Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

 • June 2021
  M T W T F S S
   123456
  78910111213
  14151617181920
  21222324252627
  282930  
 • Archives

 • Categories

 • Recent Posts

Posts Tagged ‘ሲ.አይ.ኤ.’

ፕሮፊሰር ሀይሌ ስለ አሜሪካ ተንኮል | ኢትዮጵያ ጠንካራ አገር እንዳትሆን መንግስቷ ከጦርነት እንዳይላቀቅ ማድረግ አለብን

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 27, 2019

አንድ ኢትዮጵያዊ እንዲህ ነው መሆን የሚገባው፤ ረጅም እድሜ ይስጥዎት፡ ጋሽ ሀይሌ ላሬቦ፤ እንወድዎታለን!

በተለይ ተቃራኒ ወገኖች መስለው በዓለም የፖለቲካ መድረክ ላይ ዋና ተዋንያን የሆኑት ምዕራባውያን እና ምስራቃውያን እርስ በእርሳቸው ጠላቶች በመምሰልና የተለያዩ ርዕዮተ ዓለማትን በመከተል ለአንድ ዓላማ በመነሳሳት ፀረክርስቶስ የሆነውን ተግባራቸውን በማካሄድ ላይ ናቸው። በተለይ በጠላትነት የሚዋጓቸው አገራት የኦርቶዶክስ ክርስትና ተከታዮች የሆኑትን አገራትን፤ በዋናነት ደግሞ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ የኦርቶዶክስ ክርስቲያኖችን መናኸሪያዎች ነው። ኦሮቶዶክስ በሆኑት በግሪክ፣ ቆጵሮስ፣ ጆርጅያ፣ አርሜኒያ፣ ዩክሬይን፣ ሰርቢያ፣ ሩሲያ፣ ግብጽና ሶሪያ ላይ ላለፉት ሺህ ዓመታት ሲፈጽሙት የነበረው ተንኮልና ግፍ በታሪክ መጻሕፍት በደንብ የተመዘገበና ዛሬም የምናየው ነው።

በነገራችን ላይ፤ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ወዳጅና እህታማ ኦርቶዶክስ አገሯ አርሜኒያ ከኢትዮጵያ ጋር እስከ አሁን ድረስ የዲፕሎማቲክ ግኑኝነት አልነበራትም። ግን በቅርቡ ኢምባሲ እንደምትከፍት ዛሬ የወጣው መግለጫ ይጠቁማል።

We are opening this new direction by way of establishing close cooperation with Ethiopia, our historical friend in Africa,” the minister added. “It’s planned to open our diplomatic mission in [the Ethiopian capital city of] Addis Ababa, as early as this year.”

ኢትዮጵያና አርሜኒያ ጠላት የሆነችው የክርስቶስ ተቃዋሚዋ ቱርክ ሳተላይት ሃገር አዜርቤጃን ግን አዲስ አበባ ላይ ኤምባሲ ከከፈተች ቆየታለች። እንዲያው ይገርማል!

ከፀሐይ በታች ምንም አዲስ ነገር የለም ፥ በዓለም ላይ በጣም ጥንታዊ የሆነውን የኢትዮጵያ ክርስቲያን ህዝብ ለመቆጣጠር ፣ ለማዳከም እና በመጨረሻም ለማጥፋት ሉሲፈራውያኑ ምዕራባዊያን ፣ ሶቪዬቶች እና ሙስሊም አረቦች ፀረክርስቲያናዊ ርዕዮተ ዓለማትን በወጣቱ ሕዝባችን ዘንድ በማስፋፋት(ሊበራሊዝም፣ ዲሞክራሲ፣ ኮሚኒዝም እና እስልምና)፣ የአየር ሁኔታን የሚቀይሩ ጦርነቶችን በማካሄድ(ድርቅ እና ረሀብ)፣ በሽታዎችን በማሰራጨት(ኤድስ እና ኮሌራ)እንዲሁም ብዙ ደም የሚፈስባቸውን ጦርነቶች በመቀስቀስ(ለኤርትራ ፣ ለሶማሊያ) 50 ዓመታት ያህል(1966 .ም– እስከ ዛሬ ድረስ)በግልጽ ተግተው ሲን፡ቀሳቀሱ በግልጽ ይታያሉ። ልብ በል፤ “66፥ “50ኢዮቤልዩ።

ልክ እንደ እነ ዶ/ር ሀይሌ ላሬቦ ወደ ማንንታችን በመመለስ ይህን የዔሳውያን እና እስማኤላውያን ዲያብሎሳዊ ተልዕኮ አንድ ላይ ሆነን በተደጋጋሚ ካላጋለጥን የሕዝባችን ስቃይ እና ቁልቁል ጉዞ መቀጠሉ አይቀረም። ዶክተሮች ብቅ ብቅ ባሉበት በዚህ ዘመን የህመማችንን መንስኤ የሚነግረን ዶክተር እንጅ መርዛማውን መርፌ የሚወጋን ወይም የሉሲፈራውያኑን “መድኀኒት” እንድንገዛ ሪሴፕት የሚጽፍልንን ወስላታ ዶክተር አይደለም የምንፈልገው።

ቪዲዮው ላይ በተጨማሪ እንዳቀረብኩት፤ የቀድሞው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር የዘጠና ስድስት ዓመቱ ሰይጣን ሄንሪ ኪሲንጀርና አጋሮቹ አፄ ኃይለ ሥላሴን በማታላል ከተዋሕዶ እምነታቸው እንዲርቁና ሆራ/ደብረዘይት ላይ ለዋቄዮአላህ መስዋዕት እንዲያደርጉ፣ ቀጥሎም ኢትዮጵያ ከእስራኤል ጋር የነበራትን የዲፖሎማቲክ ግኑኝነትን በማቋረጥ ልክ እንደ አሁኑ ከከንቱዎቹ አረቦች ጋር እንድትቀራረብ በማድረግ የገበጣ ጨዋታውን ጀመሩት። ብዙም አልቆየም፤ ኢትዮጵያን ለማናጋትና በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ድርቅና ረሃብ ለመፍጠር አየሩን ቀያየሩት (Weather Manipulation/ Weather warfare)። በጊዜው ኤርትራ ውስጥ ተቀማጭነት የነበረው የአሜሪካ ሠራዊት(ቃኘው ስቴሽን) አንዱ ተልዕኮ ይህ ነበር። ከስድስት ዓመታት በፊት ይህን አስመልክቶ ጦማሬ ላይ ቀርቦ ነበር። “አየሩን ሊቀይሩብን – አለመረጋጋት ሊፈጥሩብን?

ይህን ከሃምሳ ዓመታት በፊት  በኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ የቀረበውን ጽሑፍ(እንደ አጋጣሚ ሆኖ፡ ልክ በዛሬው ዕለት(ዋው!)እናንብብ፦ “ኢትዮጵያውያን በታላቁ የአሜሪካ ሬዲዮ ጦር ሠፈር ላይ ተጠርጣሪዎች ናቸው፡፡Ethiopians Are Suspicious of Big U. S. Radio Base. https://www.nytimes.com/1970/08/28/archives/ethiopians-are-suspicious-of-big-us-radio-base.html

ዛሬ ግን ኤምባሲዎቹ ናቸው መሬት ውስጥ የተቀበሩ ብዙ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ሃገራችንን በመቃኘት ላይ ያሉት።

ለአምስት ሺህ ዓመታት ያህል ሰፍኖ የነበረውን ጥንታዊ የንጉሣዊ ሥርዓት ሲያስወግዱ የብዙ መቶ ዓመታት ቅደም ተከተል በያዘ የውጊያ ስልት ነው። እስኪ እናስብው፤ በድርቁ፣ ረሃቡ፣ ጦርነቱና በሽታው ሲተናኮሉን ኃያል ሊሆን የሚገባውን ተዋሕዶ ክርስቲያኑን ሕዝብ ለማድከም/ለማዳከም በመሻት ነው። ወገኔ፡ እስከ ዛሬ ድረስ የረሃብ፣ በሽታ፣ ጦርነትና ስደት ሰለባ የሆነው እኮ ሕዝበ ክርስቲያኑ ነው፤ አዎ አሁንም ለውድ ሃገሩ ክቡር ደሙን እያፈሰሰ ያለው ሕዝበ ክርስቲያኑ ብቻ ነው።

እነ ሲ አይ ኤ፣ ሄንሪ ኪሲንጀር እና ጆርጅ ሶሮስ ልክ እንደ አሁኑ ተዋሕዶ ክርስቲያን ያልሆኑትን እንደ መንግስቱ ኃይለማርያም የመሳሰሉትን ቅጥረኞቻቸውን ስልጣን ላይ ካስቀመጧቸው ጊዜ አንስቶ የሃገራችን የቁልቁለት ጉዞው ያው እስካሁን ድረስ ቀጥሏል።

በእግዚአብሔር ድጋፍ የጽዮን ተራራን እንደገና መውጣታችን አይቀርም፤ ነገር ግን የአቀበቱ ጉዞ አጭር እንዲሆንና ብዙም እንዳያደክመን ማንነታችንን በማወቅ ጠላታችንና ጠላቶቻችንን ያለምንም ይሉኝታ ማጋለጥ እና መምታት ይኖርብናል

_____________________

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

በተዋሕዶ ኢትዮጵያ ላይ ጦርነት ያካሂዱ ዘንድ በሉሲፈራውያኑ የተመረጡት ፲ የሲ አይ ኤ ወኪሎች

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 5, 2019

ቅጥረኞቹ የ ዶ/ር ማዕረግ የተሰጣቸው ኢአማንያን,ጴንጤዎች,ተሀድሶዎች እና ሙስሊሞች ናቸው። በአፋቸው፣ አፍንጫቸውና ዓይናቸው ዙሪያ የሚተነውን መንፈስ፡ በሦስተኛው የመንፈሳዊ ዓይናችን እንየው!

__________________

Posted in Conspiracies, Ethiopia | Tagged: , , , , , , , , , | Leave a Comment »

በሐረርጌ ከሰማይ እንደዘነበው ዓይነት እሳት በቬኔዙዌላም ታየ | በ ሲ.አይ.ኤ መፈንቅለ-መንግሥት ማግስት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 10, 2019

የቆቅ ለማዳ የለውም፤ እባብንም ቆዳው ለሰለሰ ብለህ ቀበቶ አርገህ አትታጠቀውም

የሉሲፈራውያኑ የስለላ ድርጅት፡ ሲ.አይ.ኤ ብጥብጥ በፈጠረባት ቬኔዙዌላ ከሰማይ እሳት ዘነበ (‘ሜቲዎሪትነው አሉ!) ግን ዘመናዊ የጠፈር ቴክኖሎጂ እየተሞከረ ይሆን? የእግዚአብሔር እሳት ከመውረዱ በፊት ሉሲፈራውያኑ ቀድመው ማውረዳቸው ይሆን?

ፍጻሜ ዘመን ላይ እንገኛለን፤ የሉሲፈር ሠራዊት ተደናግጧል፤ ጌዜው በጣም አጥሮበታል፤ እርኩስ ድርጊቱን በየአገሩ ለመፈጸም በመጣደፍ ላይ ይገኛል። አሁን ሰብዓዊ ወታደሮች ወይም ታንኮች እምብዛም አያስፈልጉትም፤ በጠፈር መሣሪዎች የታጀቡ ሙከራዎችን ማካሄድ የሚችልበት ዘመን ነውና።

አሁን ክርስቲያኖችን እና አፍሪቃውያንን ሙሉ በሙሉ ማጥፋት እንችላለን ብለው ያስባሉ/ይመኛሉ፤ አላማቸውም ይህ ነው፤ የዘገዩት እግዚአብሔር ስለከለከላቸው ነው። እርኩስ ሥራዎቻቸውን እንድንቀበል የእኛን ፈቃደኝነት ይሻሉ፤ ለዚህም እንደ እነ ዶ/ር አህመድ ያሉትን መሪዎች ስልጣን ላይ ያስቀምጣሉ፤ ከዚያም እሳቱን ባወረዱ ቁጥር፡ ለማይፈልጓቸው ፖለቲከኞች፡ “ዋ! ቴክኖሎጂው አለን፤ ከመላው ሕዝባችሁ ጋር ሙልጭ አድርገን እናጠፋችኋለን።” በማለት ያስፈራሯቸዋል። ለእኛ ለበጎቹ ደግሞ፡ “ኦ!! ከሰማይ የወረደ ሜቲዎሪት ነው” ይሉናል፤ ለእግዚአብሔር ደግሞ፡ “ያው በራሳቸው ፈቃድ ነው ይህን ያደረግነው” ይሉታል፤ “አመንዝራ የአፍሪቃ ትውልድ በሃጢአታቸው ነው በኤይድስ የተለከፉት…” እንደሚሉት። ከእነርሱ የባሰ ጣዖት አምላኪና አመንዛሪ እንደሌለ፤ ዲያብሎስ ስራው እንዲህ ነው።

በጂጂጋ ክርስቲያኖች ላይ የተካሄደው ጂሃዳዊ ጭፍጨፋ በሉሲፈራውያኑ በደንብ የተቀነባበረ ነበር። በማግስቱ የወረደው እሳትስ የእግዚአብሔር ቁጣ ወይስ ሉሲፈራውያኑ በኢትዮጵያ ላካሄዱት የመንግስትግልበጣ ሊያስጠንቀቁት ለፈለጉት ወገን የተላከ እሳት?

አዎ! በአሁኑ ዘመን ይህችን ምድር በመምራት ላይ ያለው ዲያብሎስ ነው። ስለዚህ በእያንዳንዱ አገር በመሪነት ቦታ ላይ መቀመጥ ያለባቸው የእርሱን ተልዕኮ ለማሟላት ፈቃደኞች የሆኑት ሰዎች ብቻ ናቸው። በኢትዮጵያ ያየነው ዓይነት መፈንቅለመንግስት ለቬኔዙዌላም ታስቧል፤ ልዩነቱ በኢትዮጵያ አገልግሎታቸውን የጨረሱት ፖለቲከኞች ወደውም ይሁን ተገድደው ከስልጣን ሲሰናበቱ፤ የቬኔዙዌላው ሌላ ወስላታ ማዱሮ ግን ፈቃደኛ አይደለም። ስለዚህ፡ እራሳቸው ያስቀመጡትን ይህን ሶሻሊስት አሁን ጠምደውታል፤ በሌላ አገር ጉዳይ የማዘዝ መብት እንዳላቸው፡ “ከስልጣን ውረድ፣ ጊዜህ አብቅቷል ይሉታል።!” በዚህም እንደ ሩሲያ፣ ቻይና፣ ኢራን እና ቱርክ የመሳሰሉ የድራማው ተካፋዮች በቁጥጥር ሥር እንዳሉ ተቃዋሚዎች ተቃራኒውን ሚና ለመጫዋት ይገደዳሉ። የወስላታው ፈላስፋ ጆርጅ ሄገል ዲያሌክቲክስ (Thesis + Antithesis = Synthesis)

በአገራችንም እየሠሩ ያሉት ሥራ ይህን ይመስላል፤ የራሳቸው የሆነውን ዶ/ር አብይን ስላጣን ላይ አወጡት፤ ከሩቅ የሚቆጣጠሩትን ተቃዋሚ ዶ/ር ደብረጽዮንን በተቃራኒው በኩል አስቀመጡት፤ ሁለቱ ሲፋጩ ለተፈለገው የሕዝብ ቁጥር ቅነሳ ጦርነት ይካሄዳል ሰው ያልቃል ማለት ነው። አቶ መለሰ ዜናዊ እና ኢሳያስ አፈወርቂ በባዳሜው ጦርነት ለአንድ ሚሊየን ተዋሕዶ ክርስቲያኖች ሕይወት መቀጠፍ መሣሪያ ለመሆን እንደበቁት።

ልብ ብለን ካየን፤ በየአገሩ 666ቱ አውሬ የሚመረጡት ሁሉ ከየት እንደመጡ የማይታወቁ፣ ልምድ የሌላቸው ወጣት ፖለቲከኞች ናቸው ልክ እንደ ፈረንሳዩ ፕሬዚደንት ማክሮን (በጊዜው 39)እና የቬኔዙዌላው ተቃዋሚ መሪ ሁዋን ጋይዶ(35ቱ ነው)፤ ዶ/ር አህመድም ከአመት በፊት በፍጹም የማይታወቅ ሰው ነበር። እነ መንግስቱ ኃይለማርያምም በጣም ተመሳሳይ የሆነ አመጣጥ ነበር የነበራቸው። በአንድ ነገር ግን እርግጠኞች መሆን አለብን፡ እርሱም፤ እነዚህ ቅጥረኞች ሁሉም በአንድ ወቅት በአሜሪካ የስለላ ድርጅት(CIA) ትምህርት ተቀብለዋል፤ ተመልመለዋል።

_________

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

አስደንጋጭ አዲስ መረጃ | የአሜሪካ እና የእንግሊዝ የስለላ ተቋማት በጥቁር አፍሪቃውያን ላይ “ኤድስ” አሰራጭተዋል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 29, 2019

የቀድሞው የተባብሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊን፤ የስዊድናዊውን ዲፕሎማት ሃመርስጆልድ አሟሟት አስመልክቶ አንድ በዴንማርካዊ ፊልም ሠሪ የተሠራ ጥናታዊ ፊልም በ “ሳንዳንስ ፊልም ፊስቲቫል” ላይ ባለፈው ቅዳሜ ቀርቧል።

በዚህ Cold Case Hammarskjold,’ በተሰኘው ፊልም፤ እ..አ በ 1961 .ም የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊን የገደሉት በእንግሊዝና አሜሪካ የስለላ ድርጅቶች የሚደገፉት ነጭ የደቡብ አፍሪቃ ቅጥረኞች እንደነበሩ ተጠቁሟል።

በዚህ አያበቃም፤ ከእነዚህ እርኩስ ቅጥረኞች ያፈነገጠው ግለሰብ አሁን በተጨማሪ እንደጠቆመው ከሆነ እነዚሁ የሲ.አይ.ኤና አባሮቹ ቅጥረኞች የደቡብ አፍሪቃን ጥቁር ሕዝቦች ለመጨረስ ኤች.አይ.ቪ ቫይረስ የሚያሰራጭ መርፌ ሆንብለው ይወጓቸው ነበር።

በእነዚህ ሉሲፈራውያን እየተሠራ ያለው ሥራ ለጆሮ የሚቀፍ ነው፤ ህሊና ላለው ተቀባይነት የማይኖረው ዲያብሎሳዊ ተግባር ነው። በአገራችንም እህቶቻችንን እና ሕፃናቶቻችንን በመከተብና በመመረዝ ላይ ናቸው።

እስኪ ይታየን፤ ሰው አገር ሄደው፣ እነርሱ አምላክ ሆነው በእግዚአብሔር አምሳያ የተፈጠርውን ፍጥረት ለማጥፋት ይህን ያህል ሲተጉ፤ ምን ዓየነት እርኩሶች ቢሆኑ ነው እነ ሲ.አይ.. ኤፍ..አይ እና ኤም.አይ.ፋይቭ????!!! ልክ እንደ መሀመዳውያኑ፡ ይህች ዓለም ለእነርሱ ብቻ ናት፤ ብቻቸውን ሊኖሩባት ይሻሉ።

የፍትሕ ጩኸት ጽዋ በእግዚአብሔር ፊት ሞልቶ ፈሷል፤ ሁሉን ነገር አንድ በአንድ በቪዲዮው የሚቀዳው የአብርሃም፣ ይስሃቅና፣ ያዕቆብ አምላክ ፈጥኖ ለውርደት ያብቃቸው። ይኽ ሰይጣናዊ እኩይነት፣ በእግዚአብሔር ላይ የታወጀ፣ ሆኖም ሊያሸንፉት የማይችሉት ጦርነት ነው። እግዚአብሔር አይቻለሁ ብሎ በፍርድ ተንስቷል!

[የዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ ፳፩፥፰]

ዳሩ ግን የሚፈሩና የማያምኑ የርኵሳንም የነፍሰ ገዳዮችም የሴሰኛዎችም የአስማተኛዎችም ጣዖትንም የሚያመልኩ የሐሰተኛዎችም ሁሉ ዕድላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ነው፤ ይኸውም ሁለተኛው ሞት ነው

[ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ ፲፥፩፤፪]

መበለቶችም ቅሚያቸው እንዲሆኑ፥ ድሀ አደጎችንም ብዝበዛቸው እንዲያደርጉ፥ የድሀውን ፍርድ ያጣምሙ ዘንድ፥ የችግረኛውንም ሕዝቤን ፍርድ ያጐድሉ ዘንድ የግፍን ትእዛዛት ለሚያዝዙ፥ ክፉንም ጽሕፈት ለሚጽፉ ወዮላቸው!


CIA-backed’ Mercenaries Spread HIV in S. Africa, ex-Member Claims


A Sundance documentary ostensibly about the 1961 plane crash which killed then UN Secretary-General, Dag Hammarskjold, contains explosive claims of a conspiracy to spread HIV among South Africa’s black population.

Directed by controversial Danish journalist, filmmaker, and provocateur Mads Brügger, ‘Cold Case Hammarskjold,’ debuted Saturday at the Sundance Film Festival.

It details an investigation into the largely unsolved death of Swedish diplomat and former UN Secretary-General Dag Hammarskjold, whose DC-6 plane crashed near Ndola, Northern Rhodesia (modern Zambia). Initial investigations identified the cause as pilot error or mere mechanical fault, though doubts have persisted in the 50+ years since the crash.

Throughout the course of the new documentary, Brügger and his team investigate a white militia, the South African Institute for Maritime Research (SAIMR). According to documents the filmmakers uncovered, the group operated with support from the CIA and British Intelligence and orchestrated the 1961 plane crash which killed Hammarskjold. The documentarians eventually encounter and interview a man named Alexander Jones who is allegedly a former member of the group.

Jones, who is not related to Alex Jones of InfoWars, claims the mercenary group used phony vaccinations to spread HIV with a view to wiping out the black population of South Africa, in addition to carrying out the Hammarskjold assassination.

We were at war,” Jones says, as cited by The New York Times. “Black people in South Africa were the enemy.”

However, medical experts have already dismissed Jones’ claims as medically dubious and unscientific in the extreme.

The probability that they were able to do this is close to zero,” said Dr. Salim S Abdool Karim, the director of Caprisa, an AIDS research center in South Africa, citing the immense resources that would be required to conduct such a far-fetched attempt at genocide.

Notwithstanding the technological limitations of the 1990s, including facilities to rival that of the Centers for disease control and prevention in the US in addition to millions of dollars in funding, HIV is extraordinarily difficult to isolate, transport and grow in a laboratory environment, let alone distribute en masse in a clandestine operation, Dr Abdool explains.

However, Jones claims he visited a research facility in the 1990s that was used for “for sinister experimentation” and that he was certain its intent was“to eradicate black people.”

Many have criticized the filmmakers for helping to sow distrust of the medical establishment in a country that already has one of the highest HIV infection rates in the world while reviving dangerous conspiracy theories that have persisted since the Cold War.

The filmmaker, who has previously been described as a ‘fabulist’ and ‘provocateur’, according to the Hollywood Reporter, admits he has been unable to corroborate Jones’ ever-evolving story; As the documentary makers continued to question Jones, his accounts became more and more dubious as he professed firsthand knowledge of people that had seemingly been brought to his attention by the documentarians themselves.

ምንጭ

_________

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith, Infos, Media & Journalism | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: