Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘ሰንደቅ ዓላማችን’

ጠ/ሚንስትር አብይ በጀርመን | የኢትዮጵያ ጠላቶች ጊዚያዊ ድል የተቀዳጁበት አሳዛኝ ቀን

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 1, 2018

ምንም እንኳን ከሰማይ በታች ምንም አዲስ ነገር ባይኖርም፡ በፍራንክፈርት ከተማ በዛሬው በ ጥቅምት ፳፩ / ፳፻፲ ወ ፩ ዓ.ም የታየውን የክህደት እብደት ኮስተር ብለን እንመዝግበዋለን።

ፀረክርስቶሱ እና ልጆቹ፦

ከማርያም መቀነት ያገኘናቸው አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ቀለማት የጣዖቱ ዛፍ ባረፈባቸው ቀይ፣ ቢጫና አረንጓዴ የሰዶማውያን ቀለማት መቀየር አለበት፣ የኢትዮጵያ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ በማርቲን ሉተር እና በዋቄዮ አላህ አምላክ መተካት አለበት፤ ኢትዮጵያውያንን እናጥፋቸው፣ የ ኢትዮጵያም ስም አይታሰብ” አሉ።

ይህን ሁሉ እጅግ በጣም አሳፋሪ ድራማ በደንብ ነው ያቀነባበሩት፤ ሁሉም ነገር ላይ፡ ከውጭም ከውስጥም፡ የሉሲፈራውያኑ እጅ አለበት። ባዕዳን ጠላቶቻችን በኢትዮጵያ ላይ ለ150 ዓመታት ያህል የጠነሰሱት ሤራ ግቡን እየመታላቸው እንደሆነ በማየታቸው በጣም እየፈነጠዙ ነው፤ የአምላክነት ስሜትም እየተሰማቸው ነው። ግድ የለም! ለጊዜው ነው፡ ይፈንጥዙ፣ ይታዩን፣ እንመዝግባቸው፤ መስሏቸው ነው፡ በቅርቡ ደም ያለቅሷታል።

በነገራችን ላይ፡ የሉሲፈራውያኑ “አለም ባንክ” ለኢትዮጵያ 1.2 ቢሊየን ዶላር የብድር ስጦታ እንደሚሰጥ ይፋ ሲሆን፤ በሌላ በኩል ደግሞ ኢትዮጵያውያን እህቶቻችን ወደ አረብ ኤሚራቶች የሚሸጡበትን መንገድ የሚገልጽ ረቂቅ መውጣቱን በዛሬው ዕለት ተገልጧል፤ በምዕራቡ ዓለም፡ “ሀለዊን” በመባል የሚታወቀው የሰይጣን አምልኮ በሚከበርበት በዛሬው ዕለት።

መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፹፫:

አቤቱ፥ እንደ አንተ ማን ነው? አቤቱ፥ ዝም አትበል፥ ቸልም አትበል።

እነሆ፥ ጠላቶችህ ጮኽዋልና፥ የሚጠሉህም ራሳቸውን አንሥተዋልና።

ሕዝብህን በምክር ሸነገሉአቸው፥ በቅዱሳንህም ላይ ተማከሩ።

ኑ ከሕዝብ እናጥፋቸው፥ ደግሞም የእስራኤል ስም አይታሰብ አሉ።

አንድ ሆነው በአንተ ላይ ተማከሩ፤ በአንተ ላይ ቃል ኪዳን አደረጉ፤

የኤዶማውያን ድንኳኖች እስማኤላውያንም፥ ሞዓብም አጋራውያንም፥

ጌባል አሞንም አማሌቅም፥ ፍልስጥኤማውያንም ከጢሮስ ሰዎች ጋር፤

አሦርም ከእነርሱ ጋር ተባበረ፥ ለሎጥ ልጆችም ረዳት ሆኑአቸው።

______

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: