Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • March 2023
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    2728293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘ሳሪስ አቦ’

አቡነ አረጋዊ ለከሃዲዎቹ ሻዕብያዎች/ ሕወሓቶችና ኦነጎች፤ “ዛሬም የሉሲፈርን ባንዲራ ታውለበልባላችሁን?”

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 22, 2023

💭 አቡነ አረጋዊ | ትግራዋዩ እንጀራ ሻጭ ወጣት ቤተክርስቲያኑን በአረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ እንዲቀባ በራዕይ ታዘዘ

💭 ትዕዛዙንም በሥራ ላይ በማዋል፤ ይህችን ውብ ቤተክርስቲያን በጽዮን ቀለማት እንዲቀባት ራዕይ የታየው ወንድማችን እንጀራ ጋግሮ በመሸጥ የሚተዳደር ወጣት ነው። ቤተክርስቲያኗን እና አካባቢዋን ከቀባ በኋላ በዚሁ በሳሪስ አቦ ኮረብታ ላይ በ አዲስ መልክ ለሚሰራው ለ አቡነ አረጋዊ ቤተከርስቲያን ህንፃ የግንብ አጥር በመገንባት ላይ ይገኛል።

😇 በእውነት የእግዚአብሔር ሥራ ድንቅ ነው! አባታችን አቡነ አረጋዊ ዛሬ በዕለታቸው የሚጠቁሙንና የሚያሳስቡን ቍል ክስተቶች አሉ፤

የጽዮን ቀለማት የደመቁበትን ሰንደቅ በኩራት ማውለብለብ የሚገባቸው አክሱም ጽዮናውያን የማይገባቸውን የሉሲፈርን/ቻይናን ባንዲራ ሲያውለበልቡ፤

የጽዮን ቀለማት የደመቁበትን ሰንደቅ ማውለብለብ የማይገባቸው አስመሳይ ቃኤላውያን ደግሞ የጽዮንን ቀለማት፤ ልክ እንደ ሰዶማውያኑ፤ ዛሬም ያለሃፍረት በማጠልሸት ላይ መሆናቸው፤ ሕዝበ ክርስቲያኑን ወደተጨማሪ ፈተናዎች ያስገቡታል።

🛑 እነዚህን ቀናት በጥሞና እንከታተላቸው፤ ሰይጣን ተለቅቋል፤ በግራኝ ሞግዚት በክርስቶስ ተቃዋሚዋ ቱርክ ሰማይ ላይ በቅዱስ ሚካኤል ዕለት የታየው ደማማ ደመና ብዙ የሚለን ነገር አለ። የዋቄዮአላህሉሲፈር ጭፍሮች ኢትዮጵያን፣ ተዋሕዶ ሃይማኖቷን፣ ግዕዝ ቋንቋዋንና ሰንደቋን ለመዋጋት ከምንጊዜውም በላይ ተነቃቅተውና ተደራጅተው ተሰማርተዋል። ጊዚያቸው አጭር መሆኑን ተገንዝበውታል፤ ስለዚህ በተቻላቸው አቅምና ፍጥነት የተቻላቸውን ያህል ጥፋት ለማድረስ፣ የሚችሉትን ያህል ሰው አስተው ወደ ጥልቁ አብረው ለመውረድ ወስነዋል። አጥፍተው ጠፊዎቹ ሌላ አማራጭ የላቸውም!

👉 ክፍል ፪. ጥር ፲፬ የአባታችን አቡነ አረጋዊ በዓለ ንግሥ በምዕራፈ ቅዱሳን ፈለገ ህይወት አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ አና አቡነ አረጋዊ ገዳም

❖❖❖ የደብረዳሞው ጻድቁ አባታችን አቡነ አረጋዊ የእመቤታችን የአሥራት ሃገር የሆነችውን እናት ኢትዮጵያን ያጸደቋት፣ በአባታችን በኖህ በኩል ያገኘናቸውን የጽዮን ማርያም ቀለማትን ለዓለም ያሳዩ ድንቅ አባት ናቸው።❖❖❖

ጻድቁ አባታችን አቡነ አረጋዊ ዛሬ በተለይ በትግራይ በበደልና ግፍ ከሚሰቃዩት አባቶቻችን እና እናቶቻችን፣ ወንድሞቻችን እና እኅቶቻችን ጋር ናቸው፤ ረድኤት በረከታቸው ለሁላችን ይድረሰን!

❖❖❖[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፲፫]❖❖❖

  • ፩ ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል። በሥራቸው ረከሱ፥ ጐስቈሉ፤ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም።
  • ፪ የሚያስተውል እግዚአብሔርንም የሚፈልግ እንዳለ ያይ ዘንድ፤ እግዚአብሔር ከሰማይ የሰው ልጆችን ተመለከተ።
  • ፫ ሁሉ ዐመፁ በአንድነትም ረከሱ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም፤ አንድም ስንኳ የለም።
  • ፬ ጕሮሮአቸው የተከፈተ መቃብር ነው፥ በምላሳቸው ሸነገሉ፤
  • ፭ ከከንፈራቸው በታች የእባብ መርዝ አለ፤ አፋቸው መርገምንና መራራን ተሞልቶአል፤
  • ፮ ደምን ለማፍሰስ እግራቸው ፈጣን ነው፤ ጥፋትና ጕስቍልና በመንገዳቸው አለ፥ የሰላምን መንገድ አላወቁአትምና፤ እግዚአብሔርን መፍራት በዓይናቸው ፊት የለም።
  • ፯ ሕዝቤን እንደ እንጀራ የሚበሉ ኃጢአት የሚሠሩ ሁሉ በውኑ አያውቁምን? እግዚአብሔርንም አይጠሩትም።
  • ፰ በዚያ በታላቅ ፍርሃት እጅግ ፈሩ፥ እግዚአብሔር በጻድቃን ትውልድ ዘንድ ነውና።
  • ፱ የድሆችን ምክር አሳፈራችሁ፥ እግዚአብሔር ግን ተስፋቸው ነው።
  • ፲ ከጽዮን መድኃኒትን ለእስራኤል ማን ይሰጣል? እግዚአብሔር የሕዝቡን ምርኮ በመለሰ ጊዜ፥ ያዕቆብ ደስ ይለዋል፥ እስራኤልም ሐሤት ያደርጋል።

_______________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

አቡነ አረጋዊ | ትግራዋዩ እንጀራ ሻጭ ወጣት ቤተክርስቲያኑን በአረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ እንዲቀባ በራዕይ ታዘዘ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 22, 2021

ትዕዛዙንም በሥራ ላይ አዋለው። ይህችን ውብ ቤተክርስቲያን በቀለሞቻችን እንዲቀባት ራዕይ የታየው ወንድማችን እንጀራ ጋግሮ በመሸጥ የሚተዳደር ወጣት ነው። ቤተክርስቲያኗን እና አካባቢዋን ከቀባ በኋላ በዚሁ በሳሪስ አቦ ኮረብታ ላይ በ አዲስ መልክ ለሚሰራው ለ አቡነ አረጋዊ ቤተከርስቲያን ህንፃ የግንብ አጥር በመገንባት ላይ ይገኛል።

በእውነት የእግዚአብሔር ሥራ ድንቅ ነው!

❖ ❖ ❖ የደብረዳሞው ጻድቁ አባታችን አቡነ አረጋዊ የእመቤታችን የአሥራት ሃገር የሆነችውን እናት ኢትዮጵያን ያጸደቋት፣ በአባታችን በኖህ በኩል ያገኘናቸውን የጽዮን ማርያም ቀለማትን ለዓለም ያሳዩ ድንቅ አባት ናቸው።

ጻድቁ አባታችን አቡነ አረጋዊ ዛሬ በተለይ በትግራይ በበደልና ግፍ ከሚሰቃዩት አባቶቻችን እና እናቶቻችን፣ ወንድሞቻችን እና እኅቶቻችን ጋር ናቸው፤ ረድኤት በረከታቸው ለሁላችን ይድረሰን!

💭 ባለፈው ዓመት ልክ በዚህ ሰሞን የሚከተለውን ጽፌ ነበር፦

👉 በተዋሕዶ ልጆች ላይ በኦሮሚያ ሲዖል እየተካሄደ ያለው ጭፍጨፋ በግራኝ ዐቢይ አህመድ መስተዳደር በደንብ ተጠንቶበትና በቅደም ተከተልም እንደሚካሄድ በአርሲ ነገሌ የተፈጸመው ጂሃዳዊ ዘመቻ ይጠቁመናል።

እስኪ ተመልከቱ፦ አታላዩ ዐቢይ አህመድ አገር-አቀፍ ምርጫውን ከግንቦት ወር አንስቶ የክረምቱንና የፍልሰታ ጾም ሳምንታት በመጠቀም ወደ ነሐሴ መጀመሪያ አዘዋውሮት ነበር ከዚያም ነሐሴ መጨረሻ እንዲሆን ወሰነ። ኮሮና ከመምጣቷ በፊት ይህ ምርጫ እስኪደርስ ድረስ አሁን በምናያቸው ሁለት ጉዳዮች የሕዝቡን ቀልብ ለመግፈፍ አቀዱ። እነዚህም፦

👉 ፩ኛ. የሕዳሴውን ግድብ በሐምሌ ወር ላይ “እንሞላዋለን ፥ አንሞላውም”

👉 ፪ኛ. አጫሉን ገድሎ ጂሃድ ማካሄድ”

💭 ኦሮማራዎች እና አህዛብ በትግራይ ሕዝብ ላይ ጦርነቱን እንደከፈቱ ደግሞ ይህን ጠቁሜ ነበር፦

👉“እናስታውሳለን ባለፈው ዓመት ላይ ምርጫውን መጀመሪያ ላይ ሆን ብሎ በፍልሰታ ጾም ወቅት ለማድረግ ወስኖ እንደነበር። አዎ! ዛሬ ደግሞ ልክ በዕለተ አቡነ አረጋዊ ሲውልና የገና/ የነብያት ጾም ሲቃረብ የተዋሕዶ ልጆችን ለመጨፍጨፍ በመዛት፣ በማሸበር እና በመሰናዳት ላይ ነው። “ደብረ ዳሞ!””

“Nobel Peace Laureate Treating a Whole City as a Military Target | War Crimes”

ዋው! ፋሺስቱ ሙሶሊኒ እና ናዚው ሂትለር እንኳን ለመናገር ያልደፈሩትን ነገር ነው እነዚህ አውሬዎች በመናገር ላይ ያሉት!

👉 ግራኝ ሰኔ ፲፬/14ትን ለ’ምርጫው’የመረጠበት ‘ምስጢር’አቡነ አረጋዊ + ጾመ ሐዋርያት (የሰኔ ጾም)

💭 ዘንድሮም እባቡ ግራኝ እና መንጋው ኢትዮጵያን በብርሃን ፍጥነት እያፈራረሱ በሚያንቀላፋው ሕዝብ ላይ ተመሳሳይ ድራማዎችን በመሥራት ላይ ይገኛሉ። ልክ ከወር በኋላ በኦሮማራ ቃኤላውያኑ ተከታዮቹ “ተመርጫለሁ” የሚሉበትን “የምርጫ ቀን” ሆን ብሎ በማዛወር ሰኔ ፲፬/14የሰኞ ዕለትን መርጠዋል። አዎ! ተዋሕዶ ክርስቲያኖች ከቤታቸው እና ከቤተ ክርስቲያናቸው የማይርቁበትን የጻድቁ አባታችን የአቡነ አረጋዊ ዕለትን። ጾመ ሐዋርያት(የሰኔ ጾም)የሚገባውም በዚሁ ዕለት ነው።

ኃይለኛ መንፈሳዊ ውጊያ ላይ ነን!!!

👉 “አለም (ዲያብሎስ) “ማየት ማመን ነው” ይለናል | እግዚአብሔር ደግሞ “ማመን ማየት ነው” ብሎ ያስተምረናል”

❖ “መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ።” [ኤፌሶን ፮፡፲፪]

👉 ታኅሣሥ ፳፬ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም – (ተክለሃይማኖት ነው) ሰበታ የሚገኘው የአቡነ አረጋዊ ቤተክርስቲያን በእሳት ቃጠሎ ሙሉ በሙሉ ወደመ።

👉 ጥር ፲፬ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም – ስለዚህ ቆሼ አስከፊ ቆሻሻ ሽታ እንዲሁም አካባቢው በመስጊድ ጩኽት ስለመበከሉ፤ ብሎም ዲያብሎስ እንደዚህን በመሳሰሉት መሰናክሎች በኩል ምዕመናኑን እየተዋጋ ከቤተክርስቲያን በማራቅ ከክርስቶስ ለመለየት እነደሚሞከር አወሳን።

👉 መጋቢት ፪ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም – በተለምዶ ቆሼ ሚባለው ስፍራ የተከሰተው አሳዛኝና አስደንጋጭ ዜና በመላው ዓለም መነጋገሪያ ለመሆን በቃ።

👉 በሰበታ አቡነ አረጋዊ ቤተ ክርስቲያን በእሳት ቃጠሎ ሙሉ በሙሉ ስትወድም ጽላቶቹ ግን በተአምር አንዳችም ጉዳት ሳይደርስባቸው ተገኝተዋል

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይግቡ፦ (ቪዲዮዎቹን ሌላ ጊዜ እንደገና አቀርባቸዋለሁ)

👉 “የአማሌቃዉያን ጂሃድ በአርሲ| መሀመዳውያን በነጌሌ ከተማ የሚገኘውን መስቀል ማየት የለብንም ብለው አነሱት”

“ጂሃድ በአርሲ | መጀመሪያ መስቀሉን አነሱ ፥ ዝም ተባሉ ፥ አሁን የመሰቀሉን ልጆች እያረዱ ነው”

አርሲ ነገሌ ቡሄ ፪ሺ፲፪ ዓ.ም

የተዋሕዶ ልጆች ዝምታ ብዙ መስዋዕት እያስከፈለ ነው!

በራዕይ የታየው ትግራዋይ ኢትዮጵያዊ | የአቡነ አረጋዊ ቤተ ክርስቲያንን በጽዮን ቀለማት ቀባው ክፍል ፩ ❖

👉 በክፍል ፩ ቪዲዮ የቀረበ ጽሑፍ፦

❖ አቡነ አረጋዊ ቤተ ክርስቲያን(አዲስ አበባ-ሳሪስ)

መስከረም ፪ሺ፯/2007 ዓ.ም(ያለ ጽዮን ማርያም ቀለማት) አቡነ አረጋዊ ቤተ ክርስቲያን (አዲስ አበባ-ሳሪስ)

❖ መስከረም ፪ሺ፲፩/2011 ዓ.ም (ከጽዮን ማርያም ቀለማት ጋር)

አንድ ባካባቢው የሚኖርና እንጀራ በመሸጥ የሚተዳደር ትግራዋይ ወጣት የቤተ ክርስቲያኗን ጣራ በአረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀይ ቀለማት እንዲያስቀባ በታየው ራዕይ በመታዘዙ በራሱ ወጭ እንዲህ አሳምሮ አስቀብቶታል። (ድንቅ ነው!)

👉 በትናንትናው የአቡነ አረጋዊ ዕለት፤ የነነዌ ጾም በሚገባበት ወቅት፤ የአህዛብ የጥፋት (ሰ)አራዊት በትግራይ ላይ የመጨረሻ የሚሆነውን ጭፍጨፋውን ማጧጧፉና ወደ ተከዜ ግድብ ማምራቱም በደንብ ታስቦበት ነው።

በአቡነ ተክለ ሐይማኖት ዕለት በትግራይ ላይ የክርስቶስ ተቃዋሚዎቹ የኢትዮጵያ ጠላቶች የጀመሩት ስጋዊ ጥቃት ለምን አክሱም ጽዮንን፣ ደብረ አባይን እና ደብረ ዳሞ ገዳማትን አስቀድመው ማጥቃት እንዳስፈለጋቸው ሁላችንም እያየነው ነው። ይህ ከዚህ በፊት በሺህ አራት መቶ ዓመታት ውስጥ ያልታየ ክስተት እንደሆነ ልብ እንበለው።

ዘንድሮ በትግራይ ላይ የተከፈተው ጥቃት ከመቶ ሰላሳ ዓመታት በፊት ኤዶማውያኑ አውሮፓውያንና እስማኤላውያኑ አረቦች በአፄ ምኒሊክ በኩል የጀመሩትን ጥቃት አጠናክሮ የቀጠለ ነው። በተለይ ኤርትራ እና ጂቡቲ በክርስቶስ ተቃዋሚው ኃይል ቁጥጥር ውስጥ እንዲገቡ ሲደረጉ ልክ ዛሬ አህዛብ መናፍቃኑ ግራኝ አብዮት አህመድ እና ኢሳያስ አፈቆርኪ ተግተው በስኬት እየሠሩት እንዳሉት ፥ ዋናው ዓላማቸው፤

፩ኛ. ኢትዮጵያዊነትን

፪ኛ. አክሱም ጽዮንን(ጽላተ ሙሴን)

፫ኛ. አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ሰንደቁን

፬ኛ. ተዋሕዶ ክርስትናን

❖ የኢትዮጵያና ተዋሕዶ ክርስትና የጀርባ አጥንት ከሆኑት ከትግራውያን መንጠቅ ነው።

👉 በዚህም ተጠቃሚዎቹ፤

፩ኛ. ኢትዮጵያ/እስራኤል ዘ-ስጋ

፪ኛ. አህዛብ የዋቄዮ-አላህ ልጆች

፫ኛ. መናፍቃን

፬ኛ. ኢ-አማንያን

፭ኛ. ሰዶምና ገሞራ(ግብረ-ሰዶማውያን)

👉 ሁሉም ኢ-አማንያን 666 የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ናቸው።

ጽላተ ሙሴን የአክሱም ጽዮን ልጆች ውስጥ እንደተቀበረ አድርገን እንውሰደው። ምዕራባውያኑ የቴክኖሎጂው ባለቤቶች የጽላቱን ‘ጨረር’ እያንዳንዱ ያልተበከለ የአክሱም ጽዮን ልጅ ውስጥ እንዳለ የመለካት/የማየት ችሎታው/አጋጣሚው አላቸው። ይህንንም ጨረር ከግለሰቦቹ ፈልቅቀው ለማውጣት (ጽላተ ሙሴን ለመስረቅ) እንደማይቻላቸው አይተዋል። ስለዚህ ልክ የአውሬውን 666 ምልክት በፈቃዱ ግንባሩና እጁ ላይ ለማስቀበር እንደሚሻው የወደቀ ሰው እያንዳንዱ የጽላተ ሙሴ ‘ተሸካሚ’ የአክሱም ጽዮን ልጅም ኢትዮጵያዊ መልኩን፣ ተዋሕዶ እምነቱንና ሰንደቁን በፈቃዱ እንዲያስረክብ የተለያዩ ፈተናዎችን እያቀረቡለት ነው። ዛሬ በትግራይ ላይ የተከፈተው ጦርነት ከመቶ ሰላሳ ዓመታት በፊትም በትግራይ ላይ የተከፈተው ጦርነት(አደዋ)ቀጣይ ደረጃ ነው። ያኔ አባቶቻችን እና እናቶቻችን ኢትዮጵያዊነታቸውን፣ ተዋሕዶ እምነታቸውንና ጽዮን ማርያም እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ያስዋቡትን ሰንደቃቸውን ለጥያቄ እንኳን አቅርበዋቸው አልነበረም፤ በዚህም እስካፍንጫው የታጠቀውን ወራሪ የዔዶማውያን ኃይል ድል ሊያደርጉት ተችሏቸው ነበር።

ይህ ትውልድም እራሳቸውን ለአውሬው አሳልፈው በሸጡ ደካሞች ተንኮል ሳይታለልና ሳይሸነፍ “እምብዬው ማንነቴንና ምንነቴን አሳልፌ አልሰጥም!” ማለት አለበት። አልያ ከኢርትራውያን የከፋ ዕጣ ፈንታ ነው የሚደርሰው።

ከአድዋው ድል በኋላ የስጋ ማንነትና ምንነት ያላቸው ደቡባውያን(ጋላማሮች)ኢትዮጵያን መረከብ እንደጀመሩ የአደዋውን ድል የመንፈስ ማንነትና ምንነት ያላቸው የአክሱም ጽዮን ልጆች እንዳስገኙት በመገንዘባቸውና እነርሱንም/ይህንም ለመዋጋት በክህደት ወደ አህዛብ እውቀትና ጥበብ በመዞር በተለይ ኤዶማውያኑን አውሮፓውያኑን በጣም ማስጠጋት ጀመሩ። በመጀመሪያ ያኔም አፄ ምንሊክ ኤርትራንና ጂቡቲን ለአውሮፓውያኑ አሳልፈው በመስጠት የሞትና ባርነቱን መንፈስ ወደ አክሱም ጽዮን ለማምጣት ከኤዶማውያኑ ጋር አስቀድመው ተፈራረሙ፤ በስምምነቱም ጦርነቱ በደቡብ ኢትዮጵያ ሳይሆን ልክ እንደ ዛሬው በአክሱም/አደዋ እንዲካሄድና የአክሱም ጽዮን ልጆች ጦርነቱን ተከትሎ በሚመጣው ጥፋትና ውድመት ለዘመናት ተቸግረውና ተጎሳቁለው እንዲኖሩ ተደረጉ።

ከአርባ ዓመታት በኋላም ፋሺስቱ ሙሶሊኒ በተመሳሳይ መልክ ወደ አክሱም ጽዮን ተመልሶ ተምቤንና አካባቢዋን በኬሚካል ቦምብ ጨፈጨፋቸው።

ዛሬም ፋሺስቶቹ ግራኝ አብዮት አህመድና ኢሳያስ አፈቆርኪ የኤዶማውያኑን ተልዕኮ ለማስፈጸም በደቡብ ኢትዮጵያ ሳይሆን አሁንም በአክሱም ጽዮን ላይ ጭፍጨፋውን ተያይዞታል። አረመኔው ግራኝ አብዮት አህመድ በትግራይ ሕዝብ ላይ በጣም አደገኛ ኬሚካሎችንና ራዲዮ አክቲቭ ዝናቦችን በኤሚራቶች ድሮኖች አውርዶባቸዋል፤ ኤሚራቶች ከአሰብ ተጣድፈው የወጡት ለዚህ ነው! ገለልተኛ መርማሪዎችንም የማያስገባው ይህ እጅግ በጣም አስከፊ ወንጀል ስላስደነገጠው ነው። በእኔ በኩል ገና ከዓመት በፊት ግራኝ የኑክሌር ወይንም የኬሚካል መሳሪያዎችን ካገኘ ሰሜን ኢትዮጵያን ላይ እንደሚጠቀምባቸው በደንብ ታይቶኝ ነበር። ይህ አውሬ እጅግ በጣም አረመኔ እንደሆነ ገና ለመጀመሪያ ጊዜ እንዳየሁት ነበር የተገለጸለኝ።

_______________________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ትክክለኛ ውሳኔ | ቅዱስ ሲኖዶስ ቤተ ክርስቲያን እንዲከፈት ወሰነ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 13, 2020

👉  በዕለተ ረከበ ካህናት እና አቡዬ

______________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , | Leave a Comment »

ቤተ ክርስቲያን ሆይ መከራሽ መብዛቱ፤ ከአንቺው አብራክ ወጥተው ጎራዴ አነገቱ፤ ተባብረው ሊወጉሽ ባንቺ ላይ ዘመቱ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 15, 2019

+_________________________+

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

አቡነ አረጋዊ | እንጀራ ሻጩ ወጣት ቤተክርስቲያኗን በአረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ እንዲቀባ በራዕይ ታዘዘ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 24, 2018

ትዕዛዙንም በሥራ ላይ አዋለው። ይህችን ውብ ቤተክርስቲያን በቀለሞቻችን እንዲቀባት ራዕይ የታየው ወንድማችን እንጀራ ጋግሮ በመሸጥ የሚተዳደር ወጣት ነው። ቤተክርስቲያኗን እና አካባቢዋን ከቀባ በኋላ በዚሁ በሳሪስ አቦ ኮረብታ ላይ በ አዲስ መልክ ለሚሰራው ለ አቡነ አረጋዊ ቤተከርስቲያን ህንፃ የግንብ አጥር በመገንባት ላይ ይገኛል።

በእውነት የእግዚአብሔር ሥራ ድንቅ ነው!

____________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , | Leave a Comment »

አዲስ አበባ / Addis – ሳሪስ አቦ / Saris Abo

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 13, 2013

ሳሪስ አቦ – የምዕራፈ ቅዱሳን ፈለገ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ እና አቡነ አረጋዊ ቤ/ክርስቲያን

ቀኑ መጋቢት 5 ዕለቱ ቅዳሜ ለእሁድ አጥቢያ ሰዓቱ ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ሆኗል፤ አሁንም ህማሙን እየታገለ እያላበው በድካም ለፍጥረቱ ሁሉ ይለምናል፤ “አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህን ኢትዮጰያንም ባርክ” ይላል። ህመም የጀመረው መጋቢት 3 ዓርብ ቀን ነው፤መታመሙን የሰሙ እንደርሱ ቅዱሳን የሆኑት ዘርአ ቡሩክ፤ ፍሬ ቅዱስ፤ያዕቆብ፤ብንያምና ዮሴፍ እንዲሁም በወቅቱ የኢትዮጰያ ንጉስ የነበረው እንድርያስ ሊጠይቁት ተሰብስበዋል ወደ አጠገቡ መድረስ ግን አልተቻላቸውም አባታችን ገብረመንፈስ ቅዱስ የሚጋርደው እንጨት ዛፍ በሌለበት በርሃ እንደ አንበሳ ተኝቶ አዩት በላዩ ያረፈው የእግዚአብሔር ጸጋ ከፊቱ የሚወጣው ብርሃን ቀይ መልኩ ረዥም የራስ ጠጉሩ እንደ ነጭ ሐር የሚሆን ጽሕሙ አስደነቃቸው።

ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት ሲሆን ከሰማይ ታላቅ ነጎድጓድ ድምጽ ተሰማ ጌታችን መላአክትን አስከትሎ ወደ አባታችን ወረደ፤ ከሰማይ ወደ ምድር ህብሩ አምሳያው ልዩ ልዩ የሆነ እንደ ጸሐይና እንደ ጨረቃ የሚያበራ እንደ ወንጪፍ ድንጋይ ይወረወር ነበር ከዚያ የነበሩ ሁሉ ፈሩ ወደ ኃላም ሸሹ ምድር ራደች ተራሮች ኮረብቶች ተናወጡ ብርቱ ጩኸት ንውጽውጽታ ሆነ።

ወዳጄ ገብረመንፈስ ቅዱስ ሰላም ላንተ ይሁን” እነሆ የማይታበል ቃል ኪዳን እገባልኃለው ስምህን የጠራ መታሰቢያህን ያደረገውን፤ እጣን ቋጥሮ ግብር ሰፍሮ መባ ይዞ ቤትህ የመጣውን እምርልኃለው አንተ ከገባህበት ገነት መንግስተ ሰማያት አገባዋለሁ አለው፤ አባታችንም “አቤቱ ጌታ ሆይ የኢትዮጰያን ህዝብ ማርልኝ” አለው፤ እነሆ ምሬልኃለው አስራት በኩራት አድርጌም ሰጥቼሃለው፤ ከመጋቢት አምስት ቀን ጀምሮ ዝክርህን ያድርጉ በአማላጅነትህም ይማጸኑ አለው።

ከዚህ በኃላ ሰባቱ ሊቃነ መላክት የአባታችንን ነፍስ ሊቀበሉ ወረዱ በታላቅ ምስጋናም ወደ ሰማይ አሳረጉት ስጋውንም ይዘውት ሄዱ የት እንደተቀበረ ግን እስካሁን አይታወቅም አንዳንዱ በእየሩሳሌም ነው ይላሉ፤ ሌላው በምድረ ከብድ ነው ይላል ግን እስካሁን ልክ እንደ ሊቀ ነብያት ሙሴ ስጋ የት እንደተቀበረ አይታወቅም።

ገድሉ ትሩፋቱ ከሰማይ ከዋክብት ከምድር አሸዋ ይበዛል ኢትዮጰያን አብዝቶ ይወዳታል፤ ምድራዊ ምግብ አልተመገበም የእናቱን ጡት እንኳን አልጠባም፤ ልብስ፤ መጠለያ አልፈለገም፤ የክረምት ቁር የበጋ ሐሩር እየተፈራረቀበት በተጋድሎ 562 ዓመት ኖረ፤ በዛሬዋ ቀን ሩጫውን ጨረሰ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም ከአባታችን በረከት ያሳትፈን።

ቢዲዮው ላይ በሚታየው የአዲስ አበባ ሳሪስ አቦ ቤተክርስቲያን ከዕለታት በአንዱ ቀን ጻደቁ አባታችን አቡነ መንፈስ ቅዱስ ወደ ዝቋላ ሲጓዙ ለጥቂት ቀናት ቦታው ላይ አርፈውበት እንደነበር ይነገራል። ከቤተክርስቲያኗ ወረድ ብሎ ሸለቋማ ቦታ ላይ በጣም የምትማርክ አነስተኛ ቤተክርስቲያን በ አቡነ አረጋዊ ስም እየተጠራች መንፍሳዊ ግልጋሎትን ትሰጣለች።

_

Posted in Ethiopia, Ethnicity, Genetics & Anthropology | Tagged: , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: