል ወኪሎች ነው
  • 5. ሁለቱም ቅዱስ በሆኑ ቦታዎች ላይ ነው የተገድሉት፤ ስመኘው በ “መስቀል” አደባባይ፣
  • አባ ኤፒፋኒዮስ በቅዱስ መቃሬ ጽድቅ ገዳም

ስለ ፃድቁ አባ መቃርስ ከቀረበ ትዕይንት የተወሰደ፦

አባ መቃርስአንተ እርኩስ መንፈስ፡፡ እነሆ በእግዚአብሔር ስም ይዤሃለሁ እንዳትንቀሳቀስ! … ለመሆኑ ከየት ነው የምትመጣው;

ሳጥናኤልበረሀ ላይ ያሉትን መነኮሳት እየተፈታተንኩ ነው፡፡ ከዛው ነው የምመጣው

አባ መቃርስአንተ ዲያቢሎስ አንተ ክፉ ለበረሃ ካሉት መነኮሳት ጋር በምታደርገው ውጊያ ዙሪያ ስራህ እንዴት ነው;

ሳጥናኤልበጣም መጥፎ ነው፡፡ ምንም እንኳን መነኮሳቱን ክፉ ኃጥያት እንዲሰሩ ባሳስባቸውም ሁሉም ያሳሰብኳቸውን ኃጥያት ለንሰሐ አባታቸው ይናገራሉ፡፡ አንዱ ግን ለንሰሐ አባቱ ስለማይናገር ከኔ ጋር ተወዳጅቷል፡፡

አባ መቃርስአንተ ርኩስአንተ አስመሳይ ዘላለምህን ትዕቢተኛሀሰተኛቅናተኛ የጠላህና የተዋረድክ ነህ። ክፉነፍሰ ገዳይእውነት እንዲሰማ የማትሻለጥፋት አነሳሽጌተን እንኳን ያልፈራህ ፈታኝ ነህ። መልካምን ወደ ክፉ የምትለውንለክፋት የምታነሳሳና የምትመራአታላይአስመሳይ ከበጎ የምታዘገይ እንቅፋት ነህ። በምትሃት ተዓምር እያደረግህ ነገር የምታባብስ ሰዎችን በሕመም በምታሰቃይመንቻካና ምቹ ጊዜን የምትጥብቅ ባለጋራ ነህ። አሁን በመስቀሉ ሳላስርህ ካጠገቤ ራቅ። (ሰይጣን ይሰወራል) (ከጥቂት ዝምታ ቦሃላ) አዎን ያን የተሳሳተ መነኩሴ ማግኘት አለብኝ።

______

Posted in Ethiopia, Faith, Life | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: