Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

 • February 2023
  M T W T F S S
   12345
  6789101112
  13141516171819
  20212223242526
  2728  
 • Archives

 • Categories

 • Recent Posts

Posts Tagged ‘ሰማያት’

ጽላተ ሙሴ? | የትግራይ ወገኖቼ እንባ በዓለም ዙሪያ ባሉ ሰማያት ላይ መታየት ጀምሯል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 14, 2021

👉 በዓለም ዙሪያ ባሉ ሰማያት ላይ ያልተለመዱ ብርሃናት ወይም ብልጭታዎች ብዙ ሰዎችን በማስደንገጥ ላይ ናቸው።

❖[የዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ ፲፩፥፲፱]

በሰማይም ያለው የእግዚአብሔር መቅደስ ተከፈተ፥ የኪዳኑም ታቦት በመቅደሱ ታየ፥ መብረቅና ድምፅም ነጐድጓድም የምድርም መናወጥ ታላቅም በረዶ ሆነ።

❖ በቪዲዮው የተካተተ ነው፤ ታዋቂው የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቄስ ጎብኚ ፍዮዶር ኮንኙኮቭ በአክሱም ጽዮን፦

🔥 “እንደ ጽላተ ሙሴ ጠባቂ ኢትዮጵያዊ ዓይኖች ዓይነት የሚያበሩ ሌሎች ዓይኖች አይቼ አላውቅም”

ሰማይን ተመልከት አንድ መጥፎ ነገር ሊከሰት ይመስላል! በአክሱም ስለተካሄደው ጭፍጨፋ ዝም ማለት ተገቢ አይደለም፤ እኛ ዝም ብንል የሠራዊት ጌታ ልዑል እግዚአብሔር ግን ዝም አይልም።

በአክሱም ጽዮን ላይ ተደርጎ የነበረው ጥቃትና ጭፍጨፋ የታየኝ እንደሚከተለው ነው፤

በቄሮ እና ፋኖ ፋሺስቶች እንዲሁም በኢሳያስ አፈቆርኪ የሚደገፈው የግራኝ አብዮት አህመድ አሊ አህዛብ ሠራዊት ወደ አክሱም ጽዮን ቤተ ክርስቲያን በማምራት ጽላተ ሙሴን ማውጣት/መስረቅ ፈለገ፤ ሌቦቹ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ልክ ሃይለማርያም ደሳለኝ ኢየሩሳሌም በሚገኘው የኢትዮጵያ ገዳም ከእነ ጫማው እንደገባውና አባታቸው ግራኝ አህመድ ቀዳማዊ “አላህ ዋክብረ!” እያለ አክሱም ጽዮንን እንዳፈራረሰው፤ እነዚህ የመንፈስ ወንድሞቹ “እስኪ አምላካችሁ ያድናችሁ እንደሆነ እናያለን፣ እስኪ የጽላቱን ኃይል እናየዋለን!” በምል የትዕቢት፣ እብሪትና ጥላቻ መንፈስ ወደ ቤተ መቅደሱ ዘው ብለው ገቡ። ከዚያም እነዚህ ማንነታቸውንና ምንነታቸውን የሸጡት አህዛብ ወታደሮች ወዲያና ወዲህ እያሉ መበርበር ሲጀምሩ ጨረር እንደተለቀቀባቸው ዝንቦች እየተቃጠሉ ረገፉ፤ ይህን ያዩ ሌሎች የአጥፊው ሠራዊት አባላት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የነበሩትን ቀሳውስታና ምዕመናንን ወደ ውጭ አውጥተው ረሸኗቸው።

🔥 በግብጽ፣ ሶርያ፣ ኢራቅና ሌባኖን  ክርስቲያኖችን  የሚገድሉና ዓብያተ ክርስቲያናትን  የሚያቃጥሉ  የሙስሊም  ወንድማማቾችና አይሲስና ኢዝቡላ ሽብር ፈጣሪዎች ናቸው፣ 

🔥 በኬኒያና ሞዛምቢክ ክርስቲያኖችን የሚገድሉ እና ዓብያተ ክርስትያናትን  የሚያቃጥሉት አል-ሸእባቦች ናቸው፣ 

🔥 በናይጄሪያና ካሜሩን ክርስቲያኖችን የሚገድሉና ዓብያተ ክርስቲያናትን የሚያቃጥሉ ቦኮ ሃራም እና ፉላኒ  መሀመዳውያን ሽብር ፈጣሪዎች ናቸው፣

🔥 በአውሮፓ እና አሜሪካ ክርስቲያኖችን የሚገድሉና ዓብያተ ክርስቲያናትን የሚያቃጥሉት መሀመዳውያን፣ ግብረ-ሰዶማውያን፣ ፌሚንስቶች፣ ኮሙኒስቶች፣ ጣዖት አምላኪዎች ናቸው፣

🔥 በሃገረ ኢትዮጵያ ግን ክርስቲያኖችን የሚያሳድደው፣ የሚገድለውና ዓብያተ ክርስቲያናቱንና የድኾችን መኖሪያዎች የሚያፈርሰውና የሚያቃጥለው “መንግስት” ነው። የራስ መንግስት?

👉 ይህ በየትኛውም ዓለም ታይቶና ተሰምቶ የማይታወቅ ነው

❖❖❖የወገኖቻችንን ነፍስ በቅዱሳኑ እቅፍ ያኑርልን ከማህበረ ፃድቃን ይደምርልን!❖❖❖

________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: