Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘ሰዶም እና ገሞራ’

በእነ አቶ ልደቱ ላይ እየተሠራ ያለው ድራማ፡ ግራኝ ፍርድ ቤቶችን እንደ ናይጄሪያ ለሰዶማውያን አጀንዳ እያዘጋጃቸው ስለሆነ ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 28, 2020

ሉሲፈራውያኑ በአፍሪቃውያን ላይ በተለይ በኢትዮጵያውያን ላይ ጦርነቱን ከሁሉም አቅጣጫ ነው እያካሄዱ ያሉት።

ባለፉት ቀና ቢሾፍቱ የተባለው ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ በአስቸኳይ አቶ ልደቱን እንዲፈታ፤ ካለበለዚያ ግን ችሎቱ እርምጃ እንደሚወስድ የምሥራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ማዘዙን ከዚህ ዜና ጋር አዛምደን እንየው፦

👉 ለግብረሰዶማውያን ድጋፍ የሰጠው የናይጄሪያ ፍርድ ቤት

👉 አህዛብ እና መናፍቃን የግብረሰዶማዊነት አጀንዳ አራማጆች እንደሆኑ

👉 ግራኝ አብዮት አህመድ በግብረሰዶማውያኑ ተመርጦ ስልጣኑን እንደያዘ

👉 ግራኝ አብዮት አህመድ “ፍርድ ቤቶችን” የሰዶማውያን አጀንዳ ማስፈጸሚያዎች እንዲሆኑ እያዘጋጃቸውና ሕዝቡንም እያለማመደው መሆኑን

👉 የግራኝ አብዮት አህመድ ደጋፊዎች አህዛብ + መናፍቃን እንደሆኑ

አንድ የናይጄሪያ ፍ / ቤት ማክሰኞ ተመሳሳይ ፆታ ካላቸው ወንዶች ጋር በአደባባይ “በአጸያፊ ፍቅር” የተከሰሱ ፵፯/47 ወንዶች ላይ አንስቶ የነበረውን ክስ ጣለ። በዚህም ውሳኔ የግብረ-ሰዶማዊነት ግንኙነቶችን የሚከለክሉት የሀገሪቱ ህጎች ፈተና ላይ ወድቀዋል።

በንግድ ዋና ከተማ ሌጎስ ውስጥ የተሰማው የፍርድ ሂደት እ.ኤ.አ. በ 2014 ዓ.ም ተመሳሳይ ጾታ “የፍቅር ግንኙነቶች” ን ለሚያግደው ሕግ እንደ ሙከራ ጉዳይ እንደሆነ በስፋት ታይቷል።

የ ፲፬/14 ዓመት እስራት የሚያስቀጣ እና የተመሳሳይ ፆታ “አጸያፊ ግንኙነቶች” የሚፈጸሙ የግብረ ሰዶማውያን ጋብቻን የሚከለክለው የናይጄሪያ ሕግ እ.ኤ.አ. በ 2014 ዓ.ም በቀድሞው የናይጄሪያ ክርስቲያን ፕሬዝዳንት ጉድላክ ጆናታን ስልጣን ላይ ሲውል ዓለም አቀፍ ተቃውሞ አስነስቶ ነበር።

ዛሬ በናይጄሪያ ስልጣኑን የያዙት መሀመዳውያኑ የዓለም ዓቀፉ ግብረሰዶማውያን አጀንዳ አስፈጻሚዎች ናቸው።

ወገኖቼ፤ ይህ ጉዳይ ቀላል ጉዳይ አይደለም፤ በጣም ብዙ መዘዝ ያለው ጉዳይ ነው። በአፍሪቃና አፍሪቃውያን ላይ የተጠነሰሰ አንድ ትልቅ ሴራ አለ። በሃገራችንም እነ ግራኝ አብዮት አህመድን ስልጣን ላይ ያስቀመጧቸው ይህን ዲያብሎሳዊ አጀንዳ ያስፈጽሙላቸው ዘንድ ነው። በዚህ 100% እርግጠኛ ነኝ! ግራኝ አብዮት አህመድ አንድም ቀን ስለ ግብረ-ሰዶማዊነት እና ግብረ-ሰዶማውያን ተንፍሾ አያውቅም። አምና ላይ ግብረሰዶማዊው የአሜሪካ የጉዞ ወኪል “ቶቶ ቶርስ” ወደ ላሊበላ ለመጓዝ እንዲያስብን ዓለምን እንዲያነጋግር የተደረገው በግራኝ አብዮት አህመድ ተባባሪነት ነው፤ ስለጉዳዩ ትንፍሽ ያላለውም ለዚህ ነው፤ ኢትዮጵያውያኑን ቀስበቀስ ግብረ-ሰዶማዊነትን ሊያለማምዳቸው ፈቅዷልና።

ባለፈው ዓመት ልክ በዚህ ጊዜ (ሐምሌ ፪ሺ፲፩ ዓ.) ላይ “የተጠለፈ ትግል/ The Hijacked Revolution)የተባለና ብዙ ድብቅ መረጃዎችን የያዘ መጽሐፍ ለገበያ ውሎ ነበር። መጽሐፉን የግራኝ ዐቢይ አህመድ አገዛዝ ከገበያ እንዲነሳና የታተሙት ቅጅዎች ሁሉ ተለቃቅመው እንዲቃጠሉ አድርጓል። በዚህ መጽሐፍ ገጽ ፳/20 ላይ የሚከተለውን መረጃ እናገኛለን፦

ጠቅላይ ሚኔስቴሩ ለጉብኝት ወደ ፈረንሳይ አገር ባመሩበት ጊዜ አንድ የግብረሰዶማውያን ማህበር አባላቶቹ ኢትዮጵያን መጎብኘት እንደሚፈልጉ ገልፆውላቸው እርሳቸውም ፈቅዶላቸው ነበር። ይህን ሚስጥር የሚያውቀው የጠቅላይ ሚኔስቴሩ የቅርብ ወዳጅና አማካሪ የሆነው ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ብቻ ነበር። እርሱም ይህንን ሚስጥር አሳልፎ ለኦርቶዶክስ ሃይማኖት ማህበራት በመስጠቱ ማህበራቱ የግብረሰዶማዊያንን ጉዞ በመቃወም ሊያስቀሯቸው ችለዋል።”

ይህ ክስተት ብዙዎቹን ዛሬም ሊገርማቸው ይችላል። ነገር ግን ሰውዬው በግብረሰዶማውያን የዓለማችን ፈላጭ ቆራጮች የሥልጣኑ ዙፋን ላይ የተቀመጠ መሰሪ ሃገር አጥፊ ነው። አወቁትም አላወቁትም፣ ፈለጉትም አልፈለጉትም ደጋፊዎቹና ወኪሎቹ ነፍሳቸውን ቁራጭ በቁራጭ እየቆረሱ የሚሸጡ አህዛብግብረሰዶማውያን ናቸው። ገዳይ ዐቢይ አህመድ ዳንኤል ክብረትን ልክ እንደ ሌሎች ብዙዎች“እኔ የምልህን ካላደረግክ እገድልሃለው!” በማለት የእርሱ አጎብዳጅ ሊያደርገውና ጠፍሮ ሊያሰረውም እንደሚችል የሰውዬው ባሕርይ በደንብ ይናገራል። ለዚህም ይመስላል ዳንኤል ክብረት፣ ዘመድኩን በቀለ እና አጋሮቻቸው ግራኝ ዐቢይ አህመድን በማጋለጥ ላይ ያሉትን ድሕረገጾችና ዩቲውብ ቻነሎች በማዘጋቱና በማፈኑ ሥራ ላይ የተሰማሩት። የቀድሞውን የእኔን ዩቲውብ ቻነል ጨምሮ ማለት ነው። ይህ ትልቅ ቅሌት ስለሆነ መታወቅ አለበት! ገና ብዙ የሚያሳፍርና የሚያስደነግጥ ነገር ይወጣል!

ግራኝ አብዮት አህመድ ልክ እንደ ኢምኑኤል ማክሮን ተመሳሳይ ጽንፈኛ ተግባር በሃገራችን በመፈጸም ላይ ነው፤ በደንብ እስኪደላደል ድረስ ለሙቀት መለኪያና ሕዝቡንም ማለማመጃ ይሆነው ዘንድ ሰሞኑን በአቶ ልደቱ አያሌው ጉዳይ ላይ ሆን ብሎ “ፍርድ ቤቱ ነፃ አውጥቶታል፤ ፖሊስ ግን ለመልቀቅ ፈቃደኛ አይደለም! ቅብርጥሴ” የሚለውን ድራማ በመስራት ላይ ያለው። ፍርድ ቤት ተብዪዎቹን እንደ ናይጄሪያ ለግብረሰዶም አጀንዳ እያዘጋጃቸው ነው።

👉 የሚከተለውን ጽሑፍ አምና ላይ አቅርቤው ነበር

አይለቁንም! | አገራችንን ግብረ-ሰዶማውያን እንደሚመሯት ይህ ሌላ ማስረጃ ነው

ግብረ-ሰዶማዊቷም “አዲስ አበባ ኬኛ” አለች። እንዴት ደፈረች? ለምን አሁን? ማን ይህን ያህል አደፋፈራት ብለን ብንጠይቅ፤ መልሱ፦ ኦሮሞ ቄሮዎችን፣ ጴንጤዎችንና ሙስሊሞችን ሁሉንም ያስደፋፈራቸው ዲያብሎሳዊ ዕቅድ ያለው የግራኝ ዐቢይ አህመድ መንግስት። የሚለው መልስ ነው። መንግስቱ(ካቢኔው) በጴንጤዎች መናፍቃን፣ በመሀመዳውያን አሕዛብ እና በፌሚኒስት ግብረ-ሰዶማውያን የተሞላ መሆኑ አንድ ሌላ ምልክት ሊሆን ይገባዋል።

ምን ያድርጉ፤ ጊዜው የነርሱ ነው፤ በኃያሉ መስቀል ስም በተሰየመው አደባባያችን ሕዝበ ክርስቲያኑ ብሶቱን በሰላማዊ ሰልፍ እንኳን እንዳይገልጽበት ተደርጓል። በተቃራኔው ይህ አደባባይ የዋቄዮ-አላህ ልጆች እና ሰዶማውያን መፈንጫና መፈንደቂያ አደባባይ ሆኗል። ያለ ምክኒያት ይመስለናልን በደመራ ዋዜማ የኢትዮጵያና አምላኳ ጠላቶች ኢሬቻ የተባለውን የሰይጣን አምልኮ በመስቀል አደባባይ ዛፎቻቸውን ተክለው እንዲያክብሩ የተደረገው? “ታላቁ ሩጫ” በተካሄድበት ወቅትም ኢትዮጵያዊው አጋጣሚውን ተጠቅሞ ወደ አራት ኪሎ በቁጣ እንደማምራት፣ የወደቁት ኢትዮጵያውያን እና ግብረ-ሰዶማውያን ዳንኪራቸውን በየአዳባባዩና ጎዳኑ ሲያሳዩ አይተናል። አዲስ አበባ ሰዶም እና ገሞራን ነበር የምትመስለው። እውነት ይህ ዳንኪራ የሚደረግበት ዘመን ነውን? ጂኒ ጃዋርን እግሩን የሚሰብር እንኳን ጀግና ጠፍቷል። በዚህ በዚህ ድክመታችን ዲያብሎስ ጠላት እየሰለጠነብን ነው። ግብረ-ሰዶማዊቷ ፖሊስም ይህን ያህል የደፈረችው፡ በዚሁ ነው፣ በእነ ዐቢይ ፈቃድና ስምምነትም ነው፤ ወደ ስቲዲየምም ሲልካት ብዙ ወጣት ኢትዮጵያውያን ተከታዮችና አፍቃሪዎች የሚገኝበትን የእግር ኳስ ስፖርት መረጠ። ይህን ሁሉ ዐቢይ እንዳቀነባበረው እግጠኛ ነኝ። ዐቢይ ከላሊበላ ጋር በተቆራኘ ቶቶ በተባለው የግብረ-ሰዶማውያን የጉዞ ወኪል ጉዳይ ላይ ምንም ነገር አለማለቱ ብዙ የሚነግረን ነገር ነበር። እስኪ አሁን ጠይቁት?

የፕሬዚደንት ማክሮን ወዳጅ ዐቢይ አህመድ ግብረ-ሰዶማዊ ነውን?

በአሁኑ ሰዓት በመላው ዓለም ብቅ ብቅ በማለት ከሁሉም ሰው በላይ የሚጮኹት ኢ-አማንያን መሀመዳውያኑ እና ግብረ-ሰዶማውያኑ ናቸው። የኛዎቹ “ኦሮሞ ነን” ባዮችም ከእነርሱ ጋር ነው የሚደመሩት።

እነ ዐቢይ አህመድ ኢትዮጵያዊ የሆነውን ነገር ሁሉ እያዋረዱ ለማዳከም ባላቸው ተልዕኮ የኢትዮጵያ አየር መንገድን፣ የኢትዮ ቴሌኮምን፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን፣ የታላቁ ሕዳሴ ግድብን፣ የጦር እና ፖሊስ ሠራዊቶችን (ተመለከቱ እንዴት በቄሮና በግብረ-ሰዶማዊቷ እያዋረዱት እንዳሉ)፣ ወዘተ ናቸው።

የአንድን አገር ሕዝብ አእምሮ እንዴት ማጠብ እንደሚቻል የአራት ደረጃዎች ሂደት፦

+ ፩ኛ. የሕዝቡን ሥነ ምግባር መስበር (ሞራሉን መንካት) (ከ15-20 አመት)

+ ፪ኛ. ህብረተሰቡን ማደፍረስና ማናጋት (2-5 ዓመት): የራሳችሁ ስለሆነው ግድ የለውም፤ አስፈላጊ ጥቃት በ መከላከያ፣ በኢኮኖሚ እና ባሕል ላይ ይደረጋል

+ ፫ኛ. ቀውስ እና ችግር (6 ሳምንታት): በሀገሪቱ አስቸኳይ ለውጥ እንዲካሄድ በሚያስችል መልክ ህብረተሰቡን ወደ አስጊ ሁኔታ መውሰድ

+ ፬ኛ. መረጋጋት እና መደበኛነት(አዕላፍ ጊዜ)

ለማንኛውም ሁሉም ይታዩን! ጥሩ ነው! በያሉበት አፋቸውን እንዲህ ይክፈቱ፣ ይገለጡ፤ እራሳቸውን ያጋልጡና እንያቸው፣ የኛዎቹም ይታዩን፣ እንግዲህ ሃቁ ፊት ለፊት እየታየን ነውና አላየንም! አልሰማንም! አላወቅንም! የለም።

[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፺፥፪፯]

“ኃጢአተኞች እንደ ሣር ሲበቅሉ ዓመፃ የሚያደርጉ ሁሉ ሲለመልሙ፥ ለዘላለም ዓለም እንዲጠፋ ነው።”

____________________________

Posted in Ethiopia | Tagged: , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ኃይለኛ የመሬት መንቀጥቀጥ ሊመጣ ነው | ወገኖች ሰዶም እና ገሞራ ካሊፎርኒያን እና ኔቫዳን ቶሎ ለቅቃችሁ ውጡ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on July 4, 2019

ዛሬ በአሜሪካ 4th Of July,Independence Day ወይም የነፃነት ቀን የሚባለው ሃገራዊ ክብረበዓል ይከበራል። በዚህ ዕለት በደቡብ ካሊፎርኒያ ኃይለኛ የመሬት መንቀጥቀጥ ተመዝግቧል። ይህ ባጋጣሚ አይደለም፣ ይህ የመጀመሪያው ምልክት ነው! ካሊፎርኒያውያን The Big One“ ወይም ትልቁን መንቀጥቀጥ በማንኛውም ጊዜ በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ፤ ያመንዝራና የግብረሰዶማውያን ማዕከላት የሆኑት ካሊፎርኒያ እና ኒቫዳ (ላስ ቬጋስ)ይጠፋሉ። የሆሊውድ ታዋቂ እና ኃብታም ሰዎች ይህን ተገንዝበው ቤቶቻቸውን እና ንብረቶቻቸውን እየሸጡ ወደ ሌላ ግዛት መዘዋወር ከጀመሩ ስንብተዋል። እዚያ ያላችሁ ወገኖች እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን፤ ግን እንደ ሎጥ ሚስት የጨው ኃውልት እንዳትሆኑ ፈጥናችሁ ካሊፎርኒያን እና ኒቫዳን ለቅቃችሁ ውጡ!

__________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Infos | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

የኖኅ ዘመን እንደ ነበረ | እንግሊዝ እስካሁን ታይቶ የማይታወቅ መብረቅ ወረደባት፤ የኢትዮጵያ ቀለማት ታዩ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 28, 2018

[የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፳፬፥፴፯]

የኖኅ ዘመን እንደ ነበረ የሰው ልጅ መምጣት እንዲሁ ይሆናልና።”

እጅግ በጣም የሚገርም ነው፤ አመጸኞቹ አውሮፓውያን የዔሳውና የእስማኤል ዘሮች የእግዚአብሔርን አሠርቱ ት ዕዛዛት ሙሉ በሙሉ በማፍረስ የራሳቸው የሆነ ዓለም በመፍጠር ከራሳቸው አልፈው እኛንም በጽኑ በመጉዳት ላይ ናቸው። ግን ፈጣሪያችን ትዕግሥቱ እያለቀበት ነው፤ ምልክቶቹን ለመጨረሻ ጊዜ እያሳየን ነው።

በአገራችን ላይ እያውጠነጠኑት ያለውን ዲያብሎሳዊ ሤራ ብዙዎቻችን አሁንም አልተረዳነውም፤ ሁሉን የሚያይ እግዚአብሔር ግን ዝም አይለም። ኢትዮጵያ በእግዚአብሔር የተመሰረተችና በቅዱሳን ቃል ኪዳን የተጠበቀች፤ ከሁሉ በላይ ደግሞ የእመቤታችን አስራት አገር ስለሆነች እንኳን በአገር ዉስጥ ለጥፋቷ የተሰለፉ አይደለም፤ እርሷን ለማጥፋት የተሰለፉ የዉጭ መንግሥታት በሙሉ በእግዚአብሔር ቁጣ ይጠፋሉ፤ ከምድር ይጠረጋሉ። እርሷ ግን በእግዚአብሔር መንግሥትነቷ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ትቆያለች።

ቅዳሜ ሌሊት ላይ፡ በእንግሊዝ አገር ታይቶ የማይታወቅ ነጎድጓድና የመብረቅ ብልጭልጭታ ብዙዎችን ከእንቅልፋቸው ቀስቅሷል። በአንድ ምሽት ብቻ 22 ሺህ ጊዜ የለንደን ሰማይ በመብረቅ ተብለጭልጯል።

ቪዲዮው መጨረሻ ላይ እንደሚታየውም በሆነ ወቅት ላይ ደመናው በአረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ቀለማት ተቀብቶ ነበር። የሚገርም ነው።

ይህ ሁሉ የተከሰተው፤ እንግሊዝ ፀረእስላም የሆኑ ጋዜጠኞችን ማሠር በጀመረችበት፣ ወኪሏን አቶ አንዳርጋቸውን የኢትዮጵያ መንግስት እንዲፈታ ትዕዛዝ ካሰተላለፈች፣ እንዲሁም እህቷ አየርላንድ ደግሞ የጸነሱ ሴቶቿ ጨቅላዎቻቸውን እንዲያስወርዱና እንዲገድሉ በሬፈረንደም አጽድቃ ፈቃዱን በሰጠቻቸው ማግስት መሆኑ ነው።

ጻድቁ አባታችን፡ አቡነ ተክለሃይማኖት በሀገሬ ላይ የታዘዙ አምስት መቅሰፍቶች አሉ ብለው ነበር።

እነሱም፡

1. መብረቅ

2. ቸነፈር፣

3. ረሃብ፣

4. ወረርሽኝ፣

5. የእሳት ቃጠሎ ናቸው፡፡

______

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: